Wisdom Books Proverbs

Iron Sharpens Iron

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 27-29 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 477 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዚህ ሳምንንት የምሳሌ መፅኀፍን እንጨርሳለን ፡፡ ምናልባትም ከኢዮብ ዉጪ ለማስተማር ምሳሌ አስቸጋሪ መፅሀፍ ነው ፡፡ ምሳሌ 27 ሀያ ሰባት ጥቅሶች ሲኖሩት እያንዳንዳቸዉ ቁጥሮች በግልፅ ስብከት መሆን ይችላሉ ፡፡ በተጨማሪም በዚህ ሳምንት የመክብብ መፅሀፍን በመጀመር እንጨርሳለን ፡፡ በዚህ ምዕራፍ የእግዚአብሄርን ቃል እንድናይ ዛሬ ዉይይታችንን እግዚአብሄር እንዲመራን እፀልያለሁ ፡፡

ትምህርት

ምሳሌ (27፡ 1-6)፡ ምዕራፉ ነገ በሚሆነዉ ነገር አትጎሩ በማለት በመገሰፅ ይጀምራል ምክንያቱም ዛሬ በቀረዉ ጊዜ ላይ ምን ሊሆን እንደሚችል ሀሳቡ/እዉቀቱ ስለሌለን (ቁጥር 1) ፡፡ ለነገ ስለሚኖራችሁ ወይም ዛሬ ስለሚያስፈልጋች ነገር አትጨነቁ ስለሚለዉ የቀድሞ እስራኤል ማስጠንቀቂያ አለው ፡፡ ያለን ሁሉ የዛሬ ነው ፤ እንዲሁም ኢየሱስ በዚህ ላይ አስተምሯል፣ የሚሰሙትን በመጨነቅ ምንም ነገር መቀየር እንደማይችሉ አሳሰባቸው (ማቴ 6፡ 23-34) ፡፡

እራሳችንን የምናመሰግን አይደለንም (ቁጥር 2) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ለጥበበኛ ሰዉ ራስን ማመስገን ከስፍራ ዉጪ የሆነና ለነገሮች መመቸት/መስማማት በማይሆን መልኩ የሚገልጥ ነው ፤ ምስጋና የሚያስደስት ልብስ ስለሆነ ለመልበስ እንፈልጋለን፣ ይህን ሁል ጊዜ ሌሎች በላያችሁ ላይ ሲያለብሷችሁ የተሸለ እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡ ሌሎችን ስናመሰግን ትኩረት የምናደርግ መሆን አለብን ፡፡ ቁጥር 3-4 ስለ ብስጭት፣ ስለ ኃይለኛ ንዴት፣ ስለ ቁጣና ስለ ቅናት ያወራል ፡፡ የተገለጠ ወቀሳ/ዘለፋ ከተደበቀ ፍቅር ይሻላል (ቁጥር 5) ፤ እንዲሁም የታመነ ወዳጅ ሊያቆስለን ይችላል ከጠላት የሆነ መሳም ደግሞ የባሰ ነው (ቁጥር 6) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ቁጥር 6 “ በፍቅር የተሰጠ የወዳጅ ማስተካከያ/እርማት ከአንገት በላይ/የዉሸት ከሆነ የፍቅር ድርጊት የተሸለ ነዉ “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡

ምሳሌ (27፡ 17)፡ ቁጥር 17 በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ በብዙ የወንዶች ቡድን ጥቅም ላይ እየዋለ ያለ ነው፡ “ ብረት ብረትን ይስለዋል ሰዉም ባልንጀራዉን ይስላል “ ፤ እርግጥ ነዉ ይህ ለሁሉም ይሰራል ፡፡ ይህ በሌላ ወዳጁ ላይ ስለሚናገረዉ ወዳጅ ከቁጥር 6 ጋር የተገናኘ ነው ፡፡ ብረት ብረትን ይስለዋል በሚለዉ ሀሳብ ዉስጥ መጓዝ/መሄድ እፈልጋለሁ ፡፡ ሀሚልተን ዶግ “ የክርስቲያኖች መሳሳል/መተራረም “ የሚል ርዕስ ያለዉ ፅኁፍ ፅፏል፣ በዚህም ዉስጥ የብረትን ታሪክና አስፈላጊነት ዘርዝሯል፡

  • 1300 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነሀስ በመሳሪያ መሰሪያነት ጥቅም ላይ የዋለ ዋነኛዉ ብረት ነበር ነገር ግን በተፈጥሮ የሚቀርበዉ ነሀስ አለቀ/አበቃ ፤ ስለሆነም ምናልባትም በፍልስጤማዊያን ብረት ጠንካረዉ ብረት ተፈጠረ ፡፡

