A Collection of Solomon's Proverbs
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 14-15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ምሳሌ በደንብ በመግባት ልንከባከበዉ የምንፈልገዉ ሰለሞን የፃፋቸዉ ወርቃማ ቁም ነገሮች ናቸው ፡፡ ችግሩ ለምሳሌ ምሳሌ (15) 33 በትክክል ስብከት የሆኑ 33 ጥቅሶች መኖራቸዉ ነው ፤ ስለሆነም ይህ ሳምንት በጥቂት ስፍራዎች ላይ ብቻ እንቆያለን ፡፡ ዛሬ ንግግራችን እና ቤተሰባችን ላይ እንነጋገራለን/እናወራለን ፡፡ ስለ ምሳሌ በምናስብ ጊዜ ከአንድ ትዉልድ ወደ ሌላ ትዉልድ ደግሞ ደግሞ እንደገና ስለሚተላለፈዉ የጥበብ ክምችት እናስባለን ፡፡
ትምህርት
ምሳሌ (15፡ 1-2)፡ የተረጋጋች አንድ መልስ ቁጣን ስትመልስ የሻከረ ሁሉ ግን በይበልጥ ቁጣን የሚያስነሳ ነው ፤ የኔልሰን ማብራሪያ “ ብዙ ጊዜ በምንናገረዉ ነገር ሳይሆን በምንናገርበት መንገድ ይሆናል “ ይላል ፡፡ የለዘበች ንግግር የተሻለችን ምላሽ ታገኛለች ፤ አስተዋይ ሰዎች ሰዎችን ከእነርሱ ጋር እንዲገናኙ እንዲፈልጉ የሚያደርጉ መመለሻ መንገዶች ያውቃሉ (ቁጥር 2) ፡፡ የሚያስተምሩበት፣ መስተጋብር የሚያደርጉበት እና የሚነጋገሩበት መንገድ ሰዎችን ብዙ ለማወቅ እንዲፈልጉ ያደርጋቸዋል ፤ እያሉ ወዳሉት ሰዎችን ይስባሉ ፡፡ በተቃራኒዉ ሰነፎች የከንቱነትን ቃል ያፈልቃሉ (ቁጥር 2) ፡፡ ደርክ ኪንደር “ አስተዋይ ሰዉ እዉቀቱን እንደማያሳይ ሰነፍ ግን እንደሚያሳይ “ አመልክቷል፡፡ ብዙ የማይሉትን አስተዋይ ሰዎች መስማት እንፈልጋለን ነገር ግን በሚናገሩ ጊዜ የሚያወሩት አስፈላጊ ነው ፡፡
ዋረን ዋይርስቤ ምሳሌ ስለ ሰዉ ንግግር አራት ነገሮችን ያስተምረናል ብሏል፡ “ 1) ንግግር ከእግዚአብሄር የተሰጠ አስደናቂ ስጦታ ነው፣ 2) ንግግርን መልካም ነገር ለማድረግ መጠቀም ይቻላል፣ 3) ንግግርን ለክፉ ነገር ለማድረግ መጠቀም ይቻላል እና 4) ንግግርን ለመልካም ነገር እንድንጠቀምበት እግዚአብሄር ብቻ ሊረዳን ይችላል “ ፤ ምን ማለት እንዳለብን በእግዚአብሄር ላይ ስንደገፍ ይህ ይሰራል ፤ በስጋችን ስናደርግ ደግሞ ይህ አይሰራም ፡፡ እንደ ቤተሰብ በዚህ ላይ የተሻለ እናደርጋለን አሁንም በዚህ ላይ ፍፁምነትን እንቀርባለን ፡፡ በተጨማሪም ይህ እንዴት እንደሚሰራ መጀመሪያ በልጆቻችን ላይ እናየዋለን ፡፡ ንግግር በፍጥነት የሆነ ሰዉ ህይወት ላይ ተፅዕኖ ማምጣት ይችላል ፤ በንግግራችሁመሰረት ሰዎች ወደ እናንተ ይሳባሉ ወይም ደግሞ ይርቃሉ ፡፡
