Wisdom Books Psalms

Adoration Through Praise

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 148-150 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 462 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በመዝሙር 150 የመዝሙር መፅሀፍ ጥናታችንን እናጠናቅቃለን ፡፡ እያንዳንዳቸዉ የመጨረሻዎቹ አምስት መዝሙሮች “ ሃሌ ሉያ እግዚአብሄር ይመስገን ! “ በማለት ይጀምራሉ ፤ እያንዳንዳቸዉ መዝሙሮች እስከ መዝሙር 150 እስክንመጣ ድረስ በመጨመር በምስጋናና በደስታ ይገነባሉ ፡፡

በዕብራዊ “ ሃሌ ሉያ “ ታላቅ ቃል ነው ! በዕብራዊ “ ሃሌሉ “ “ ይመስገን “ ወደሚል የእንግሊዘኛ ቃል ይተረጎማል ፤ በቀጥታ/ቃል በቃል “ ሃሌ ሉያ “ ማለት “ እግዚአብሄር ይመስገን ! “ ማለት ነው ፤ ፓስተር ዳዊት ጊዚክ “ እያንዳንዱ የመዝሙር መፅሀፍ እግዚአብሄርን በሚያመሰግኑ መዝሙር ይዘጋል (መዝ 41፡ 13, 72፡ 18-19- 89፡ 52, 106፡ 48) ፤ ይህ ጠቅላላ መዝሙሩ ለአምስተኛዉ እና ለመጨረሻው የመዝሙር ስብስብ ብቻ የሚቀርብ ያልሆነ አምላክን እንደ ማመስገኛ መዝሙር ማየት የሚቻል በተጨማሪም ደግሞ መላዉ የመዝሙር መፅኀፍን የቀረበ ነው ፡፡ መዝሙር 150 ክርክሮችን፣ እዉን የሆኑ ትምህርቶችን፣ እዉን የሆኑ ገለፃዎችን አልያዘም ፤ ይህ ለእርሱ ለያሕዌ ምስጋና ለመስጠት ለሁሉም ፍጥረት ልብ የሚነካ ቀስቃሽ ጩኸት እንደሆነ “ ይገልፃል ፡፡

ራሳችንን ምስጋናና ክብር በሚገባዉ ፊት ብቻ እናቆማለን ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (150፡ 1-2)፡ፓስተር ኢዩኤል ፓንካዉ እነዚህን ጥቅሶች “ ሄሌሉያ/እግዚአብሄር ይመስገን- ለምን “ በማለት ገልፆአቸዋል ፤ ይህ ሁሉ ወደ መሲሁ ያመለክታል ፡፡ “ በመቅደሱ ዉስጥ “ እግዚአብሄር የሚያድርበትን ቤተ መቅደስ አመልካች ነው ፤ ኢየሱስ ሞቶ ከተነሳ አሁን እግዚአብሄር “ ቤተ መቅደሱን “ በሰዎች ዉስጥ አደረገ በህንፃ ዉስጥ ማደርንም አልመረጠም ፡፡ ቤተ መቅደሱ ስለሆንን ምን ማለት እንደሆነ ከትርጓሜዉ በመዉጣት መኖር አለብን ፡፡

“ የኃይሉ ድርጊቶች “ በፍጥረት ላይ የታዩ ናቸው ፤ በተጨማሪም ይህ አረፍተ ነገር እግዚአብሄርን እንደ አሸናፊ የሚል ሀሳብን ይናገራል ምክንያቱም በኢየሱስ በኩል በመስቀል ላይ ባሸነፈዉ ድል (ቆላ 1፡ 19-20) ፤ ይህ በክርስቶስ በተገኘዉ ይቅርታ ብቻ በሚቻለዉ እንደ ቅዱስ በእግዚአብሄር ፊት የምንቆምበት አስደናቂ ተዓምር ነው ፤ “ የላቀ ታላቅነቱ “ ለእኛ መልካም ማሳሰቢያ/ማንቂያ ነው ፡፡ አምላክ/ታላቅ ስለሆነ ብቻ ዝምብለን ልናመሰግነዉ ይገባናል ፡፡ እግዚአብሄርን ማክበራችንበሙዳችን፣ ወይም በስሜታችን ወይም ደግሞ በሁኔታዎቻችን የተመሰረተ ነዉ ማለት አይደለም ፡፡

