A Collection Of Solomon's Proverbs
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 16-17 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የሁል ጊዜ ጥበበኛ ሰዉ የሰለሞን ፅሁፍ ወደ ምሳሌ 16 ይቀጥላል ፤ ሰለሞን ለወጣቶቹ ትዉልድ በንግግራቸው በይበልጥ ህይወት የሚሰጣቸዉን አስቸጋሪዉን እና ጠባቡን መንገድ መምረጥ እንደሚችሉ አመለክቷል ፤ ነገር ግን በሰዎች ላይ ቀልደን ማድረግ፣ ሰዎችን መዝለፍ እና ከእግዚአብሄር ያልሆነን ቃል መናገን የሚያካትተዉን ጨለማ መንገድ ወይም ደግሞ ቀላሉን፣ ሰፊዉን መምረጥ እንደሚችሉ አመልክቷል ፡፡
ትምህርት
ምሳሌ (16፡ 1-2)፡ የምትፈልጉትን ሁሉ መሞከር ትችላላችሁ ነገር ግን ይህን ለእግዚአብሄር እስክትሰጡ ድረስ በእናንተ ዉስጥ ስጋችሁ ወይም የእግዚአብሄር መንፈስ ይናገር ይሆናል (ቁጥር 1) ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር “ የሰዉ ኃላፊነት ሁልጊዜ ለእግዚአብሄር ልዓላዊነት ነው “ ፤ በሌላ ቋንቋ ሰዉ ማቀድ፣ ማለም እና ተስፋ ማድረግ ይችላል ነገር ግን የመጨረሻዉ ዉጤት ከእግዚአብሄር የተሰጠ ነው ፤ ይህ ስዕል በቁጥር 2 በመገንባት ይቀጥላል ፡፡ ሰዎች በሚስሉት ሁሉም ነገር በህይወታቸዉ ዉስጥ እንደሚያልፉ ያስባሉ ነገር ግን እግዚአብሄር ፍላጎታቸዉን ያውቃል (ቁጥር 2) ፡፡ ሁልጊዜ እግዚአብሄር ሰዎች የሚያደርጉትን ነገር ለምን እንደሚያደርጉት ያውቃል ፤ በምናደርገዉ ነገር ሁሉ እግዚአብሄር የመጨረሻዉ ዳኛ ይሆናል ፡፡ ምሳ (21፡ 2) እግዚአብሄር ፍላጎታችንን እንደሚመዝን ያረጋግጣል ፤ ምሳ (24፡ 12) እግዚአብሄር የምናደርገዉን ሁሉንም ነገር ለምን እንደምናደርገዉ እንደሚያዉቅ ያረጋግጣል ፡፡ 1ሳሙ (16፡ 7) ሰዎ የሚታየዉን ነገር እንደሚያይ እግዚአብሄር ግን ልባቸዉን እንደሚያይ ያመለክታል ፡፡ 1ቆሮ (4፡ 4) እግዚአብሄር እንደሚመረምረን ይናገራል ፤ ይህ እንዴት እንደምናወራ፣ ምን እንደምንል እና እንዴት እንደምንናገረው ያካትታል ፡፡
ምሳሌ (16፡ 3)፡ በቁጥር 1-2 ነገሮችን በራሳችን ስናደርግ ሰዎች የማን እንደሆን እንኳን አያውቁም ነገር ግን ተግባራችንን ለእግዚአብሄር በምንፈፅም ጊዜ እቅዳችን የተፈፀመ እንዲሆን ይፈቅዳል (ቁጥር 3) ፡፡ ይህ እርሱን ለመከተል ሁሉንም ነገር ለኢየሱስ በመማረክ አንድ ክርስቲያን ተገቢ/ልክ ሆኖ የሚሄድበት ነው ፡፡ በዕብራዊያን “ መፈፀም/ማድረግ “ የሚለዉ ቃል “ በሙሉ እምነትና መታዘዝ በሁለቱም ስሜት/ሁኔታ ለእግዚአብሄር ፍቃድ የተገዛ/የታመነ መሆን “ ማለት ነው ፡፡ ምሳ (3፡ 5-6) ይህን የሚመሰል አስተሳሰብ ያቀርባል ፤ መዝ (22፡ 8) በእግዚአብሄር ላይ እዉነተኛ መታመን/መደግፍ አለ ይላል ፡፡ መዝ (37፡ 5) መንገዳችንን ለእግዚአብሄር እንድንሰጥ፣ እንድንታመነዉ ቀጥሎም ሲያደርግ እንድንመለከተዉ ያሳስበናል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ በዉሳኔአችን ላይ እግዚአብሄርን መታመን በችግሮቻችን ከመዋጥ/ከመወሰድ ነፃ ያወጣናል “ ይላል ፡፡
