Wisdom Vs. Foolishness
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 8-9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መሲሀችንን በምሳሌ መፅሀፍ የሚገልፅልን ቃላችን ወይም ሀረጋችን ጥበብ ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ምሳሌ መፅሀፍ ከሰለሞን ለልጆቹ የተፃፈ ደብዳቤን ይመስላል ፤ ነገር ግን ምሳሌ 9 በትንሹ የተለዬ ነው ፤ የተጠቀሰ አንድ ወንድ ልጅ የሌም በተጨማሪም ምዕራፉ በብዛት በግብዣ/ድግስ ላይ ያነሳል ፡፡ አንድ ግብዣ በሚኖራችሁ ጊዜ ለማክበር የሆነ ነገር ይኖራችኋል ፤ ለነገሩም እዉቅና በመስጠት ትዘጋጃላችሁ ፤ ከዚያም በትክክል ድግስ/ግብዣ ይኖራችኋል - ምሳሌ 9 የሚያወራዉ ስለዚያ ነው ፡፡ ጥያቄው ለዚህ ግብዣ ምላሽ የሚሰጠዉ ማነዉ ነው ?
ትምህርት
ምሳሌ (9፡ 1-2)፡ ጥበብ ቤቷን በማዘጋጀት በገበታዋ ላይ ግብዣን አዘጋጅታለች ፡፡ በቀደምት እስራኤል ወይን የግብዣ/የድግስ ዋና የምግብ አካል ነበር ፡፡ በዮሐንስ ወንጌል ላይ የተመዘገበው የኢየሱስ የመጀመሪያ ተዓምራት ዉሃዉን ወደ ወይን መቀየሩ ነበር ፡፡ የጥበብ ቤት በሰባት ምሰሶዎች ላይ የቆመ ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ ኮንስታብል ቶም ይህ ምን ማለት እንደሆነ ብዙ አማራጮችን ሰጥቷል፡ “ እግዚአብሄር በሰባት ቀናት ዉስጥ ለአለም የሰራቸዉን ነገሮች ማዉሳት ሊሆን ይችላል (ምሳ 8፡ 22-31) ፤ አንዳንድ የጥንት/የቀድሞ አመለካከቶች አለም በሰባት ምሰሶዎች ላይ እንደተቀመጠች ያስባሉ “ ፡፡ ሌሎች ደግሞ ከምሳሌ 2 እስከ 7 ዉስጥ ሰባት ክፍሎች እንዳለ ያመለክቷሉ ፤ በተጨማሪም ሰባት ቁጥር ፍፁምነትን፣ ሙሉነትን ወይም መጨረስን ይገልፃል ፡፡
ምሳሌ (9፡ 3-9)፡ ሴት አገልጋዮች ልምድ ለሌላቸዉ እና ትርጉም አጥተዉ ለነበሩት ተጠሩ (ቁጥር 3-4) ፤ ከተራራ ጫፍ ላይ ሲጠሩ አገልጋዮቹ ሁሉም ሕዝብ እንዲመጡ ጋበዟቸዉ (ቁጥር 5) ፡፡ የእንጀራና የወይን መልክ ወደ አዲስ ኪዳን ያመለክታል ፡፡ በዮሐ (6፡ 51) ኢየሱስ “ ከሰማይ የወረደ ሕያዉ እንጀራ እኔ ነኝ ፤ ሰዉ ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል “ አለ ፤ በኢየሱስ ትምህርት/ንግግር እንጀራዉ እና ወይኑ ህይወትን ይወክላሉ ፡፡ ስለዚህም አገልጋዮቹ ህይወትን ለመቀበል ወደ ግብዣዉ እንዲመጡ ግብዣ ተደረገላቸው ፤ ምላሽ የሰጡት “ አላዋቂነትን በመተዉ በህይወት በመኖር “ ተበረታቱ (ቁጥር 6) ፡፡ ዛሬም ቤተ ክርስቲያን ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር እንዲመጡ ስትጠራ ተመሳሳይ ነገር ማለት ያስፈልገናል ፤ ልምድ ማጣትን እና አላዋቂነትን ተዉ ማለት ፡፡ የተሳለዉ ይህ ሁሉም ነገር