Learning To Trust God
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እስካሁን በጥበብ መፅሀፍት ዉስጥ 100 ክፍሎች አሉን ኢዮብን እና መዝሙርን በማካተት ፡፡ ዛሬ በምሳሌ መፅሀፍ ሁለተኛ ክፍላችን ላይ እንቀጥላለን ፡፡ የመጀመሪያዉ ነገስት ሰለሞን ከ3,000 በላይ ምሳሌዎችን እንደፃፈ ይናገራል ፡፡ እግዚአብሄርን ለሁል ጊዜ ኑሮ መለኮታዊ መርህን ለመፃፍ ሰለሞንን ተጠቀመ ፡፡ ለምሳሌ ጥናታችን ጥበብ መሲሁን የሚገልፅልን ቃላችን ነው (1ቆሮ 1፡ 24) ፡፡ ሰለሞን እንደ ጥበብ የጠቀሰዉ/ያስቀመጠው ሁሉም ነገር ከእግዚአብሄር የመጣና በመጨረሻም እንደ መሲህ ወደ ኢየሱስ ያመለክታል ፡፡ በምዕራፍ 2 ፀሀፊዉ የእግዚአብሄርን ህግ እና የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ሁለቱንም ጠቅሷል ፡፡ ምሳ (3፡ 4-6) ከምሳሌ ዉስጥ ዓይነተኛ ፅሁፍ እና ዛሬ የምንነሳበትም ነው ፡፡
ትምህርት
ምሳሌ (3፡ 1-4)፡ ምሳሌ 3 ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ምዕራፎች “ ልጄ “ ከሚለዉ ቋንቋ ይቀጥላል ፡፡ ዋይርስቤ ቁጥር 1-10 የሰለሞን ልጅ በህይወቱ እንዲከተለዉ የተቀመጠለትን ሁኔታ እንደሚያመለክቱ ይገልፃል ፡፡ ቁጥር 2 እንደ እግዚአብሄር ህግ እና ትዕዛዝ ከኖርክ ረጅም እድሜ እንደምትኖር ያመላክታል ፤ ሁኔታ ነው ? ህይወታችንን በእግዚአብሄር ትዕዛዝ መሰረት ከኖርን ህይወትን እስከ መጨረሻዉ/የተሰጠን ዘመን ሙሉ) ትኖራላችሁ እያለ እንደሆነ አስባለሁ ፡፡ ቆላ (1፡ 9-10) የሚናገረው፡ “ ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን የፈቃዱ እዉቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን ስለ እናንተ ጸሎትን አልተዉንም ፡፡ በበጎ ስራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሄርም እዉቀት እደጉ “ ፡፡ የመጀመሪያዉ ሁኔታ የምህረቱን እና የታማኝነቱን “ የእግዚአብሄርን እዉነት “ መማር ያስፈልገናል (ቁጥር 3) (ሉቃ 2፡ 52) ፡፡ በቁጥር 3 ያለዉን ሁኔታ/ግዴታ ስንከተል የኢየሱስን ምሳሌ እየተከተልን ነው ፡፡
ምሳሌ (3፡ 5-8)፡ ሁለተኛው ግዴታ “ የእግዚአብሄርን ፍቃድ እንድናከብር “ (ቁጥር 5) ይጠራናል ፡፡ ስለ እግዚአብሄር መማር ብቻ በቂ አይደለም፣ በኑሮአችን ፍቃዱን ማክበር ይጠበቅብናል ፡፡ በሁሉም ማንነታችን በራሳችን ላይ ከመደገፍ ይልቅ እግዚአብሄርን በመታመን መስራት ያስፈልገናል ፤ ወደ ትክክለኛ አቅጣጫ እንዲመራን እግዚአብሄርን እንታመን (ቁጥር 6) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ በእግዚአብሄር መታመን “ የሚለዉን ሀረግ “ ለድጋፍ በዛፍ ላይ እንደመደገፍ በእግዚአብሄር ላይ በማሰብ መደገፍ “ በማለት ይተረጉመዋል ፡፡ ስለ ጠባብ/አጭር መንገድ ለማሰብ እናዘነብላለን - በአጭር ጊዜ ቆይታ ዉስጥ የተያዘዉን ንብረት ከፍሎ ለማስለቀቅ እንዲሁም ብዙ ገንዘብ ስለሚያስገኝ ስራዉን ለመዉሰድ እንደሚደረግዉ አይነት ነው ፤ ነገር ግን በክስተቱ ላይ ከፊት ለፊታችን ትክክል ምንድን ነዉ በማለት ብቻ ስለምናተኩሩ ያልተመለከትነዉ ሌላ መንገድ እግዚአብሄር ለኛ ይኖረዋል ፡፡ ለእኛ ያለዉን እቅድ ባንመለከትም እንኳን ጥረታችንን እንዲባርክ እግዚአብሄርን እንጠይቀው ፡፡ ቁጥር 7 ራሳችሁን ጥበበኛ እንደሆናችሁ አትመልከቱ እግዚአብሄርን በመፍራት ከክፉ ተመለሱ እንጂ ይላል ፤ ቁጥር 8 እነዚህ ነገሮች ስለ ፈዉስ እና ስለ ኃይል እንደሚመጡ ይናገራል ፡፡
ዋይርስቤ ስለ መታመን ሀሳብ የተለያዩ ስዕሎችን በማምጣት “ አንድ አገልጋይ የጌታዉን ትዕዛዝ ለመታዘዝ በመዘጋጀት እንደሚጠብቀው “ “ ረዳት እንዴሌለዉ ሆኖ እንደ መዉደቅ “ በማለት ይገልፀዋል ፡፡ በእግዚአብሄር እንታመን ነገር ግን የሚፈልገዉን እንጠብቅ ፡፡ ትዕዛዞቹ በራሳችን ሳይሆን በእግዚአብሄር እንድንታመን ይናገራሉ ፤ ስለ እግዚአብሄር እንዲመራን በማሰብ እግዚአብሄርን በመፍራት ከክፉ እንድንርቅ እንዲረዳን ጥበቡን እንፈልግ ፡፡ እነዚህ ትዕዛዞች ሰዉነታችን እንዲፈወስ እና አጥንቶቻችን እንዲጠነክሩ ያደርጋሉ ፤ ፈዉስ በእግዚአብሄር ስንታመን ይመጣል ፡፡ ጥያቄአችን፡ በእርሱ ፊት በግንባራችን በመደፋት እግዚአብሄርን በመታመን መንገዳችንን እንዲመራን ለመጠበቅ ፍቃደኞች ነን ? ያ ማለት እግዚአብሄር በመምጣት የፈለገዉን ማድረግ ይችላል ምክንያቱም እግዚአብሄር ስለሆነ ማለት ነው ፡፡
ምሳሌ (3፡ 9-18)፡ ዋይርስቤ ሰዎስተኛ ግዴታዉን/ሁኔታውን “ የእግዚአብሄርን በረከት ማካፈል “ (ቁጥር 9-10) እንደሆነ ይገልፃል ፤ እግዚአብሄርን ከኃብታችን እና ከፍሬአችን በኩራት እንሰጣለን (ቁጥር 9) በእርሱም በረከት እንባረካለን (ቁጥር 10) ፡፡ ይህ በአሜሪካ ማህበረሰብ ዉስጥ ከምናምነዉ በተቃራኒ ይሄዳል - ያለንን ሙሉ በመዉሰድ ለራሳችን ማዋል ነው ያለዉ እምነት ፤ ይልቁንም ለእግዚአብሄር ቢደረግ/ቢሆን ለእርሱ በመታዘዛችንም ይባርከናል ፡፡ ለእግዚአብሄር በፍፁም ልዩ ነገር ልንሰጠዉ እንደማንችል አስታዉሱ ፡፡ ዋይርስቤ “ ለእግዚአብሄር ቅጣት እንታዘዛለን/እንገዛለን “ (ቁጥር 11-12) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የእግዚአብሄር ቅጣት የፀጋዉ ሌላ ጎን ነው ፤ በኑሮአችን በእግዚአብሄር እርማት/ማስተካከያ ደስ ሊለን ይገባል ምክንያቱም እግዚአብሄር የሚወዳቸዉን ስለሚቀጣ “ (ዕብ 12፡ 7-10) ፡፡
መደምደሚያ
ይህ ሂደት ነው ፡፡ የእግዚአብሄርን እዉነት ስንማር በኑሮአችን ፍቃዱን መታዘዝ እንችላለን ፡፡ ስንሄድ የእግዚአብሄርን በረከት ስናካፍል እና በፍቅሩ የሚደረገዉን የእግዚአብሄርን ቅጣት ለመቀበል ዝግጁ ስንሆን እዉነቱን መማርን እንድንቀጥል ይረዳናል ፡፡ ይህ የእግዚአብሄርን መርሆች በመዉሰድ በሁል ቀን ኑሮአችን ላይ እንዴት እንደሚተገበሩ አስደናቂ የጽሁፍ ክስተት ነው ፤ እንዲሁም ይህን በማድረግ ሁልጊዜ በደንብ ኢየሱስን እንመስላለን ፡፡
David Guzik, “Psalm 150–Let All Things Praise the Lord”; available at https://enduringword.com/bible-commentary/psalm-150/.
