Hallelujah!
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 146-147 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መዝሙር 146 እና 147 አንዱ በሌላዉ ላይ የተገነባባ ነው ፤ በሁለቱ መዝሙሮች መካከል ያለዉ የጋራ ነገር በመፅሀፍ ባሉት ደንቦች ዉስጥ የእነዚህን ስራ ስፍራ ወደታዘዘው ወደ መለኮታዊ አርክቴክት ያመለክታል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (146፡ 1፣ መዝሙር 147፡ 1)፡ ሁለቱም መዝሙሮች እግዚአብሄርን በማመስገን አዋጅ ይጀምራሉ፡ “ ሀሌ ሉያ !“ መዝሙር 147 አምልኮአችን ለእግዚአብሄር “ እንደ ሚያስደስትና እንደ ተወደደ “ ይገልፀዋል ፡፡ መዝሙር 146 እግዚአብሄርን ለማመስገን “ ነፍሴን ይጣራል “ ፤ ነፍስ የህያዉነታችን ዘላለማዊነት መጠቃለል ይችላል ፤ ይህ ሁሉም ነገራችን በምስጋና ከእግዚአብሄር ጋር ተያይዘናል ፡፡
መዝሙር (147፡ 2-5)፡ የመዝሙር 147 ዋና ጭብጥ እስራኤልን መልሶ መገንባት ነው ፡፡ ኢሳያስ 61 ተመሳሳይ ቋንቋ ይጠቀማሉ፡ “ ከጥንትም ጀምሮ ባድማ የነበሩትን ይሰራሉ ከቀድሞ የፈረሱትንም ያቆማሉ ፤ ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትዉልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደ ገና ይሰራሉ “ (ኢሳ 61፡ 4) ፡፡ ኢየሩሳሌምን መልሶ የመገንባት ክፍል እግዚአብሄር “ ልባቸዉ የቆሰሉትን ሲፈዉስ ሕመማቸዉንም ሲጠግን “ (ቁጥር 3) ይታያል ፡፡ እንደ ገና ይህ ከኢሳ (61፡ 1) ንግግር/ቋንቋ ጋር ይመሳሰላል፡ “ የጌታ የእግዚአብሄር መንፈስ በእኔ ላይ ነው ለድሆች የምስራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሄር ቀብቶኛልና ፤ ልባቸው የተሰበረዉን እጠግን ዘንድ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛልና “ ፡፡
መዝሙረኛው እግዚአብሄርን ስለ እዉቀቱ አመሰገነው ፡፡ በተለይም እግዚአብሄር በሰማይ ስላሉት ከዋክብቶች ቁጥር ብቻ አይደለም የሚያውቀው እያንዳንዳቸዉንም በስማቸው ይጠራቸዋልም ፤ በዚህም ምክንያት እግዚአብሄር “ ታላቅ፣ ኃይሉም ታላቅ ነው፣ ለጥበቡም ቁጥር የለዉም “ (ቁጥር 5) ፡፡ ስነ መለኮት አዋቂዉ/አስተማሪው ኤ.ዋ. ቶዘር የእግዚአብሄርን 18 መለያዎችን ዘርዝሯል፡
- ሁሉም ጥበብ አለው ፡፡
- ለቁጥሩ ገደብ/መጠን የለዉም ፡፡
- ሉዓላዊ ነው ፡፡
- ቅዱስ ነው ፡፡
- በሰዎስትነት ዉስጥ አንድ ነው ፡፡
- ሁሉን አዋቂ ነው ፡፡
- የታመነ ነው ፡፡
- የማይቀየር/የማይለዋወጥ ነው ፡፡
- ዘላለማዊ ነው ፡፡
- ራሱን የቻለ ነው ፡፡
- ራሱን ችሎ የሚኖር ነው ፡፡
- ሁሉ ቦታ ይገኛል ፡፡
- ምንም የማይሳነው/ሁሉን ቻይ ነው ፡፡
- መልካም ነው ፡፡
- ትክክለኛ ነው ፡፡
- ምህረት የተሞላ ነው ፡፡
- የሚወድድ ነው ፡፡
- ከሁሉም/ከማንም የላቀ ነው ፡፡
መዝሙር (146፡ 8-9፣ መዝሙር (147፡ 6))፡ መዝሙረኛው የእግዚአብሄርን እርዳታ “ ስለ ተጠቁት “ በማወጅ ይህን ፍላጎት በክፉዎች ላይ ከእርሱ ተቃዉሞ ጋር ማነፃፀር ቀጠለ (147፡ 6) ፤ እንደ ገና ይህ ከኢሳ (61፡ 2-3)፡ “ የተወደደችዉን የእግዚአብሄርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ ፤ እግዚአብሄር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ በአመድ ፋንታ አክሊልን በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት በኃዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጎናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል “ ፡፡
