Wisdom Books Ecclesiastes

The Limitations of Wisdom

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Eternal Ecclesiastes 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 479 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለመክብብ የሜንዲ ስዕል ሰባት የሱፍ አበባዎችን ያካትታል ፡፡ በብዛት ሰባት ከፍፁምነት ጋር የተገናኜ ነው ፤ እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር በስድስት ቀን በመፍጠር በሰባተኛዉ ቀን ላይ አረፈ ፡፡ በተጨማሪም ሰባት የጊዜ መፈፀምን ወይም ሙሉነትን ያመለክታል ፡፡ በዕብራዊያ ቃል ሰባት ማለት “ ሸቫህ “ ሲሆን “ ሙሉ፣ የሚያረካ እና በቂ “ ማለትም ነው ፡፡ ወደ ልጁ ስንመለከት ማረፍ እንችላለን ፡፡ ክርስቶስ በመክብብ መፅኀፍ እንዴት እንደሚታይ ስንመለከት የምንጠቀመዉ ቃል ዘላለማዉ ነው ፡፡ መክ (3፡ 11) እያንዳንዱ ግለሰብ እየፈለገ/እየጣረ እንደሆነ ያመለክታል ምክንያቱም እግዚአብሄር በልባቸዉ ዉስጥ ዘላለምን ስላስቀመጠ ፡፡

መክብብ የሚለዉ ቃል “ አስተማሪ “ ወይም “ ሰባኪ “ ማለት ነው ፡፡ ስቴድማን ራይ የተሸለዉ ትርጓሜ “ ፈላጊ “ የሚለዉ ነዉ ይላል ምክንያቱም ፀኀፊው “ በሁሉም ህይወት ላይ ከሰዎች ድርጊት ኋላ ምን እንዳለ የተመለከተበት የሚፈልግ/የሚመረምር አይምሮ ስለ ነበረው “ ፡፡ ኤክሌሺያ የሚለዉ የግርክ ቃል “ ጉባኤ “ ማለት ነው ፡፡ ሰባኪ ለሚለዉ የዕብራዊያን ቃል ኦህሌዝ ሲሆን “ የሚያቀርብ፣ የሚሰበስብ እና የሚለቅምን “ የሚገልፅ ነው ፡፡ በዚህ ሁሉ ሀሳብ ዉስጥ ያለ ማቋረጥ ፍለጋዉን እና ንግግሩን በሌላ በማንኛዉም ላይ እንደሚያደርግ ሰዉ የመክብብን ፀኀፊ ሰለሞን ላይ መመልከት እንጀምራለን ፡፡ ዕብ (13፡ 8) “ ኢየሱስ ክርስቶስ ትናትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው “ ይህ ማለት የዘላለም ህይወታችን ነዉ ማለት ነው ፡፡

ዮሐንስ ማክአርቱር ሰለሞንን እንደ ፀኀፊ የሚለዩ ነገሮችን ዘርዝሯል ፤ መምህሩ/ሰባኪዉ “ በኢየሩሳሌም የነገሰ የሰባኪው የዳዊት ቃል “ (ቁጥር 1) እና “ በእስራኤል ላይ በኢየሩሳሌም ንጉስ ነበርኩ “ (ቁጥር 12) በማለት ተለይቷል ፤ “ የፀኀፊዉ የሞራል ጀብድ በሰለሞን ህይወት ስር ሰድዷል “ (1ነገስት 2-11) ፡፡ ሰባኪዉ “ ለሕዝቡ እዉቀትን አስተማረ “ በተጨማሪም “ ብዙ ምሳሌዎችንም “ ፃፈ (መክ 12፡ 9) ፤ ምናልባትም መክብብ በሰለሞን ባለፈው ህይወቱ የተፃፈ ነበር ፡፡ ማክአርቱር እንዳለው ምናልባትም በዚህ ብዙ ጊዜ ስላለማፍሰስ/ስላለማሳለፍ እየሳለ ነበር ምክንያቱም የሚበልጥ ነገር ስላለ ፡፡ ሰለሞን በአባቱ በዳዊት የተለዬ ጥበብ እንደሚኖረዉ የታወቀ ነበር (1ነገ 2፡ 6, 9) ፤ በ 1ነገ (3፡ 7-12) ሰለሞን እስራኤልን ለማስተዳደር እግዚአብሄርን ጥበብ ጠየቀው እግዚአብሄርም ከማንኛዉም ሰዉ የበለጠ ጥበብን ሰጠው ፡፡ በመክ (12፡ 13-14) ሰለሞን “ እግዚአብሄርን ፍራ ትዕዛዙንም ጠብቅ ፡፡ እግዚአብሄር ስራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን ወደ ፍርድ ያመጣዋልና “ በማለት አጠቃለለ ፡፡ ስንተነፍስ፣ ስንሄድና ስንመጣ ስለ ህይወት እናወራለን ነገር ግንአሁንም እንዴት እንደምንኖር ለእግዚአብሄር ተጠየቃኒት አለብን ፡፡ አይኖቻችን በዘላለም ላይ ማድረግ አለብን - በልጁ ላይ ፡፡

