Dedicate A Child
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 22-23 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ይህ ትምህርት/ክፍል 110 ነው ፤ ያ ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ ? በጥበብ ፅሁፍ ላይ ያለማቋረጥ 110 ቀን ሆነ ማለት ነው ፡፡ ከዚህ በኋላ ሰዎች የማስተዋል ስሜት እንደሚሰማቸዉ ተስፋ አደርጋለሁ ፤ እስካሁን በምሳሌ መፅሀፍ ብዙ ስለማዉራት፣ ትክክለኛ ሚስት ስለመምረጥ እና ትክክለኛዉን መንገድ ስለመያዝ ተወያይተናል ፡፡ ምሳሌ ከእዉነት የወርቅ ክምችት/ወርቃማ እዉነቶች የተሰራ ነው ፡፡ ተስፋዬ እነዚህን ጥቅሶች በመዉሰድ በሚረዳ መልኩ በህይወታችሁ ላይ እንደምትተገብሩት ነው ፡፡
ትምህርት
ምሳሌ ( 22፡ 1)፡ ብዙ ገንዘብ ከመኖር ይልቅ መልካም ስም መኖር ይበልጣል ፤ እያወራን ያለነዉ ስለ ዝና ነው ፡፡ በአለም ላይ ያለዉ ገንዘብ ሁሉም ሊኖራችሁ ቢችልም አስቸጋሪ ሰዉ በመሆን ትታያላችሁ ፤ ማንም ሰዉ ያንን ለመሆን አይፈልገዉም ፡፡
ምሳሌ (22፡ 2)፡ በለጠጋ ከሆናችሁ እግዚአብሄር ነዉ ያደረጋችሁ ፤ ድሀም ከሆናችሁ እግዚአብሄር ነዉ ያደረጋችሁ፡፡ አድሎን ለማሳየት እንዳልሆነ መጠንቀቅ አለብን (ያዕቆብ 3) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ይህ ማለት በድሆች ላይ ለባለጠጎች የሚያዳሉት (ያዕቆብ 3) የመፈጠራቸዉን አላማ ብቻ ሳይሆን የሳቱት የፈጠረዉንም እየሰደቡ/እየዘለፉ ነዉ ማለት እንደሆነ “ ያጠቃልላል ፡፡
ምሳሌ (22፡ 3)፡ ጠንቃቃ ሰዉ አርቆ አሳቢና አስተዋይ ሰዉ ነው ፤ ጠንቃቃ ሰዉ በአደጋ ጊዜ ሽፋንን ይወስዳል ፡፡ ሰነፍ ሰው ያለሚታይ ጥበብ ይሄዳል ፡፡
ምሳሌ (22፡ 4)፡ ይህ ጥቅስ የመልካም ህይወት ጥሩ መልክ ነው፡ ትህትና፣ ባለጠግነት፣ ክብርና ህይወትን የያዘ ፡፡
ምሳሌ (22፡ 5)፡ ጠማማን መንገድ ከመረጣችሁ ችግርና ህመም የሚሆን ማላሽ አለው ፡፡
ምሳሌ (22፡ 6)፡ “ ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም “ ፤ በዚህ ፅሁፍ ዉስጥ ሳስተምር ስለልጆቼ እያሰብኩ ነው ፡፡ አስተምር የሚለዉ ቃል አስለምድ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል ፡፡ አስተምር/አስለምድ የሚለዉ ቃል በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሰዎስት የተለያዩ ጊዜ ላይ ይከሰታል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ አስለምድ/አስተምር የሚለዉ ቃል ከዕብራዊያን የመሰጠት ከተለመደዉ የበዓል ስም አንኩህ ከሚለው ጋር የተገናኘ ነው…. ይህ የቤተሰብ ዋና/መርሀዊ ተግባር ልጆችን ከእግዚአብሄር እንደ ኃላፊነት በመቀበል ከዚያም በኑሮአቸዉ ለእግዚአብሄር መንገድ መስጠት/መለየት እንደሆነ “ ይገልፃል ፤ (ዘዳ 20፡ 5፣ 1ነገ 8፡ 63፣ 2ዜና 7፡ 5) ፡፡ በመፅኀፍ ላይ ይህ ትምህርትና ልምድ በመፅሀፍ ላይ መለየት/መቀደስን ይወክላል ፡፡
