Wisdom Books Proverbs

A Collection of Solomon's Proverbs

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 10-11 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 468 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የዳዊት ልጅ ሰለሞን ብዙ ምሳሌዎችን ፅፏል ፡፡ በአንድ ላይ ከነገስት መፅሀፍ (1ነገ 4፡ 32) ሰለሞን ቢያን 3,000 ምሳሌዎችን እና 1,000 መዝሙሮችን እንደፃፈ እናዉቃለን ፡፡ ሰለሞን ብዙ ፀሀፊ እንደ ነበር አብዛኞቹ ምሳሌዎቹ ቁም ነገር የሚናገሩ፣ ጥቂት የተጠራቀመ ጥበብን በአንድ ላይ የያዙ ናቸው ፡፡ በእያንዳንዱ ምዕራፍ ዉስጥ ስናነብ አንዳንድ ጊዜ የምናስተምርበት መንገድ በአይምሮአችን ዉስጥ የሚፈስ/የሚገባ አይደለም ፡፡ ኮንስታብል ቶም ምዕራፍ 11 ቁጥር (1-15) “ የማስተዋል ኑሮ “ በማለት እና ቁጥር (16-31) “ የማስተዋል ተግባር ማድረግ “ ብሎ በመግለፅ ወደ ሁለት ክፍል ከፍሎታል ፡፡

ትምህርት

ምሳሌ (11፡ 1)፡ “ አስጸያፊ “ የሚለዉ ቃል በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ የዋለ አይደለም ፡፡ ቀድሞ እግዚአብሄር አስፀያፊ ሆነዉ ካገኛቸዉ ሰባት ነገሮች ዝርዝር ዉስጥ አልነበረም ስለዚህም ይህ እግዚአብሄር የሚጠላቸዉ ሌሎች ነገሮች እንዳለ የሚናገር ይመስላል ፡፡ ከእነዚያ ዉስጥ አንዱ ሰዎችን ለማጭበርበር ትክክል ያልሆነ ሚዛን በመጠቀም ታማኝነትን ማጉደል ነው ፤ ይህን የእግዚአብሄርን ምልከታ ከሚዛን እና ከመስፈርት ጋር ያለዉን ከሚያብራራዉ ከምሳ (16፡ 11) ጋር አወዳድሩ ፡፡ እግዚአብሄር መስፈርትን/ደረጃን አስቀምጧል ስለዚህም የማስተዋል ኑሮ በእርሱ መስፈርት ላይ የተደገፈ ነው ፡፡ ስራን በሀቀኝነትና በታማኝነት መስራት እግዚአብሄርን ያስደስተዋል ፡፡ ምሳ (20፡ 10, 13) እግዚአብሄር የተለዩ ሚዛኖችን እና ታማኝትን ማጉደል እንደሚፀየፍ ያብራራሉ ፡፡ መፅኀፍ አለቅነትን ለማግኘት ስርዓትን ማጭበርበር ተቀባይነት እንደ ሌለዉ ይናገራል ፡፡

ምሳሌ (11፡ 2-3)፡ ይህ የማስተዋል ኑሮ ፍሬ ነገር በሀቀኝነት ላይ የተደገፈ ነው ፡፡

ምሳሌ (11፡ 4)፡ ባልተገባ መንገድ ገንዘብ በመቀበል/በመዉሰድ ስርዓቱን ሰረቃችሁት/አጭበረበራችሁ እንበል ፤ የእግዚአብሄር ቁጣ በሚመጣበት ጊዜ ያ ሀብት ከፍርድ ቀን አያድናችሁም ፡፡ ሀብት የሞት ቅጣትን እንድታመልጡ አያደርጋችሁም/አይፈቅድላችሁም ፤ ነገር ግን ፅድቅ ከሞት ይታደጋችኋል ፡፡ እንዲሁም ሕዝ (7፡ 19) በእግዚአብሄር የቁጣ ቀን የማያምኑትን ብራቸዉና ወርቃቸዉ አያድናቸዉም ይላል ፡፡ ሰለሞን ይህን ለማስተዋል ትሁት መሆን አለባችሁ ብሏል (ቁጥር 2) ፡፡

