There Is A Generation
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 30-31 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ምሳሌ እኛ በተለያዬ መንገድ መናገር የሚችል በጣም የበለፀገ ነው ፤ እነዚህ ሁለት ምዕራፎች ደግሞ ብዙ ታላቅ እዉነቶችን ይዘዋል፣ ከዛሬዉ ምዕራፎች ዉስጥ በሁለት ቁልፍ ፅሁፎች ላይ እናያለን ፡፡
ትምህርት
ምሳሌ (30፡ 1)፡ እነዚህ ሰዎች እነማን ነበሩ ? የጥንት አይሁድ የሕግ መፅኀፍ ሰለሞንን ቢያንስ በስድስት ስሞች ጠቅሶታል፡ የያቄ ልጅ፣ አጉር፣ ልሙኤል እና ሳሙኤል ፡፡
ምሳሌ (30፡ 7-9)፡ እንደ ወደቀ ፍጥረት በኃጢዓተኛ ተፈጥሮአችን በራሳችን ወደ መታመን፣ ወደ ምችታችን እና ራሳችንን ወደ መጠበቅ ተስበናል ፡፡ ራሳችንን በእግዚአብሄር ላይ ያለን መታመን በኃይል ደክሞ በምናገኘዉ ጊዜ በእግዚአብሄር ላይ ከመታመን ይልቅ በራሳችን ላይ የታመንን እንሆናለን ፤ በጣም ጥቂት መታመን ብቻ በሚኖረን ጊዜ በሌላኛዉ መጠነ ሰፊ በኩልም እግዚአብሄር እንደሚሰጠን ልንጠራጠር ስለምንችል ለኃጢዓት የተፈተንን በመሆን ለራሳችን እንሰጣለን ፡፡
በ 1ሳሙኤል 21 ዳዊት ከካህኑ አቢሜሌክ ቤት ለሰዎቹ የተቀደሰ እንጀራ ወሰደ ምክንያቱም ሊያቀርብላቸዉ የሚችልበት መንገድ ስላልነበረው ፡፡ በቁጥር 9 እንደተጠቀሰው ዳዊት ራሱን በሚያስቸግር ሁኔታ ዉስጥ አገኘው፡ “ ድሀም እንዳልሆን እንዳልሰርቅም በአምላኬም ስም በሀሰት እንዳልምል “ ፡፡
“ ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ ጎስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕዉርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ ተጎናጽፋህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለዉን ኩል ከእኔ ትገዛ ዘንድ እመክርሃለሁ “ (ራዕ 3፡ 17-18) ፡፡ ሎዶቃዊያን በእግዚአብሄር የሚያስፈልጋቸዉን መትረፍረፋቸዉን አጥተዉት ነበር ፤ በቁጥር ሰባት ላይ በተጠቀሰዉ አስቸጋሪ ሁኔታዉስጥ ከእግዚአብሄር በተቃራኒ ራሳቸዉን አገኙት፡ “ እንዳልጠግብ እንዳልክድህም ፡፡ እግዚአብሄርስ ማነው ? እንዳልል “ ፡፡
ሰለሞን ተፈጥሮአዊ ሰዉን ከመለኮታዊዉ እግዚአብሄር ጋር ለማገናኘት በመሞከር የፃፈዉ ይመስላል ፤ ሰለሞን ሙሉ በነበረበት ጊዜ ደስተኛ እንዳልነበር እና ተርቦ በነበረበት ጊዜ ደግሞ እምነት የሚጣልበት እንዳልነበር ያውቃል ፡፡
ምሳሌ (30፡ 11-14)፡ እግዚአብሄር ራሱን በታሪክ ዉስጥ በሰባት ኃይማኖታዊ ስርዓት ዉስጥ ገልጧል፡
- የንፁኅነት ቃል ኪዳን ስርዓት፡ እግዚአብሄር አዳምና ሒዋንን በፍፁምነት ከእግዚአብሄር ጋር መጓዝ ሙሉ ቀላል እንደ ነበር በኤደን ገነት በሰብዓዊነት በማሳየት ፍፁም እንዲሆኑ ፈጠራቸው ፡፡ በዚህ ፍፁምነት መካከል ላይ ለሰብዓዊነት ለኃጢዓት የተፈተነ መሆን ቀላል ነበር ፤ ይህ ቃልኪዳን/ስርዓት አዳም እና ሒዋን ፍሬዉን በመብላት ከኤደን ገነት በተባረሩ ጊዜ አበቃ ፡፡