ሊኖራችሁ አይገባም - በመምጣት ተካፈሉ ፡፡ ሁላችንም ኃጢዓተኞች ስለሆንን ስፍራን ማግኘት አንችልም (ሮሜ 3፡ 23) ፤ ይህን ግብዣ ከጎልጎልታ ከመስቀሉ ላይ ቃል በቃል ሰምተናል ፡፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ባደረገዉ ምክንያት ወደ ገበታዉ/ግብዣዉ ጋብዦናል ፡፡ በደሙና በአካሉ በኩል ወደ ራሱ ጋበዘን ፤ ይህ መዳን ከእግዚአብሄር የተሰጠ እንደሆነ ከሚያብራራው ከኤፌ (2፡ 8-9) ጋር ይገናኛል/ይተሳሰራል ፡፡
ግብዣ በተደረገ ጊዜ ከላይ ያሉትን ሁሉንም የጠየቁት ሰዎች ሞኞች እና ፌዘኞች ይሆናሉ (ቁጥር 7) ፡፡ ሰዎች ለግብዣዉ ምላሽ ሲሰጡ ትሁት መንፈስ ስለሚኖራቸው የበለጠ ለመቀበል ክፍት ናቸው (ቁጥር 8-9) ፡፡ ለዚህ መልዕክት እንዴትም ብንመልስለት የሚያመጣዉ ዉጤት አለው ፤ በትህትና እንቀበለዋለን ወይስ በትዕቢት እንጓዛለን ?
ምሳሌ (9፡ 10-12)፡ “ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው “ (ቁጥር 10) ፤ ዕብ (12፡ 28-29) እግዚአብሄርን በመፍራት ላይ ትክክለኛ/ጤነኛ የሆነ አመለካከትን ይሰጠናል ፡፡ ግብዣዉን የእግዚአብሄር በሆነ መደነቅና አምልኮ ወደ ግብዛው እንምጣ ፡፡ በተጨማሪም “ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው “ (ቁጥር 10) ፤ ምላሽ በሰጠን ጊዜ ታላቅ ከበሬታና የጠለቀ እዉቀት ስለ እግዚአብሄር እናገኛለን ፡፡ እግደ እግዚአብሄር ቃል መሰረት ስንኖር እግዚአብሄር የሰጠን ጥበብ “ የሕይወትህም ዕድሜ ይጨምርልሃል “ (ቁጥር 11) ፡፡ ምላሽ ስንሰጥ የእግዚአብሄርን መገኘት እናገኘዋለን/እንቀምሰዋለን ፤ ነገር ግን በመልዕክቱ እና በእግዚአብሄር መገኘት ላይ ከቀለድን/ካፌዝን ዉጤቱን እንሸከማለን (ቁጥር 12) ፡፡
ምሳሌ (9፡ 13-18)፡ ከጥበብ ድግስ ተቃራኒ የሆነ ሌላ ድግስ/ግብዣ አለ ፡፡ ሰነፍ ሴት ሁከተኛ፣ አሳብ የሌላት እና ምንም የማታውቅ ናት (ቁጥር 13) ፤ በመንገድም የሚያልፉትን ከከተማዋ ከፍታ ስፍራ በመሆን ትጣራለች (ቁጥር 14-15) ፡፡ በስንፍና/በሞኝነት እና በጥበብ መካከል ያለዉን ልዩነት አስተዉሉ ፤ ሞኝነት/ስንፍና ለአላዋቂዎች እና ከማስተዋል ዉጪ ለሆኑ ተመሳሳይ ግብዣን ያቀርባል (ቁጥር 16) ፡፡ ጠላት ሁልጊዜ ራሱን በብርሃን ይሸፍናል ፡፡ ተመሳሳይ መልዕክት ተሰጠ/ቀረበ ነገር ግን የጥበብ ግብዣ ህይወትን ሲያመጣ የሞኝነት ግብዣ ደግሞ ወደ ሞት ይመራል ፡፡ በሰነፍ የቀረበዉን የዉሸት ምግብ ተመልከቱ፡- የተሰረቀ ዉሃ እና በድብቅ የተበላ ጣፋጭ እንጀራ (ቁጥር 17) ፡፡ ሰይጣን ለእዉነት ዉሸታም/አስመሳይ ነው ፤ ሰዎች እንዲፈለጉት በበቂ ራሱን የሚስብ ያደርጋል - ነገር ግን ዉሸት ነው ፡፡ ከንቱነት/ስንፍና ድግስን ሳይሆን የቀብር ስነስርዓትን ያስተዋዉቃል - ሞትን እንጂ ሕይወትን አይደለም (ቁጥር 18) ፡፡
