Wisdom Books Proverbs

Love, Listen, Discern, And Response

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 18-19 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 472 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በጥበብ መፅሀፍት ብዙ ክፍል/ትምህርት እሆነዉ ክፍል 108 ላይ ነን ! ያወራንበት የመጀመሪያዉ የጥበብ መፅኀፍት ኢዮብ ነበር ፤ ከዚያም በብዛት በዳዊት ተፅፎ የነበረዉን መዝሙርን ተመለከትን ፤ አሁን በዳዊት ልጅ በሰለሞን የተፃፈዉ ምሳሌ መፅኀፍ ላይ ነን ፤ ቀጣይ ሳምንት ወደ መክብብ እና ወደ መኃለይ መኃለይ ሰለሞን እንገባለን ፡፡ ስለ ምሳሌ መፅሀፉ የሚያስደንቀዉ ነገር ሰለሞን ብዙ የተለያዩ ርዕሶችን ማብራራቱ/መግለፁ ነው ፡፡ በእዚህ መጣበቅ ከቻላችሁ ህይወታችሁን መቀየር የሚችሉ ተግባረዊ እዉነቶችን ታስታዉላላችሁ ብዬ አስባለሁ ፡፡

ትምህርት

ምሳሌ (18፡ 1)፡ ራሱን ስለ ፍላጎቶ ወይም ስለ ደህንነቱ/ስለ መጠበቅ የሚለይ በመጨረሻም ይጠፋል ፡፡ መጥፎ ባህሪያቸዉ ከተገለጠ በኋላ ባለፉት ጥቂት አመታት የወደቁትን ሁሉንም መሪዎች፣ ክርስቲያኖች እና ሌሎችን ተመልከቱ ፡፡ ራሳችሁን መለየት በመጀመር ፍላጎታችሁን መከተል ስትጀምሩ ጥፋት እየመጣ ነው ፡፡ እግዚአብሄር የአካሉ አካል እንድንሆን ነዉ ያቀደው ፤ የኔልሰን ማብራሪያ የተለዬ አንድ ሰዉ አንዱ ማሳያው “ በሁሉም የማስተዋል ፍርዱ ስህተትን በማግኘቱ ከእርሱ ጋር የማይስማሙትን የማይደግፍ ይሆናል “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ሁልጊዜ ትክክል ሆናችሁ ሌሎች ደግሞ ሁልጊዜ ስህተት ከሆኑ ወደ ኃላ በመመለስ ህይወታችሁን ተመልከቱ ፡፡

ምሳሌ (18፡ 2)፡ ራሳችሁን ስትለዩ የሌሎችን አስተያዬት ከመስማትና ከማስተዋል ወደ ሚከለክላችሁ አስገዳጅነትን/ትዕዛዝ ወደ ሚናገር አስተሳሰብ መሄድ ትጀምራላችሁ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪ “ ትዕዛዝ ተናጋር በፍፁም አያዳምጥም ቀጣይ ምን እንደሚናገር ለማቀድ ብቻ ይቆማል እንጂ ፤ ሁሉም ንግግር ሞኝ እንደ ሆነ እንደሚያረጋግጡ “ ይናገራል ፡፡ እንዲህ አይነቱ ንግግር ተራ ንግግር ተብሎ ይጠራል ፡፡ ተራ ንግግር በቀላሉ የሚገኙ ትርጉም የሌሽ ቃላቶች የሞሉት ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ቃላችን እንዴት እንደሚመዘን እና ከተራ ንግግር እንዴት እንደምንርቅ መንገዶችን ሰጥቷል፡

  • “ አንዳንድ ጊዜ የማስተዋል መንገድ ዝምታ ነው ፡፡ ረዳቶች/አጋዦች ለመሆን ከፈለግን ቃላችንን እና አስተሳሰባችንን በጥንቃቄ መመዘን ያስፈልገናል (ምሳ 11፡ 2) “ ፡፡ ራሳችሁን ትሁት በማድረግ ሰዎች እስከሚሉት ድረስ ራሳችሁን ክፍት ስታደርጉት ጥበብ ማለት ያ ነው ፡፡

“ በፍፁም ማዉራት መፈለግ የሌለብን አንድ ነገር ስላስቀመጥነዉ/ስለደበቅ ነው ሚስጥር ነው (ምሳ 11፡ 13) “ ፡፡ የሆነ ሰዉ የሰጣችሁን መረጃ በዙሪያችሁ ለመናገር ከሚሄዱት ዉስጥ ለመሆን በፍፁም እንዳትፈልጉ ፤ አሉባልተኛ ወይምአሉባልታ አስራጭ መሆን እንዳትፈልጉ ፡፡ እምነት የሚጣልበት ሰዉ ሚስጥር ይጠብቃል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ክርስቲያኖች አሉባልታን በፀሎት ጥያቄ ዉስጥ ሊደብቁት ይችላሉ ፤ በጥርጣሬ ጊዜ ሽሽሽ !