ምሳሌ (11፡ 5-7)፡ የማስተዋል ኑሮ በአላችሁ ነገር ላይ ተስፋችሁን አታስቀምጡ ይላል ምክንያቱም በእናንተ ማምጣት ስለማትችሉ ፡፡

ምሳሌ (11፡ 8-11)፡ ክፉዎች ሲሞቱ ሰዎች ደስ ይላቸዋል (ቁጥር 10) ፡፡ ይህ ቁጥር ወደ አይምሮ ሳዳም ሁሴንን እና ኢራቅን ያመጣል ፤ በሞተና ስርዓቱ በወደቀ ጊዜ ባግዳድ እንዴት እንደተደሰተች ታስታዉሳላችሁ ? ክፉ በተያዘ ጊዜ የሚያስደስተን የሖነ ነገር በዉስጣችን አለ ፡፡ አንድ አምባገነን አንድን ሀገር በመያዝ ነገሮችን ከዜጎቿ የወስደበትን ሁኔታ አስቡ ፤ አምባገነኑ በወደቀ ጊዜ ሁሉም ሰዉ ይደሰታል ፡፡

ምሳሌ (11፡ 12-13)፡ ምንም ነገር የማንልባቸዉ ጊዜያቶች አሉ ፡፡

ምሳሌ (11፡ 14)፡ በጥሩ አማካሪዎች ዙሪያችሁን ባስከበባችሁ ጊዜ በባርነት ዉስጥ ከያዙአችሁ ነገሮች ነፃ መዉጣት ትችላላችሁ ፡፡ ሁሉም ሰዉ ወደ ኋላ ከሚመልሰው ነገር ነፃ መዉጣት ይችላል ፤ መካሪዎች/አማካሪዎች ወደ ኃላ ጎትተዉ የያዙአችሁን ነገሮች በመለየት ህይወታችሁን እንድትመረምሩ በመርዳት ለህይወታችሁ እዉነትን ይነግሯችኋል ፡፡ “ ብቻዉን የቀረ “ አስተሳሰብ ልትይዙ አትችሉም - በዚህ ህይወት የሚያስኬዷችሁ ሰዎች ያስፈልጓችኋል ፡፡ ምሳ (15፡ 22) እና (20፡ 18) በኑሮአችን ብዙ አማካሪዎች ወይም ደግሞ መካሪዎች የመኖራቸዉን አስፈላጊነት ያብራራል ፤ ምሳ (24፡ 6) ተመሳሳይ ነገር ይላል ፡፡ ምናልባት ይህ የአሜሪካ ቤተ-ክርስቲያን ችግር ነው - ምክርና ምሪት ስለምንፈራ በኃጢዓት ዉስጥ እንወድቃለን ፡፡ መፅሀፍ በብዙ አማካሪዎች ስንከበብ ድል ማድረግ ይመጣል ይላል ፡፡ አማካሪዎች ሁሉንም “ አዎ ” የሚሉ ሰዎች መሆን የሌባቸው - ለሁሉም ነገር አዎ የሚሉ ሰዎች እናንተ የመረጣችኋቸዉ ናቸው ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር “ ዉሳኔ በጣም አስፈላጊ ከሆነ በጣም ተገቢዊ የጋራ/ማህበራው ጥበብ ነዉ “ ብሏል ፡፡ በፍጹም ከምክር በላይ ስላልሆናችሁ ለዚህ አይነት የማስተዋል ኑሮ ራሳችሁን ትሁት አድርጉ ፡፡ ሁል ጊዜ መጀመሪያ እግዚአብሄርን ፈልጉ ከዚያም ስለምንሄድበት መንገድ ምን እንደሚያስቡ (ዳዊት፣ ሰለሞን እና ናታን እንዳደረጉት) መካሪዎችን አስተዋይ መካሪዎችን ማማከር ፡፡ መጀመሪያ እግዚአብሄርን ከመፈለግ በፊት ሌሎች አማካሪዎችን በምንፈልግ ጊዜ ነገሮች ይበላሻሉ ፡፡

