Avoid Seduction
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ምሳሌ 5 በተለዬ መልኩ ወንዶችን ይደርሳል ፡፡ ዛሬ በተፈጥሮ በጣም ስሜታዊ ስለሆነ ተፈጥሮ እናወራለን ፤ የአሜሪካ ግማሽ በምሳሌ 5የተጠመዘዘ/የተዳረሰ እንደሆነ ይሰማል እንዲሁምከእነርሱ ዉስጥ ጥቂቶቹ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥም የተዳረሱ መሆናቸዉ እዉነት ነው ፡፡ ይህ መልዕክት ዛሬ በማንም ላይ ለመፍረድ ወይም ለመኮነን በሆነ መንገድ አይደለም ፡፡ ዛሬ የት ስፍራ ላይ እንደሆናችሁ በምዕራፍ 5 በትክክል መሄድ እፈልጋለሁ ፤ ፀሎቴ በትክክለኛዉ መንገድ እንድንሄድ ለመምራት እግዚአብሄር ይህንን ትምህርት/ክፍል እንደ መከላከያነት እንዲጠቀምበት ነው ፡፡ ይህ ስለ ወሲባዊ ምኞት ነው ፡፡ ዋይርስቤ እግዚአብሄር ወሲብን እንደፈጠረው እና እንዴት እንደምንጠቀምበጥ ሊነግረን ሁሉም መብት እንዳለዉ ያሳስበናል ፡፡ ወሲብ ሰይጣን እግዚአብሄር ለመልካም እንዲሆን የሚፈልገዉን ተፅእኖ አድርጎ በመዉሰድ ለጥፋትና ለክፋት ሊጠቀምበት የሚፈልገዉ አንዱ ዘርፍ/ስፍራ ነው ፡፡ ዋይርስቤ ወሲባዊ ኃጢዓት “ ወደ ብስጭት እና ወደ ተሳሳተ ሀሳብ “ ሊመራ እንደሚችልና ኃጢዓተኞቹን “ የሚፈልጉትን ሀሳባዊ ደስታ ላይ ለመድረስ ከፍተኛ ወሲባዊ ጀብድ/ጥማት እንዲፈልጉ ምክንያት እደሚሆን “ ይገልፃል ፡፡
ትምህርት
ምሳሌ (5፡ 1-6)፡ በቁጥር 1 ሰለሞን ልጁን ወደ ጥበብ እንዲያደምጥ ነገረው ፡፡ ከቀናት በፊት እንዳልነው እነዚህ ምዕራፎች ሰለሞን አይኑን ከእግዚአብሄር ላይ ከማንሳቱ በፊት የተፃፉ ነበሩ ፡፡ በዚህ ክፍል ላይ ሰለሞን ስለ መዳራት/ማታለል/ማባበል አደገኝነት ፅፏል ፡፡ የንፁኅ ጎልማሳ ወንድ ልጁን ከንፈር ሊያማልልቱ ከሚሞክሩት ከተከለከሉት ሴቶች ጋር አወዳደረ (ቁጥር 2-3) ፤ ሰለሞን ወጣት ወንድ ልጅ ምን እያደረጉ እንደነበር በትክክል ወደ ሚያዉቁት ወደ እነዚያ ሴቶች እንደሚሳብ ያውቃል ፡፡ ሰለሞን ሴቷ/ገለሞቶቹ አግኝተዉ የነበረዉ የሚፈልጉትን ከነበር ለልጁ መራር እና ሰይፍ እንደሚሆንበት ተረድቷል (ቁጥር 4) ፡፡ ሰይጣን ለህመም፣ ለብስጭት እና ለጥፋት ምክንያት የሚሆኑ ሴቶችን ሊጠቀምባቸዉ ይችላል ፤ እርግጥ ነው በቁጥር 5 ጉዞዋ በሲዖል ያበቃል - በሞት ፡፡ ኮንስታብል “ አማላይ/አታላይ ጣፋጭ (የተስተካከለ) እና ለስላሳ (በሚያስደስት) ቃል (ቁጥር 3) እንደሚመጣ “ ይገልፃል ፡፡ ምንም ይሁን ምን ከዋጡ/ ካሳመኑ ሰዉን በእነርሱ በመሳብ ምሬት (እፍረት) እና መቁሰል (መጎዳት(ቁጥር 4)) እንዲሰማው ያደርጋሉ ፤ አንዳንድ ጊዜ መዳራትም ይህን ስሜት እንዲሰማ እንደሚያደርግ “ ይገልፃል ፡፡