ሁሉም የመፅኀፍ ቅዱስ ገፅ ላይ እግዚአብሄርን የማምለክ ሀሳብ ያለዉ ነው - የተፈጠርነዉ እና የዳንነዉ ክብሩን ለማመስገን ስለሆነ ፤ ነገር ግን ዛሬ አምልኮዉን የሚያልፉ ብዙ ነገሮች ሀሳቡን ይስታሉ ፡፡ ማክበር ስለ እኔ አይደለም እግዚአብሄር ለእኔ ስላደረገዉ ነገር እንጂ ፤ ማክበር ስለ እርሱ ነው እኔም የእርሱ ስለመሆኔ በማስተዋል የሚደረግ ነው ፡፡ ስለ እርሱ እናገራለሁ ፤ ስለ እርሱ እኖራለሁ ፤ ስለ እርሱ ህይወቴን አሳልፋለሁ ፤ የእግዚአብሄርን ትክክለኛና ተገቢ ስፍራዉን በማወጅ ፡፡

በማር (12፡ 28-30) ኢየሱስ “ ከሁሉ ፊተኛይቱ ትዕዛዝ ማንኛይቱ ናት ? ተብሎ ተጠየቀ ኢየሱስም “ አንተም በፍፁም ልብህ በፍፁምም ነፍስህ በፍፁምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ዉደድ የምትል ናት “ በማለት መለሰ ፡፡ ማክበር ትኩረትን ይጣራል - በመደነቅ ወደ እግዚአብሄር በብዛት እንደ ሚፈስስ ፍቅር እንደምናተኩረዉ የጋለ ስሜት አስተሳሰብ ትኩረት አይደለም ፤ ይህ ስራችንን ስለ መስራት አይደለም - ባለቤታችንን ወይም ቤተሰባችንን ስለ ማስደሰት አይደለም - እግዚአብሄርን ስለ ማመስገን ነው - አብን፣ ወልድን እና መንፈስ ቅዱስን - አምላክ ስለሆነና ስላደረገዉ ነገር ሁሉ የሚደረግ ነው ፡፡

መዝሙር (150፡ 3-5)፡ ፓስተር ኢዮኤል ፓንኮዉ እነዚህን ጥቅሶች “ ሀሌሉያ/እግዚአብሄር ይመስገን - እንዴት “ በማለት ገልፆአቸዋል ፡፡ መዝሙር 150 አንድ የሚያስደንግ የምስጋና ባንድ ይገልፃል ፤ በእስራኤላዊያን አምልኮ ሙዚቃዉ የሚጮኽ እና ሁከት የበዛበት ነበር ፡፡ በእያንዳንዳቸዉ መሳሪያዎች ላይ ሁሉንም ልዩነትና ስሪታቸዉን ብማር እንደምወድና እንደምችል ታውቃላችሁ - ነገር ግን ያ ዛሬ አላማችን/ግባችን አይደለም ፡፡ እግዚአብሄርን ለማመስገን ማንኛዉንም ነገር መጠቀም ትችላላችሁ ፡፡ መዝሙረኛው ለመጠቀም የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ዝርዝር አድርጓል - ጡርምባ/መለከት፣ በገና፣ ክራር፣ ማስንቆ፣ ዋሽት-ጭፈራም - መዘርዘር/መጥራት ትችላላችሁ ፡፡

ታቦቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ በመጣ ጊዜ ዳዊት በ 2ዜና (15፡ 27-28) ከዚህ ጋር ተመሳሳይ አይነት የሖነን ምስጋና አሳይቷል ፤ እንዲሁም ይህን እንዲሰራ አጋዥ የሆነዉን ፍሬ ነገር ከሌላ “ መነሻ “ ጥቅሶች ጋር (ዝርዝሮች) ይታያል፡ ዘጸ (15፡ 20-21, ነህ 12፡ 27 እና 1ቆሮ 15፡ 51-52) ፤ ሀሳቡ በተለያየ ነገር እግዚአብሄርን ለማምለክ ነፃ መሆናችን ነው - የእግዚአብሄርን ስም ለማመስገን ችሎታችንን እና መሳሪያዎቻችንን መጠቀም እንችላለን ማለት ነው ፡፡

