Wisdom Books Proverbs

Tame Your Tongue

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 12-13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 469 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ ድንገተኛ የሆነ አይነት ሳምንት ነው ፤ የምሳሌ መፅሀፍ ጥናታችን ስለ መለኮታዊ ወርቃማ መርሆች እና በህይወታችን ላይ ተግባራዊ ስለ ማድረግ ነው ፡፡ በምሳሌ መፅኀፍ ዉስጥ በትክክል የምሰማው አባቱ ልጁን ሲያወራው ነው ፤ ከብዙ አመለካከት አንፃር ሰለሞን ለሁሉም ጠቅለል ያለ ምክርን ሰጠ ፤ እነዚህ ተግባራዊ ማሳያዎች ናቸው ፡፡ ለዚህ መፅሀፍ አንድ ቃላችን በዚህ በጥቅላላ መፅሀፉ ዉስጥ ያየነዉ ጥበብ ነው ፤ ይህ ጥበብ ወደ ክርስቶስ ያመለክታል (1ቆሮ 1፡ 24, 30) ፡፡

ትምህርት

ምሳሌ (13፡ 1)፡ አስተዋይ ልጅ የአባቱን ተግሳፅ/ቁጣን ያደምጣል አያፌዝምም አልቀበልምም አይልም ፡፡ እግዚአብሄር እንደ ወንድ እና እንደ ሴት ልጆቹ ከእኛ ጋር ይህን እያደረገ ነው ፡፡ አባቶች ልጆቻቸዉን እንዲቀጡ ይጠበቃሉ ፡፡ ተግሳፅ ዋጋ አለው ፡፡

ምሳሌ (13፡ 2-4)፡ ከአፋችን ለሚወጣዉ ቃል መጠንቀቅ አለብን ፡፡ ሁልጊዜ ሁሉንም ነገር መናገር የለባችሁም ፤ ምን እንደምንል መመልከት ያስፈልገናል ፡፡ ሁልጊዜ የመጨረሻ ንግግር አላችሁ ? በሁሉም ነገር ላይ አስተያየታችሁን ታጋራላችሁ ? በፉክክር መንፈስ የሚጎዳ ነገር ትላላችሁ ? ሁልጊዜ ትክክል ትሆናላችሁ ? በንግግራችሁ ሌሎችን ትጎዳላችሁ ?

በራሴ ቤተሰብ ዉስጥ ንግግሮቻችንን ለማረም/ጥሩ ነገር ለማስለመድ እንታገላለን ፡፡ ይህን ስነግራችሁ ግልፅ ለመሆን በመሞከር ሲሆን ይህ እኔና ቤተሰቦቼ የምንታገልበት ነው ፤ ሁሉም ሰዉ በኑሮዉ ዉስጥ ደካማ የሚሆንበት ስፍራ አለው፣ ይህኛዉ የእኛ ነው ፡፡ ከአንደበታችሁ ከሚወጣዉ ቃል ጋር ስትታገሉ ሉቃ (6፡ 45) እና ያዕ (3፡ 6-8) ላይ ተመልከቱ ፡፡

የምንለዉ ማንኛዉም ነገር ከልባችን በመዉጣት በንግግራችን የሚወጣ/የሚነገር ነው ፡፡ በአንደበታችን ቃል የምናደርገዉ ነገር ማንሳት የሚችል ወይም ደግሞ ልክ እንደ እሳት ማጥፋት ይችላል ፡፡ ከአንደበታችን የሚወጣው የጌታ ንግግር እንዲሆን ትዕዛዝ ነው ፡፡ ንግግርን ለመግታት በሚያስችሉ መንገዶች ዉስጥ መሄድ እፈልጋለሁ ፡፡ የብሪ ጀምስ አንደበትን ለመግታት 12 መንገዶችን ሰጥቷል፡

  1. ኃጢዓትን/ክፋትን አለመናገር ፡፡
  • “ አንደበትህን ከክፉ ከልክል ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ “ (መዝ 34፡ 13) ፡፡

ለማነቃቃት መናገር ፡፡

“ እኔ እላችኋለሁ ሰዎች ሰለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል “ (ማቴ 12፡ 36) ፡፡

“ የሚያሳፍር ነገርም የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸዉና አይሁኑ ይልቁን ምስጋና እንጂ “ (ኤፌ 5፡ 4) ፡፡