ብዙ ጊዜ ወደ ታች ወደ ጨለማ ሊመራን የሚችለዉ ጥቂት ነገር ነው ፡፡ ኮንስታብል የተከለከለ ሴቶችን “ ትክክለኛ ትንሽ ዋጋ ያለዉ ህይወት ለመኖር ፍላጎቱ እንደሌላቸዉ ነገር ግን አንዳንድ አካላዊ ፈጣን እና ስሜታዊ ድምፅ ብቻ ለማግኘት የሚያስቡ እንደሆኑ (ቁጥር 6) “ ይናገራል ፡፡ ሰዎች ከማድረጋቸዉ በፊት ስለሚያደርጉት ድርጊት ዉጤት አያስቡም ፡፡ ስለ ሴተኛ አዳሪነት ታስረዉ ወደ ነበሩት በተቀባይነት መልዕክት ስለ ተጓዙት 20 ወንዶች አዲስ ታሪክ አለ ፤ ታውቃላችሁ መያዝ እንደሚያገኛቸዉ እና ለድርጊታቸዉ ከባድ ነገር እንደሚገጥማቸው እያሰቡ አልነበረም በዚያ ክስተት አካላዊ ጥያቄአቸዉን ማርካትን ብቻ ፈለጉ እንጂ ፡፡
ምሳሌ (5፡ 7-14)፡ ሰለሞን አለመታመን ልጁን ምን ዋጋ ሊያስከፍለዉ እንደሚችል መናገሩን ቀጠለ ፤ ልጁን ከእርሷ ርቆ እንዲቀመጥና በቤቷ በር አጠገብ እንኳን እንዳይሄድ/እንዳያልፍ ነገረው (ቁጥር 7-8) ፡፡ ምኞቶች የማይወገዱ እና በዙሪያችን ያሉ ናቸው (ዘፍ 4፡ 7) ፡፡ ሰለሞን ምኞትን ለማስወገድ ርቆ እንዲቀመጥ ልጁን ነገረው (2ጢሞ 2፡ 22) ፤ በሚያናድድ ሁኔታ ቅርብ መሆን በሌለብን በር ላይ በተያዝን ጊዜ ማንም ከማያውቃቸዉ ከሌሎች ራሳችንን በደንብ ለይተናል ፡፡ ኮንስታብል “ የአለመታመን ዋጋ የማይገለፅ በጣም ትልቅ ነው ፤ ስለሆነም ራሱን ወይም ራሷን ከፈተና ለማስወገድ ማስታወቂያን/ማሳየት ማድረግ የሚቀጥል ጥበበኛ ነው ፤ አብዛኛዉ የጋብቻ ቃል ኪዳን መፍረስ ፓሪቲዎቹ በአንድ ላይ ጊዜ በማሳለፍ ተሳትፎ በማድረግ በመቀጠላቸዉ ይከሰታል ፡፡ እዚህ ጋር ሰለሞን የአማላዮችን/የፈታኞችን ካምፓኒ/ጉባኤ እንድናስወግድ እንደመከረ “ ገልፆአል ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር ወሲብን ለመራቢያነት ብቻ ሳይሆን ለመደሰቻነትም እንደፈጠረዉ እና ደስታችንን ለመዘረፍ በወሲብ ዙሪያ የጋብቻ ግንብን አላስቀመጠም ደስታችንን በመጨመረ ለመጠበቅም እንጂ “ በማለት ያሳስባል ፤ ሰለሞን ልጁን ከዚያ በር እንዲርቅ የነገረዉ ለዚህ ነው ፡፡ ከዚህ ዉጪ በዚያ በር ዉስጥ መሄድ የልጁን ጥንካሬ በማሳጣት ጨካኝ እና ደንታ እና በካይ ከነበረ ሰዉ ጋር ይተሳሰራል (ቁጥር 9-10) ፤ ጤንነቱም ሊወሰድ ይችላል ፡፡ ሰለሞን ልጁን በህይወቱ መጨረሻ ላይ ይህ ሊያድነዉ እንደሚችል እንዴት ተግሳፅን ጠልቶ እንደ ነበር እንደሚያስተዉል አረጋገጠለት (ቁጥር 12-14) ፡፡