ምሳሌ (16፡ 4)፡ በዚህ ፅሁፍ መሰረት እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር ለፃድቆች እና ለመልካሞች ብቻ ሳይሆን ለክፉዎች እና ለኃጢዓተኞች አዘጋጅቷል ፡፡ እግዚአብሄር ሁሉም ነገር በቁጥጥሩ ስር ነው ትርጉም የማይሰጥ ነገር እንኳን ቢሆንም ፡፡ እግዚአብሄር ለሕዝቡ ነገሮችን ለማዘጋጀት ፈርዖንን እንደተጠቀመ እናስታዉሳለን ፤ እነዚህ ሁሉ በፍርድ ቀን ላይ ለእግዚአብሄር ክብር ያመጣሉ ፡፡
ምሳሌ (16፡ 5)፡ ይህ ጥቅስ ተግባራችንን ለእግዚአብሄር እያደረግን እንዳልሆነ በምናስተዉልበት ጊዜ የሚሆን ጥቅስ ሲሆን ነገሮችን በራሳችን ማድረግን እየሞከርን ነው ፡፡ የትዕቢት ልብ ካላችሁ እርገጠኛ መሆን ያለባችሁ “ ሳትቀጡ እንደማትቀሩ ነው “ ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ ትዕቢት ወደ ኃላ የሚስብ ሁሉም ነገር አለዉ ፤ ያለ ምንም ምስጋና በማትረፍረፍ ለሰጠዉ እና ለተቀባዩ ከሸለመዉ ከሰጮዉ ላይ ዋጋዉን መዉሰድ ማለት ነው “ ይላል ፤ ተግባርን ለእግዚአብሄር ከመፈጸም ይልቅ ላደረጋችሁት ነገር ዋጋዉን መዉሰድ ማለት ነው ፡፡ እግዚአብሄርን ሰዎች የእርሱን ክብር ሲሰርቁት ይጠላል ፡፡
ምሳሌ (16፡ 6)፡ የዚህ ጥቅስ ሁለተኛዉ ግማሽ ቀላል ነው ፡፡ ጌታን ስንመለከት እርሱን በመፍራት (በፍርሀት በመያዝ) ከክፉ እንመለሳለን ፤ ኃጢዓት ቢኖርም እንኳን እግዚአብሄር ሸፍኖታል ፤ የእግዚአብሄር ምህረት፣ ፍቅር፣ እዉነት፣ ታማኝነት እና መታመን ያነፃዋል ፡፡ እግዚአብሄር ለእኛ ያደረገልንን በማስተዋል ከክፉ ስንመለስ ኃጢዓታችን ተሸፍኖአል/ጠፍቷል ፡፡ ይሁን እንጂ ትሁት እና የተፀፀተ ልብ ያላቸዉ ይህን ይቀበላሉ ፡፡
ምሳሌ (16፡ 7)፡ መንገዳችን እግዚአብሄርን በሚያስደስት ጊዜ ጠላቶቻችን እንኳን ከእኛ ጋር “ በሰላም እንዲሆኑ “ ያደርጋል ፤ እግዚአብሄር ጠላቶቻችንን ልክ እንደኛ ማድረግ ይችላል ፡፡ በተራራው ስብከት ላይ ኢየሱስ ስለ አስታራቂ መልክ ስሏል “ የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው የእግዚአብሄር ልጆች ይባላሉና “ (ማቴ 5፡ 8) ፡፡ አስባችሁበት ሰላምን በምታደርጉ ጊዜ የእግዚአብሄር ልጆች ናችሁ ፤ የክርስቶስ ፍቅርን ለመግለፅ በመንገዳችሁ ስትሄዱ - ሰዎች -ጠላቶቻችሁም እንኳን ወደዚያ ይሳባሉ ፡፡
በምሳ (16፡ 7) ያለዉ አንድ ፅሁፍ፡ ይህ ጥቅስ ጠላታችሁ ከእናንተ ጋር ምንም እንኳን ሰላም እንደሚሆኑ ቢናገርም በኃይማኖታችሁ መከራ አይደርስባችሁም ማለት አይደለም ፤ 2ጢሞ (3፡ 12) “ በእዉነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሄርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ “ ይላል ፡፡