በጥቂቱ መናገር ፡፡

“ በቃል ብዛት ዉስጥ ኃጢዓት ሳይኖር አይቀርም ፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው “(ምሳ 10፡ 19) ፡፡

በቁጥብነት መናገር ፡፡

በጩኸት እና በእምቢተኝነት የሚናገሩ አለመሆን ፡፡ “ ሁከተኛና አባያ ናት እግሮችዋም በቤትዋ አይቀመጡም “ (ምሳ 7፡ 11) ፡፡

“ እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ እድላቸዉ የሚያጉረመርሙ ናቸው እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጥን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል “ (ይሁዳ 16) ፡፡

ኢየሱስ እንደማይከራከር እና እንደማይጮኽ ተናገረ፡ “ አይከራከርም አይጮህምም ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም “ (ማቴ 12፡ 19) ፡፡

ያለ ችኮላ/ያለ ጥድፊያ መናገር ፡፡

“ የፃድቅ ልብ መልሱን ያስባል የኃጥዓን አፍ ግን ክፋትን ያፈልቃል “ (ምሳ 15፡ 28) ፡፡

በማወደስ መናገር ፡፡

ድርጊታችን በኢየሱስ እንደሆንን በሚያሳይ ጊዜ በስልጣን በዉዳሴ/በአምልኮ መናገር እንችላለን ፤ “ እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን እንደ ባለ ስልጣን ያስተምራቸዉ ነበርና “ (ማቴ 7፡ 29) ፡፡

“ ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተዉለዉ አደነቁ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸዉ “ (ሐዋ 4፡ 13) ፡፡

ለክርስቶስ አምባሳደሮች ናችሁ ፤ በእርሱ ፊት ጊዜ ከማሳለፍ ዉጪ እዚህ ስፍራ ላይ መድረስ አስቸጋሪ ነው ፡፡

በእምነት መናገር ፡፡

ስለምናምን በእምነት የመናገር መብት አለን ፤ “ ነገር ግን አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን “ (2ቆሮ 4፡ 13) ፡፡

“ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ፤ እኔም እጅግ ተቸገርሁ “ (ምሳ 116፡ 10) ፡፡

ትግል ዉስጥ ስትሆን እምነትን እንዲጨምርላችሁ ጌታን ጠይቁት ፡፡

እግዚአብሄር በህይወታችሁ ሲያደርገዉ ስላያችሁት እና ስለሰማችሁት ነገር መናገር ትችላላችሁ ፤ “ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነዉንና የሰማነዉን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን ፡፡ ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው “ (1ዮሐ 1፡ 3)፡፡

ለመናገር ስንፈልግ ሌሎች ወደ ክርስቶስ ይመጣሉ ፡፡

በፀሎት መንፈስ/ሁኔታ መናገር ፡፡

ስለምናገረዉ ነገር መባረክ ፤ “ ንጉሱም ምን ትለምነኛለህ ? “ (ነህ 2፡ 4) ፡፡

በማስተዋል መናገር ፡፡

“ የእግዚአብሄር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ ፡፡ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ ፡፡ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሄር ዘምሩ “ (ቆላ 3፡ 16) ፡፡

በፍርሃት መናገር ፡፡

“ በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ ፤ ኃጢዓተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ አልሁ “ (መዝ 39፡ 1) ፡፡

በርህራሄ መናገር ፡፡ “ በአንደበቱ የማይሸነግል በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ ዘመዶቹንም የማይሰድብ “ (መዝ 15፡ 3) ፡፡

ራሳን ካለማወደስ መናገር ፡፡

“ሌላ ሰዉ ያመስግናችሁ/ያወድሳችሁ ፡፡ “ ሌላ ያመስግንህ እንጂ አፍህ አይደለም ፤ ባዕድ ሰዉ እንጂ ከንፈርህ አይደለም “ (ምሳ 27፡ 2) ፡፡

መደምደሚያ

“ እግዚአብሄር ሆይ አንደበታችንን ለመቆጣጠር የተማርን ወንዶችና ሴቶች እንድንሆን ፤ በመነቃቃት እግዚአብሄርን ማክበር እንድንችል እፀልያለሁ ፡፡ የፀሎት ሴቶች እና ወንድች እንድንሆን እርዳን ፤ ሁልጊዜ ሌሎችን ወደ አንተ እንድናመለክት እርዳን ፡፡ አሜን “ ፡፡

  1. James Fraser, 12 Ways to Tame the Tongue (Reformation Scotland, Feb 1, 2018); available at https://www.reformationscotland.org/2018/02/01/12-ways-to-tame-the-tongue/.