ምሳሌ (15፡ 3-4)፡ እግዚአብሄር ያለማቋረጥ በእነዚህ ሁለት ጥቅሶች መሰረት አንደበታቸዉን እንዴት እየተጠቀሙበት እንደሆነ በመመልከት ሕዝቡን እየተመለከተ ነው ፡፡ በሚሉትና በሚያደርጉት ሁሉ ክርስቶስን ያንፀባርቃሉ ? በልባችን ዉስጥ ስላለዉ የእግዚአብሄር ማወቅ በ 2ዜና (16፡ 9) እና 1ሳሙ (16፡ 7) የተገለፀ ነው ፡፡ መፅሀፍ በአፋችን የሚወጣዉ በልባችን ያለዉ እንደ ሆነ ያረጋግጣል (ሉቃ 6፡ 45) ፡፡ ከኢየሱስ ጋር ግንኙነት/ትስስር በሚኖረን ጊዜ በንግግራችን ዉስጥ ስለሚወጣ ሌሎች ሰዎችን ያለን እንዲፈልጉ ያደርጋቸዋል ፡፡
ቁጥር 4 ከኃላ ላይ ከቁጥር 1 እና 2 ጋር ይተሳሰራል ፡፡ የለዘበች መልስ (ቁጥር 1) የምታረካ ንግግር እና የህይወት ዛፍ ነች (ቁጥር 4) ፤ የሚያስቆጣ ቃል ግን መንፈስ የሚሰብር “ ጠማማ ነገር “ አለው ፡፡ መልካም ነገርን ስንናገር አንደበታችን ፈዉስን ማምጣት ይችላል - ወንጌልን፣ መፅኀፍትን፣ እዉነትን ስንናገርበት - ይህ ሰዎችን መጀመሪያ እግዚአብሄር ወደአቀደላቸዉ ይወስዳቸዋል ፤ ነገር ግን ቅን ያልሆነ ንግግር በምትሰጡ ጊዜ መንፈስን ይሰብራል ፡፡
ምሳሌ (15፡ 5)፡ እዚህ ጋር ሰለሞን ሙሉ ለሙሉ ርዕስ የቀየረ ቢመስልም ይህ ጥቅስ ከኃላ ከቁጥር 2 ጋር ይገናኛል ፤ ጥበብ የሆነ ነገር በምትናገሩ ጊዜ በተናገራችሁት/ባነጋገራች መሰረት ሰዎች በትክክል ያላችሁትን ይቀበላሉ (ቁጥር 5) ፡፡ “ ሰነፍ የአባቱን ተግሳፅ ይንቃል “ (ቁጥር 5) ምናልባትም አባቱ ካለዉ ጋር እርሱ ያለዉ እንዴት እንደሚገናኝ የሚያመለክት ይሆናል ፡፡
ምሳሌ (15፡ 6)፡ ሁልጊዜ ችግር በክፋት(ተገቢ ያልሆነ/ያልተፈቀደ) ዉስጥ የሚገኝ ዋጋን ይከተላል/ተከትሎ ይመጣል፡፡
ምሳሌ (15፡ 7)፡ ይህ ጥቅስ በቀጥታ ከቁጥር 2 ጋር ይገናኛል ፡፡ “ አሰራጨ/አሰማ “ የሚለዉ ቃል በትክክለኛ ንግግር በትክክለኛ ጊዜ ለመታወቅ የሚያስፈልገዉን ነገር የታወቀ ማድረግ የሚለዉን ይገልፃል ፤ በተቃራኒው መስማት ለሚችሉት ሰነፍ የሚያዉቀዉን ሁሉ ለሁሉም ሰዉ ያሰራጫል ፡፡
መደምደሚያ
ምሳሌ ከእግዚአብሄር የሚመጣ የቀን ለቀን ዉድ ተግባራዊ ነገሮች ናቸው ፡፡ እነዚህን እዉነቶች መዉሰድና በትክክል ከሰዎች ጋር መስተጋብር ስናደርግ መተግበር ከቻልን በኢየሱስ እርምጃ እንሄዳለን ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 760.
Derek Kidner, Tyndale Old Testament Commentaries: Proverbs (Downers Grove, IL: IVP Academic, 1964, 2008), p. 105.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2004), p. 1086.
Nelson’s Commentary, p. 760.
