A Collection of Solomon's Proverbs
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 25-26 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ምሳሌ 25 “ የሕዝቅያስ ስብስብ “የተሰየመ ነው ፡፡ በኔልሰን ማብራሪያ መሰረት “ በምሳ (25-30) የተሰበሰቡት ምሳሌዎች በይሁዳ ንጉስ በሕዝቅያስ አስፈላጊ የለዉጥ ተግባሮችን እንደሚያንፀባርቁ “ ነው ፡፡ የሕዝቅያስ አባት አካዝ ጣዖቶችን በማምለክ እና ልጆችን በመሰዋት ከእግዚአብሄር ዞር ብሎ ነበር ፤ በዚህም ምክንያት ይሁዳ ከፍተኛ ጥፋት በአሶር እና በእስራኤል የሰሜን መንግስት ደረሰበት ፡፡ ሕዝቅያስ ዙፋኑን ሲያስብ ሁሉንም የጣዖት ተግባሮች እና ማዕከላት አስወገደ፣ የቤተ መቅደሱንም አምልኮ አደሰ በተጨማሪም የፋሲካን ሀገራዊ አምልኮ መለሰ ፡፡ ሕዝቅያስ ሕዝቅያስ ቀድመዉ በምሳሌ መፅሀፍ ተካተዉ የነበሩትን የሰለሞንን ምሳሌዎች አግኝቶ ኮፒ አደረጋቸው ፡፡
ትምህርት
ምሳሌ (25፡ 1-5)፡ በዚህ ምዕራፍ ሁሉም ጥቅሶች ወደ መጨረሻዉ ጥቅስ ያመለክታሉ ፡፡ ንፁህ ያልሆነ ነገሩን ስታስወግዱ ብር ይኖራችኋል (ቁጥር 4) ፡፡ ኃጢዓንን/ክፉዎችን ስታስወግዱ ንጉስ ይኖራችኋል ፡፡ ሕዝቅያስ አባቱ በይሁዳ ፈቅዶላቸዉ የነበሩትን ርኩሰት እና ኃጢዓቶችን አስወገደ ፡፡
ምሳሌ (25፡ 6-7)፡ ራሳችሁን ከፍ ከፍ አታድርጉ ምክንያቱም አስፈላጊ እንድሆናችሁ ስለምታስቡ (ቁጥር 6) ፤ ይልቁንም በንጉስ እዉቅና ቢሰጣችሁ ወይም ወደ ፊት ብትጠሩ የተሻለ ነው (ቁጥር 7) ፤ ለራሳችሁ ክብርን አትጠይቁ እግዚአብሄር በዚያ ስፍራ እንዲያስቀምጣችሁ ፍቀዱ እንጂ ፤ ያ ራስን መቆጣጠር ይፈልጋል ፡፡
ምሳሌ (25፡ 8-11)፡ ሌሎችን ወደ ፍርድ በመዉሰድ ሂደት ላይ ዝግ ያላችሁ ሁኑ (ቁጥር 8) ፤ ይህ የመናገር ችግር/ሁነት ብቻ ሳይሆን ራስን የመቆጣጠርም ነው ፡፡ ከተፎካካሪህ ጋር ንግግርህ ጀምር እንጂ እጅህን አትግለጥ (ቁጥር 9) ፤ በተጨማሪም ይህ ስለ መለየት እና ራስን ስለመቆጣጠር ነው (ቁጥር 10) ፡፡ “ የጊዜዉ ቃል እንዲሁ ነው “ (ቁጥር 11) የሚለዉ ቃል የሆነ ነገርን በትክክለኛው ጊዜ ላይ ስትናገሩ - ያ ፅሁፍ፣ ኢ-ሜይል፣ ስልክ፣ ደዉል፣ ንግግር - “ በብር ፃህል ላይ እንዳለ የወርቅ እንኪይ “ (ቁጥር 11) እንደሆነ ያመለክታል ፡፡ ይህ ራስን መቆጣጠር ይፈልጋል ምክንያቱም አንድ ቃል ለመናገር በምትጠብቁ ጊዜ ትክክለኛ ጊዜ ስለሚሆን ፡፡
ምሳሌ (25፡ 12-15)፡ እንደ ገና አንድ የጥበብ ቃል በትክክለኛዉ ወቅት እና ጊዜ ላይ በምትናገሩ ጊዜ የወርቅ ማሰሪያ ወይም የወርቅ ጌጥ ከነበረ ሌሎች ሊቀበሉት ይችላሉ ፡፡ ሁሉም ነገር ራስን ስለመቆጣጠር ነው ፡፡ እንዴት የለዘበች ንግግር/የተረጋጋ ንግግር አጥንትን ይሰብራል (ቁጥር 15) ? በማስተዋል እና በእርጋት ጥቅም የሚጠቀሙ ቃላቶች የአየሩን ፀባይ እና ሁኔታዉን መስበር ይችላል ፡፡ በመረጋጋት/በለዘብታ የሚናገር በመጮኽ እና በመነጫነጭ ከሚናገር የተሸለ መልካም ነገሮችን ማድረግ ይችላል ፡፡