ምሳሌ (11፡ 15)፡ በመሰረቱ ለአንድ ወዳጅ/ጎረቤት ገንዘብ ተበድራችሁ ስታስቀምጡ ችግር ዉስጥ ናችሁ ፤ ነገር ግን እንዲህ አይነት ስምምነቶችን ከጠላችሁ ደህንነታችሁ የተጠበቀ ነው ፡፡

ምሳሌ (11፡ 16)፡ አሁን ወደ ማስተዋል ተግባሮች/የማስተዋል ሟለንዋዮች በመግባት እንጀምራለን ፡፡ ማክአርቱር “ ክፉ ሰዎች በኃብት ላይ ቢስገበገቡም በከበሩ ሴቶች በፍፁም ክብርን አያገኙትም “ ብሏል ፡፡ ገንዘብ ክብርና መከበር አይሰጣችሁም ለረጅም ጊዜም አይቆይም ፡፡

ምሳሌ (11፡ 17-19)፡ “ ኃጢዓተኛ ሰዎ ደሞዙ/ዋጋዉ ባዶ/ሞት ነው “ (ቁጥር 18) ምናልባትም ልክ ያልሆነ መስፈርትን ተጠቅሞ ሌሎችን በማጭበርበር ኃብትን ማግኘት የሚፈልጉትን ይገልፃል ፡፡ ፃድቃኖችን ወደ ህይወት እና ክፉዎችን ወደ ሞት የሚመሩ ሁለት ግልፅ ሁለት መንገዶች አሉ ፡፡

ምሳሌ (11፡ 20)፡ “ ልበ ጠማሞች በእግዚአብሄር ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው “ ፤ እግዚአብሄር ከሚጠላቸዉ ሰባት ነገሮች ጋር የት ላይ ይጣጣማል ? ጠማማ ልብ/ሀሳብ የሚለዉ ሀሳብ የንፁኀን ደም በእጃቸዉ ላይ ያለ ማፈሪያዎችን ሊያመለክት ይችላል ፤ “ በመንገዳቸው ፍጹማን የሆኑ ግን የተወደዱ ናቸው “ (ቁጥር 20) ፡፡ ያ ፅሁፍምበሀቀኝነት በመስራት እግዚአብሄርን በማክበር ወደ ሚደሰተቱ መጀመሪያ ላይ ወዳለዉ ይመልሰናል ፡፡

ምሳሌ (11፡ 21-23)፡ ኃጢዓን የተቀጡ እንደሚሆኑ ሁሉም ማብራራታቸዉን ይቀጥላሉ ፡፡

ምሳሌ (11፡ 24-26)፡ በነፃ በምትሰጡ ጊዜ ጎተራችሁ ይትረፈረፋል ፤ ይህን ነገር መስጠት በምትቀጥሉ ጊዜ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ እሰጣችኋለሁ ይላል ፡፡ በመጨረሻም ይህ ስዕል አላችሁ፡ ኃብታም ሆነዉ እንኳን በድህነት መንፈስ የሚኖሩ ሰዎች ያላቸዉን ያከማቻሉ ምክንያቱም ድሀ እንዳይሆኑ ስለሚፈሩ ፡፡ ከማከማቸት ይልቅ በሮችን በመክፈት ስጡት ፤ ይህ የአስተዋይ ተግባር መንገድ ነው ፡፡ በመጀመሪያ ስፍራ ላይ ገንዘብ እንድታገኙ እግዚአብሄር ችሎታን ወይም ብቃትን ሰጥቷችኋል ስለዚህ ይህን ስትሰጡት እግዚአብሄር አብልጦ ይሰጣችኋል ፡፡ ለምን ? እግዚአብሄር ቅደሚያ መንግስቱን ለመስጠት ስለሚፈልግ ፤ የእግዚአብሄር ሰዎች በመስራት ለመቀጠል የሚያስፈልጋቸዉ እንዲኖራቸዉ ይፈልጋል ፡፡

