The Heart Is What's Important
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 20-21 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እንደ ቶም በምሳሌ መፅኀፍ ዉስጥ በመስራት በምሳሌ 20 ወይም 21 ላይ ለማስተማር ለመወሰን እየሞከርን ነበር፡፡ የምሳሌ 21 የመጀመሪያዉ ጥቅስ ዉሳኔአችንን ቀላል አደረገልን፡ “ የንጉስ ልብ እነደ ዉኃ ፈሳሾች በእግዚአብሄር እጅ ነው ፤ ወደ ወደደዉም ያዘነብለዋል “ ፡፡ “ መንገድ/መፍሰሻ “ የዉሃን አቅጣጫ ያመለክታል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ሰዉ በአንድ ወንዝ ላይ በመመልከት በድንገት የሚፈስ እንደሆነ ያስባሉ ነገር ግን ዉሃው የእግዚአብሄር እጅን አቅጣጣ ይከተላል ፤ ንጉስም እንደዚሁ ነው ፤ የዚህ አለም ግልፅ የሆነ መዘበራረቅም የእግዚአብሄር ስራ እንደሆነ “ ይናገራል ፡፡ እግዚአብሄር ለማንኛዉም አምባገነን ፕሬዜዳንት እና ጠቅላይ ሚንስተር ኃላፊ ነው ፡፡ እግዚአብሄር የሰዉን ልብ በፍጥነት ወደ መረጠበት ማንኛዉም መንገድ በመምራት መቀየር ይችላል ፡፡
ከአንድ ቡድን ጋር ወደ አንድ ባልካን አገር በመሄድ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ከተገናኘሁ ረጅም ጊዜ አልቆየም ፤ ከቤቱ ተናጋሪዎች እና ከዉጭ ጉዳይ ሚንስተሩ ጋር ተገናኝተን ነበር ፤ እንደ ጌታ አምባሳደሮች እነርሱን ወደ ኢየሩሳሌም በመምጣት ኢምባሲዎችን በኢየሩሳሌም ለማስቀመጥ እንዲመለከቱ በመጠየቅ ለመጋበዝ ሄድን ፡፡ በእስራኤል የኢኮኖሚ ቢሮዎችን ለመክፈት እየተለከቱ ነበር በራሱ ይህ ተዓምራት ነው ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሌላ ሰዉን በመጥራት ያን ቢሮ የት ለማስቀመጥ እንደተመለከቱ ጠየቀዉ እርግጠኛ እንዳልሆነና ምናልባትም ቴላቪቭ እንደሆነ ነገረው ፡፡ ከእኛ ጋር ካሉት ሰዎች መካከል አንዱ የእግዚአብሄርን ቃል በመጠቀም በማክበር ለምን ቢሮዉን በዚያ እንዲሚያስቀምጡ በትህትና ገለፀላቸው ፤ በዚያ ቃለ ምልልስ ጠቅላይ ሚንስተሩ አቅጣጫዉን በመቀየር በኢየሩሳሌም ቢሮዉን እንዲከፍቱ ሲነግራቸዉ አየሁ ፡፡ ከዚያም ወዲያዉኑ ወደ ምሳ (21፡ 1) ሄድኩኝ ምክንያቱም በአይኖቼ ፊት እግዚአብሄር የጠቅላይ ሚንስተሩን ኃሳብ ሲቀይር ስላየሁ ፡፡ ሁሉም ነገር በእግዚአብሄር እጅ በኩል ቀላል ነው (ሮሜ 13፡ 1, 5) ፡፡
ትምህርት
ምሳሌ (21፡ 1-3)፡ ማንኛዉም ነገር ሰዉን ለእርሱ ትክክል ይመስለዋል ነገር ግን እግዚአብሄር ከድርጊቱ ጀርባ ያለዉን ፍላጎት ይመዝናል (ቁጥር 2) ፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ትክክል የሆነዉን ነገር ለእርሱ ማድረግ መስዋዕት ከማቅረብ ይልቅ አስፈላጊ ነው (ቁጥር 3) ፡፡ ጠቅላላ ጊዜ አችንን በቁጥር 3 ላይ ማሳለፍ እንችላለን ፤ ይህ በአምልኮ ዉስጥ ልባችን የት ላይ መሆን እንዳለበት የሚናገር ነው ፡፡ እግዚአብሄር ከመጀመሪያ ልብ በኋላ ነው፡
