ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ምሳሌ 24 ረጅም ፅሁፍ ስለሆነ እግዚአብሄርን እንዳስተምር የሚፈልገዉን አጉልቶ እንዲያሳየኝ ጠየኩት አደረገዉም ፤ ተጨንቄአለሁ ነገር ግን ስሜቴ ተነሳስቷል ! ዛሬ ስለ ማር እናወራለን ፡፡ ስለ ማር አስፈላጊነት እናወራለን እንዴት ከመፅኀፍ ጋር እንደሚገናኝ እና እንዴት ለምሳሌ መፅሀፍ ካለን ቃል ጥበብ ከሚለዉ ጋር እንዴት እንደሚገናኝ እናወራለን ፡፡ ዛሬ አዲስ የሆነ ነገር እንሞክራለን ! የሚመጣዉ መሲህ ጥላ እንዴት ሊያሳይ እንደሚችል ማርን በተለያዬ አመለካከት እናቀርባለን ፡፡ እዙህ ብዙ አይነት የማበረታታት አይነቶች አሉ ፤ በዚህ ክፍል መጨረሻ ላይ በመፅኀፍ ላይ ማር ምን ማለት እንደሆነ እንድታዉቁ እፈልጋለሁ ፡፡
ትምህርት
ምሳሌ (24፡ 1-12)፡ ራሳችሁን በጥበብ እና በእዉቀት ክበቡ ፤ ያ እዉቀት በዙሪያችሁ እንዲሆኑ ከመረጣችኋቸው ሰዎች ይመጣል ፤ ይህ ኃይለኛ የፍትህ ፅሁፍ ነው ፡፡ በዙሪያችሁ ስላሉት የሚያስፈልጋቸዉን ነገር ለማወቅ ኃላፊነትን መዉሰድ አስፈላጊ ነው ፡፡
ምሳሌ (24፡ 13-14)፡ የምንጊዜም ጥበበኛ ሰዉ ከሆነዉ ከሰለሞን ለልጁ ምክሩ ማር እንዲበላ ነው ፡፡ ሰለሞን ማርን ከጥበብ ጋር አወዳደረ ፤ ማር መልካምና ጣፋጭ ከሆነ ጥበብ መልካምና ጣፋጭ ነው ፡፡ በተጨማሪም ማር እና ጥበብ ሁለቱም ተስፋን እና እድልን እንደሚያመጡ ፅፏል ፡፡
የማር ጥቅሞች ምንድን ናቸዉ ? “ በመፅሀፍ ቅዱስ ስድስት ጥቅስ መሰረት ስለ ማር “ መፅኀፍ ቅዱስ የሚለዉ፡
- “ ተስፋይቱ ምድር ወተትና ማር የምታፈስስ በመባል ተገልፃለች “ ፤ ይህን ሀሳብ ለማጠቃለል የምጠቀመዉ ቃል “ መትረፍረፍ “ ነው (ዘጸ 3፡ 6-8) ፡፡
- “ ማር የመልካም ጤንነት ምልክት ነበር “ (1ሳሙ 14፡ 24-27) ፡፡
- “ ማር የከበረ ስጦታ ነበር “ (ዘፍ 43፡ 11) ፡፡
- “ የጥበብ መፅሀፍት የማርን መልካምነት በማሞገስ ይናገራሉ “ (ምሳ 24፡ 13) ፡፡
- “ መጥምቁ ዮሐንስ በማር ኖረ “ (ማቴ 3፡ 1-4) ፡፡
- “ ማር በራዕይ መፅሀፍ ላይ አለ “ (ራዕ 10፡ 7-11) ፡፡
የማር አይነቶች ምንድን ናቸው ? በመፅሀፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ማብራሪያ መሰረት አራት አይነት ማር በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ተጠቅሷል፡
ይአር - የንብ ማር ወይም ደግሞ በእንጨት ዉስጥ የሚገኝ ማር (1ሳሙ 14፡ 24, 27)
ኖፍቴህ - የሚጠባጠብ ማር (መዝ 19፡ 10, ምሳ 5፡ 3)
ደባሽ - “ ከዛፎች የሚጣራ የተክል የሆነ የንብ ማር “ (ዘፍ 43፡ 11, ዘጸ 3፡ 17)
ፆፍ - “ ማር የሞላበት የማር ወለላ (ምሳ 16፡ 24) “ ፡፡