ጥያቄዎች
-
ምሳ (14፡ 12) አንብቡ ፤ በመንገዱ ላይ እያላችሁ ስታስቡት ትክክል የነበረ ነገር ግን ተመልሳችሁ ስትመለከቱት አጥፊ መንገድ እንደ ነበር ባስተዋላችሁት “ ተጉዛችሁ “ ወይም “ ኖራችሁ “ ታውቃላችሁ ? አዎ ከሆነ ግለፁ ፤ ሌሎች ይህን ሲያደርጉት እንዴት አያችሁት ? ይህ ጥቅስ ለራስ ፅድቅ መተግበር ይቻላል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
እንደ ምሳ (14፡ 16) መሰረት ጥበበኛ ሰዉ ጠንቃቃ እና ከክፋት ይመለሳል ፤ ይህን ለማድረግ አንድ ሰዉ እንዴት ጥበብ ያገኛል ? (ምሳ 1፡ 7, 2፡ 1-6, 15፡ 33)
-
ሰለሞን የለዘበች መልስ ቁጣን እንደምትመልስ አስተምሯል ፤ ከብስጭት ይልቅ እና በሁኔታዉ ከማሰራጨት ይል በለዘብታ (በትህትና) የሚመልስ አንድ ሰዉ ገጥሟችሁ ያውቃል ? ከመጥፎ/ከአስቆጪ ምላሽ ይል የለሰለሰ መልስ የምትመልሱለት ምን አይነት ሁኔታ ነው ? “ ፍቅር፣ ማዳመጥ፣ መለየት ከዚያ መመለስ “ እነዚህን ቃላቶች መጠበቅ ለሆነ ሰው ይህን እንዲያደርግ ይረዳዋል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
ምሳ (15፡ 3) ታምኑታላችሁ ? ይህ ጥቅስ ፍርሃትን፣ መበረታታትን፣ ሰላምን ወይም ሌላ ምላሽ በእናንተ ላይ ያመጣል ? ያ ለምን የእናንተ ምላሽ እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
-
ምሳሌ (15፡ 8) እና 1ቆሮ (13፡ 3) ተመልከቱ ፤ በእነዚህ ሁለት ጥቅሶች መካከል ተመሳሳይነት አይታችኋል ? ለምን ወይስ ለምን አላያችሁም ? (1ሳሙ 15፡ 22, መዝ 51፡ 16-17, ኢሳ 1፡ 11-17)
-
በምሳሌ (14-15) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Proverbs 15:1–2
“A gentle answer turns away anger, but a harsh word stirs up wrath. The tongue of the wise makes knowledge attractive, but the mouth of fools blurts out foolishness.”
እግዚአብሔር ለመግባባት ያስችልህ ዘንድ ንግግርን ወይም ቃላትን ድንቅ ስጦታ አግርጎ ሰጥቶሃል ፡፡ እርሱ ንግግርህን ከቁጣ ለመመለስ ፣ እውቀትን ለማካፈል እናም ሌሎችን ለማበረታታት እንድትጠቀምበት አሰልጥኖሃል ፡፡ ሆኖም ግን ንግግር ለክፋትም ሊውል ይችላል ፡፡ ንግግርህ ቁጣን ሊቀሰቅስ ይችላል ፣ ሞኝነትን ይገልጣል እናም በዙሪያህ ላሉት ሰዎች ቁስል ህመም ምክንያት ሊሆን ይችላል ፡፡ ምላስ በዓለም ላይ ለጥፋት እና ጉዳት ምክንያት ሊሆን ይችላል ወይም ወንጌልን በመመስከር የኢየሱስን ፍቅር ያሰራጫል ፡፡ በንግግርህ ውስጥ ለጥሩም ለመጥፎም የሚሆን ኃይል አለ ፡፡
እንዴት ነው ምላስህን መቆጣጠር የምትችለው እናም ደግሞ ለመጥፎ ሳይሆን ለመልካም መጠቀም የምትችለው ? ምን ማድረግ እንደምትፈልግ ታውቃለህ ነገር ግን ምን እንደምትናገር ለመቆጣጠር ትቸገራለህን ? ራስን መግዛት የመንፈስ ፍሬ ነው ፡፡ ስለዚህ በክርስቶስ ኑር ፣ በመንፈስ ተመላለስ ከዚያም የመንፈስን ፍሬ ታፈራለህ ፡፡ በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ስትኖር ንግግርህ የበለጠ ህይወትን የሚሰጥ ይሆናል ፡፡ ለእርሱ ፍቃድህን ስትሰጠው ፣ እርሱ እንድትረጋጋና ከመናገርህ በፊት ማሰብ እንድትችል ያበረታሃል ፡፡ ንግግርህ ለሌሎች ፍቅርን እንጅ ጥፋትን እንዳያመጣ ፣ እግዚአብሔር ልብህንና አሳብህን ይለውጥ ዘንድ ጸልይ ፡፡
“ የለዘበች መልስ ቍጣን ትመልሳለች፤ ሸካራ ቃል ግን ቍጣን ታስነሣለች ። የጠቢባን ምላስ እውቀትን ያሳምራል፤ የሰነፎች አፍ ግን ስንፍናን ያፈልቃል ። “ - ምሳሌ 15፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
- ምሳሌ 15:3-4 — “ የእግዚአብሔር ዓይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው፤ ክፉዎችንና ደጎችን ይመለከታሉ ። ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፤ የጠማማ ምላስ ግን ነፍስን ይሰብራል ። “
- ዮሐንስ 15:4 — “ በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም ። “
- ገላትያ 5:16–17 — “ ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ ። ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።