- የህሊና ቃል ኪዳን ስርዓት፡ አዳም እና ሒዋን የእዉቀትን ዛፍ ፍሬ ከበሉ በኋላ በራሳቸዉ እይታ ልክ የነበረዉን አደረጉ ፤ ይህ ቃል ኪዳን መፍረስ/ስርዓት አበቃ ምክንያቱም “ ምድርም በእግዚአብሄር ፊት ተበላሸች ምድርም ግፍን ስለተሞላች “ (ዘፍ 6፡ 11) ፡፡
የሰዉ አስተዳደር ቃል ኪዳን ስርዓት፡ ኖህና ቤተሰቡ ወደ መርከቢቱ ከመጡ በኋላ እግዚአብሄር፡ “ ነፍሳችሁ ያለችበትን በእርግጥ እሸዋለሁ ከአራዊት ሁሉ ፤ ከአራዊት ሁሉ እጅ እሸዋለሁ ፤ ከሰዉም እጅ ከሰዉ ወንድም እጅ የሰዉን ነፍስ እሻለሁ “ (ዘፍ 9፡ 5-6) ፡፡ አሁንም ሁሉም ሰዉ በፊቱ ትክክል የመሰለዉን ሁሉ እያደረገ ነዉ ነገር ግን አሁን ክፉን ለማረጋጋት የሚያመጣዉ ዉጤት መፍትሄዉ የተገለጠ ነበር ፡፡
የቃል ኪዳን ስርዓት፡ ተስፋዉ ለአብርሃም ተሰጥቶት ነበር ፤ እግዚአብሄር በእግዚአብሄር ፍርድ ላይ የእግዚአብሄርን በረከት የሚያዩ አዲስ ሰዎች ከአብርሃም አዉጥቶ እንደሚሰራ ወሰነ ፡፡
የህግ ስርዓት፡ የአብርሃም ዘር ከግብፅ ሲወጡ እግዚአብሄር እስራኤልን የህጉን ዝርዝር እንዴት ከእርሱ ጋር እንደሚገናኝ ሰጣቸው ፡፡
የፀጋ ስርዓት፡ በመጨረሻ በኢየሱስ ስቅለት እና ትንሳኤ ለይ ደርሷል ፡፡
የሰላም ስርዓት፡ ሁላችንም በዚህ ጊዜ እየጠበቅነዉ ነው ፡፡
ኃይማኖታዊ ስርዓት እግዚአብሄር በተወሰነ ጊዜ ከሰብዓዊ/ከሰዉ ጋር እንዴት እንደተገናኜ ይገልፃል ፡፡ በእያንዳንዱ ስርዓቶች ዉስጥ በኃጢዓተኝነት ምክንያት ለሌለኛዉ ትዉልድ ለማድረስ አንድ ትዉልድ መጣ ፡፡ ቁጥር 11-14 ለቀጣዩ ትዉልድ ሊያደርስ ስለሚችለዉ ትዉልድ ባህሪያት ይገልፃል ፤ እያንዳንዱ ጥቅስ ዛሬ ልንመለከታቸዉ የምንችላቸዉን አመለካከቶች ይገልፃሉ ፤ 2ጢሞ (3፡ 1-5) “ ነገር ግን በመጨረሻዉ ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ ፡፡ ሰዎች ራሳቸዉን የሚወዱ ይሆናሉና ገንዘብን የሚወዱ ትምክህተኞች ትዕቢተኞች ተሳዳቢዎች ለወላጆቻቸዉ የማይታዘዙ የማያመሰግኑ ቅድስና የሌላቸው ፍቅር የሌላቸው ዕርቅን የማይሰሙ ሐሜተኞች ራሳቸዉን የማይገዙ ጨካኞች ችኩሎች በትዕቢት የተነፉ ከእግዚአብሄር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ክደዋል ከእነዚህ ደግሞ ራቅ ! “
ምሳሌ (30፡ 24-28)፡ የተገለፁት እያንዳንዳቸዉ እንስሳቶች ለመኖር መንገዶችን በመሳል በማንኛዉም ትዉልድ መካከል ላይ ማዳበር ፡፡ ሰለሞን ከእነርሱ ትምህርትን እንድንማር ያሳስበናል ይህ ከሆነ ክፉዎች እና ኃጢዓተኞች ምንም ቢሆኑ ራሳችንን በምናገኝበት በትዉልዱ ዉስጥ መኖር እንችላለን ፡፡
መደምደሚያ
በሰላም ስርዓት በደረሰዉ ትዉልድ ዉስጥ የምንኖር ከሆነ እግዚአብሄር በማስተዋል እንዴት በዚህ ላይ መኖር እንደምንችል አዝዞናል ፡፡
ጥያቄዎች
-
ምሳ (30፡ 4) ስለ ማን እያወራ ነው (ቆላ 1፡ 16-17) ? በመፅኀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ላይ ተመሳሳይ ጥያቄ ትሰማላችሁ ? (ኢዮብ 38-41)
-
ምሳ (30፡ 8-9) ድህነትን ከባለፀግነት ጋር ያወዳድራል ፤ የትኛዉ አደገኛ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ?