ዶር. ሊጎን ዱንካን የመስጠት አስር መርሆችን ይገልፃል ፡፡ ኢየሱስ እንድንሰጥ ይጠብቃልም ይፈልጋልም ፤ ኢየሱስ ለትክክለኛ ምክንያት እንድንሰጥ ይፈልጋል ፤ ኢየሱስ በቅንነት ወይም በበጎ አድራጎት መስጠትን እንድንለምድ ይፈልጋል ፡፡ የምነሰጠዉ ሁሉ ሁሉን ለሚያ አምላክ ነው ፤ የክርስቲያን ስጦታ የአምልኮ ተግባር ነው ፡፡ መስጠት በብርኃን በተገለጠ መሆን አለበት ፤ (ክርስቶስ ራሱን ከሰጠን እኛ ለምን እንይዛለን ?) መስጠት በራሳችን መንገድ የሚሆን ነው ፡፡ ለእኛ የእግዚአብሄር በረከት ለጋስነት በመስጠት ከለጋስነታችን ጋር የተገናኘ ነው ፤ መስጠት ደስተኛ በሆነ ልብ መደረግ አለበት ፡፡ መስጠት በፍቃደኝነት መሆን አለበት ምክንያቱም በነፃ ስለተቀበልን ፡፡

መደምደሚያ

በዚህ ምሳሌ የማስተዋል ኑሮን እናያለን ፡፡ እዚህ ስፍራ እንድንደርስ እግዚአብሄር በፋይናንስ ባርኮናል ፤ አሁን ለማስተዋል ተግባር ለማዋል ተጨማሪ አንድ እርምጃ ልንወስደዉ ያስፈልገናል ፡፡ የማስተዋል/የጥበብ ተግባሬ ምንድን ነው ? ይህ ኃብት ለእግዚአብሄር መንግስት መስጠት እንዴት እቀጥላለሁ ? ይህ የሚያስደንቅ የእዉነት ወርቅ ነው ምክንያቱም ጥበበኛ ሰዉ የነበረዉ ሰለሞንስለ ገንዘብ፣ ስለ ዝና ወይም ስለ ኃብት ስላልጠየቀ፣ ስለ ጥበብ ጠየቀ ፤ ጥበብን ባገኜ ጊዜ ሌላ ምን እንዳገኘ ገምቱ ? ሁሉንም ነገር አገኜ ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Proverbs, p. 80 & 84; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/proverbs.pdf.

  2. John MacArthur, The John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 709.

  3. MacArthur, p. 709.

    MacArthur, p. 709.

  4. J. Ligon Duncan, III, “Ten Principles for Christian Giving,” available from https://www.fpcjackson.org/resource-library/blog-entries/ten-principles-for-christian-giving-part-1/print and https:// www.fpcjackson.org/resource-library/blog-entries/ten-principles-for-christian-giving-part-2.

ጥያቄዎች

  1. በምሳሌ 10 ብዙ ጥቅሶች አንዳንድ የንግግር አይነቶችን ይጠቅሳል (በአፋ፣ በከንፈር እና በጉርምርታ) ፤ ምን ያክሉን ልታገኙት ትችላላችሁ ? በዚህ ምዕራፍ ላይ ብዙጊዜ ሰለሞን ለምን አጉልቶ እንዳሳየዉ ምን ታስባላችሁ ? (ሉቃ 6፡ 45) ፡፡
  2. ምሳሌ (10፡ 19) አንብቡ ፤ NASB እትም “ ንግግራችሁን ቆጥቡ “ የሚል ሀረግን ይጠቀማል ፤ መቆጠብ ወይም ራስን መግዛት ከመንፈስ ፍሬዎች አንዱ ገፅታ ነው (ገላ 5፡ 22-23) ፡፡ በህይወታችሁ ይህ “ ፍሬ “ እንዴት የተትረፈረፈ ይሆናል ?
  3. እንደ ሰለሞን አገላለፅ ፃድቃን በፍፁም አይናወጡም (ምሳ 10፡ 30) ፤ እንደ አማኝ ተናዉጣችሁ እንደ ነበር ተሰምቷችሁ ያውቃል ? በእነዚያ ጊዜ ምን እዉነት ሊያቆማችሁ ቻለ ? (መዝ 55፡ 22, 112፡ 6, ዕብ 12፡ 26-27)
  4. ምሳሌ 10 እና 11 ፃድቃኖችን እና ኃጢዓንን ያነፃጽራሉ ፤ በአሁኑ ጊዜ ይንን ንፅፅር በባህላችን ዉስጥ ታዩታላችሁ ? ከእነዚህ ከሁለቱ ቡድኖች ጋር እንዴት መስተጋብር ታደርጋላችሁ ?
  5. ምሳሌ (11፡ 4) አንብቡ ፤ የጳዉሎስን ንግግር በፊል (3፡ 9)፣ በመዝ (53፡ 3) እና ኢሳ (64፡ 6) ላይ ተመልከቱ ፤ አሁን 1ቆሮ (1፡ 30), 2ቆሮ (5፡ 21), ኤር 23፡ 6 እና 33፡ 16) አንብቡ ፤ እነዚህን ጥቅሶች ካነበባችሁ በኋላ በምሳሌ (11፡ 4) ከሞት ነፃ ያወጣንን መሲሁን ማየት ትችላላችሁ ?
  6. በምሳሌ (10-11) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Proverbs 11:24–25