መዝሙር (150፡ 6)፡ ፓስተር ኢዩኤል ፓንኮዉ እነዚህን ጥቅሶች “ ሀሌሉያ/እግዚአብሄር ይመስገን-ማን “ በማለት ገልጦአቸዋል ፡፡ አክብሮትን/ማክበርን አሁን ለዋስትና አንዉሰድ ፤ በሚተነፈስ ጊዜ በአፍንጫ ቀዳዳ የወጣዉ ተመልሶ እንደገና የማይመጣበት ጊዜ ይመጣል ፡፡ እግዚአብሄር እያንዳንዳችንን መተንፈስን ሰጥቶናል ፤ አሁን ምስጋናዉን እንድናወራ ተጠርተናል ፡፡ እግዚአብሄር ስለ ንግግር ችሎታ ጉዳዩ አይደለም ስለ ትህትናና ስለ ታዛዥነት እንጂ ፡፡ አምልኮአችሁ ከልብ የመነጨ እስከሆነ ድረስ ተቀባይነት አለው ፤ ከዚያ በላይ ሌላ ቅርፅ ማግኘት አያስፈልጋችሁም ፡፡

መዝሙረኛው “ ድምፅኅን ልስማ እሺ ፤ እገምታለሁ ቅኝትን/ዜማን መናገር ስለምትችል “ በማለት በበሩ ላይ የምታረጋግጡ ሁኑ አላለም ፤ እግዚአብሄርን ለማመስገን ክራር፣ ጊታር ወይም ከበሮ እንዴት እንደምትጫወቱ አታዉቁም ይሆናል ፤ ጠይቋቸዉ የነበረዉ ሁሉም “ ትንፋሽ አላችሁ ? ሕያዉ ናችሁ ? ሰዉነታችሁ/አካላችሁ ንቁ ነው ? ስለዚህ እናነቃችሁ/እንቀሰቅሳችኋለን “ ፤ የእግዚአብሄርን ቃል በተመለከታችሁ ጊዜ ሰዎች ካልሆኑ ነገሮች እንኳን ምስጋናን ይቀበላል (መዝ 148፡ 7-11, ራዕ 5፡ 13) ፡፡

ይህ መዝሙር እግዚአብሄርን በማመስገኛ ትዕዛዝ ይጀምራልም ያበቃልም ፡፡ በማንኛዉም ስፍራ በምንችለዉ መንገድ ሁሉ እናመሰግነዋለን ሁሉን የሚያደርግ እሱ ስለሆነ ፡፡ በሰፊ የተለያዩ አጋዥ መሳሪያዎች በአምልኮ የድል/የአሸናፊነት ስሜት እናመሰግነዋለን ፡፡ ለምርጥ የምስጋና መሳሪያ የማክበር የኑሮ ስታይል መኖር ሙሉ ለሙሉ በግል ለእርሱ የተሰጠ መሆን ነው ፡፡

የድርጊት እርምጃ የመጀመሪያው፡ ከተመልካች ተግባርነት ወደ ተሳታፊነት ወደፊት እንድትቀጥሉ/እንድትራመዱ እጋብዛችኋለሁ ፤ አክብሮት/ማክበር አንድን ነገር እንደምንመለከተዉ ወይም እንደምናየዉ ዝም/የማንሳተፍበት ነገር አይደለም ፤ በሚደረግ አምልኮ ላይ ራሳችንን፣ ልባችንና እና እጆቻችንን በመማረክ ለእግዚአብሄር ምስጋናችንን በማንሳት ሙሉ ለሙሉ የምንሳተፍ ነን ፡፡ ራሳችሁን ጠይቁ፡ አምልኮ ተመልካች ነኝ ወደ አምልኮዉ ዉስጥ እንዳልገባ የሚከለክለኝ ምንድን ነው ? ይህን መሰናክል እንዲረዳችሁ ወደ እግዚአብሄር ዉሰዱት ፡፡