ከቤተልሄም ኮሌጅ እና መንፈሳዊ ት/ቤት ዘሮቼይ ጃሶን፡ “ ስለተለመደ ለኃይማኖት እና ለተገቢ አቅጣጫ የመቀደስን ተገቢ መዋቅሮች ትርጉምን ያደከሙ በመሆን እንደሚስቱ “ ፅፏል ፤ ስለምናደርገዉ ነገር መለየት ያስፈልገናል ፤ ይህ መለየት በዓላትንም ያካትታል ፡፡ ዘሮቼይ በመቀጠልም፡
“ ምሳሌ በምሳ (22፡ 6) ላይ ያለዉ የመቀደስ ተግባር በይበልጥ ወደ ወጣትነት ሲያድጉ የልጆቻችንን ልብ በማሰብ፣ በመረጋጋት እግዚአብሄርን የተደገፈ እረኝነት ላይ ያተኩራል - አንዴ ልጆች በራሳቸዉ የቤተሰቦቻቸዉን መንገድ ካወቁ/ከተገነዘቡ ሀሳባቸዉን/ፍላጎታቸዉን በዚያ ያስቀምጣሉ ፤ ለአባቶች እና ለእናቶች ይህ ቀላል ጥሪ አይደለም “፡፡
ይህ መለየት/መቀደስ የሚቀጥል ሂደት ነው ፡፡ ልጆቼ በማደግ ሂደት ዉስጥ ከጌታ ጋር እንዲጓዙ እንደምፈልግ እንዲረዱ እፈልጋለሁ ሁልጊዜም ይህን ማድረግ እወዳለሁ/እፈልጋለሁ ፡፡ ይህ ቀላል ተግባር አይደለም በተለይ ደግሞ በመፍራት በልጆቻችን ትዕግስት በምናጣ ጊዜ ፡፡ ልጆቻችሁን ለመለየት/ለመቀደስ ከአገልግሎት በዓል የሚበልጥ ነገር ስላለ የሚያስፈልጋቸዉን መንፈሳዊ እዉቀት የሰንደይ ት/ቤት እንደሚሰጣቸዉም ተስፋ እናደርጋለን ፡፡
ልጆች የእግዚአብሄር ስጦታዎች ናቸው (መዝ 127፡ 3) ፤ ልጆቻችን በረከቶቻችን ናቸው ፡፡ ልጆች ልጅ መሆንን ባቆሙ ጊዜ ትልቅ/ጎልማሳ ይሆናሉ ? ልጆቻችሁ ጎልማሳነትን ቢያልፉም እንኳን ሁልጊዜ የእናንተ ልጆች ናቸው ፡፡ በየቀኑ ይህን መስማት ቢፈልጉም ባይፈልጉም እዉነቱን ሁልጊዜ ከእነርሱ ጋር ተነጋገሩ (ዘኁ 25፡ 18፣ ዘዳ 6፡ 7-9፣ 12፡ 28) ፤ ለምሳሌ በሀና እና በሳሙኤል፣ በዮሴፍ እና በኢየሱስ፣ በአብርሃም እና በይስሐቅ እናም በመጨረሻ ጢሞቲዎስ እና በአያቱ ያለዉን ግንኙነት ተመልከቱ ፡፡ እነዚህን ወጣቱን ትዉልድ ለማስተማር እነዚህን እዉነቶች በልባችን ዉስጥ መያዝ ዋጋ አለው ፤ እዉቀቱ በእኛ ዉስጥ ከሌለ ለማካፈል እና ለማስተማር አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ፡፡ ልጆቻችንን በህይወት ሁለት ምርጫ እናዳለ ማስተማር አስፈላጊ ነገር ነው - የጥበብን መንገድ እና ህይወትን እና የሰነፍ/የሞኝ መንገድ እና ሞትን ፡፡
ልጆቻችንን ማስተማር ዉስጥ መገሰፅ አንዱ አካል በመሆን ይካተታል (ምሳ 3፡ 12, 29፡ 15, 17, ዕብ 12፡ 5-6, 10)፡፡ ዘሮቼይ “ ለራሳቸዉ በተዉንላቸዉ ጊዜ ልጆች/ወጣቶች ፍርድን በማጣት በስንፍና/በሞኝነት የተሞላ ልብ ይኖራቸዋል “ በማለት ፅፏል ፡፡ ተግሳፅ/ቅጣት ለምን አስፈላጊ ነው ? ብላቴኖች ማስተዋል የጎደላቸዉ ናቸው ፡፡ ዘሮቼይ “ ያለ ቅጣት ብላቴኖች ቤተሰቦቻቸዉን የማያከብሩ እንደሚሆኑ “ ፅፏል ፤ ባህሪን በማስተካከል ልጆች ቅጣታቸዉን እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ ነው (ምሳ 29፡ 15) ፡፡ በዚህ ተግሳፅ ሂደት ላይ መጓዝ አለብን ፤ ልጆቻችን ለእግዚአብሄር የተለዩ/የተቀደሱ እንዲሆኑ ስንፈልግ ከእርሱ አይለዩም ፡፡ ብላቴኖች በሆኑ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በየቀኑ ወደ ልጆቻችን መሙላት/ማስተማር አለብን ፡፡