ስለ ማር አጠቃላይ እዉነቶቹ ምንድን ናቸው ? “ እንደ ማር አገላለፅ ከፈጣረዉ የመፈወስ ስጦታ የተሰጠው ማለት ነው “ ፡፡
20,000 የንብ ዝርያዎች አሉ ፤ ሰባቱ ዝርያዎች የማር ንቦች ናቸው ፡፡
“ የማር ንቦች የሚመቹ አበባዎችን በመፈለግ ወለላዎችን ይሰበስባሉ “ ፡፡
ቀጭኑ፣ በቀላሉ የሚበሰብሰው፣ ጣፋጩ ፈሳሽ ወለላዉ በማር ንብ ወደ ሚመች፣ ከፍጠኛ መጠነቁስ እና ከፍተኛ የምግብ ጉልበት ወዳለዉ የሚቀየር ነው “
“ የማር ንቦች ሁለት ጨጓራ አላቸዉ ወለላ ለመያዝ የሚጠቅም አንድ የማር ጨጓራ እና የተለመደ ጨጓራ፡፡
“ የማር ንቦች የማር ጨጓራቸዉን ለመሞት ከ1,500 የሚበልጡ አበባዎችን ይጎበኛሉ/ይቀስማሉ “ ፡፡
“ በወለላዉ ላይ ወደ ማር መቀየር የሚጀምሩ ኢንዛይሞችን ይጨምራሉ “ ፡፡
የምንበላዉ ማር የንብ ማሮች በተደጋጋሚ የሚያመነዥኩት(አንዳንድ ጊዜ በሌላ የማር ንብ አፍ ዉስጥወይም በቀጥታ ማር ወላላ ዉስጥ) እና የሚያደርቁት አስፈላጊ ወለላ ነው ፡፡
“ ይህ የመድረቅ ሂደት በሰራተኛ ንቦች ከማር እንጀራዉ ላይ እርጥበቱን ክንፋቸዉን በማርገብገብ በማስወጣት ያፋጥኑታል “ ፡፡
እግዚአብሄር ይህን ማር የመስራት ሂደትን በንብ ዉስጥ እንዴት እንዳስቀመጠዉ የሚያስደንቅ ነው ፤ ማር እና ወተት የምታፈስሰዉ ምድር በምን የእግዚአብሄር ቃል ጥላ ነበር ?ፓስተር ማይክ ስቶርቲ “ (ማር እና ወተት) ጌታ የሆነዉን ኢየሱስ ክርስቶስን የእግዚአብሄርን ቃል ወክሎ እናገኘዋለን ፤ የእግዚአብሄር ቃል ምድር እስራኤል የተፃፈዉ የእግዚአብሄር ቃል እና የሚኖረዉ የእግዚአብሄር ቃል ሁለቱም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ ክርስቶስ ከተስፋይቱ ምድር የእስራኤል ተስፋ የተገባዉ ዘር ነው (ገላ 3፡ 16) “ በማለት ፅፏል ፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ቃል ማርና ወተት ነው ፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር መግቢያ መንገድ ነው ፡፡ ኢየሱስ ማር እንደሆነ ተናገረ ፡፡
ስቻፈር “ ማር ለጤናማ ህይወት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ነገሮች ኢንዛየሞችን፣ ቫይታሚኖችን፣ ሚኒራሎችን እና ዉሃ የያዘ ብቸኛዉ ምግብ ነዉ፣ እንዲሁም ደግሞ በተጨማሪ የአይምሮን ተግባር ከማሳደግ ጋር የተገናኜ ፀረ ወክሳጅ ፓይኖከምብሪን የያዘ ብቸኛዉ ምግብ ነው “ በማለት ይናገራል ፡፡ ክርስቶስ “ የሚያስፈልጋችሁ ሁሉም ነገር እና የምትመለከቱት ሁሉም ነገር ነኝ ፤ እኔ ያ ነኝ “ ይላል ፡፡
መደምደሚያ
አንዳንዶቻችሁ ይህ የተዘረጋ/የተጋነነ ነዉ ብላችሁ እንደምታስቡ አዉቃለሁ ነገር ግን ማር ወደ ኢየሱስ የሚያመለክት የእግዚአብሄር ቃል ነዉ እያልኩ ያለሁት ፡፡ በዶር. ካትሪን ማሬንጎ መሰረት የገሀዱ/የጥሬ ማሩ ስድስት ዋና ጥቅሞችን እነዚህ ናቸዉ፡
ማር “ ሰዉነታችሁን ከህዋስ ጉዳቶች ለመከላከል የሚረዳ ጥሩ የፀረ ወክሳጅ ምንጭ ነው “ ፤ ይህ ክርስቶስም የሆነዉ ነው ፤ እርሱ ጠባቂአችን ነው ፡፡
ማር “ የማይፈለጉ ባክቴሪያና ፈንገሶችን የመግደል ፀረ-ባክቴሪያ እና ፀረ- ፈንገስ ባህሪይ አለው “ ፤ ኢየሱስ ጠባቂአችሁ እና ሚከላከልላችሁ ነው ፡፡
ማር “ ቁስሎችን መፈወስ፣ የፈዉስ ጊዜን ማፍጠን እና ማመርቀዝን መቀነስ ይችላል “ ፤ ኢሳያስ ኢየሱስ የመጨረሱ ፈዋሽ እንደሆነ ፅፏል ፡፡
ማር “ ነፍሳት እንዳይቀርቡ የሚጠብቅ ወይም እፅዋት ከፀሀይ ጨረር የሚጋርድ/የሚከላከል የዕፅዋት ምግብ ነው “ ፤ ኢየሱስ ሰይጣንን እና አጋንንቶችን ከእኛ እንዲርቁ ያደርጋቸዋል ፡፡
ማር “ የመፍጨት ተግባራትን ይረዳል “ በእግዚአብሄር ቃል ስትሆኑ ለነፍሳችሁ ሰላምን የሚያመጣ የሚያረካ ነገር አለ ፡፡
ማር “ ቁስልን ያስታግሳል “ ፡፡
ስለ ማር ትልቁ ጉዳይ/ነገር ምንድን ነው ? የተስፋይቱን ምድር እና ማር በክርስቶስ በኩል እንቀበላለን ፤ እዉነቱ እንዳለን ካወቅን ስለ እዉነቱ የሆነ ነገር ማድረግ ያስፈልገናል ፤ ንቦች ያለማቋረጥ ማርን ለመስጠት እንደሚሰሩት ለሌሎች መልካሙን ዜና ማድረስ አለብን
1 Six Verses About Honey in the Bible; available at https://www.benefits-of-honey.com/honey-in-the-bible.html.
7 Marengo, 2018.
M.G. Easton, Illustrated Bible Dictionary: Honey, 3d ed. (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1897); in Public Domain; available at https://www.biblestudytools.com/dictionary/honey/.
Patrick Clark, Honey: A Healing Gift from the Creator, Creation.com; available at https://creation.com/gods-healing-gift-of-honey.
Mike Stortie, Christ-The Milk and Honey of the Promised Land, Bible Watchman.com; available at http://biblewatchman.com/milkandhoney.htm.
Susan Schaefer, Interesting Facts about Honey & Bees, WasatchBeekeepers.com; available at http://www.wasatchbeekeepers.com/2016/04/29/interesting-facts-about-honey-hon- ey-bees/.
Katherine Marengo, The Top 6 Raw Honey Benefits, Health Line; available at https://www.healthline.com/health/food-nutrition/top-raw-honey-benefits.