መዝሙር (147፡ 7-9)፡ እንደ አይሁዶች አዉደ ጥበብ አገላለፅ ክራር ለግል አምልኮነት ጥቅም ላይ የዋለ ትንሽ የበገና አይነት ክፍል ነበር ፡፡ መዝሙረኛው እግዚአብሄርን የምድርን ፍጥረታት ስለሚመግባቸው ስለማፅናቱ አመሰገነው ፤ መዝ (136፡ 25) በተመሳሳይ “ ለስጋ ሁሉ ምግብን የሚሰጥ ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነዉና “ ይላል ፡፡
መዝሙር (147፡ 10-11)፡ መዝሙረኛው “ ስለሚፈሩትና “ እና በሰዎች እና በፈረሶቻቸዉ ሳይሆን በእግዚአብሄር ተስፋ ስለሚያደርጉት የእግዚአብሄርን ዋጋ አወጀ “ እግዚአብሄር የቀባዉን እንዳዳነው ዛሬ አወቅሁ ፤ ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል ፤ በቀኙ ብርታት ማዳን ፡፡ እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሄር ስም ከፍ ከፍ እንላለን “ (መዝ 20፡ 6-7) ፡፡ በአለም ነገሮች ላይ ከመታበይ ይልቅ መዝሙረኛዉ ከሁሉም በላይ በጌታ ላይ እንድንጣበቅ አጥብቆ አሳስቦናል ፡፡ “ በዓለም ያለዉ ሁሉ እርሱም የስጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከአባት ሳይሆን ከአለም ነዉ እንጂ “ (1ዮሐ 2፡ 6) ፡፡
መዝሙር (147፡ 12-20)፡ እግዚአብሄር ስለ እስራኤል ብልፅግናና ሀብት ኃላፊነት ይወስድ / ተጠያቂ ነበር (ቁጥር 12-14) ፡፡ ሉዓላዊ ኃይሉ የአየር ሁኔታን በመቆጣጠር እንኳን በተለይም በረዶን በማምጣት እና ከምድራቸዉ በማስወገድ ተዘረጋ (ቁጥር 15-18) ፡፡ እግዚአብሄር “ ቃሉን ለያዕቆብ ሰጠ “ (ቁጥር 19) ፤ መዝሙረኛዉ “ ይህን ለሌላ ለማንም ህዝብ እንዳላደረገ “ ፅፏል (ቁጥር 20) ፡፡ ባርነስ “ ከሌላ ከማንኛዉም ህዝብ በላይ የተገለጠ እዉነቱን በመስጠት ለእስራኤል ሞገስ/አድሎ አለው ፤ ይህ እርግጥ ነበር ፡፡ በቀደመዉ አለም ዕብራዊያን በዚህ ክብር እንደታዩበት አድሎ/ ሞገስ የታዬ ሌላ ሕዝብ አልነበረም ፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተገለጠዉ የእግዚአብሄር ፍቃድ -መፅኀፍ ቅዱስ ካላቸዉ ሌላ የተወደደ ሕዝብ የሌም ፤ የዚያ መፅኀፍ ንብረት/ኃብት ሕዝቦቹን በሌሎች በሁሉም ላይ በሁሉም ነገር ታላቅ የበላይነትን ይሰጣቸዋል ፤ በህግ፣ በልምድ፣ በስርዓት፣ በችሎታ፣ በማህበራዊ ሕይወት፣ በንፅኅና፣ በለጋስነት፣ በብልፅግና “ በማለት ፅፏል/አስቀምጧል ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሄር ለእስራኤል ቃሉን ሰጠ የሚለዉ ቀላል እዉነት ለመዝሙረኛዉ ይህን መዝሙር “ ሃሌ ሉያ !“ በማለት እንዲጨርስ በቂ ነበር ፡፡
A.W. Tozer, The Knowledge of the Holy: The Attributes of God, (San Francisco: Harper Collins, 1961).
Emilil G. Hirsch and Immanuel Benzinger, “Harp and Lyre,” Jewish Encyclopedia; available online at http://www.jewishencyclopedia.com/articles/7266-harp-and-lyre..
Albert Barnes, Albert Barnes’ Notes on the Whole Bible; available at https://www.studylight.org/commentaries/bnb/psalms-147.html.
ጥያቄዎች
-
መዝሙር 146 ጳዉሎስ በፊል (1፡ 21) እና በቆላ (3፡ 4) ላይ ከተናገረዉ እምነት ጋር እንዴት ይወዳደራል ?