ምሳሌ (15፡ 8)፡ “ የኃጥዓን መስዋዕት በእግዚአብሄር ዘንድ አስጸያፊ ነው ፤ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው “ ፡፡
ምሳሌ (16፡ 6)፡ “ በምህረትና በእዉነት ኃጢአት ትሰረያለች እግዚአብሄርንም በመፍራት ሰው ከክፋትይመለሳል “ ፡፡
መዝሙር (40፡ 6-8)፡ “ መስዋዕትንና ቁርባንን አልወደድህም ፤ ስጋን አዘጋጀህልኝ ፤ የሚቃጠለዉንና ስለ ኃጢዓት ሚቀርበዉን መስዋዕት አልሻህም ፤ በዚያን ጊዜ አልሁ ፡፡ እነሆ መጣሁ ፤ ስለ እኔ በመጽሐፍ ራስ ተጽፎአልና ፤ አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ ሕግህም በልቤ ዉስጥ ነው “ ፡፡
ኢየሱስ ፈሪሳዊያን ለማምለክ ወደ ቤተ መቅደስ እንደሚሄዱ ነገር ግን ለቤተሰባቸዉ ግድ እንደሌላቸዉ ገልፆአል (ማቴ 15፡ 3-6, ማር 7፡ 9-13) ፤ ምናልባቱም ቃሉ ሚክ (6፡ 8) አንፀባርቆአል፡ “ ሰዉ ሆይ መልካሙን ነግሮሃል ፤ እግዚአብሄርም ከአንተ ዘንድ የሚሻዉ ምንድር ነው ? ፍርድን ታደርግ ዘንድ ምህረትንም ትወድድ ዘንድ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን ? “ (1ሳሙ 15፡ 22-23, ሆሴ 6፡ 6, ማቴ 9፡ 9-13, 12፡ 1, 15፡ 3, 23፡ 23) ፡፡
መስዋዕት ልብን በእዉነት የማያሳይ በግብዝነት ሊቀርብ የሚችል ይሆናል ፤ እግዚአብሄር መስዋዕት ሳይሆን ምህረትን ይፈልጋል ፡፡ የልባችን ሁኔታ ያሳስበዋል ፡፡
ምሳሌ (21፡ 4-8)፡ “ ኃጢዓንን የሚመሩ መብራቶች “ አይን እብሪት ከሞላዉ ትዕቢተኛ ልቦች የሆነ ኃጢዓት የሚያሳይ ነው (ቁጥር 4) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ በተለዬ እቅድ ወደ ጥጋብ እንደሚመራና ድህነትን እንደሚጠላ “ ይገልፃል (ቁጥር 5) ፤ ነገር ግን ከዉሸታም አንደበት የሆነ ትርፍ አይቆይም (ቁጥር 6) ፡፡ ቁጥር 7-8 የኃጢዓንንና የክፉዎች ተግባር ከንፁኃን እና ከፃድቃን ድርጊት ጋር ያነፃፅራል ፤ ይህ ለሰለሞን የተለዬ ፍሬ ነገሩ ነበር - የኃጢዓን እና የፃድቃን መንገድ ፡፡
ምሳሌ (21፡ 9, 19)፡ ቁጥር 9 ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር አንድ ቤት ዉስጥ አብሮ ከመኖር በሌላ ስፍራ ዉጪ መኖር እንደሚሻል ያመለክታል ፡፡ የሚጨቃጨቅ ሰዉ በጊዜ ቆይታ ቢያሸንፋችሁም ይህ እግዚአብሄር የትዳር ግንኙነት እንዲሆን የሚፈልግበት መንገድ አይደለም ፡፡ እግዚአብሄር የንጉሱን ልብ መቀየር ከቻለ የባለቤታችሁን ልብ ይቀይራል ፡፡
መደምደሚያ
“ እግዚአብሄር ሆይ አንደበታችንን ለመቆጣጠር የተማርን ወንዶችና ሴቶች እንድንሆን እፀልያለሁ ፤ እኛን ስለሚያነቃቃን እና አንተን ሊያከብር ስለሚችል ፡፡ የፀሎት ሴቶች እና ወንዶች እንድንሆን እርዳን ፤ ሁልጊዜ ሌሎችን ወደ አንተ እንድናመለክት እርዳን ፡፡ አሜን “ ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999) p. 748.