ምሳሌ (25፡ 16, 27)፡ የሚያስፈልጋችሁን ብቻ ዉሰዱ ፤ የማንኛዉም ነገር መብዛት - መልካም ነገር መብዛትም ቢሆን እንኳን - ለህመም እና ለጉዳት መንስኤ ሊሆን ይችላል ፤ ይህ ራስን መቆጣጠር የሚያስፈልገዉ ሌላ ምሳሌ ነው ፡፡
ምሳሌ (25፡ 17)፡ በወዳጃችሁ ቤት እግር አታብዙ/ብዙ አትቆዩ (ቁጥር 17) ፤ ሁል ጊዜ የሆነ ነገር የምትበደሩ ወይም በዙሪያ የምታደፍጡ አትሁኑ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ፡ “ የበዛ ወዳጅነት አስቸጋሪ ይሆናል “ በማለት ይናገራል ፡፡
ምሳሌ (25፡ 18-26)፡ እነዚህ ሁሉ ጥቅሶች በቁጥር 28 ላይ ላለዉ ፅሁፍ መስሪያዎች ናቸው ፤ የኢየሱስ ቃል በማቴ (5፡ 43-48) የእነዚህን ጥቅሶች ትምህርት ያጠናክራል ፡፡ በግልፅ ኢየሱስ ጎረቤቶቻችሁን/ወዳጆቻችሁን እንዴት እንደምትወዱና ከጠላታችሁ ጋር እንዴት መስተጋብር መፍጠር እንዳለባችሁ እያወራ ነበር ፤ በአጠቃላይ በጠላቶቻችሁ ላይ ስለሚኖረዉ ፍቅር፣ ማንን እንደምታገቡ ስለመጠንቀቅ፣ ከሌሎች ጋር መልካሙን ዜና ስለ መናገር እና በክፉዎች/በክፋት ስላለመሸነፍ ነው ፡፡
ምሳሌ (25፡ 28)፡ ስሜታችሁን ካልተቆጣጠራችሁ ራሳችሁን ለሁሉም ሰዎ በማጋለጥ/ራስን አሳልፎ በመስጠት ዋስትናችሁ እንዲወርድ እየፈቀዳችሁ ነው ፡፡ ራስን መግዛት ከመንፈስ ቅዱስ ይመጣል (ገላ 5፡ 22-23) ፤ ራስን መግዛት የላችሁም ማለት ከመንፈስ ይልቅ በስጋ እየሰራችሁ ነዉ ማለት ነው ፡፡ በቤተሰብ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ድርጅቶች ስለ ራስን መግዛት፡ “ ራስን መግዛት ለታላቅ አላማ ስሜትን ወይም ታላቅ ደስታን የማዘግየት ባህሪይ ነው ፤ ራስን መግዛት መለማመድ ዋናዉ ግቡ ክርስቶስን በአለም ላይ መምረጥ ነው ፤ ፈተናን የማሸነፍ ኃይል እና ራስን የመግዛት ተግባር ከእግዚአብሄር መንፈስ የሚመጣ ነው “ በማለት እነዚህን ነገሮች ጠቅሰዋል ፡፡
ክርስቲን ዌዘርል “ ራሳችንን ስንገዛ አምላካችንን እና ወንጌሉን እናሳያለን “ ብሏል ፤ በሌሎች ላይ ትዕግስትን እናሳያለን ፤ ቃላችንም የሚያነፃ ይሆናል ፤ የምንለዉን እንመለከታለን ፡፡ ራስን መግዛት በምንተገብር ጊዜ በክፉ ወይም በኃጢዓት ላይ አንገኝም/አንሳተፍም ፡፡ ዌዘርል “ ራሳችንን ስንገዛ ነፍሳችንን እንጠብቃለን “ በማለት ቀጠለ ፤ ራስን መግዛት ተግባራዊ ስናደርግ ለምኞት የመጋለጥ እድላችን የቀነሰ ነው ፡፡ ለራስን መግዛት የግሪክ ቃል “ የራሱን ፍላጎትና መነሳሳት የሚያዝዝ በተለይም የፍትወት ፍላጎት የመግዛት ባህሪይ እንደሆነ የተገለፀ “ ኢግክራቲያ ነው ፡፡ በሌላ አነጋገር እነዚህ ፍላጎቶች በሚገባ ስሜቶች ናቸው ፡፡ ለእኛ ዋነኛ ምሳሌአችን የተፈተነ ቢሆንም በሕይወቱ ኃጢዓት ሰርቶ ያልነበረው ኢየሱስ ነው (ዕብ 4፡ 15) ፤ ኢየሱስ እነዚህን ፈተናዎች አገልግሎአቸዋል ፤ ራስን መቆጣጠርም ተጠቅሞ ነበር ፡፡ ሉቃ (22፡ 42) ኢየሱስ የምድራዊ ሞቱን ከመሞቱ በፊት ወደ እግዚአብሄር “ ይህን ፅዋ ከእኔ ዉሰድ “ በማለት እንደ ፀለዬ ይናገራል ፡፡ ኢየሱስ በመሰቀል ዉስጥ ማለፍ አልፈለገም ነበር ነገር ግን ለአባቱ ፍቃድ ታዘዘ ፡፡
መደምደሚያ
WikiHow በሚለዉ ድህረ ገፅ ላይ ስጋን ለመግዛት ወይም ለመገሰፅ የተገለፁ ደረጃዎችን አዘጋጅቷል ፤ መጀመሪያዉ በልምምድ ጊዜ ዉስጥ ማለፍ(ዕብ 12፡ 11)፣ ሁለተኛው የስጋን ፍትወቶችን/ምኞቶችን መግደል (ሮሜ 8፡ 13, ቆላ 3፡ 5) ፤ ሰዎስተኛው ራስን መግዛት ለመዉደድ መማር (1ቆሮ 6፡ 12) ፤ አራተኛው ትኩረታችሁን በሌሎች ላይ ሳይሆን በራሳችሁ ላይ ማድረግ (ማቴ 7፡ 1-3) ፡፡ ሌሎች ራስን መግዝት ቢጠቀሙም ባይጠቀሙም አያሳስባችሁ ፡፡ አምስተኛው ራስን መካድ (ሉቃ 9፡ 23) ፤ ስድስተኛው የመጨረሻ ዉጤቱን በምልከታ ዉስጥ ማድረግ (ዮሐ 12፡ 24) ፤ በመጨረሻም የራስን መግዛትና የራስን መገሰፅ አስፈላጊነት መረዳት (ማቴ 10፡ 38) ፡፡
ራስን መግዛት እየተጠቀማችሁ ካልሆነ ከእርሱ ይልቅ በብዛት ስለራሳችሁ የምታደርጉ ናችሁ ፡፡ በስጋ በመስራት/በመተግበር ስፍራ ላይ እንዳትኖሩ ፤ ይልቁንም በእግዚአብሄር መንፈስ መስራት ላይ አትኩሩ ፤ ስሜታዊ ስንሆንና ራሳችንን ስንገዛ የእግዚአብሄር መንፈስ በነፃነት መንቀሳቀስ ይችላል ፡፡
6 Strong’s Concordance #1466: egkrateia; available from https://www.bibletools.org/index.cfm/fuseaction/Lexicon.show/ID/G1466/egkrateia.htm.
1 Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 773.
Nelson’s Commentary, p. 773.
Focus on the Family, “Got Self-Control?” Available from https://www.focusonthefamily.com/parenting/spiritual-growth-for-kids/fruit-of-the-spirit/got-self-control.
Kristen Wetherell, “The Eternal Importance of Exercising Self-Control”; available from https://unlockingthebible.org/2016/04/the-eternal-importance-of-exercising-self-control/.
Wetherell, available online.
WikiHow, “How to Discipline Your Flesh as a Christian”; available from https://www.wikihow.com/Discipline-Your-Flesh-As-a-Christian.