ምሳሌ (5፡ 15-23)፡ በቁጥር (15-23) ሰለሞን ለምን እምነት አስፈላጊ እንደሆነ ያቀርባል ፤ እነዚህ ቁጥሮች በኃይለኛዉ የአንድ ወንድ እና ሴት ወሲብ ማድረግን በጉልህ የሚያሳዩ ናቸው ፡፡ ሰለሞን ወሲብ ለት በባል እና በሚስት መካከል ብቻ እንጂ በሌላ እንዳልሆነ በመግለፅ አብራራ ፡፡ ወሲብ ከእንግዳ/ከሌላ ሰዉ እና ከሴተኛ አዳሪ ጋር የሚካፈል/የሚደረግ አይደለም ፡፡ ወሲብ በባል እና በሚስት መካከል ብቻ የሚደረግ ማለት ነው፡ “ ከራስህ ዉሃ ማጠራቀሚያ/ገንዳ ጠጣ “ (ቁጥር 15-17) ፤ “ ከጉብዝና ሚስትህ ጋርም ደስ ይበልህ “ ፡፡ ትዳር አስቸጋሪ ከሆነባችሁ አብሮ በመሆን እንዲረዳችሁ እግዚአብሄርን በመጠየቅ እግዚአብሄር ለእናንተ የፈጠረዉን ትዳራችሁን ለማዳን የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ ፡፡ በትዳር ዉስጥ ሰዎች ከባለቤታቸዉ ጋር በመደባበር ራሳቸዉን ለማርካት ሌላ ሰዉን ይናፍቃሉ ፤ ነገር ግን ሰለሞን ልጁን በሚስቱ ሰዉነት እና ፍቅር ለዘላለም የረካ/የተደሰተ እንዲሆን ነገረው (ቁጥር 19-20) ፡፡ በቁጥር 20 “ በአይን ፍቅር አይያዝህ/አትዉደድ “ የሚለዉ ቃል “ በስሜት መሞላት/መፈለግ “ ወይም “ መስከር “ እንደ ማለት ነው ፡፡ ዋይርስቤ “ አመንዝራዎች ወንዙን ወደ ቱቦ ሲቀየር ይመለከታሉ ነገር ግን ታማኝ ባል ዉሃዉ ወይን ሲሆን ያያል “ በማለት ይገልፃል ፡፡ ቁጥር 21- 23 እግዚአብሄር ሳያዉቀዉ ማንኛዉንም የወሲብ ኃጢዓት ማራቅ አንችልም ፤ እግዚአብሄር በስልካችን እና በኮምፒተራችን ያለዉን ሁሉንም ነገር ያውቃል ፤ ማንኛዉንም ነገር ከእርሱ መደበቅ አንችልም ፡፡ ቁጥር 22-23 ክፉ/ኃጢዓተኛ ሰዉ በራሱ የኃጢዓት ገመድ በመያዝ (ዮሐ 8፡ 34, ሮሜ 6፡ 16) ስርዓት ስላልነበረዉ ይሞታል ይላሉ ፡፡
መደምደሚያ
ወደ አንድ ሁኔታ ከተሳባችሁ በራስ ወዳድነት ምክንያት ነው ፤ ስለራሳችሁ ብቻ እንጂ ስለሌሎች ስለማታስቡ ነው ፡፡ ምኞት ከተቆጣጠራችሀ የማትሰሙ/የማትረቡ ትሆናላችሁ ፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሰዎችን ነፃ በማዉጣት ስራ ላይ ነው ፡፡ ጅልነታችሁ ለማስተካከል ለክርስቶስ ትልቅ አይደለም ፡፡ ከመዳራት በመራቅ አይኖቻችሁን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አድርጉ ፡፡ ስልካችሁን በመወርወር አዲስ ስልክ ቁጥር በመያዝ ማህበራዊ ድህረ ገፆችን ለመዝጋት ለእናንተ አልረፈደም - ምንም ይሁን ያን በር አቃጥሉት አጥፉት ፡፡
ስለ ትዳራችሁ የምትችሉትን ሁሉ ታገሉ ፡፡ ዴቭ ዊልስ ስለ ትዳራችሁ የምትታገሉባቸዉን መንገዶች ይዘረዝራል፡