ጥያቄዎች
-
ምሳሌ 20 በጥንቃቄ አንብቡ ፤ የትኛዉ ጥቅስ ነዉ የተደገመው ? ይህ የተለዬ ጥቅስ ለምን እንደተደገመ ምን ታስባላችሁ ይህ ጥቅስ ምና ማለት እንደሆነ እና ለምን አስፈላጊ እንደሆነ ግለፁ
-
ምሳ (21፡ 2) ስታነቡት ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? ይህ መፅሀፍ ላይ ሌላ የት ይገኛል (1ሳሙ 16፡ 7, ምሳ 16፡ 2, ሉቃ 16፡ 15) ? መንገዳችሁ ትክክል እንደሆነ ይሰማችኋል ? ጌታ እንደሚስማማ ታስባላችሁ ?
-
ምሳ (21፡ 9 እና 19) በተቀራራቢነት አንድ ናቸው ፤ በመካከላቸዉ ልዩነቱ ምንድን ነው፣ ፀሀፊዉስ በእነርሱ ምን ለማለት እንደፈለገ ምን ታስባላችሁ ? ፀሀፊው እንደገለፀው ወንድንም ሊያካትት ይችላል ወይስ ሴትን ብቻ ነው ?
-
በምሳሌ (20-21) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Proverbs 21:1
“A king’s heart is like streams of water in the LORD’s hand: He directs it wherever He chooses.”
የሆነን ሰው የህይወት መስመር መቀየር እንድትችል ተመኝተህ ታውቃለህ ? ምናልባት ቀዝቃዛ ልብ ያለውን የትዳር አጋር ፣ አባካኝ ልጅ ፣ የተራራቀ ቤተሰብን ወይም ሞኝ የሆነ ጓደኛን ፡፡ እግዚአብሔር የተሰበረን የተጎዳን ልብ ያያል እናም እርሱ በዚያ እንዳለ ተናግሯል ፡፡ በዚህ እውነት ላይ ተጣበቅ ፡፡ እግዚአብሔር የንጉሥን ልብ መምራት ከቻለ ፤ እርሱ ደግሞ አንተ የምትወደውንም ሰው ልብ መመለስ ይችላል ፡፡
በመጠበቅ ላይ ሳለህ ምንድን ነው ማድረግ የምትችላው ? ከመሪው ላይ እጅህን አንሳ ፣ የህይወት አቅጣጫቸውን ለመቆጣጠር መሞከርህን አቁም እናም ጸልይ ፡፡ እግዚአብሔር ጸሎትህን ይሰማል ፡፡ እርሱ በስራ ላይ እንደሆነ እመን ፡፡ እርሱ ያያል ስለዚህ ልጅህን ፣ የትዳር አጋርህን ወይም ጓደኛህን ወደ እርሱ መልሶ እንድመራቸው ፍቀድለት ፡፡ በመጠበቅ ላይ ሳለህም እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ ፣ ነፍስህና አሳብህ መውደድህን እንዳታቋርጥ ፡፡ በዚህ መንገድ በጌታ ላይ የበረታህ ትሆናለህ እናም ያጠፋህ ዘንድ ጠላት ያዘጋጀውን እቅድ መቋቋም ትችላለህ ፡፡ ይህንን አስታውስ ፡- እግዚአብሔር የንጉሥን ልብ መምራት ከቻለማ አንተ የምትወዳቸውን ሰዎች ልብ ደግሞ አብልጦ መለወጥና መምራት ይችላል ፡፡ በዚህ ተስፋ ላይ ተጣበቅ ፡፡
“የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል ። “ - ምሳሌ 21፡1
ተጨማሪ ጥቅስ
- ዘጸአት 15:6 — “ አቤቱ፥ ቀኝህ በኃይል ከበረ፤ አቤቱ ቀኝህ ጠላቱን አደቀቀ ፡፡ “
- መዝሙር 27:14 — “ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ። “
- 1ኛ ቆሮንቶስ 10:13 — “ ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል “ ።
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።