ከልጆቼ ዉስጥ ሁሉም ለወንጌል በተለያዬ መልክ ምላሽ ይሰጣሉ ይህ በጣም አስቸጋሪ ነው ፤ ሁሉም ክርስቶስን ተቀብለዋል ነገር ግን ሁሉም በራሳቸዉ በተለያዬ ደረጃዎች ላይ ናቸው ፡፡ በእግዚአብሄር ላይ ፊታቸዉን ሊያዞሩበት የሚችል አንድ ቀን ሊኖር ይችላል ያ ሲሆን አላየሁም ነገር ግን ለምን ያን አደረጉ ?ስቴቨን ኮል “ ቤተሰብን መጉዳት ለልጆቻቸዉ የእግዚአብሄርን ፍቅር እና ይቅርታ ማድረግን እንደሚያሳይ “ ፅፏል ፡፡ ኮል የቤተሰቦቹን ኃብት እና ኩራት ትቶ የሄደዉ ነገር ግን በመጨረሻ በትህትናና በማስተዋል ወደ ቤቱ ተመልሶ ስለመጣው(ሉቃ 15፡ 11-32) ስለ ከንቱ/ስለ አባካኝ ልጅ ታሪክ ያደረጋቸዉ ጥቂት ሀሳቦች አሉ ፡፡ ኮል ያመለከተው፡
- “ አባቱ ተጎድቶ ነበር “
- “ የመገፋት/የመተዉ፣ የመዋረድ እና የጥፋተኝነት ስሜት ነበር “ ፤ እነዚህ ሁሉ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ነገሮች ናቸው ፡፡
“ አባቱ በፍቅር ስለነበር ለይቅርታ ዝግጁ ነበር “
የአባት ፍቅር፡ “ ያለ መግፋት ተወዉ፣ ጥልቅ የሆነ ጭንቀት ነበረው፣ ከልብ የመነጨ ርህራሄ ነበረው፣ የተገለጠ ጉጉት/ፍቅር ነበረው፣ ያልተቀየረ ትህትና ነበረው፣ ያልተገባ ለጋስነት እና ያልተገባ ተቀባይነት ነበረው “ ፡፡
እነዚህ ነገሮች ከሌሏችሁ በምድር ላይ ልጅ ተመልሶ እንዲመጣ ለምን ትፈልጋላችሁ ?
የአባት ይቅር ባይነት፡ “ይቅርታዉ ፈጣን ነበር፣ ሙሉ፣ ሁሉንም የረሳ፣ ዋጋ ያለዉ፣ የሚያድስ፣ ጥፋተኝነት የሚወቅስ አቀራረብ ያልሆነ እና የደበዘዘ ሳይሆን ንቁ ይቅር ባይነት ነበር “ ፡፡
መደምደሚያ
ወደ ወጣቱ ትዉልድ ላይ ማፍሰስ/ማስተማር አስፈላጊ ነው ፡፡ ከእኛ ዉስጥ ለጥቂቶቻችን ከቤተሰባችን በላይ መመልከት አያስፈልገንም ፤ ለሌሎች መሪነት በሚያስፈልጋቸዉ ነገር ላይ መፈለግ አለብን ፡፡ ፍፁም ቤተሰብ አይኖራችሁም ፤ ቀን በቀን በቤተሰባችሁ ስለሚደርስባችሁ ነገር ችግር የለዉም ልጆቻችሁን የማታስተምሩበት፣ የማትለዩበት እና የማትሞሉበት ምክንያት በፍፁም አይኖርም ፡፡ ያለማቋረጥ በቤተሰባችን ላይ ስናፈስስ የእግዚአብሄር ቃል ወደ ፍሬአማነት እንደሚመጣ ማመን እንችላለን ፡፡
4 DeRouchie
5 DeRouchie.
6 DeRouchie.
8 Cole.
9 Cole.
10 Cole.
11 Cole.
James Fraser, 12 Ways to Tame the Tongue (Reformation Scotland, Feb 1, 2018); available at https://www.reformationscotland.org/2018/02/01/12-ways-to-tame-the-tongue/.
Nelson’s Commentary, p. 771.