ምሳሌ 9 በሉቃስ 14 ወደ ድግሱ/ግብዣዉ ሁሉንም ከጋበዘበት ከኢየሱስ መልዕክት ጋር ይመሳሰላል ፡፡ በአጠቃላይ በእነዚህ ድግሶች ሁለት ግብዣዎች ነበሩ ፡፡ ቀበዓሉ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ አዘጋጁ የድግሱ ቀንና ስዓት ለእንግዶቹ ያሳዉቃል ፤ ከዚያ በድግሱ ቀን ላይ አዘጋጁ እንግዶቹ መጥተዉ እንደ ነበር ለማረጋገጥ ተመልሶ ይሄዳል ፤ አዘጋጁም የእንግዶቹን ትክክለኛ ቁጥር ስለሚያውቅ የድግሱ ምግብ በሰላ ይዘጋጃል ፡፡ በምሳ (1፡ 22) ጥበብ ወደ ሰዎስት የእንግዳ ቡድኖች ተጣራች፡- አላዋቂዎችን፣ ፌዘኞችን እና ሰነፎችን ፤ በምሳ (8፡ 5) በግብዣዉ ለሁለት ቡድን ብቻ ተደረገ፡- ለአላዋቂዎች እና ለሰነፎች ፤ ቀጥሎ በምሳሌ 9 ላይ ሰዎስተኛዉ ግባዥ ለማያስተዉሉት ብቻ ተደረገ ፡፡
በሉቃ (14፡ 16-24) ኢየሱስ ታላቅ ግብዣን ስለሰጠ/ስላደረገ አንድ ጌታ አንድ ምሳሌ ነገራቸው ፤ የመጀመሪያ ግብዣዉን በማድረግ በግብዣዉ/በድግሱ ቀን ላይ አገልጋዮቹ የተጋበዙትን ለመሰብሰብ በዉጡ ጊዜ ሁሉም እንግዶች/ተጋባዦች ወደ ግብዣዉ ላለመምጣታቸዉ ምክንያትን አደረጉ ፤ የአለቆቹ ሁሉ አለቃም ሁሉንም ለመጋበዝ ወደ ታላቅ ጥረት ሄደ - ድሀዎች, አካለ ጉዳተኞችን፣ እዉሮችን እና አላዋቂዎችን - ወደ ግብዣዉ እንዲመጡ ጋበዛቸዉ ፤ እነዚህ ቤቱን ሲሞሉት አለቃዉ/ጌታው ከእነዚህ ሰዎች ዉስጥ ማንም በግብዣዉ እንዲደሰት እንዳልተጋበዘ ተናገረ ፡፡ በምሳሌ 9 ፅሁፍም ላይ በተለዬ አይነገር እንጂ አንዴ ግብዣዉ ስለተላከ ግብዣዉን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል መወሰን አለባችሁ ፡፡ የጌታዉን/የባለቤቱን ግብዣ ላለመቀበል ሰዎች ዝርዝር ምክንያቶች አሉአቸው - ዝግጁ አይደሉም, ወዳጆቻቸዉ እና ቤተሰቦቻቸዉ እንዳበዱ ያስቡናል ብለዉ ያስባሉ, በጣም ብዙ ቀልዶች አሉዓቸዉ/ይቀልዳሉ ወይም ደግሞ በጣም ብዙ መጥፎ ነገሮችን አድርገዋል ፤ ዝርዝሩ መቀጠል ይችላል !
መደምደሚያ
ምንም ምክንያቶች ቢቀርቡም ችግር የለዉም ወደ ጌታ ግብዣ ከመምጣትና ሰዎችን ከመጋበዝ ስለማናመልጥ ፤ ክርስቶስ ያደረገልንን ለሌሎች ከመናገር አናመልጥም - ሰዉነቱን መሰዋቱን (እንጀራው) እና ደሙን አፍስሷል (ወይኑ) ስለዚህም ግብዣዉን መቀበል እንችላለን ፡፡ ዜናዉን/ግብዣዉን ለማድረስ ኃላፊነት አለብን፣ እንዴትም ምላሽ ቢሰጡን ለሱ ተጠያቂ/ኃላፊነት የለብንም ፡፡ ምሳሌ 9 በግብዣዉ ላይ እንደሚያበረታታን ያስተማረን ማነው? ሰዎች ግብዣዉን አግኝተዉ ሲቀበሉት ለማክበር/ለመደሰት ጊዜዉ ነው ፡፡
Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes: Proverbs, p. 65. Available from https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/proverbs.pdf.
ጥያቄዎች
-
በምሳሌ 8 መሰረት እግዚአብሄርን እንደምትፈሩ እንዴት ልታሳዩ ትችላላችሁ ? እግዚአብሄርን መቼ ትፈራላችሁ በምላሹስ ምን ታገኛላችሁ ? (ምሳ 9፡ 10)
-
ምሳሌ 8 ከወርቅ፣ ከብርና ከእንቁ የሚበልጡ ብሎ የለያቸዉን ቢያንስ ሰዎስት ነገሮችን ጥቀሱ ?
-
በምሳሌ 8 መሰረት እግዚአብሄር የሚወዳቸዉ እነማን ናቸው ? በሁሉም ቀን/በየቀኑ ህይወታችሁ በትጋት እንዴት እግዚአብሄርን ትፈልጋላችሁ ?
-
ምሳ (8፡ 22-31) ስለ ማን እያወራ ነው ? (ምሳ 3፡ 19, ዮሐ 1፡ 1-2, ቆላ 1፡ 17) እዚህ እየተናገረ የነበረዉ ማን እንደሆነ ታስባላችሁ ?
-
በምሳሌ 9 ለአስተዋዮች እና እርሱን ለሚፈሩት እግዚአብሄር ምንን ተስፋ ገባላቸው ?
-
በምሳሌ (8-9) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Proverbs 9:4–6
“‘Whoever is inexperienced, enter here!’ To the one who lacks sense, she says, ‘Come, eat my bread, and drink the wine I have mixed. Leave inexperience behind, and you will live; pursue the way of understanding.’”
በጥበብ ጎዳና ላይ ለመራመድ ግብዣው ለሁሉም ሰው ቀርቧል ፣ ባለ አዕምሮ መሆንን አይጠይቅም ፡፡ ሁሉንም ነገር በአንድ ላይ የያዘ ሰው መሆን አይጠበቅብህም ፡፡ ብዙ የእውቀት ክምችትም አያስፈልግህም ፡፡ በጥበብ ጎዳና ላይ ለመሄድ መልካም ስራዎችን መስራት እንድሁም የራስህን መንገድ ማግኘት አይጠበቅብህም ፡፡
ኢየሱስ ደሙን አፍስሷል እንድሁም አለምን በሙሉ ከሞት ያድን ዘንድ ሞቷል ፤ ስለዚህም በእርሱ የሚያምን ሁሉ የእርሱን ጸጋና የዘላለምን ህይወት ይቀበላል ፡፡ ነገር ግን የሞኝነትን መንገድ የመተው እናም በምትኩ በጠባብዋ የጥበብ መንገድ የመሄድ ደግሞም እንድሁ እውቀትን የመከተል ፣ ምርጫው የአንተ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ግብዣውን ለሁሉም ሰው አቅርቧል ፤ አላዋቂ ለሆኑትም ጭምር ፡፡ አንተም የህይወት እንጀራ የሆነውን ኢየሱስን መጥተህ ትቀበል ዘንድ ተጋብዘሃል ፡፡ ምርጫው ያአንተው ነው ፡፡ በምን አይነት መንገድ ለመሄድ ትመርጣለህ ?
“ አላዋቂ የሆነ ወደዚህ ፈቀቅ ይበል፤ አእምሮ የጐደላቸውንም እንዲህ አለች ፦ ኑ፥ እንጀራዬን ብሉ፥ የደባለቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ ። አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በማስተዋልም መንገድ ሂዱ ። “
- ምሳሌ 9፡4-6
ተጨማሪ ጥቅስ
- ማቴዎስ 7:13–14 — “ በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ፤ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው ። “
- ዮሐንስ 3:16 — “ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ። “
- ኤፌሶን 2:8–9 — “ ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።