የድርጊት እርምጃ ሁለተኛው፡ በፀሎት ምን ያክል እንደምትወዱት ለእግዚአብሄር መንገርን ልምድ አድርጉት ፡፡ እርዳታ ካስፈለጋችሁ ይህን ሞክሩት፡ “ የነፍሴ የዘላለም አባት ሆይ ዛሬ የመጀመሪያ አሳቤ አንተ ሁን፣ የመጀመሪያ ስሜቴ አንተን ማምለክ ይሁን፣ የመጀመሪያ ንግግሬ ስምህ ይሁን፣ የመጀመሪያ ድርጊቴ በፀሎት መንበርከክ ይሁን ፤ አሜን “ ፡፡

መደምደሚያ

ኢየሱስ እንዳለዉ በዚህ የሆንበት ምክንያት በሰዉ ፊት ሁሉ ብርሃናችንን ይብራ መልካሙን ስራችሁን በማየት የሰማይ አምላካችሁን እንዲአከብሩት በሚለዉ ነው (ማቴ 5፡ 16) ፡፡ እግዚአብሄርን ለማመስገን በዚህ አለን ፤ በእዉነት ይህ አስቸጋሪ አይደለም ፡፡ የምህረትና የቸርነት አምላክን እያመሰገንን ለምን - ሀሌሉያ/እግዚአብሄር ይመስገን የሚለዉን ባስተዋል ጊዜ - የቀረዉ ሁሉ ወደ ስፍራዉ ይመጣል ፡፡ ማንም እንሁን ምንም እናድርግ ችግር የለም በክርስቶስ ስለ ምህረቱና ስለ ቸርነቱ ለእግዚአብሄር ምስጋና እስከሰጠን ድረስ - ብርሃናችን በመብራት ለእግዚአብሄር ክብርን ይሰጣል ፡፡

“ በፍላጎታችን እና በፍቃዳችን/በደህንነታችን ላይ መለኮታዊነቱን ተፅዕኖ ከሚያደርግ ማንኛውም ምልከተ በመለየት ራሱ እሱ/አምላክ በመሆኑ ስናመልክ እስከዚያ ክስተት ድረስ በእዉነት በፍፁም አናከብረዉም ፡፡ ቀጥሎም ብቻዉን እንወደዋለን ፤ ከዚያም ማንኛዉንም ግላዊ ጥቅም ሳይታሰብ ተስፋ በማድረግ ወይም ባለማድረግ እናከብረዋለን ፡፡ ይህም ለእኛ ስላደረገልን ወይም እንዲያደርግልን ስለምንጠብቀዉ ነገር አይደለም ነገር ግን ከመፈጠራችን በፊት ከዘላለም ጀምሮ ስላለ እና እርሱን በመፈለግ በዚህ ባንኖር እንኳን አሁንም በመኖሩ እና ለዘላለም ስለ ሚኖር ነው … ይህ በአምልኮ እኛን በመማረክ የራስ ወዳድነት የሌለበትን የራስ ቁርባንን/ስጦታን ያስከትላል ፡፡ ንፁኅ አክብሮት ያ ነው ፤ ምንም የሚያንስ ነገር የስሙ ዋጋ ነዉ “ ፡፡

3 Joel Pankow.

4 Joel Pankow.

5 Joel Pankow.

  1. David Guzik, “Psalm 150–Let All Things Praise the Lord”; available at https://enduringword.com/bible-commentary/psalm-150/.

  2. Joel Pankow, The Last Psalm Explains What “Hallelujah” Is All About, https://www.sermoncentral.com/sermons/the-last-psalm-explains-what-hallelujah-is-all-about-joel-pankow-sermon- on-worship-definition-59218?ref=SermonSerps, June 12, 2003.

  3. Albert E. Day, An Autobiography of Prayer (New York: Harper, 1952).

ጥያቄዎች

  1. በመዝሙር 148 በሰማይ እና በምድር ላይ የተመሰገነ የሚሆነዉ ማነው፣ ለምንስ የተመሰገነ ይሆናል ?
  2. በመዝ (148፡ 14) እግዚአብሄር ከሕዝቡ “ ቀንድ “ ከፍ ከፍ ያለ ነዉ ማለት ምን ማለት ነው ? (1ሳሙ 2፡ 1, ሉቃ 1፡ 69)
  3. መዝ (149፡ 1) አንብቡ ከሌሎች አማኞች ጋር በአንድ መሰብሰባችን ለእግዚአብሄር ለምን ያስፈልገዋል/ይጠቅመዋል (ኤፌ 5፡ 19, ቆላ 3፡ 16, ዕብ 10፡ 25) ? ለአምልኮ በአንድ ላይ መሰባሰብ የመጀመሪያ ትኩረቱ ምንድን ነው ?
  4. መዝሙር 149 በአምልኮአችን እግዚአብሄርን እንድናመሰግነዉ ጥሪ ነው ፤ እርሱን እንዴት እንደምናመልከዉ ለምንድን ነዉ መጠንቀቅ ያለብን (ዮሐ 4፡ 22-24, ቆላ 2፡ 16-23) ? የእግዚአብሄርን ታላቅ ደስታ የሚያመጣው አንድ ባህሪይ ምንድን ነው ? (ኢሳ 66፡ 1-2)
  5. የመዝሙር ጥናት በምስጋና ሲያጠቃልል እግዚአብሄር እርሱ አምላክ ስለሆነ ለማመስገን አሁን ጥቂት ጊዜ ዉሰዱ ፤ በመፅኀፍ ላይና በህይወታችሁ ላይ በምን ድርጊት ልታመሰግኑት ትችላላችሁ ? በጥቂት ነገሮች አመስጋኝ መሆናችሁን እርግጠኞች ሁኑ
  6. በመዝሙር (148-150) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 150:6

“Let everything that breathes praise the LORD. Hallelujah!”

ኢየሱስ ታላቁ ትዕዛዝ እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ ፣ በፍጹም ነፍስና በፍጹም አሳብ መውደድ እንደሆነ ተናግሯል ፡፡ በነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ውደድ ፡፡ ባለህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ማመስገን ፣ ለእርሱ ያለህን ፍቅር ያሳያል ፡፡ ለእነርሱ ያለህን ፍቅር ለመግለጽ ወንድ ልጅህን ወይም ሴት ልጅህን እንደምታበረታታ ወይም እንደምታደንቅ ሁሉ እግዚአብሔርን ስለ ሰራቸው መልካም ነገሮች አመስግነው ፡፡

ያልተቃኘ የዝማሬ ድምጽ ፣ የመዝሙር ስጦታ ወይም ችሎታ ማነስ ከማምለክ እንድከለክልህ እንድያቀዘቅዝህ አትፍቀድ ፡፡ እግዚአብሔርን አንተ በሆንከው ነገር ሁሉና ባለህ ነገር ሁሉ ማመስገን ትችላለህ ፡፡ እስትንፋስ ያለው ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ማመስገን ይችላል ፡፡ ይህ አንተንም ያካትታል ! አሁን ለደቂቃ ቆም በልና እግዚአብሔርን አመስግን ፡፡ በቃ ጮክ ብለህ እንድህ በል ፡- “ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ! አሜን ! “ ህይወት በውጣ ውረድ የተሞላች ናት ነገር ግን ትላንትናም ፣ ዛሬም ነገም ያማይቀየረው ያው የሆነው ሁሉን ቻዩ እግዚአብሔር አምላክ ነው ፡፡ ሃሌ ሉያ !

“ እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን ፦ ሃሌ ሉያ ። “ - መዝሙር 150፡1

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 148:7–11 — “እባቦች ጥልቆችም ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑት ፤ እሳትና በረዶ አመዳይና ውርጭ፥ ቃሉን የሚያደርግ ዐውሎ ነፋስም ፤ ተራሮች ኰረብቶችም ሁሉ፥ የሚያፈራም ዛፍ ዝግባም ሁሉ ፤ አራዊትም እንስሳትም ሁሉ፥ ተንቀሳቃሾችም የሚበርሩ ወፎችም ፤ የምድር ነገሥታት አሕዛብም ሁሉ፥ አለቆች የምድርም ፈራጆች ሁሉ “
  • ማቴዎስ 22:36–38 — “ መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው ። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት ። “
  • ራእይ 5:13 — “ በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ፦ በረከትና ክብር ምስጋናም ኃይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን ሲሉ ሰማሁ ። “