ትምህርት

መክብብ (1፡ 1-2)፡ ዳዊት እንደ ንጉስ 40 አመታት አገለገለ ፡፡ ሰለሞንም እንደ ንጉስ 40 አመታትን አገለገለ ፤ የሰላምና ጦርነት ያልነበረበት ጊዜ ነበር ፡፡ የሰለሞን መክፈቻ ንግግር “ ሁሉም ከንቱ ከንቱ “ (ቁጥር 2) የሚል ነው ፤ ሌሎች ትርጓሜዎች “ የከንቱ ከንቱ “ (ESV) በማለት ወይም “ (NIV) ትርጉም የሌለው “ በማለት ይነበባሉ ፡፡ በመጨረሻም ህይወት የምትመጣና የምትሄድ ንፋስ/ከንቱ ነው ፤ በአይምሮአችን ዉስጥ መያዝ ያለብን ነገር ይህ ህይወት በፍጥነት ቢያልፍም እንኳን ከእርሱ ጋር ለዘላለም አብረን መሆን እንችላለን ፡፡ ጥያቄው ሁሉም ነገር ትርጉም አልባ ከሆነ በብዙ ጊዜያዊ እሆነ ነገር ላይ ለምን እናተኩራለን ? ሰዎችን ከሚያልፈዉ ይልቅ ወደ ዘላለም ለምን አናመለክታቸዉም ? ይህ ከመፅኀፍ ቅዱስ ዉስጥ አንዱ አስፈላጊ መፅሀፍ ነው ፡፡ ያለን ሁሉም ነገር ዋጋ እንደሌለዉ እንደ ንፋስ የሚመጣና የሚሄድ እንደሆነ ከተረዳን ሁሉንም ትኩረታችንን በዘላለም ላይ ማስቀመጥ እንችላለን ፡፡

መክብብ (1፡ 3-7)፡ በህንድ በፋብሪካ ዉስጥ ወይም በሌላ ስራ ላይ በየቀኑ ጠንክራችሁ መስራታችሁ ምንድን ነዉ የሚያስገኝላችሁ ? የሰዎች ትዉልድ ይሄዳል ይመጣል ነገር ግን ምድር ብቻ ትቀራለች (ቁጥር 4) ፡፡ ሰለሞን የምድርን መኖር፡ እንደ ፀሀይ መዉጣትና መግባት፣ እንደ ንፋስ ኡደት/ዙረት እና ወደ ባህር እንደሚፈስስ ዉሃ ይገልፀዋል (ቁጥር 5-7) ፡፡

መክብብ (1፡ 8-11)፡ ሰዉ አይረካም/አይጠግብብ - ሁልጊዜ ተጨማሪ እንፈልጋለን ፡፡ አንዴ የሆነ ነገር ሲኖረን በትንሹ የተደሰትን እንሆናለን ነገር ግን እስከመጨረሻ አይቆይም ፡፡ የሆነ ነገር ስብስብ ስትጀምሩ - ምንድን ታደርጋላችሁ ? መሰብሰባችሁን ቀጥሉ ፡፡ “ ከፀሀይም በታች አዲስ ነገር የለም “ (ቁጥር 9) “ መታሰቢያም የላቸዉም” (ቁጥር 11) ፡፡ አብዛኞቻችን ቅርስን ትተን መሄድ እንደምንፈልግ እናወራለን ነገር ግን ከ20 እስከ 30 አመት እዉን የሆነ ይመስላል ከሞትን በኋላ ቤተሰቦቻችን ብቻ ያስታዉሱናል ፡፡

መክብብ (1፡ 12-18)፡ ሰለሞን አድርጎት የነበረዉ ሁሉም ነገር “ ንፋስን እንደ መከተል “ (ቁጥር 14) እንደ ነበር አገኘው ፤ ጥበብን እና እዉቀትን ማግኘትም እንኳን ቢሆን “ ንፋስን እንደ መከተል ነበር “ (ቁጥር 17) ፡፡

መደምደሚያ

ከእኛም ዉስጥ እያንዳንዳችን እየፈለግን ነው ፡፡ ከፀሀይ በታች ባለዉ ህይወት ላይ ትኩረት ስናደርግ ትርጉም የለሽ ባዶ እስትንፋስ ሆኖ እናገኘዋለን ፤ ነገር ግን ከፀሀይ በላይ በልጁ በኢየሱስ ላይ በምናተኩር ጊዜ ሙሉ የሆነ ሙሉነት እናገኛለን ፡፡ ልጁ ዘላለማዊ ነው ፡፡ ኢየሱስ ህይወትን በማምጣት ይሰጠናል ፤ በ 1ዮሐ (5፡ 11) “ እግዚአብሄርም የዘላለምን ህይወት እንደ ሰጠን ይህም ህይወት በልጁ እንዳለ “ ምስክሮች ነን ፡፡