Wiersbe, p. 402.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999) p. 748.
Wiersbe, p. 402.
Wiersbe, p. 403.
Wiersbe, p. 403.
Nelson’s Commentary, p. 749.
ጥያቄዎች
-
በምሳሌ 3 የቶቹ ሁለት ቃላቶች የእግዚአብሄር ባህሪይ ይገልፃሉ (መዝሙር 100) ? በዮሐ (1፡ 14) ሐዋሪያዉ ዮሐንስ የኢየሱስን ባህሪያ እንዴት ገለፀው ?
-
በምሳ (3፡ 1-12) መሰረት የእግዚአብሄርን ምሪት ለመቀበል አራቱ ሁኔታዎች/ግዴታዎች ምንድን ናቸው ? (ቁጥር 1-4, 5-8, 9-10, 11-12)
-
ስትታመኑት እና ስትታዘዙት ከእግዚአብሄር የሚገኙት ጥቂት በረከቶች ምንድን ናቸው ? (ምሳ 3፡ 13-35)
-
በምሳ (4፡ 4) ሰለሞን “ ትዕዛዜን ጠብቁ “ የሚለዉን ደግሞ ተናገረ ፤ ይህ ለምን በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? (1ዜና 28፡ 9, ምሳ 3፡ 1, 7፡ 2, ኤፌ 6፡ 1-4)
-
በምሳሌ (3-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Proverbs 3:5–6
“Trust in the LORD with all your heart, and do not rely on your own understanding; think about Him in all your ways, and He will guide you on the right paths.”
አንድን ዛፍ ስትደገፍ ፣ አንተን ደግፎ እንደሚይዝህ በዛፉ አቅምና ጥንካሬ ላይ እምነትን ትጥላለህ ፡፡ እንዳትወድቅ የደገፈህ ዛፍ እንደማይወድቅ ታምናለህ ፡፡ እስኪ አሁን ዛፉን እንደ እግዚአብሔር አድርገህ አስበው ፡፡ አንተን ደግፎ ለማቆም እርሱ በቂ እንደሆነ ታምናለህ ፡፡ ልክ እንደ ዛፉ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ እስከተደገፍክ ድረስ ደግሞም ከመውደቅ እንደሚጠብቅህ በእርሱ ጥንካሬ ላይ እስከታመንክ ድረስ ፣ አትወድቅም ፡፡
ደግፎ እንድያቆምህ በእግዚአብሔር ላይ እየተደገፍክ ነውን ወይስ በሌላ ነገር ላይ እየተደገፍክ ነው ? እግዚአብሔር በተስፋ ላይ ተስፋን ሰጥቶሃል ፤ በምትረዳበት መንገድ ሁሉም ያጽናናሃል ያበረታህማል ፡፡ እርሱ ከአንተ ጋር ነው ፡፡ እርሱ አምላክህ ነው ፡፡ እርሱ ያበረታሃል ፡፡ እርሱ ያግዝሃል ፡፡ እርሱ ይጠብቅሃል ፡፡ ስለዚህ በነገር ሁሉ እግዚአብሔርን እመን ፤ በእርሱ ችሎታ ፣ ብርታት እመን ደግሞም እንደሚደግፍህ እና በእውነተኛው መንገድ እንደሚመራህ ተማመን ፡፡ በዚያ ዛፍ ላይ ተደገፍ - የህይወት ዛፍ በሆነው - በኤልሻዳዩ እግዚአብሔር አምላክ ፡፡ ራስህን በእግዚአብሔር ላይ እንደተደገፍክ አድርገህ መሳል ትችላለህን ? በእርሱ ብቻ ተደገፍ ፡፡ እርሱ ይደግፍሃል ይመራሃልም !
“ በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል ። “ - ምሳሌ 3፡5-6
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 62:1 — “ ነፍሴ ለእግዚአብሔር የምትገዛ አይደለችምን? መድኃኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና ። “
- ምሳሌ 3:7–8 — “ በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ከክፋትም ራቅ ፤ ይህም ለሥጋህ ፈውስ ይሆንልሃል፥ ለአጥንትህም ጠገን ። “
- ኢሳይያስ 41:10 — “ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።