Jason DeRouchie, Train Up a Child in the Way He Should Go; available at https://www.desiringgod.org/articles/train-up-a-child-in-the-way-he-should-go).
Steven J. Cole, Lesson 73: A Model for Hurting Parents (Luke 15:11–32); available at https://bible.org/seriespage/lesson-73-model-hurting-parents-luke-1511-32,1999.
ጥያቄዎች
-
ምሳ (22፡ 6) ስታነቡ ተስፋዉ ከእግዚአብሄር እንደሆነ ያሳየናል ይህ እዉነተኛ ንግግር እንደሚሆን ታምናላችሁ ? በዚህ ማንኛዉም ልምድ ነበራችሁ ? እስካሁን የእግዚአብሄር ተስፋ አልፏል ?
-
በምሳ (22፡ 14 እና 23፡ 27-28) ጸሀፊዉ ስነ-ምግባር በሌላቸዉ ሴቶች ላይ ይናገራል ፤ በመፅሀፍ ላይ ከምሳሌ አጠገብ ስነ-ምግባር የሌላቸዉን ሴቶች ላይ ያስጠነቅቃል ? (ዘፍ 39፡ 9-12, ሮሜ 1፡ 26, 1ቆሮ 15፡ 33)
-
ምሳ (23፡ 13-14) አንብቡ ፤ እንደ አጠቃላይ ማህበረሰቡ እነዚህን ትዕዛዞች ይከተላል ? እነዚህን ትዕዛዞች ተከትሎ በነበረ አለም እንዴት የተለይ ይሆናል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ከእነርሱ ጋር ትስማማላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አትስማሙም ?
-
በምሳሌ (22-23) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Proverbs 22:6
“Teach a youth about the way he should go; even when he is old he will not depart from it.”
ወላጆች እንድሁም ሌሎች አዋቂ ሰዎች ልጆችን ሊሄዱበት በሚገባው በትክክለኛው መንገድ የመምራት ሀላፊነት አለባቸው ፡፡ የልጆች የህይወት መንገድ ከወላጆችና በዙሪያቸው ካሉ ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ይጀመራል ፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ነው የተመሰረትከው ደግሞም ልክ ክርስቶስ እንደተመላለሰው በፍቅርና በትህትና እየተመላለስክ ነውን ? እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ ፣ ነፍስህና ኃይልህ ትወደዋለህን ?
ከእግዚአብሔር ጋር ስትመላለስ ፣ ስለ እግዚአብሔር ቃል ስታወራ በህይወትህ ያሉ ልጆች ከአንተ ምሳሌነት ይማራሉ ፡፡ ልጆች ክርስቶስን ስለሚከተል ሰው ምስክርነትን ይሰጣሉ ፡፡ ልጆችን እንዴት ከጌታ ጋር ሊመላለሱ እንደሚገባቸው ማስተማር እሁድ ጠዋት ብቻ ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ የሚሳካ ነገር አይደለም ፡፡ ይህ የሚሆነው በትምህርት ፣ ማድረግ የሚገባቸውንና የማይገባቸው ነገሮች በመለየት ወይም ገደብን በማበጀት ፣ እናም ሳምንቱን በሙሉ የክርስቶስን ፍቅር በማንጸባረቅ ነው ! እናም ከልጆችህ ጋር እንዴት እግዚአብሔር በቀናችሁ ላይ መልካም ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ተነጋገሩ ወይም የሆነ የመጽሀፍ ክፍል በህብረት አንብቡ ፡፡ እናም ልጆችህ እንድጸልዩልህ ጠይቃቸው ከዚያም ደግሞ አንተም ለእነርሱ እንዴት እንደምትጸልይላቸው ጠይቃቸው ፡፡ ልጆችህን በጌታ ለማሰልጠን ዝግጁ ሁን ፡፡ ዋና ጉዳይ አድርገህ ቁጠረው ፡፡ እግዚአብሔር ታማኝ ነው ልፋትህንና ጥረትህንም ይባርካል ፡፡
“ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም ። “ - ምሳሌ 22፡6
ተጨማሪ ጥቅስ
- ዘዳግም 6:4-9 — “ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው ፤ አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ ። እኔም ዛሬ አንተን የማዝዘውን ይህን ቃል በልብህ ያዝ ። ለልጆችህም አስተምረው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም ተጫወተው ። በእጅህም ምልክት አድርገህ እሰረው፤ በዓይኖችህም መካከል እንደክታብ ይሁንልህ ። በቤትህም መቃኖች በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው ። “
- ኤፌሶን 6:4 — “እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው ። “
- 1ኛ ዮሐንስ 2:6 — “ በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።