“One person gives freely, yet gains more; another withholds what is right, only to become poor. A generous person will be enriched, and the one who gives a drink of water will receive water.”

እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጥን ሰው ይወዳል ፡፡ በመንገድህ ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚመራህ ሁሉ ፤ እርሱ የሰጠህን ሃብት ስታካፍልም እርሱ መንገድህን ያቃናል ፡፡ እውነቱ ምንም ነገር ወደ ዘላለም ይዘህ መሄድ አለመቻልህ ነው ፡፡ ገንዘብ በፍርድ ቀን አያድንም ፡፡ በገንዘብህ ላይ ያጣልከው ተስፋ ስትሞት ይጠፋል ፡፡ ስለዚህ በምድር ላይ ሳለህ በምድር ላይ ባለህ ነገር ላይ ተስፋህን እንዳትጥል ፡፡

እግዚአብሔር የሰጠህን የተለያዩ ስጦታዎች እንዴት እንደምትጠቀም ፣ እንዴት እንደምታውል እርሱን ጠይቅ ፤ ጊዜህን ፣ ብቃትህን እንድሁም ገንዘብህን ፡፡ እግዚአብሔር ቸር ሰው ወይም ያለ ስስት የሚሰጥ ሰው እንደሚበለፅግ ይናገራል ደግሞም በልግስና የሚዘራ እርሱ በብዙ እንደሚያጭድ ይናገራል ፡፡ እግዚአብሔርን ፈልግ እርሱም መንገድህን ያቀናልሃል ፡፡ ምናልባት ከምትችለው በላይ እንድትሰራ እንድትጥር ፣ በእምነት እንድትመላለስ ሊጠበቅብህ ይችላል ምናልባትም ደግሞ የማይሆን ግራ የሚያጋባ ሊመስልም ይችላል ፡፡ ነገር ግን በመታዘዝ ስትሄድ ፣ እግዚአብሔር ታማኝ ነው ፡፡ ያንን እርምጃ ውስድና እግዚአብሔር ታማኝነትህን ፣ በልግስና መስጠትህን ፣ መታዘዝህን ሲያከብረው ተመልከት ! በአንተ ላይ በሚፈሰው በህይወት ውሃው ተጥለቅለቅ ፡፡

“ያለውን የሚበትን ሰው አለ፥ ይጨመርለታልም፤ ያለ ቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ፥ ይደኸያልም ። የምትባረክ ነፍስ ትጠግባለች፥ የረካም እርሱ ደግሞ ይረካል ። “ - ምሳሌ 11፡24-25

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ምሳሌ 11:4, 7 — “ በቍጣ ቀን ሀብት አትረባም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች …….. ኀጥእ በሞተ ጊዜ ተስፋው ይቈረጣል፥ የኃያል አለኝታም ይጠፋል ። “
  • 2ኛ ቆሮንቶስ 9:6–7 — “ ይህንም እላለሁ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፥ በበረከትም የሚዘራ በበረከት ደግሞ ያጭዳል ። እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም ። “
  • ፊልጵስዩስ 4:19 — “ አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል ። “