- ከሁሉም አይነት መተጫጨቶች፣ ጭቅጭቆች እና አሽሙሮች እረፍት ዉሰዱ ፡፡
- ባለቤታችሁን ለማጠንከር እና ለማበረታታት ጥሩ የሆነ ነገር አግኙ ፡፡
- ትክክለኛዉን መደገፊያ/ማገዣ ዘዴን መምረጥ ፡፡
- ስለ ባለቤታችሁ እና ስለ ትዳራችሁ ፀልዩ ፡፡
አንድ ነገር ልጨምርላችሁ ፤ ሁልጊዜ ሚስቴን ሳቅፋት ልጆቹ በአካል የተገናኘን እንደሆንን ያያሉ ፤ እነዚህን ነገሮች ስታደርጉ ለምኞት በራችሁን መዝጋት እና በእናንተና በባለቤታችሁ መካከል ያለዉን ስፋትም ማጥበብ ትችላላችሁ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2004), p. 407.
Wiersbe, p. 407.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Proverbs, p. 49; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/proverbs.pdf.
Constable, p. 49.
Constable, p. 50.
Wiersbe, p. 407.
Wiersbe, p. 408.
Wiersbe, p. 408.
Dave Willis, “4 Ways to Fight for Your Marriage When You are Fighting Alone”; available at https://homeword.com/jims-blog/4-ways-to-fight-for-your-marriage-when-you-are-fighting- alone/#.XJlpl9EpBPM.
ጥያቄዎች
-
በምሳሌ (5፡ 4) ሰለሞን ጋለሞታ ሴት “ ሁለት አፍ ካለዉ ሰይፍ አደገኛ እንደ ነበር “ ተናግሯል ፤ እንደዚህ አይነት ሰይፍ አደገኛነቱ ምንድን ነው ? በመፅኀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ሁለት አፍ ያለዉ ሰይፍ ተጠቅሷል ? (ዕብ 4፡ 12-13, ራዕ 1፡ 16)
-
በምሳ (5፡ 8) ሰለሞን፡ “ መንገድህን ከእርስዋ አርቅ ወደ ቤትዋም ደጅ አትቅረብ “ በማለት አስጠነቀቀ ፤ ልጁ እንዲያደርገዉ ምን እየነገረዉ ነበር ? (ማቴ 26፡ 41, 1ቆሮ 10፡ 13, ያዕ 1፡ 13-15)
-
ምሳ (5፡ 15) ስታነቡት ለእናንተ ያ ምን ማለት ነው ? በመፅኀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ ከሚስት ጋር ስለሚደረግ ወሲብ ይናገራል ? (ዘፍ 2፡ 24, 1ቆሮ 7፡ 2, ዕብ 13፡ 4)
-
መዝ (119፡ 9, 2ቆሮ 7፡ 1, ኤፌ 5፡ 3 እና 1ጴጥ 1፡ 14-16) ፤ እነዚህ ጥቅሶች እንድናደርገዉ ስለሚነግሩን ነገር ምን ታስባላችሁ ? ይህ ሰለሞን በምሳሌ 5 ሊናገረዉ እየሞከረዉ ከነበረ ጋር ይመሳሰላል ? ለምን ወይስ ለምን አይመሳሰልም ?