ጥያቄዎች
-
ምሳ (24፡ 1) በክፉ ሰዎ የቀናችሁ አትሁኑ ይላል ፤ ራሳችሁን የቀናችሁ ሆናችሁ አግኝታችሁት ታውቃላችሁ? ቀናተኛ በመሆን ዉስጥ አደጋ አለው ? መፅሀፍ ቅዱስ ሌላ ስለ ቅናት ምን ይላል ? ቅናት መልካም ነገር ሊሆን ይችላል ? (ምሳ 3፡ 31, ማር 15፡ 10, ሮሜ 11፡ 11, 14, ያዕ 4፡ 5)
-
አንዳንድ ሰዎች እዉቀትና ጥበብ ተመሳሳይ ነገር እንደሆኑ ያምናሉ ፤ ምሳሌ 24 ስለ እነርሱ/ስለ ሁለቱ ነገር ምን ይላል ? በመካከላቸዉ ያለዉ ልዩነት ምንድን ነው ? (መክ 7፡ 11-12, 1ቆሮ 8፡ 1)
-
ምሳሌ 24 ስለ አንድ “ ኃጢዓተኛ “ እና “ ፃድቅ ሰው “ ምን ይላል ? ጠላታችን ሲደናቀፍ እንደሰታለን ? ለምን ወይስ ለምን አንደሰተም ? (ምሳ 25፡ 21-22፣ ማቴ 5፡ 44)
-
በምሳሌ 24 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Proverbs 24:13–14
“Eat honey, my son, for it is good, and the honeycomb is sweet to your palate; realize that wisdom is the same for you. If you find it, you will have a future, and your hope will never fade.”
በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ማር የእግዚብሔርን ቃል ወይም ደግሞ ከእግዚአብሔር የሚሰጥ የልብ መሻትን ይወክላል ፡፡ ልክ ማር በተፈጥሮው ሰውነትህ ከህመም እንድያገግም እንደሚረዳው ደግሞም የታመመን ጉረሮ እንደሚያክም ሁሉ ፣ የእግዚአብሔርም ቃል በህይወትህ እንድሁ ያደርጋል ፡፡ ጭንቀት ፣ ፍርሀት ፣ ቁጣ ፣ ግራ መጋባት ወይም ደግሞ ብቸኝነት ይሰማሃልን ? የእግዚአብሔር ቃል የእረፍትና የእርዳታ ምንጭህ ነውና ወደ እርሱ ዘወር በል ፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል አንብብ ደግሞም ሳምንቱን ሙሉ ከቀን ወደ ቀን እግዚአብሔር ልብህን ይለውጥ ዘንድ ፍቀድ ፡፡
እግዚአብሔር ቃሉ ፈጽሞ እንደማያልፍ ተናግሯል ፡፡ እርሱ ፍጻሜና ተስፋ እንደሚሰጥህ ተናግሯል ፡፡ ቃሉ ለነፍስህ እረፍት ለአጥንትህ ደግሞ ፈውስ ይሆንልሃል ፡፡ ክርስቶስ ሰላምን ይሰጥሃል ፡፡ በየቀኑ በቃሉ ላይ እረፍትን ስታደርግ ስትታመን ለነፍስህ ምን እንደሚሆንላት ተመልከት ፡፡ ወደ ፊት ተራመድ በመብላት ላይ ሳለህም እንድ ማንኪያ ማር ብላ !
“ ልጄ ሆይ፥ መልካም ነውና ማር ብላ፤ ወለላም ለጣምህ ጣፋጭ ነው ። ጥበብም ለነፍስህ እንዲሁ እንደሚሆን እወቅ ብታገኘውም ፍጻሜህ መልካም ይሆናል፥ ተስፋህም አይጠፋም ። “
- ምሳሌ 24፡13-14
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘጸአት 3:7-8 — “ እግዚአብሔርም አለ፦ በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ ፤ ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ሰፊይቱና ወደ መልካሚቱ አገር ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ ። “
1ኛ ሳሙኤል 14:29 — “ ዮናታንም፦ አባቴ ምድሪቱን አስቸገረ፤ ከዚህ ማር ጥቂት ብቀምስ ዓይኔ እንደ በራ እዩ ። “
መዝሙር 119:103 — “ ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።