ጥያቄዎች
-
በአጠቃላይ የምሳሌ መፅሀፍ ምክርንና የማስተዋል ምክሮችን ይሰጣል ፤ ለሌሎች መናገር የምትወዱት ሲጀመር መፅሀፍ ቅዱሳዊ የሆነ ምሳሌ አላችሁ ? ከምታገኟቸዉ እና ከምሳሌአቸዉ ከምትማሩት አስተዋይ ሰዎች በማዳመጥ ሳምንታችሁን ተጓዙ ፡፡
-
በምሳ (25፡ 3) ላይ አሰላስሉ ፤ ይህ ስሜታችሁን ይጎዳል ? ምድራዊ ነገስታትን ከሰማያዉ ንጉስ ጋር እንዴት ታወዳድራላችሁ ? (ዳን 2፡ 47, 1ጢሞ 6፡ 15, ራዕ 17፡ 14, 19፡ 16)
-
“ ብዙ መልካም ነገር ሊኖራችሁ አይችልም “ የሚል ንግግር ሰምታችሁ ታውቃላችሁ ? በምሳ (25፡ 16) መሰረት ይህ እዉነት ነው ? ብዙ መልካም ነገር መኖር መጥፎ ነገር ሊሆን ለምን እንደሚችል ምን ታስባላችሁ ? የዚህን ምሳሌ ተናገሩ/ጥሩ ፤ (ዘጸ 16፡ 17-20፣ ዘኁልቁ 11)
-
ምሳ (25፡ 17) ቶሎ ቶሎ ስለመምጣታችሁ ምን ይላል ? በግል አስተያየታችሁ ይህ ሁል ጊዜ ጉዳይ/እዉነት ነው ?
-
በምሳሌ 26 ለአለቆች ምክር የተሰጠ እንደሆነ የት ላይ ታያላችሁ ? ይህን ላደረገ ሰዉ ሰርታችሁ/አድርጋችሁ ታውቃላችሁ ? ሁሉንም ድፓርትመንት ወይም የስራ ስፍራዎች ላይ እንዴት ተፅዕኖ አደረገ ?
-
በምሳሌ 26 ሽንገላ ከዉሸት ጋር እንዴት የተነፃፀረ ነው ? ይህ ለሸንጋይ ሰዎች መጥፎ ነገር ነው ? ለምን ወይስ ለምን አይደለም ?
-
በምሳሌ (25-26) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Proverbs 25:28
“A man who does not control his temper is like a city whose wall is broken down.”
በህይወትህ ውስጥ መገዛት ያቃተው ክፍል ካለ እጆችህን አንሳ ፡፡ ራስህን ማስቆም ከባድ ነው አይደል ? በልጆችህ ወይም በባለቤትህ ላይ መጮኽ አትፈልግም ፡፡ ሰዎችን ሁልጊዜ በከባድ አስተያየቶች መተቸት አትፈልግም ፡፡ እዳ እንድኖርብህ አትፈልግም ፡፡ በቃ ምን ማድረግ እንዳለብህ አታውቅም እንድሁም ከቁጥጥር ውጪ እንሆንክ ይሰማሃል ፡፡ እና ግን ምን እንደሆነ ከማወቅህ በፊት ትዘገይና ጥፋት ይፈጸማል ፡፡ ከባባድ ሁኔታዎችን ለመቆጣጠር ስትጥር ፣ ራስህን መቆጣጠር ያቅትሃል ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ በዚህ ቦታ ውስጥ ብቻህን አይደለህም ፡፡
አሁን ራስህን መቆጣጠር ካቃተህ ፣ እረፍት አድርግ ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የስጋን ነገር እንድትገድል ይናገራል ፡፡ በመጀመሪያ ለራስህ ልትሞት እናም ከዚያ ይህንን የህይወትህን ክፍል ለጌታ አሳልፈህ ልትሰጥ ያስፈልግሃል ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል አንብብ ፤ ምናልባትም ደግሞ እራስን ስለ መግዛት በሚያወሩ የመጽሀፍ ክፍሎች ላይ አትኩር ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ይሞላህ ዘንድ ፍቀድ ፡፡ በጌታ ላይ ስታርፍ ስትታመን ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ይመራሃል ፡፡ በቃሉ አዕምሮህን ለማደስ ጊዜ ውሰድ ፡፡ ለአንድ ቀን ብቻ አይደለም ፣ ነገር ግን በየቀኑ እንጅ ፡፡ አንተ ከማወቅህ በፊት ፣ መንፈስ ይመራሃል ደግሞም አሳብህን ፣ እርምጃህን ያስተካክላል እንድሁም ራስን የመግዛት ፍሬን እንድታፈራ ያስችልሃል ፡፡ እግዚአብሔር ጥሶ የማለፍ የመውጣት አምላክ ነው ፡፡ አንተ በየቀኑ በእርሱ ስትኖር ፣ እርሱ በመንፈሱ ፍሬዎች እንደሚሞላህ እመን ፡፡
“ ቅጥር እንደሌላት እንደ ፈረሰች ከተማ፥ መንፈሱን የማይከለክል ሰው እንዲሁ ነው ። “ - ምሳሌ 25፡28
ተጨማሪ ጥቅስ
- ሮሜ 8:13 — “ እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ ። “
- ሮሜ 12:2 — “ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ ። “
- ገላትያ 5:22–23 — “ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው ። እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።