-
እግዚአብሄር ልጆቹን ንፁህ እና ቅዱስ ህይወት እንዲኖሩና ከወሲባዊ ኃጢዓት ነፃ እንዲሆኑ ይነግራቸዋል ፤ በራሳችሁ አገላለፅ በወሲባዊ ኃጢዓት፣ ከጋብቻ በፊት በሚደረግ ወሲብ እና በአመንዝራነት ጥቂት አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች ምን ሊሆኑ ይችላሉ ?
-
በምሳሌ 5 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Proverbs 5:7–8
“So now, my sons, listen to me, and don’t turn away from the words of my mouth. Keep your way far from her. Don’t go near the door of her house.”
ከተሳሳተ ሰው የሚቀርብ የመዳራት ግብዣ ትዳርን ያፈርሳል ፤ ነገር ግን ከዚህ ማምለጥ ይቻላል ፡፡ ተጠንቀቅ ! ብዙውን ጊዜ ሴሰኛ ሰው ደስታንና እርካታን የሆነ ሰው ጋር እንደምታገኝ ውሸትን በሚነግርህ በሰይጣን እየታገዘ ትዳርን ለማፍረስ በመሻት ሌላን ሰው ከባል ወይም ከሚስት ላይ በማባበል በዘዴ ይወስዳል ፡፡
የሰሎሞንን ምክር ተቀበል ፡- ወደ ጋለሞታ ደጅ አትቅረብ ! ወደ ጥፋት ይመራል ከዚያም አልፎ ወደ ከባድ ኃጢአት ውስጥ ያስገባል ፡፡ አዳምጥ ፣ የሚያጓጓ ሊመስል ይችላል እናም ስትፈልገው የኖርከውን ነገር ሁሉ የያዘም እንድሁ ፤ ነገር ግን በእውነቱ እርካታን አይሰጥም ወይም ዘለቄታ የለውም ፡፡ ለመሸሽ ወስን ፣ የእንደዚህ አይነቱን ሰው ስልክ ብሎክ አድርግ ፣ መንገድህን ከሚያስተጓጉሉ ቦታዎች ራቅ ፣ በመንገዱ በሌላኛው አቅጣጫ ተራመድ በተጨማሪም ከኮሚቴው ወይም ከማህበሩ ጭምር ራስህን አግልል ፡፡ የመዳራትን ማባበል ትቋቋም ዘንድ እርምጃ ውሰድ በተጨማሪም ማድረግ የሚገባህን ሁሉ አድርግ ፡፡ ድካምህን ለጌታ ተናገር ብርታትን እንድሰጥህም ጸልይ ፡፡ በየቀኑ አይኖችህን በኢየሱስ ላይ አድርግ ፡፡ ከታማኝ ጓደኛ እርዳታን ጠይቅ ፡፡ እግዚአብሔር ብርታትን ይሰጥሃል ፡፡ እርሱ የለውጥና የኋይል አምላክ ነው ! ነገር ግን አንተም ከግልሙትና ወይም ከመዳራት ለመራቅና ለመሸሽ ልትወስን ይገባል ፡፡
“ አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፥ ከአፌም ቃል አትራቁ ። መንገድህን ከእርስዋ አርቅ፥ ወደ ቤትዋም ደጅ አትቅረብ ፡፡ “
- ምሳሌ 5፡7-8
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ 5:22–23 — “ ኀጥኣንን ኃጢአቱ ታጠምደዋለች፥ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል ። አልተቀጣምና እርሱ ይሞታል፤ በስንፍናውም ብዛት ይስታል ። “
1ኛ ቆሮንቶስ 6:18 — “ ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል ። “
2ኛ ጢሞቴዎስ 2:22 – “ ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።