ሌላ ማንም ሰራዊት የብረት መሳሪያ አልነበረዉም ምክንያቱም ፍልስጤማዊያን ከብረት መሳሪያ የሰሩበትን ሂደት በድብቅ አድርገዉት ስለ ነበር ፤ ይህ በግልፅ ፍልስጤማዊያን አደገኛ ጠላት አድርጓቸዉ የነበረዉ አንዱ ምክንያት ነው (1ሳሙ 13፡ 19-22) ፡፡ እስራኤላዊያን የእነርሱ መሳሪያዎች እና የተሳሉ የእርሻ መሳሪያዎች እንዲኖሯቸዉ ለፍልስጤማዊያን ይከፍሉ ነበር ፡፡ በሂደቱ ዉስጥ እስራኤላዊያን መሳሪያዎችን ስለ መሳል ሂደት ሁሉንም ተማሩ ፡፡

በቀጣዮቹ አስርዕርት አመታት ዉስጥ በንጉሳ ዳዊት ጊዜ አካባቢ በብረት የመስራት ሚስጥር ተሰራጭቶ በመዉጣቱ ከብራት እስራኤል የራሷን መሳሪያ መስራት ጀመረች ፡፡ ሰለሞን (ምሳ 27፡ 17) በፃፈ ጊዜ በእስራኤል ያለ ሁሉም ሰው በዉጊያ ነፃነታቸዉን አግኝተዉ ስለነበር መሳሪያን ስሎ የማስቀመጥን አስፈላጊነት ያውቃሉ ፡፡

ብረትን የመሳል ሂደት፡

መጀመሪያው የብረት ሰይፍ ለመስራት የብረቱን ጫፎች ለማጠፍጠፍ በብረት መዶሻ መቀጥቀጥ ነበር ፡፡

ሁለተኛው አንድ የብረት መሞረጃ ወይም የብረት ማዕድን ድንጋይ በጣም የሰላ ምላጭ ለማድረግ ይጠቀም ነበር ፡፡

ሰዎስተኛው ሌለኛዉ የብረት ቁራጭ የብረቱ ጫፍ እንደሰላ ለማቆየት ጫፉን ለመሳል ጥቅም ላይ ይዉሉ ነበር ፡፡

ብረት ብረትን ይስለዋል በሚለዉ መረዳት እነዚህን ጥቅሶች ተመልከቱ፡

ምሳ (13፡ 20)፡ “ ከጠቢባን ጋር የሚሄዱ ጠቢብ ይሆናል ፤ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል”፡፡

1ቆሮ (15፡ 33)፡ “ አትሳቱ ፤ ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል “ ፡፡

የትም ስፍራ ብንሆን በሆነ ሰዉ እንስተካከላለን/እንሳላለን ወይም ደግሞ የሆነ ሰዉ በእኛ ይስተካከላል/ይሳላል ፤ በእነርሱ ተፅዕኖ ይደረግብና ወይም በእኛ ተፅዕኖ ይደረግባቸዋል ፡፡ ለዚያም ነዉ ዙሪያችንን በእግዚአብሄር ወንዶችና ሴቶች ማስከበብ ያለብን ፡፡

ሀሚልተን “ ክርስቲያኖች እርስ በእርሳቸዉ ጊዜን በሚያሳልፉ ጊዜ የሚከሰት አስደናቂ መሳሳል/መተራረም ይኖራል …. ይህ አንድኛዉ ለሌላው እንደ ቅዱስ ሕዝብ፣ የንጉስ ካህናትና ለእግዚአብሄር ርስት እንደተለዬ ሕዝብ በዙሪያ በምንሆን ጊዜ በዚህ አለም ላይ አሸናፊዎች በመሆን ወደ ሰማያዊዉ አለም ለመምራት የሚያስፈልገንን መንፈሳዊ ጥቅም እና የሰላ/የሚቆርጥ ጫፍን/ጠርዝ እናገኛለን “ በማለት ይፅፋል ፡፡ ከእግዚአብሄር ሕዝብ ጋር እንድንሰባሰብ ታቅደናል/ድዛይን ተደርገናል ስለሆነም በዉጊያ ዉጤታማ እንሆናለን ፡፡

መደምደሚያ

ሀሚልተን ፅሁፉን ከሌሎች አማኞች ጋር ብረትን መሳል የምንችልበትን ዘዴ በመዘርዘር ያጠቃልላል፡

አንዱ ለሌላዉ ፍቅርን ማሳየት (ዮሐ 13፡ 34-35) ፡፡

አንዱ ለሌላዉ ኃጢዓትን መናዘዝ እና ከእርሱ/ከእርሷ ጋር መፀለይ (ያዕ 5፡ 16) ፡፡

ምስጋናን መዘመር እና የእግዚአብሄር ቃል ከሰዉ ጋር ማጥናት (ቆላ 3፡ 16) ፡፡

ለሰዉ ትህትናን ማሳየት (ፊል 2፡ 3-4) ፡፡

ለሰዉ በቃል እና በድርጊት ማበረታታትን መጋራት/ማካፈል (1ተሰ 4፡ 18, 5፡ 11, ዕብ 3፡ 13) ፡፡

ጥሩ ጊዜን ከሌሎች ጋር ማሳለፍ (ቆላ 3፡ 12-13) ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 774.

  2. Nelson’s Commentary, p. 774.

  3. Doug Hamilton, “The Sharpening of the Christian,” p. 1; available at http://camphillchurch.org/publication_files/the-sharpening-of-the-christian.pdf.