ምሳሌ (16፡ 8)፡ ሰለሞን ስለ ገንዘብ ማዉራት ይወዳል ፤ በፅድቅ የተገኘዉ ጥቂት ገንዘብ ያለአግባብ ከተገኘዉ ብዙ እንደሚሻል አብራርቷል ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር በትክክል መቆም ከእግዚአብሄር ዉጪ ከገንዘብ ጋር ከመቆም የተሸለ ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ቅድስና የሚበልጥ/እዉነተኛ ኃብት እንደሆነ “ ያሳስበናል ፡፡
ምሳሌ (16፡ 9)፡ ይህ ጥቅስ ከቁጥር 2 እና 3 ጋር ይነፃፀራል ፡፡ በመንገዳችን ላይ መጓዝ መጀመር እንችላለን ነገር ግን ጉዞአችንን ያቀደልን እግዚአብሄር ነው ፤ “ የልብ እቅዳችንን “ መፃፍ እንችላለን ነገር ግን መንገዱን እንዲያሳየን በእግዚአብሄር ላይ መታመን አለብን - ሁሉአንም እርምጃዎቻችንን ለመወሰን ፤ ይሁን እንጁ ያ የሚሆን መልካም ነገር አይደለም ቢለን እንኳን ለመስማት ፍቃደኞች መሆን አለብን ፡፡ ለእርሱ ራሳችንን በማስገዛት (ቁጥር 3) እርምጃዎቻችንን እንዲወስንልን በመፍቀድ ሙሉ በሙሉ ስንታመን ሁሉም ይሆናል (ቁጥር 3) ፡፡ የሚያበሳጨዉ ነገር ምናልባት ጊዜዉን አለማወቃችን ነው ፡፡ በዘፍ (50፡ 20) ዮሴፍ ህፃን እንደ ነበር ለግብፃዊያን እንደ ባሪያ ሸጠዉት ለነበሩት ለወንድሞቹ፡ “ እናንተ ክፉ ነገርን አሰባችሁብኝ ፤ እግዚአብሄር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲድን ለማድረግ ለመልካም አሰበው “ ብሎ ነገራቸው ፡፡ ወንድሞቹ በዮሴፍ ላይ ያቀዱትን ሁሉንም ስህተቶች እግዚአብሄር በመዉሰድ እቅዱን አደረገ ፡፡
መዝ (119፡ 133)፡ “ አካሄድን እንደ ቃልህ አቅና ፤ ኃጢዓትም ሁሉ አይግዛኝ “ ይላል ፤ ይህ ሁሉንም እርምጃችንን የቀና ማድረግ እንደሚችል እንድናስተዉል ይመራናል ነገር ግን ምሳ (16፡ 2) ፍላጎታችንን ለመመዘን እግዚአብሄር ያስፈልገናል ፡፡
መደምደሚያ
የልባችሁን እቅድ ካስቀመጣችሁ ፍላጎታችሁን/መነሳሳትችሁን እንዲመዝን ለእግዚአብሄር ፍቀዱለት ይህ ሲሆን ነገሩ ከእርሱ ወይም ከእናንተ መሆኑን ማየት ትችላላችሁ ፤ ከእርሱ ከሆነ ተዘጋጁ ፤ አደገኛ ጉዞ ስለሚሆን ተያያዙ ፡፡ ይህ ካልሆነ ለአንድ ወቅት ይቆያል ነገር ግን ለዘላለም አይደለም ፡፡ አባጣ ጎርባጣ ሊሆን ይችላል፣ ለጥ ያለ ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን ከእርሱ ካልሆነ የሚቆይ አይደለም ፡፡
John MacArthur, The John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 713.
MacArthur, p. 713.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 762.
Nelson’s Commentary, p. 762.
Nelson’s Commentary, p. 762.
