Wisdom and Discipline
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Wisdom Proverbs 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በምሳሌ መፅኀፍ ላይ ነን ! የአብዛኛዉ የምሳሌ ፀሐፊ ሰለሞን ነው ፡፡ ማክአርቱር “ በሰለሞን በጥብቅ ተነግረዉ ከነበሩት 3,000 ምሳሌዎች ምሳሌ በጣም ጠቃሚ 513 ምሳሌዎችን በአንድ ላይ እንዳስቀመጠ “ ፅፏል (1ነገ 4፡ 32, መክ 12፡ 9) ፡፡ በምሳሌ መፅኀፍ ዉስጥ 31 ምዕራፎች አሉ ፡፡ ከምሳሌ መፅኀፍ ዉስጥ መሲሁን ለመግለፅ የተጠቀምንበት ቃል ጥበብ ነው (ማቴ 12፡ 42) ፡፡ በ 2ዜና (1፡ 8-12) ሰለሞን እግዚአብሄርን ስለ ጥበብ /ጥበብ እንዲሰጠዉ ጠየቀው ፤ ኢየሱስ ሰለሞን ከነበረዉ ጥበብ ይበልጣል ፡፡ ጥበብ የሚለዉን ቃል ስትሰሙ ይህ ጥበብ በዋናነት ወደ ክርስቶስ ያመለክታል (1ቆሮ 1፡ 30) ፡፡
ኮንስታብል “ ከምዕራፍ 1-9 በብዛት ምሳሌዎችን እንዳልያዙ ነገር ግን ረጅም የጥበብን ንግግር እንደያዙ “ ያመለክታል ፤ “ ሰለሞን አብዛኞቹን ምሳሌዎች (10፡ 1 – 22፡ 16 እና ምዕራፍ 25-29 ሙሉ ለሙሉ እና ምናልባትም ምዕራፍ 1-9) አመነጫቸዉ እንዲሁም ሰበሰባቸው “ ፡፡ ምዕራፍ 30 የአጉር ቃል/ንግግሮችን ሲይዝ ፤ በመጨረሻም ምዕራፍ 31 ደግሞ የልሙኤልን ቃል/ንግግር የያዘ ነው ፡፡
ትምህርት
ምሳሌ (1፡ 1)፡ ማክአርቱር “ ምሳሌ ማለት እንደዚያ ይሆናል ማለት ሲሆን፣ ምሳሌ በተለመዱ፣ ትክክለኛ በሆኑ ስዕሎች እና በሕይወትን ጥልቅ እዉነቶች መካከል የሚያነፃፅር መፅኀፍ ነው ፡፡ ምሳሌዎች ስለ ህይወት መሰረታዊ እዉነታዎችን አጉልተዉ የሚያሳዩና የሚያስተምሩ ቀላል ስነ ምግባራዊ ንግግሮች ናቸው “ በማለት ፅፏል ፡፡ ማክአርቱር ሰለሞን ስለ ጥበብ እግዚአብሄር መጠየቁን (2ዜና 1፡ 8-12) እና ሰዎችን 1) እግዚአብሄርን መፍራት እና 2) በጥበቡ መኖርን እንዲያስቡ ለማድረግ የታቀደን ቁም ነገር ንግግርን ማቅረቡን “ ለማመልከት/ለማሳየት ይቀጥላል ፡፡ ይህ ጠቅላላ መፅኀፉ እዉነትን በማንሳት እንዴት የሕይወት ሁኔታ ላይ እንደሚተገበሩ ይመለከታል ፡፡ እነዚህ መርሆች በምሳሌ መፅኀፍ ብቻ የተወሰኑ አይደሉም (ዘፍ 10፡ 9, 1ሳሙ 10፡ 12, 24፡ 13, ኤር 31፡ 29, ሕዝ 12፡ 22) ፡፡