“ ቃላትን እንዴት እንደምንጠቀም ካወቅን የሚያሸልፍ ፍፃሜን ማሳካት እንችላለን “ ፤ በምን እየተናገርን እንደሆነ ንግግራችንን ማጤን ያስፈልገናል (ምሳ 15፡ 1-2) ፡፡ እግዚአብሄር ራሳችንን በተለዬ የጋል ባህሪያት ሰርቶናል ፤ ሌላ አይነት ሰዉ ለመምሰል ለመሞከር መፈለግ የሌብንም ፡፡ የሚወደዱና የሚማርኩ ቃሎችን በመናገር የራሳችን የተሻለ ክፍል ላይ መሆን እንፈልጋለን ፡፡

“ የምንለዉን መመልከት ያስፈልገናል ፤ ንግግራችን ችግር ዉስጥ ሊያስገባን ይችላል (ምሳ 18፡ 6-7) “ ፤ በጥርጣሬ ጊዜ ዝም በሉ ፡፡

“ እዉነቱን ከመስማት በፊት የግል አስተያየታችን ከሰጠን በራሳችን ላይ እፍረትን እናመጣለን (ምሳ 18፡ 13) “ ፤ የሁሉም ነገር ባለሙያዎች እንደሆንን አክት እናደርጋለን ፤ ትህትና ካለ እግዚአብሄር ለእኛ እያለ ያለዉን እና እንዴት እንደምንመልስ እንቀበላለን ፡፡

“ ወሬ ተራ ነዉ ነገር ግን ቀላላ ወሬ ዉድ ሊሆን ይችላል ፤ የተሳሳተ ነገር በተሳሳተ ጊዜ መናገር ድንገት ወደ ሚሆን ችግር/ዉጤት ሊመራ ይችላል (ምሳ 18፡ 12) “ ፡፡ እንደ ገና በጥርጣሬ ዉስጥ ስትሆኑ ዝም በሉ ፤ ንግግሩን በትንሹ ዝቅ አድርጉት ፤ በጣም የሚያስፈልገዉ በጥንቃቄ መናገር ነው፣ እንዲሁም በጥንቃቄ ማዳመጥ ያስፈልገናል ፡፡ በጌታ ማደግ ከፈለጋችሁ ሌሎች እያሉ ስላሉት ነገር ክፍት/አዳማጮች መሆን ያስፈልገናል ፡፡

ምሳሌ (18፡ 8)፡ አሉባልታ ልክ እንደ ኦሪኩኪስ የተመረዘ ነው ፤ የሚጣፍጥ ይመስላል ነገር ግን የተመረዘ/መርዝ ነው ፡፡ አሉባልታ የሚያስቅ/የሚያዝናና እና የሚያጓጓ ይመስላል ነገር ግን ለእናንተና አሉባልታ ለሚያወሩት መርዝ ነው ፡፡ ስለምትናገሩት እና እናንተ ጋር ስለተቀመጠዉ አደራ ጠንቃቆች ሁኑ ፡፡ የሆነ ሰዉ አሉባልታን ቢያወራ አትቀበሉት ፤ አሉባልታ መስማት እንደማትፈለጉ ለሌላ ሰዉ ለመናገር በተገቢዉ ጠንካራ መሆን አለባችሁ ፡፡ አሉባልታ መቀበልና ማሰራጨት ዉስጣዉ ማንነታችሁን ያቆሽሸዋል ፤ ይህ ለመቀበል አስቸጋሪ እዉነት ነው ፡፡ አሉባልታን ለመስማት ፍቃደኞች ሳንሆን ስንቀር በሀቀኝነት መራመድ ጀምረናል ማለት ነው ፡፡

ምሳሌ (18፡ 9-11)፡ ሰነፍ ሰዉ ወደ ጥፋት ይሮጣል ፤ ፃድቅ ሰዉ ደግሞ ወደ እግዚአብሄር ይሮጣል ፡፡ ባለፀጋ ሰዎች ራሳቸዉን የማይነካ ለማድረግ በኃብታቸዉ ይደገፋሉ/ይታመናሉ (ሉቃ 12፡ 13-21) ፡፡

ምሳሌ (18፡ 12-13)፡ መዉደድ፣ ማዳመጥ፣ መለየት እና ከዚያ መልስ መስጠት አስፈላጊ ነው ፤ አንዳንድ ጊዜ ለሰዎች ታሪካቸዉን ሳናዳምጥ የሚያስፈልጋቸዉን ከመናገር በወንጌል ለመናገር እንፈጥናለን ፡፡

ምሳሌ (18፡ 14-15)፡ “ ህመምን መቋቋም ይቻላል ነገር ግን ለተሰበረ መንፈስ መድኃኒት የለዉም (ምሳ 15፡ 4, 17፡ 22, ኢሳ 66፡ 2) “ ፡፡ አስተዋይ ይማራል ፤ ለማዳመጥ፣ ለማዉራት፣ ለመዉደድ እና ለመለየት ይማራል ፡፡

ምሳሌ (18፡ 16)፡ ይህ ጥቅስ ልቤን ይናገረዋል፡ “ የሰዉ ስጦታ መንገዱን ታሰፋለታላች በታላላቆችም ፊት ታገባዋለች “ ፤ በልግስና በምትሰጡ ጊዜ ያ ስጦታችሁ በዚያ ሰዉ ህይወት ዉስጥ መስኮትን/በርን ይሰጣችኋል ፡፡ ገንዘብ፣ እንቁላል፣ መኪና ወይም ጊዜአችሁን በለጋስነት መስጠት በአንድ ሰዉ ወይም ቡድን ዉስጥ “ መግባትን/መሆንን “ ይሰጣችኋል ፡፡ አንዴ ያበር ከተከፈተ ወይም ግንኙነቱ ከተመሰረተ እግዚአብሄር ቃሉን እንድትናገሩ ሊጠቀምባችሁ ይችላል ፤ ይህ ፍላጎት አይደለም እዉነታ ነው ፡፡ ብዙ በመዝራት በሮችን መክፈት ጀምሩ እግዚአብሄር በሮች እንዲከፈቱ ብዙ እድሎችን ይሰጣችኋል ፤ ለእርሱ ክብር ለማምጣት ከእግዚአብሄር ስጦታን እንቀበላለን ፡፡

ምሳሌ (18፡ 19-20)፡ ወደ ማዉራት ተመለሱ ! በአንድ ቤተሰብ አባላት ዉስጥ ተቃዉሞ ካለ ለመቋቋም በጣም አስቸጋሪ ነው ፤ በተለዬ ይህ በቤተሰባችሁ ዉስጥ ለመዉደድ፣ ለማዳመጥ እና ለመለዬት አስፈላጊ ነው ፡፡ አሜሪካኖች ብዙ ያወራሉ ፡፡ ማዉራትን በምታደርጉበት ልክ በዚያ ቀን ሌሎቹንስ ምን ያክል ጊዜ ታደርጓቸዋላችሁ ? ማዉራት በተገቢዉ አስፈላጊ ነው ፡፡ አንደበታችንን ጨምሮ በአካላችን እግዚአብሄርን እንድናከብረዉ አበረታታችኋለሁ ፡፡ ስለተናገርናቸዉ ሁሉም ግድየለሽ ቃላቶች ተጠያቂዎች እንሆናለን (ማቴ 12፡ 36) ፤ በጥርጣሬ ጊዜ በግዴለሽ ቃላቶቻችን/ንግግሮቻች ይቅርታ መጠየቅ ፡፡

ምሳሌ (18፡ 22)፡ አዲስ ርዕስ፡ ጋብቻ/ትዳር ! በዚህ ብዙ ጊዜ እንዲኖረን ተስፋ እያደረኩኝ ነበር በአጋጣሚ ግን ያ አልሆነም ፤ ስለዚህ እዚህ በ30 ሴኮንድ ጋብቻ/ትዳር 101 ነው ፡፡ ሚስት መልካም ነገር ነች ፤ ወንድ ብቻዉን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም (ዘፍ 2፡ 18) ፤ እነዚህን ሁሉንም ንግግሮች የት ላይ እናገኛቸዋለን ? ከመፅሀፍ (ዘፍ 2፡ 18፣ ምሳ 18፡ 22፣ መክ 4፡ 9-10) ፡፡ ሁለት ከአንድ ይሻላል ፡፡ ልምዳችሁን/ተሞክሯችሁን አላዉቅም ፤ ትዳር ህይወቴን የተሸለ እንዳደረገልኝ አዉቃለሁ ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 764.

  2. 2 Nelson’s Commentary, p. 764.

  3. Nelson’s Commentary, p. 765.

  4. Nelson’s Commentary, p. 765.

  5. Nelson’s Commentary, p. 765.

  6. Nelson’s Commentary, p. 765.

  7. Nelson’s Commentary, p. 765.

  8. Nelson’s Commentary, p. 765.

  9. Nelson’s Commentary, p. 765.

ጥያቄዎች

  1. ምሳ (18፡ 2) ስለ ትዕዛዘዊ/ሰነፍ ተናጋሪዎች ምን ይላል (ምሳ 17፡ 27, መክ 10፡ 12-14) ? በመፅኀፍ መሰረት የትኛዉ ምርጥ መንገድ ነው ? (ያዕ 1፡ 19)
  2. አሉባልታ መስማት ምንድን ነዉ አደጋው (ዘኁ 19፡ 16) ? አሉባልታ ከእናንተ ጋር የሚታገላችሁ ነገር ነው ? ከአሉባልታ ወይም አሉባልታን ከመስማት እንዴት ታመልጣላችሁ/ትጠበቃላችሁ ? (ምሳ11፡ 13)
  3. ምሳ (19፡ 1) ሀቀኝነትን እንዴት ይገልፀዋል (ምሳ 3፡ 1-12, 15፡ 16, 16፡ 8) ? ምሳሌ በዚህ ላይ ያስቀመጠዉ ማብራሪያ ምን ይመስላል ?
  4. ምሳ (19፡ 6) አንብቡ ፤ ይህ ጥቅስ እንዴት እንደ ለጋስነት ወይም እንደ ጉቦ እንዴት ሊታይ ይችላል ? (ምሳ 17፡ 8, 18፡ 16)
  5. በምሳሌ 19 እንደተገለፀዉ የዉሸታም ቅጣት ምንድን ነው ? ወደ ህይወት ምን ይመራል ? ዉሸት የእግዚአብሄርን ባህሪይ እንዴት ይፃረራል ? (ዘዳ 32፡ 4, ዮሐ 14፡ 6, 1ዮሐ 5፡ 6)
  6. በምሳሌ (18-19) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Proverbs 18:13

“The one who gives an answer before he listens—this is foolishness and disgrace for him.”

ዝም በል ፡፡ ዝም በል ፡፡ ዝም በል ፡፡ ሀሜት ፣ ከባድ የሆነ መራራ ቃል ፣ አሽሙር ፣ ውሸት ደግሞም ሞኝነት በተጨማሪም በችኮላ የሚነገሩ ቃላት ወደ ጠብ ፣ ሁከትና ጥፋት ይመራሉ ፡፡ ይሀን አይነተኛ የሆነ ንግግር አስታውስ “ የምትናገረው ምንም ጥሩ ነገር ከሌለህ ፣ በቃ ምንም ነገር አትናገር ፡፡ “ ዛሬ ይህን ወደ ተግባር ለውጥ ፡፡

እንደሚታወቀው በማታወራበት ጊዜ እያዳመጥክ ነው ፡፡ ለመራዳት ማዳመጥ ፡፡ ከልብህ ስለ ሌሎች ስለምታስብና ፍቅርን ስለምትሻ ታዳምጣለህ ፡፡ መስማት የማትፈልገውን ነገር ከሰማህ ፣ ምላሽ ለመስጠት አትቸኩል ፡፡ ይህ እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቶ እንድሰራ ያስችለዋል ፡፡ እግዚአብሔር ውጊያህን እንደሚዋጋ ተናግሯል ፡፡ አንተ መታገስ ብቻ ነው የሚያስፈልግህ ፡፡ ዛሬ ዝም ብለህ የሚሆነውን ለማየት ወስን ፡፡ ከተበሳጨህም ዝም በል ፡፡ ትዕግስትህን ብትጨርስም እንኳ ፣ ዝም በል ፡፡ አንተ የተሸለ እንደምታውቅ ብታስብም እንኳ ፣ ዝም በል ፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንድትናገር እስከሚያሳስብህ ድረስ ጠብቅ ፡፡ እና ከዚያ ተናገር ፡፡ በፍቅር ተናገር ፡፡ በየዋህነት ተናገር ፡፡ በክርስቶስ ፍቅር ተናገር ፡፡ አስፈላጊው ነገር ጊዜ መውሰድና የምትናገራቸውን ቃላት በጥበብ መምረጥ ነው ፡፡ ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ “ ተናገር ! “ እስከሚልህ ምንም ነገር አትናገር ፡፡ ከዚያም ልክ እንደ ወንዝ በእግዚአብሔር ፍቅር ትጥለቀለቃለህ ፡፡

“ ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል ። “ - ምሳሌ 18፡13

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ምሳሌ 18:4 — “ የሰው አፍ ቃል የጠለቀ ውኃ ነው፥ የጥበብም ምንጭ ፈሳሽ ወንዝ ነው ። “
  • ማቴዎስ 12:36–37 — “ እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል ፤ ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ ። “
  • ቆላስይስ 4:6 — “ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ፥ በጨው እንደ ተቀመመ፥ በጸጋ ይሁን ። “