ጥያቄዎች
-
በምሳሌ 16 መሰረት አንድ ሰዉ እንዴት ከክፉ ይለያል ? አማኝ እግዚአብሄርን ለመፍራት በምን ያዘነብላል?
-
የሰዉን ኃላፊነት እና የእግዚአብሄርን ሉዓላዊነት “ ከእቅዳችን “ ጋር ስናገናኝ እንዴት ታስማሙታላችሁ ? (ምሳ 3፡ 6፣ 16፡ 2, 9, 33፣ 19፡ 21, 21፡ 1)
-
ምሳ (16፡ 20) የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ለሚቀበሉት ምን ተስፋ ገባ ? (መዝ 34፡ 8, ኤር 17፡ 7) አሁን በህይወታችሁ እግዚአብሄርን እና ጥበቡን ሳትታመኑ በአለም ጠበብ ላይ የተደገፋችሁበት ስፍራዎች አሉ ?
-
ድሆችን ሲዘልፉ ሰዎች ምን እያደረጉ ነው ? (ምሳ 14፡ 31, 17፡ 5)
-
ፍትህን ስለሚያጣምሙ እግዚአብሄር እንዴት ይሰማዋል/ያስባል ? (ዘጸ 23፡ 6, ምሳ 17፡ 23, ኢሳ 5፡ 23)
-
በምሳሌ (16-17) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Proverbs 16:2–3, 9
“All a man’s ways seem right to him, but the LORD evaluates the motives. Commit your activities to the LORD, and your plans will be achieved . . .A man’s heart plans his way, but the LORD determines his steps.”
ለቀኑ እቅድ አለህ ? ምናልባት በአመቱ ውስጥ አሳካቸዋለሁ ብለህ የምታስባቸውን አንዳንድ ግቦች ጽፈህ ይሆናል ፡፡ አሁንስ ? በእነዚህ እቅዶች እና ግቦች ላይ ለመጸለይ እናም መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ለመስጠት አስበህ ታውቃለህ ? እግዚአብሔር ለአንተ ህይወት እቅድ እንዳለው ተናግሯል ፡፡ ስለዚህ ስታቅድ ፣ ግቦችን ስታስቀምጥ እንቅስቃሴዎችህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ እናም መንገድህን እንድያቀናልህ እግዚአብሔርን ጠይቅ ፡፡
እያንዳንዷን አጋጣሚ ፣ እያንዳንዷን እንቅስቃሴ እንድሁም እያንዳንዷን ውሳኔ በንጹህ ልብና ፍላጎት ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ ፡፡ መውሰድ እንዳለብህ የምታውቀውን ቀጣዩን እርምጃ ውሰድ እግዚአብሔር እንደሚያግዝህም እመን ፡፡ ጭንቀት ተስፋ መቁረጥ ከተሰማህ ፣ በጌታ ደስ ይበልህ ፤ እርሱን ጥበብ ለምን ወደ ፊት መሄድህንም ቀጥል ፡፡ እርሱ ታማኝ እንደሆነና ፈጽሞ እንደማይተውህ ቃል ስለ ገባ ፣ የእግዚአብሔር ምህረት ይከተልሃል ፡፡ ስለ እቅዱ አብዝተህ አትጨነቅ ፡፡ ምናልባት የመጨረሻ ውጤቱ የተለየ ወይም አንተ ከምታስበው በላይ ጭምር ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን ልብህ ከእግዚአብሔር ጋር ከተጣበቀ የእርሱን ፍቅር ያንጸባርቃል……… እናም ይህ በነገር ሁሉ የመጨረሻው ግብ ነው ፡፡
“ የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኖቹ ፊት ንጹሕ ነው፤ እግዚአብሔር ግን መንፈስን ይመዝናል ። ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች ………………. የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቀናለታል ። “ - ምሳሌ 16፡2-3 ፤ 9
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 22:8 — “ በእግዚአብሔር ተማመነ፥ እርሱንም ያድነው፤ ቢወድደውስ ያድነው ። “
- መዝሙር 119:133 — “ አካሄድን እንደ ቃልህ አቅና፤ ኃጢአትም ሁሉ አይግዛኝ ። “
- ኤርምያስ 29:11–12 — “ ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም ። እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።