  4. Hamilton, p. 2.

  5. Hamilton, p. 31

ጥያቄዎች

  1. ምሳ (27፡ 14) ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? ይህን የሚመስሉ ወዳጆች አሉአችሁ ? ከእነዚያ ወዳጆች ዉስጥ አንድኞቹ ናችሁ ?
  2. ምሳ (27፡ 17) “ ብረት ብረትን ይስለዋል ሰዉም ባልንጀራዉን ይስላል “ ይላል ፤ እርስ በእርሳችን “ ልንሳሳልበት “ የምንችላቸዉ ጥቂት መንገዶች ምንድን ናቸው ?
  3. ምሳ (28፡ 6) “ በጠማማ መንገድ ከሚሄድ ባለጠጋ ያለ ነዉር የሚሄድ ድሀ ይሻላል “ ይላል ፤ ሀቀኝነት ከገንዘብ ይበልጥ ለምን አስፈላጊ ሆነ ? (ኢዮ 8፡ 20, ምሳ 22፡ 1, ማቴ 5፡ 33-37)
  4. ምሳ (28፡ 7) ምናምንቴ የሚለዉን ቃል ይጠቀማል ፤ የምናምንቴ ትርጓሜዉ ምንድን ነው፣ ይህ ለምን አባትንስ የሚያዋርድ ይሆናል ? (ዘፍ 25፡ 29-34)
  5. በምሳ (29፡ 11) እንደተጠቀሰው ቁጣችሁን ማጣት ለምን ሞኝነት/ስንፍና እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? ሰነፍ እንደ መሆን/ሞኝ እንደ መሆን ያልቆጠራችሁበት ጉዳይ/ነገር አለ ? (ማር 11፡ 15-17)
  6. በምሳሌ (27-29) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Proverbs 27:17

“Iron sharpens iron, and one man sharpens another.”

ብረትን ብቻውን ብታስቀምጡት ይዶለዱማል ፤ ፈጽሞም ነገሮችን በሚገባ መቁረጥ አይችልም ፡፡ ስለቱን ይዞ ለመቆየት በሌላ ብረት መሳልን ይፈልጋል ፡፡ በተመሳሳይ መንግድ ሰዎች ሰዎችን ይፈልጋሉ ፡፡ ሰዎች ብቻቸውን ሲሆኑ ይሰንፋሉ ፣ አይነቃቁም ምናልባትም ማስተዋል የጎደለው ውሳኔም ሊወስኑ ይችላል ፡፡ ነገር ግን ሁለት ሰዎች በአንድ ላይ በሚሆኑበት ጊዜ በእያንዳንዳቸው ውስጥ ያለውን አቅም ማውጣት ይችላሉ ፣ አሳቦችን ይካፈላሉ ፣ ይጫወታሉ ፣ ይበረታታሉ ደግሞም ይመካከራሉ ፡፡ እግዚአብሔር ሰዎች ከሰዎች ጋር እንድሆኑ ይፈልጋል ፡፡ ኢየሱስ ታላቂቱ ትዕዛዝ እግዚአብሔርንና ሌሎችን መውደድ እንደሆነ ተናግሯል ፡፡ እርሱ አናንተ ከሌሎች ጋር እንድትሆኑ ሲፈልግ ፣ አላማ ምክንያት አለው ፡፡

እያንዳንዱ ሰው ጓደኝነትን ለምን እንደማይፈልግ ምክንያት አለው ፡- “ እርግጠኛ ነኝ ስራ ይበዛበታል “ ወይም “ እሷ እንድኖራት ልትፈልግ አትችልም ፡፡ “ እነዚህ ምክንያቶች ሁለቱኑም ሰዎች ብቸኛ አድርገው ያስቀራሉ ፡፡ አንድኛችሁ ለሌላኛው ናችሁ ! በጸሎት እግዚአብሔርን ምሪት ጠይቁ ፡፡ እናም ከሆነ ሰው ጋር የሆነ ነገር ጀምሩ ፡፡ ጓደኞች ሁኑ ፡፡ በቃ በሰዎች ፊት ታዩ ፡፡ እናም ከዚያ ደጋግማችሁ ታዩ ፡፡ እናም ወድያውኑ ትለምዱታላችሁ ደግሞም ለጌታ እና እርስ በእርሳችሁ ባላችሁ ፍቅር አማካኝነት እርስ በእርሳችሁ መሳሳል ትጀምራላችሁ ፡፡ ምን ትጠብቃላችሁ ? ዛሬ ጸልዩና የሆነን ሰው አግኙ !

“ ብረት ብረትን ይስለዋል፥ ሰውም ባልንጀራውን ይስላል ። “ - ምሳሌ 27፡17

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ምሳሌ 27:9 — “ ሽቱና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤ እንዲሁ ነፍስ በወዳጁ ምክር ደስ ይላታል ። “
  • መክብብ 4:9–10 — “ ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል ። ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውን ያነሣዋልና፤ አንዱ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ጊዜ ግን የሚያነሣው ሁለተኛ የለውምና ወዮለት ። “
  • ዮሐንስ 15:12 — “ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት ። “