  1. Ray C. Stedman, Is This All There Is To Life? (Portland, OR: Multnomah Press: 1985), p. 11

  2. Stedman, p. 11.

  3. John MacArthur, The John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 731.

  4. MacArthur, p. 731.

ጥያቄዎች

  1. መክብብን የፃፈዉ እንደሆነ የሚያመለክትዉ የትኛዉ/ምን ማስረጃ ነው ? (1ነገ 3፡ 12, 10፡ 10-23, መክ 1፡ 1, 12, 16፣ 2፡ 8)
  2. በመክብብ ዉስጥ አንዱ ቁልፍ ቃል ከንቱ ነው ፤ ፀሀፊዉ ይህን ቃል በመጠቀም ምን ለመናገር/ለማዉራት እየሞከረ ነበር (መክ 1፡ 14, 6፡ 12) ? ከዚያስ ይህን ህይወት ከእግዚአብሄር ዉጭ ስለመኖር ምን ትደመድማላችሁ ? ክርስቶስ ሲኖራችሁ ይህ ምለከታ ለምን ይቀየራል ? (መዝ 16፡ 11)
  3. መክ (1፡ 8-9) አንብቡ ፤ ሰዎች በህይወት ደስተኛ የማይሆኑት ለምንድን ነው (መክ 3፡ 11) ? እርካታን/ደስታን ለማግኘት የመጨረሻዉ መፍትሄ ምንድን ነው ? (ማቴ 11፡ 28)
  4. በመክ (2፡ 11-26) ቢያንስ ሰዎስት “ ከንቱ ነገሮች/ከንቱነቶች “ አሉ ፤ ምንድን ናቸው ?
  5. በመክብብ 2 ሰለሞን ለምን ህይወትን ጠላሁ አለ ? ይህ ለምን ከሰለሞን እንግዳ ነገር የመጣ ይመስላል (ምሳ 8፡ 35) ? ሰለሞን የገለፀዉ አለመርካት ተሰምቷችሁ ያውቃል ? እንዴትስ አድርጋችሁ ያዛችሁት/አስታገሳችሁት ? በአጠቃላይ ስለ ህይወት ጤነኛ ክርስቲያን እንዴት ይሰማዋል ? (ዕብ 3፡ 10-12)
  6. በመክብብ (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Ecclesiastes 1:2–3

“‘Absolute futility,’ says the Teacher. ‘Absolute futility. Everything is futile.’ What does a man gain for all his efforts that he labors at under the sun?”

ሰሎሞን በምድር ላይ ያሉ ደስታዎችን ሁሉ ለማግኘት ጥሯል ፡- ሀብት ፣ ንብረት ፣ ዝና ፣ ሚስቶች ፣ አገልጋዮች ፣ ስኬት ደግሞም ጥበብ ፡፡ እርሱ ከምድር በታች ያለውን ሁሉ አግኝቷል ነገር ግን ይህን ሁሉ ፍጹም ከንቱ ብሎ ይጠራዋል ማለትም እንደ አስትንፋስ ነው እንደ አየርም በኖ ይጠፋል እንድሁም ታይቶ የሚጠፋ ነው ይለዋል ፡፡ ከሰሎሞን ምን ትማራለህ ?

ለምንድን ነው የምትኖረው ? ምናልባትም ለአንተ በጣም አስፈላጊ ወደ ሆነው ነገር ትኩረትህን ለማዞር ጊዜው አሁን ይሆናል ፡፡ ትኩረትህን ብዙ ፣ ትልቅ ወይም የበለጠ ከማግኘት ይልቅ ዘላለማዊ ወደ ሆኑ ነገሮች አዙር ፡፡ አለም የምታቀርበው ብዙ ብዙ ነገር አላት ነገር ግን አንተን ያረካሃልን ደግሞም በውስጥህ ያለውን ጥማትና እርሃብ ያጠፋልሃልን ? ሰሎሞን ሁሉንም ከንቱ ብሎ ይጠራዋል ፡፡ ከጸሀይ በታች ካሉ ነገሮች እርካታን እና መሻትን ለማግኘት መፈለግን ለማቆም ጊዜው አሁን ነው ፡፡ ይልቁንም ትኩረትህን በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ፣ ትላንትና ዛሬ ነገም ያው በሆነው አምላክ ላይ አድርግ ፡፡ ኢየሱስ ልጁ ህይወትን ፣ ፍቅርን ፣ ሰላምን ደግሞም ደስታን ይሰጣል በተጨማሪም እርሱ እስከ ለዘላለም ከአንተ ጋር ይሆናል ፡፡ በእርሱ መገኘት ውስጥ የትኛውም ከጸህይ በታች ያለ ነገር ሊሰጥ ከሚችለው በላይ የሆነ ፍጹም ደስታ አለ ፡፡ ዛሬ እውነት በሆነው ፤ ደስታውም ዘላለማዊ በሆነው በልጁ ላይ አትኩር ፡፡

“ ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፤ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል ። ከፀሐይ በታች በሚደክምበት ድካም ሁሉ የሰው ትርፉ ምንድር ነው ? “ - መክብብ 1፡2-3

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 107:9 — “ የተራበችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራቈተችንም ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና ። “
  • መክብብ 2:20 — “ እኔም ተመልሼ ልቤን ከፀሐይ በታች በደከምሁበት ድካም ሁሉ ተስፋ አስቈረጥሁት ። “
  • 1ኛ ዮሐንስ 5:11 — “ እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው ።