Wisdom Books Proverbs

Seven Deadly Sins

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 6-7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 466 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ለምሳሌ መፅኀፍ ጥበብ አንድ ቃላችን ነው ፡፡ የምሳሌ መፅሀፍ ያለማቋረጥ በጥበብ እና በሞኝነት መካከል ያለዉን ልዩነት ያወራል ፤ ምሳሌ የንጉሳዊ ዳኝነት አመለካከት እና ጥበባዊ ፅሁፍ የነበረዉ ቢሆንም በተጨማሪም ከቤተሰብ የሆነ ጥበብንም የተጠጋ ነው ፡፡ እነዚህ ሁሉ በመጨረሻ በክርስቶስ ወደ ሚገለጠው ወደ እግዚአብሄር ጥበብ አመልክተዋል፡ “ ለተጠሩት ግን አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ የእግዚአብሄር ኃይልና የእግዚአብሄር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው …..ነገር ግን የሚመካ በእግዚአብሄር ይመካ ተብሎ እንደ ተፃፈው ይሆን ዘንድ በእግዚአብሄር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው “ (1ቆሮ 1፡ 24, 30-31) ፡፡

ትምህርት

ምሳሌ (6፡ 1-5)፡ ኮንስታብል በእነዚህ ቁጥሮች ዉስጥ “ ስለ ሌሎች ክርክር ኃላፊነት ስለ መዉሰድ አደገኝነት “ አመልክቷል ፤ ሰለሞን ስለ ጎረቤቶች ስለ ብድር ዋስትና ስለ መሆን አስጠነቀቀ ፤ ይህ ለሌሎች ዋስ ስለመሆን ጠቅለል ያለ ተግሳፅ ነበር ፡፡ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ፡ “ በአንዳች ነገር የበደለህ ቢኖር ግን ወይም ብድር ያለበት እንደሆነ ይህን በእኔ ላይ ቁጠር ፤ እኔ ጳዉሎስ ፡፡ እኔ እመልሰዋለሁ ብዬ በእጄ እጽፋለሁ ፤ ከዚህም በላይ ለእኔ የራስህ ደግሞ ብድር እንዳለብህ አልልህም “ (ፊልሞና 18-19) በማለት ፅፏል ፡፡ ተቃራኒ በሚመስል ጳዉሎስ ስለ አናሲሞስ የፊልሞናን እዳ ለመዉሰድ ቀረበ ፤ ይሁን እንጂ ጳዉሎስ በፊልሞን እዳ ላይ ፊልሞንን ለመባረክ በመሞከር ወሰደው እንጂ የግል ትርፍን አላደረገም ፤ ፍላጎቱ ሁሉንም የተለዬ አደረገው ፡፡

ምሳሌ (6፡ 6-11)፡ ሰለሞን በስንፍና ላይ በመናገር ቀጠለ ፤ ሰለሞን ታካችን/ሰነፍን ጥበበኛ/አስተዋይ ለመሆን ጉንዳንን እንዲመለከት አዘዘ ፡፡ በዚህ ምሳሌ ጥበብ ታዛዥ ከነበሩ እና ስለ ተግባራቸዉ ከሚተጉ ፍጥረቶች ከመመልከት ይገኛል ፤ በተመሳሳይ ሰዎች ለእግዚአብሄር ታዛዥ ከሆኑ ሌሎች ሰዎች ጋር ጊዜ በማሳለፍ እና በመመልከት አስተዋይ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡

ምሳሌ (6፡ 12-15)፡ ሰለሞን ያልታመነ በመሆን ላይ አስጠነቀቀ ፤ በቁጥር 13 የሰዉነት እንቅስቃሴ - “ በዓይኑ ይጠቅሳል በእግሩ ይናገራል በጣጡ ያስተምራል “ - ይህ ሰዉዬ መንገዱን እንዲያገኙ ያሳተባቸዉ ዘዴዎች ነበሩ ፡፡ ይህ የሰዉዬው ነቀፋ በፍጥነት በመምጣት ይሚመለስበት ይሆናል (ቁጥር 15) ፡፡

ምሳሌ (6፡ 16-19)፡ ሰለሞን “ ለእርሱ የተጠሉ/አስከፊ የሆኑ “ ሰባት ነገሮችን ዘርዝሯል ፡፡

  1. ትዕቢተኛ አይኖች - ለቁጥር 13 ተቀያያሪ/ተለዋጭ መጥሪያ - “ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም ወይም በከንቱ ዉዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቁጠር “ (ፊል 2፡ 3) ፤ ኢየሱስ የትሕትናን ኑሮ በመኖር ምሳሌአችን ነው (ፊል 2፡ 5-11) ፡፡
  2. የሚዋሽ አንደበት/ምላስ - ለቁጥር 13 ተቀያያሪ/ተለዋጭ መጠሪያ - ኢየሱስ ለሌሎች ይህ የዉሸት አመለካከት ከሰይጣን ይመጣል አለ - “ እናንተ ከአባታችሁ ከዳያቢሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ ፡፡ እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ እዉነትም በእርሱ ስለሌለ በእዉነት አልቆመም፡፡ ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነዉና “ (ዮሐ 8፡ 44) ፡፡
  3. የንፁሁን ደም የሚያፈሱን እጆች - “ ለቀደሙት ፡፡ አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል ፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል ፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል ፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለዉ ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል ፤ ደንቆሮ የሚለዉም ሁሉ የገሃነም እሳት ፍርድ ይገባዋል ፡፡ እንግዲህ መባህን በመሰዊያው ላይ ብታቀርብ በዚያም ወንድምህ አንዳች በአንተ ላይ እንዳለዉ ብታስብ በዚያ በመሰዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ “ (ማቴ 5፡ 21-24) ፡፡
  4. ክፉ ሴራዎችን የሚያሴር ልብን - ለቁጥር 14 ተቀያያሪ/ተለዋጭ መጠሪያ - አንድ ግልፅ የሆነዉ ሰዎችን ለመጨፍጨፍ/ለመግደል የሚደረግ ሴራ የክፉ ሴራ ግልፅ ምሳሌ ይሆናል ፤ የዳዊት ጉዳይ ከቤርሳቤህ ጋር ለክፉ ሴራ ሌለኛዉ ምሳሌ ነበር ፡፡
  5. ወደ ክፋት ለመሮጥ የሚጓጓ/የሚቸኩል እግርን - ለቁጥር 13 ተቀያያሪ/ተለዋጭ መጠሪያ - አዳም እና ሒዋን ወደ ክፋት ሮጡ፡ “ ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች ፤ ከፍሬዉም ወሰደችና በላች ፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችዉ እርሱም ከእርሷ ጋር በላ “ (ዘፍ 3፡ 6) ፤ አዳም እና ሒዋን የሚያስጎመጅ/ምኞትን በመመልከት ወደ ነገሩም በመሳብ በማሰብ ወደ ዛፉ ሄዱ ፡፡
  6. የሐሰት ምስክር የሚሰጥ ሀሰተኛ ምስክርን - አሁንም የዉሸት አይነት ቢሆንም ይህ አይነቱ ዉሸት ሌላ ሰዉን የመስበር ባለዉ ፍላጎት ምክንያት በተለዬ ተለይቷል ፤ “ እርስ በእርሳችሁ ዉሸት አትነጋገሩ አሮጌዉን ሰው ከስራዉ ጋር ገፍታችሁታልና ፤ የፈጠረዉንም ምሳሌ እንዲመስል እዉቀትን ለማግኘት የሚታደሰዉን አዲሱን ሰዉ ለብሳችሁታልና “ (ቆላ 3፡ 9-10) ፡፡
  7. በወንድሞች መካከል ችግር የሚያስነሳን - እግዚአብሄር ሁልጊዜ ሕዝቦቹ አንድ እንዲሆኑ ይፈልጋል ፡፡

ምሳሌ (6፡ 20-35)፡ ንግግሩ ወደ ቤተሰቦቹ ተግሳፅ ወደ ልጆቹ ተመለሰ ፤ ልጁ ትምህርታቸዉን “ እንደ ብርሃን “ ለመመልከት እና ቅጣታቸዉን “ ለህይወት እንደ መንገድ “ ለማየት የደከመ ነበር (ቁጥር 23) ፡፡ ሰለሞን እንደ ገና “ በጉያው እሳትን የሚታቀፍ ልብሶቹስ የማይቃጠሉ ማነው ? በፍም ላይ የሚሄድ እግሮቹስ የማይቃጠሉ ማን ነዉ ? “ (ቁጥር 27-28) ብሎ በመጠየቅ በዝሙት ላይ (ቁጥር 25-26) እና በአመንዝራነት ላይ (ቁጥር 29) አስጠነቀቀ ፡፡

መደምደሚያ

ከእግዚአብሄር ጥበብ ተቃራኒ በሆነ መንገድ ወደ ታች መጓዝ ስንጀምር የከፋ ዉጤት ይደርስብናል ፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Proverbs, p. 52; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/proverbs.pdf.

ጥያቄዎች

  1. ምሳ (6፡ 1) ስለምንድን ነዉ የሚያወራው ? ገንዘብ ስለ መበደር መፅኀፍ ቅዱስ የሚላቸዉ ጥቂት ነገሮች ምንድን ናቸው (ዘዳ 15፡ 1-3, 23፡ 19-20, ምሳ 22፡ 26) ? ከዚያ በኋላ ገንዘብ ማበደር እና መበደር እንዴት ተቀየረ ? በአሁኑ ጊዜ ገንዘብ በማበደር እና በመበደር ሂደት ዉስጥ ከእግዚአብሄር ቃል ዉጪ እየሄድን እንደሆነ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላሰባችሁም ?
  2. እግዚአብሄር የሚጠላቸዉ ሰባት ነገሮች ምንድን ናቸው (ምሳሌ 6) ? ምሳሌ ሰባት ስለነዚህ ሰባት ነገሮች ብቻ ለምን እንዳመለከተ ምን ታስባላችሁ ? እግዚአብሄር የሚጠላቸዉ ሌሎች ነገሮች ምንድን ናቸው ? (ዘጸ 20፡ 3-17, 1ጢሞ 1፡ 9-10)
  3. ምሳሌ 6 ስለ ሰነፍ ሰዉ ምን ይላል ?
  4. በኃጢዓት ዉስጥ ላለመዉደቅ ራሳችንን እንዴት እንደምንጠብቅ ምሳሌ 6 ምን ይመክረናል ?
  5. ሰለሞን ከስጋ የዝሙት ምኞት ላይ በኃይለኛዉ ለምን እንዳስጠነቀቀ ምን ታስባላችሁ (ምሳሌ 7) ? በአሁኑ ሰዓት ይህን ሰዎች በትኩረት ይወስዱታል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  6. በምሳሌ (6-7) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ ስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Proverbs 6:20–22

“My son, keep your father’s command, and don’t reject your mother’s teaching. Always bind them to your heart; tie them around your neck. When you walk here and there, they will guide you; when you lie down, they will watch over you; when you wake up, they will talk to you.”

ምድራዊ አባት ትዕዛዝን በመስጠትና ገደብን በማድረግ ለልጆቹ ያለውን ፍቅር ይገልጻል ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የሰማዩ አባትህ እንድትከተላቸው ትዕዛዛትንና ትምህርቶችን ሰጥቶሃል ፡፡ አዎን እርሱ ያለምክንያት ይወድሃል ፡፡ አዎን እርሱ ኃጢአትህን ይቅር ብሏል ፡፡ ጸጋውና ምህረቱም በህይወት ዘመንህ ሁሉ ይከተሉሃል ፡፡ ነገር ግን ይህ ማለት ከትዕዛዛቱ ፣ ከትምህርቱና ከቃሉ ሆን ብለህ መውጣት ትችላለህ ማለት አይደለም ፡፡ ቃሉ ክፉን ከማድረግና ሰይጣን መልካም አንደሆኑ እንድታምን ከሚፈልጋቸው ነገሮች ፣ ጠብቆ ይመራሃል ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠላቸው ሰባቱ ነገሮች ልትርቃቸው የሚገቡ ነገሮች ጥሩ ምሳሌ ናቸው ፡- ትዕቢተኛ ዓይን ፥ ሐሰተኛ ምላስ ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ ፥ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር ፥ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፥ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ ።

እግዚአብሔር ጠላት አንተን የሚፈትንበትን የሚያታልልበትን መንገድ ይጠላዋል ፡፡ እርሱ ወደ ህይወትህ የሚመጣውን አጥፊ ኃጢአት ይጠላል ደግሞም ከክፉ ይጠብቅህ ዘንድ ይሻል ፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ አስፈላጊ ነው ፡፡ ህጉ ለእግርህ እንደ መብራት ለመንገድህም እንደ ብርሃን በመሆን ይመራሃል ፡፡ እግዚአብሔርም ስትራመድ ፣ ስትተኛ እናም ከእንቅልፍህ ስትነሳ ትዕዛዛቱን ለመጠበቅ የሚያስችልህን አቅም ይሰጥሃል ፡፡ በየጊዜው እርሱን ወደ መከተል እንድ እርምጃ ተራመድ ፡፡

“ ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው ፤ ሁልጊዜ በልብህ አኑረው፥ በአንገትህም እሰረው ። ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል ። “

  • ምሳሌ 6፡20-22

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 119:105 — “ ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው ። “

ምሳሌ 6:16–19 — “ እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች ፤ ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ ፥ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር ፥ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፥ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ ። “

ምሳሌ 6:23–24 — “ ትእዛዝ መብራት፥ ሕግም ብርሃን ነውና፥ የተግሣጽም ዘለፋ የሕይወት መንገድ ነውና ፥ ከክፉ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ፥ ከሌላይቱም ሴት ምላስ ጥፍጥነት ። “