ጥያቄዎች

  1. በምሳሌ (12፡ 12) ሰለሞን “ የጻድቃን ስር ግን ፍሬን ያፈራል “ ብሎ ተናግሯል ፤ ከፅድቅ ምን አይነት ፍሬ ሲመጣ ታያላችሁ ? (ገላ 5፡ 22-23)
  2. ሰለሞን በምሳ (12፡ 14) “ ሰዉም እንደ እጁ ስራ ዋጋዉን ይቀበላል “ በማለት ፅፏል ፤ ይህን ከገላ (6፡ 7) እና መዝ (90፡ 17) ጋር አወዳድሩ ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች እንዴት ይመሳሰላሉ ? ይህን በህይወታችሁ ተለማምዳችሁት/ደርሶባችሁ ያውቃል ?
  3. በምሳሌ (12፡ 15) በመቅበዝበዝና በጥፋት ባሉበት/በሚሄዱበት የተሳሳተ መንገድ ምንም የተሳሳተ ነገር የማያዩ ሰዎችን ተመልክታችኋል ? አማካሪ ወይም ምክር ለማቅረብ ሞክራችኍላቸዋል ? ከሌሎች እንዴት ምክርን ትቀበላላችሁ ?
  4. በምሳ (12፡ 20) እና በማቴ (5፡ 9) መካከል ግንኙነትን/ትስስርን ታያላችሁ ? ግለፁ
  5. ምሳሌ (13፡ 9) አንብቡ ፤ ይህ ጥቅስ ወደ መሲሁ ያመለክታልን ? (ዮሐ 1፡ 4-5, 8፡ 12, 12፡ 46)
  6. በምሳሌ (12-13) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Proverbs 13:3

“The one who guards his mouth protects his life; the one who opens his lips invites his own ruin.”

ከመናገርህ በፊት ለማሰብ የተለየ ጥረት አድርግ ፡፡ ከመናገርህ በፊት የምትናገራቸው ቃላቶች ጊዜውን ያማከሉ መሆናቸውን ፣ ያላቸውን ኃይል ደግሞም በሌሎች ላይ ስለሚኖራቸው ተጽዕኖ በደንብ ቆም ብለህ አስብ ፡፡ ቆም ብሎ ለማሰብና ለመታገስ ካልቻልክ ደግሞ በቃ አፍህን ከመናገር ለመከልከል ለአምስት ሰከንድ እጅህን በአፍህ ላይ ጫን እና ከዚያ በኋላ ተናገር ፡፡

የጥርስ ሳሙናን ካወጣኸው በኋላ መልሰህ ወደ መያዣው ለማስገባት ሞክረህ ታውቃለህ ? በግምት ሞክረህ አታውቅም ፡፡ ሂደቱ በጣም የሚያስጠላ ፣ ጊዜን የሚወስድ ደግሞም ከሞላ ጎደል የማይቻል ነው ፡፡ አንድ ሰው የጥርስ ሳሙናውን ከመያዣው ውስጥ ተጭኖ ሲያወጣው ፣ የጥርስ ሳሙናው ለበጎ ከመያዣው ውጪ ሁኖ ይቆያል ፡፡ የአንተም ንግግር እንድሁ ነው ፡፡ አንድ ጊዜ ከተናገርክ በኋላ ንግግርህን መመለስ አትችልም ፡፡ ከመናገርህ በፊት ስታስብና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ራስህን መቆጣጠር ስትችል ፣ የሆነ ሰው እንዳያዝን እንዳይጎዳ ታደርጋለህ ፡፡ ዛሬ ራስን መግዛት ስትለማመድ ንግግርህ ህይወትን ደግሞም ለሌሎች ፍቅርን ይናገራል ፡፡

“ አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋትን ያገኘዋል ። “

- ምሳሌ 13፡3

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ሉቃስ 6:45 — “ በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና መልካም ሰው ከልብ መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከልብ ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል ። “
  • ያዕቆብ 3:5–6 — “ እንዲሁም አንደበት ደግሞ ትንሽ ብልት ሆኖ በታላላቅ ነገር ይመካል። እነሆ፥ ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል ። አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል ። “
  • 1ኛ ጴጥሮስ 2:23 – “ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ ፡፡ “