ምሳሌ (1፡ 2)፡ እንደ ማክአርቱር አገላለፅ “ መፅሀፉ ሰዎስት እጥፍ ሀሳቦችን ያንፀባረቃል፡ 1) ጠቅላላ የጥበብ ፅሁፍ/ሀሳብ ፤ 2) ከንጉሳዊያን አካባቢ የሆኑ ምልከታዎች እና 3) በአባት እና በእናት ከልጆቻቸዉ ጋር ባላቸዉ የወዳጅነት ግንኙነት ላይ ትዕዛዝን ያቀርባል፣ እነዚህ ሁሉ በእግዚአብሄር ላይ ማሰላሰልን ለመፍጠር ተቀርፀዋል “ ፡፡ ብሉይ ኪዳንን “ ካህን ህግን ሰጠ፣ ነቢይ ከእግዚአብሄር ቃልን ሰጠ እንዲሁም ደግሞ ጠቢብ (አስተዋይ ሰዉ) ምክሩን ሰጠ “ (ኤር 18፡ 18, ሕዝ 7፡ 26) የሚለዉን ስናጠና ይህ ተመሳሳይ ስዕሉ ነው ፤ መነሻ ሀሳቡ ይህ ነው ፡፡ “ በምሳሌ በቀጥታ በነቢያት እና በሕግ ያልተደረሱትን ጠቢቡ ሰለሞን ወደ ሕይወት አስቸጋሪ ጉዳዮች ምልከታዎችን/ትርጓሜዎችን ይሰጣል (ምሳ 1፡ 6) ፡፡ በምሳሌ ዉስጥ ሁለቱ ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች ጥበብ እና ከንቱነት ናቸው ፡፡ ሁሉንም ቀን የትኛዉን መንገድ እንደምንወስድ ለመሳል ምርጫ አለን ፡፡
ሀቪንግ ሰለሞን ምሳሌን ከእግዚአብሄር ዞር ከማለቱ በፊት ፅፎታል ብሎ ይናገራል (1ነገ 11፡ 1-11) ፡፡ በመጨረሻም ሰለሞን የእስራኤልን መንግስት እንደከፈለዉ አስታዉሱ ፤ አሁንም እዚህ ስፍራ ላይ ሰለሞን የትኛዉን መንገድ እንደሚወስድ ይመርጥ ነበር ፡፡ ሁሉም ጥበብ እያለዉ እንኳን የተሳሳተዉን መንገድ መረጠ ፤ ማንም ፍፁም አይደለም ፡፡ እንዳንድ ጊዜ ፍፁም ህይወት የመሩ እንዲሁም ደግሞ ፍፁም ሰዎች የሆኑ የመፅሀፍ ቅዱስ ጀግኖች ልክ እንደ ዳዊትና ሰለሞን አሉን ፤ ፍፁም ግን አልነበሩም ፡፡ ወድቀዋል ምክንያቱም የሞኝነትን/የከንቱነትን መንገድ ስለመረጡ ፡፡ ሁልጊዜ የጥበብን መንገድ መምረጥ አለባችሁ ፡፡ ሰለሞን መዝሙር 72 እና 127፣ መክብብን እና መኃለይ መኃለይ ሰለሞንን ፅፏል ፡፡ ማክአርቱር “ ሰለሞን ወደ ዙፉኑ በታላቅ ተስፋ፣ በልዩ ጥቅም/መብት እና በእድል መጣ ፤ እግዚአብሄር ጥያቄዉን እንዲያስተዉል (1ነገ 3፡ 9-12, 1ዜና 1፡ 10-12) እና ጥበቡ ከሌሎች የበለጠ አድርጎ ሰጠው (1ነገ 4፡ 29-31) ፤ ይሁን እንጂ ሰለሞን በሚያዉቀዉ እዉነት መኖር እና ልጁን ሮብዓምን እንኳን ለማስተማር አልበቃም “ በማለት ፅፏል ፡፡ በዚህ ጥበብን በማስተዋል ሂደት ዉስጥ ስትጓዙ ይህን አስተዉሉ፡ የሁል ጊዜ ዉጊያ/ትግል እንደሆነ አስቡ ፡፡ አሁን ጥበብ አላችሁ ማለት በእግዚአብሄር መደገፍ ማቆም አለባችሁ ማለት አይደለም ፡፡
ምሳሌ (1፡ 3-6)፡ በምሳሌ ዉስጥ የምንሄድበት አላማዉ ጥበብ እና ስነስርዓት ምን እንደሆኑ መማር ነው ፡፡ ማክአርቱር “ በዕብራዊያን አመለካከት ጥበብ ብቻዉን እዉቀት አልነበረም ነገር ግን በጥበብና በትዕዛዝ እግዚአብሄራዊ ኑሮ የመኖር ችሎታ (ዘዳ 4፡ 5-8) “ ነዉ በማለት ይገልፃል ፡፡ ጥበብ ምርጥ/አስተዋይ መሆን ማለት ብቻ አይደለም የምታዉቁትን በህይወታችሁ የእግዚአብሄርን አላማ ለመኖር መጠቀምም እንጂ ፡፡ ማክአርቱር ትዕዛዝን “ የተፈጥሮ ስነ ምግባር ስነስርዓት “ በማለት ሲገልፀው እንዲሁም “ አንድን ሰዉ ለመንፈሳዊ ልየታ የሚያሳድግ የአይምሮ ስነስርዓት “ በማለት እንደተረዳ ይገፀዋል ፡፡
የምሳሌ መፅኀፍ ወደ ጥበብ፣ ወደ ስነ ስርዓት እና ወደ ማስተዋል/መረዳት ይመራል ፡፡ በብዛት አባት ወይም እናት ለወንድ ወይም ሴት ልጆቻቸዉ የሚያስተላልፏቸዉን ጥበብ እና እዉቀት የሚመስሉ ወደ ተራ/ቀላል ወደ ሚመስሉ፣ ወደ የዋሁ እና ንፁሁ የሚተላለፉ እዉቀቶችና ጥበቦች ብዙ ምሳሌዎች አሉ ፡፡ አስተዋይ ሰው ያዳምጣል መማርንም ይጨምራል የተማሩ ቢሆኑም እንኳን ምሪትን ይፈልጋሉ ፡፡ ጥበብ “ በሁሉም ቀን ህይወት ዉስጥ ብዙ ያስፈልገኛል “ ይላል ፤ ክርስቶስ ጥበባችን ነው ፡፡
ምሳሌ (1፡ 7)፡ በማክበር እና በአክብሮታዊ እግዚአብሄርን እንፈራለን ይሁን እንጂ በማንኛዉም በተሰጠ ጊዜ ላይ ሊፈርድብን እንደሚችል መረዳት አለብን (ዕብ 12፡ 28-29) ፤ የፍቅር እና የፍርድ ሁለት መልኮችን እናያለን ፡፡ በሁለቱ መካከል መመጣጠን አለ ፡፡
መደምደሚያ
ማክአርቱር በዚህ ፅኁፍ ሂደቱን ፅፎታል፡ “ 1) ስለ እግዚአብሄር ማስተማር፣ 2) ስለ እግዚአብሄር መማር፣ 3) እግዚአብሄርን መፍራት፣ 4) እግዚአብሄርን ማወቅ እና 5) የእግዚአብሄርን ጥበብ መምሰል “ ፤ ይህ የምሳሌ መፅኀፍን እንድትረዱ የሚረዳ ትልቅ ምሳሌ ነው ፡፡ እግዚአብሄርን ስትፈሩ እርሱን ማወቅ በመጀመር ትመስሉታላችሁ ፡፡ ለቤተሰብ የምሳሌ መፅሀፍን እንደ መመሪያ እንዲሁም የሚያስፈልገንን ሁሉ የህይወት ተግባራዊ ችሎታ ለማሳደግ እንደሚረዳም በፍፁም አላየሁትም ፡፡
3 Andrew E. Steinmann, "Proverbs 1—9 as a Solomonic Composition," Journal of the Evangelical Theological Society 43:4 (December 2000):659-74 quoted in Thomas Constable, Dr Constable’s Expository Bible Study Notes, Proverbs, pp. 1–2; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/proverbs.pdf.
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 695.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Proverbs, pp. 1; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/proverbs.pdf.
Constable, p. 2.
MacArthur, p. 695.
MacArthur, p. 695.
MacArthur, p. 695.
MacArthur, p. 695.
MacArthur, p. 695.
MacArthur, p. 696.
MacArthur, p. 698.
MacArthur, p. 698.
MacArthur, p. 699.
ጥያቄዎች
-
የምሳሌ ዋና ፀሀፊ ማን ነበር ? ሌላ ለዚህ መፅሀፍ አስተዋፅዖ ያደረገው ማነው ? (ምሳሌ 30 እና 31)
-
የምሳሌ አላማ ምንድነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ (ምሳ 1፡ 2-6) ? ይህን ጥበብ ለማግኘት እና ለመቀበል እንዴት ልትሄዱ ትችላላችሁ ?
-
በምሳሌ ዉስጥ አስፈላጊዉ ሀረግ/አረፍተ ነገር “ እግዚአብሄርን መፍራት “ ነው ፤ በምሳሌ 1-2 ይህ ሀረግ ምን ያክል ጊዜ ይገኛል ? እያንዳንዳቸዉን ላይ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚዉሉ ልዩነት አለው ?
-
ምሳሌ እንዴት ወደ ኢየሱስ ያመለክታል ? (ማቴ 12፡ 42, 1ቆሮ 1፡ 24, 30, ቆላ 2፡ 3, 1ዮሐ 2፡ 6)
-
በምሳ (2፡ 1-5) መሰረት እንዴት እግዚአብሄርን መፍራት በመረዳት የእግዚአብሄርን እዉቀት ልታገኙ ትችላላችሁ ?
-
በምሳሌ (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Proverbs 1:7
“The fear of the LORD is the beginning of knowledge; fools despise wisdom and discipline.”
ጠይቀህ ታውቃለህ ? እግዚአብሔርን መፍራት ምንድን ነው ? ሰሎሞን እግዚአብሔርን መፍራትን እንደ “ ጥበብ መጀመሪያ “ አደርጎ ይገልጸዋል ፡፡ በተጨማሪም ሰሎሞን “እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል “ ብሎ ጽፏል ፡፡ ሰሎሞን ልጁን ጥበብን እና እውቀትን እንደ ገንዘብ አድርጎ ለማግኘት እንድሻ ይህንንም በማድረግ “ እግዚአብሔርን መፍራት እንደሚማር “ በብልሃት ይመክረዋል ፡፡ በኋላም በአዲስ ኪዳን የዕብራውያን ጸሀፊ ለአማኞች “ በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ ፤ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና ። “ በማለት ተናግሯል ፡፡
እግዚአብሔርን መፍራት ለመማር ስትጥር ስትታገል ፣ ጽና ደግሞም ጥበብና ማስተዋልን ይሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔርን ፈልግ ፡፡ ልክ ሀብትን እንደምትፈልግ እንደዛ በመንገድህ ሁሉ እርሱን ለመፈለግ ወስን ፡፡ እንድመልስልህ ፣ እንድረዳህ እንድሁም ደግሞ ጸጋን እንድሰጥህ እርሱን ለመሻት መወሰንህ ፣ ለእርሱ ያለህን አምልኮ እና ክብር ደግሞም በእርሱ ላይ በመደገፍ ያለህን እምነት ያሳያል ፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሔር እርሱ የሚያጠፋ እሳት እንደሆነ ያለህን እምነት ታሳያለህ ፡፡ እግዚአብሔርን አብዝተህ ስታውቀው ፣ አብዝተህ ክፋትን ትጸየፋለህ ፡፡ አምላክህ እንደሚችል ታውቃለህ እናም ይህ በመንገዱ በፍርሃትና በአምልኮ እንድትቆም ያደርግሃል ፡፡ ራስህንም እግዚአብሔርን በመፍራት ስትመላለስ ታገኘዋለህ ፡፡ ምንም ነገር እርሱን በመፈለግ ከሚገኘው ሃብት ጋር ሊወዳደር አይችልም ፡፡
“ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ ። “
- ምሳሌ 1፡7
ተጨማሪ ጥቅስ
ምሳሌ 2:3–5 — “ ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት፥ ለማስተዋልም ድምፅህን ብታነሣ ፥ እርስዋንም እንደ ብር ብትፈላልጋት፥ እርስዋንም እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት ፤ የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ ። “
ምሳሌ 8:13 — “ እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል፤ ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ ጠማማውንም አፍ እጠላለሁ ። “
ዕብራውያን 12:28–29 — “ ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ ፤ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።