-
ምሳ (30፡ 11) ዛሬም ይተገበራል ? አዎ ከሆነ መጥፎ ወይስ የተሻለ ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? (1ሳሙ 2፡ 12-17, 22-25, 2ሳሙ 13፡ 1-14)
-
ልንማር የምንችልባቸዉ አራት ፍጥረቶች ምንድን ናቸው (ምሳ 30፡ 24-28) ? እያንዳንዳቸዉ እንዴት አድርገዉ ሊያስተምሩን ይችላሉ ?
-
የአንድ ደግ ሚስት ጥቂት ባህሪያቶች ምንድን ናቸው (ምሳሌ 31) ? ከእነዚህ ባህሪያቶች ዉስጥ ለአንድ ሚስት በጣም አስፈላጊዉ የትኛዉ እንደሆነ ታስባላችሁ ?
-
በምሳሌ (30-31) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን ጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Proverbs 30:8–9
“Keep falsehood and deceitful words far from me. Give me neither poverty nor wealth; feed me with the food I need. Otherwise, I might have too much and deny You, saying, ‘Who is the LORD?’ or I might have nothing and steal, profaning the name of my God.”
እግዚአብሔር ቃሉ ሁሉ እንደተፈተነች ተናግሯል ፡፡ በእርሱ ለሚሸሸጉት እርሱ ጋሻ ነው ፡፡ ስለዚህ ዛሬ በእርሱ መሸሸግ ላይ አትኩር ፡፡ በምትበላው ወይም በቢዝነስ ዘርፍ በሚገኝ ስኬት ወይም ሽልማት ሰላምን ለማግኘት ከመፈለግ ተጠንቀቅ ፡፡ ይልቁንም በእግዚአብሔር ዘንድ ተሸሸግ ፡፡ ራስህን በእርሱ ዘንድ ደብቅ ፡፡ ፍቃድህን ለእርሱ አሳልፈህ ስጥ ፡፡ በሁሉም የህይወት አጋጣሚዎችህ በእርሱ ላይ ተደገፍ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሀብትን ስታፈራ ፣ በስራ ስኬትን ስታገኝ ወይም ደግሞ በእለት ተእለት እንቅስቃሴህ ስትደላደል ለራስህ በቂ እንደሆንክ ወደ ማሰብ ለመምጣት ቀላል ነው ፡፡ የሚያስፈልግህን ነገር ለእግዚአብሔር የማትናገርበት ቦታ ላይ ልትደርስ ትችላለህ ፡፡
ሀብት ፣ ስኬት ደግሞም በምድር ላይ ያለ ምቾት እነዚህ ነገሮች በራሳቸው መጥፎ አይደሉም ፡፡ ይህ በዚህ ነገር ሙሉ ለሙሉ ባለመወሰድና በምድር ላይ ካሉት ነገሮች ይልቅ እግዚአብሔርን የሰላም ምንጭህ አድርገህ በመፈለግ መካከል ያለ ውጥረት ነው ፡፡ እግዚአብሔር ለአንተ ገና ብዙ ይኖረው ይሆናል ፤ ነገር ግን ምንም እንኳ “ እግዚአብሔር ማነው ? “ ወደ ማለት ደርሰህ ቢሆንም እንኳ ፣ ዙሪያህን ማመስገንህን ቀጥል እንድሁም የእግዚአብሔርን ኃይል ፣ ጥበብ እና ጋሻ ፈልግ ፡፡ እግዚአብሔር ሰላምን ይሰጥሃል ደግሞም ሞገስን ፣ ምስናንና ክብርን ስትሰጠው እርሱ ይመራሃል !
“ ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው፤ ድህነትንና ባለጠግነትን አትስጠኝ፤ ነገር ግን የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ ፥ እንዳልጠግብ እንዳልክድህም፦ እግዚአብሔርስ ማን ነው? እንዳልል፤ ድሀም እንዳልሆን እንዳልሰርቅም፥ በአምላኬም ስም በሐሰት እንዳልምል ። “ - ምሳሌ 30፡8-9
ተጨማሪ ጥቅስ
- ምሳሌ 30:5 — “ የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች፤ እርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው ። “
- 1ኛ ተሰሎንቄ 5:18 — “ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና ። “
- ዕብራውያን 13:20–21 — “ በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።