-
የምስጋና ህይወት መኖር ማለት ምን ማለት ነው ? (ሮሜ 8፡ 28, ኤፌ 5፡ 20, ፊል 4፡ 6, 1ተሰ 5፡ 18) ?
-
በመዝሙር 146 መዝሙረኛዉ እምነታችሁን በሰዉ ላይ አታድርጉ ለምን አለ (ዘፍ 12፡ 10-13) ? እስራኤላዊያን ከእግዚአብሄር ላይ ይልቅ እምነታቸዉን ማን ላይ አስቀመጡ (ዘጸ 14፡ 10-14, 16፡ 1-3, ዘኁ 14፡ 1-10) ? ከጌታ ይበልጥ እምነታችሁን ልታስቀምጡበት የምትፈለጉት ማን ወይስ ምን ላይ ነው ?
-
በመዝ (147፡ 6) እና 11 መሰረት እግዚአብሄር ማንን ያነሳል በደስታስ ማንን ይወስዳል ? (1ሳሙ 2፡ 30, ማቴ 23፡ 12, ሉቃ 1፡ 50, ያዕ 4፡ 10)
-
እግዚአብሄር መጀመሪያ ቃሉን ለማን ሰጠ (መዝ 147፡ 19-20) ? በዚያ ቃል እንዲያደርጉአቸዉ የተለዩት/የተመረጡት ምን ነበሩ (ዘዳ 4፡ 7-8, 6፡ 4-9, ሮሜ 9፡ 4) ? የእግዚአብሄር ቃል በሚገባ ማግኘት ያለን በጣም እድለኞች ነን ፤ እግዚአብሄር በቃሉ እንድናደርግለት የሚፈልገዉ ምንድን ነው ? (ያዕ 2፡ 14-26)
-
በመዝሙር (146-147) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 147:10–11
“He is not impressed by the strength of a horse; He does not value the power of a man. The LORD values those who fear Him, those who put their hope in His faithful love.”
በምን ላይ ነው ተስፋን የምታደርገው ? በዚህ አለም ነገሮች ላይ ነውን ? በገንዘብ ኢንቨስትመንት ? በኃይለኛ ጀልባ ወይም በፈጣን መኪና ? ምናልባትም በተሸሻለ በታደሰ ቤት ወይም ደስ በሚል ሽርሽር ? ምናልባትም ደግሞ በልጆችህ ስኬት ? ይህን አስተውል የዚህ አለም ነገሮች ይመጣሉ ደግሞም ይሄዳሉ ፡፡ በእርግጥ ደስ እንድትሰኝ እግዚአብሔር መልካም ስጦታዎችን ይሰጥሃል ነገር ግን እነዚህ ከእግዚአብሔር የሆኑ መልካም ሰጦታዎች መገለጫህ መለያህ ሲሆኑ ፣ እግዚአብሔር ደስ አይሰኝም ፡፡ ፈጽሞ በዚህ አለም ነገሮች በእውነት ልትረካና ልትበረታ አትችልም ፡፡ በስተመጨረሻ ይወድቃሉ እናም ይረሳሉ ፡፡
ይልቁንም ተስፋህን በጌታ ላይ አድርግ ፡፡ እርሱ ለዘላለም ታማኝ ነው ፡፡ በዚህ አለም ነገሮች ላይ ዋጋን ከማስቀመጥ በላይ እግዚአብሔርን ፍራ ፡፡ እነዚህ ምድራዊ ነገሮች ይወድቃሉ ይጠፋሉም ፡፡ ነገ ምን እንደያዘ እንኳ አታውቅም እና ታድያ ነገ በዚህ ሊኖር በማይችል ነገር ላይ ለምን ትታመናለህ ? ሆኖም ግን ፡- ሃሌሉያ ! ከጌታ ጋር ጸንተህ መቆም ትችላለህ ፡፡ ከጌታ ጋር ነጻነትና ድል ይኖርሃል ፡፡ እምነትህን በጌታ ላይ መጣል ትችላለህ ምክንያቱም እርሱ ከአንተ ጋር ለዘላለም ስለሚሆን ፡፡ ይረዳህ ዘንድ በየቀኑ ጌታን ፈልግ ፡፡ እግዚአብሔርን ፍራ እናም ትባረካለህ ፡፡ ሃሌሉያ !
“ የፈረስን ኃይል አይወድድም፥ በሰውም ጭን አይደሰትም ። እግዚአብሔር በሚፈሩት፥ በምሕረቱም በሚታመኑት ይደሰታል ። “ - መዝሙር 147፡10-11
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 20:7–8 — “ እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን ። እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነሣን፥ ጸንተንም ቆምን ። “
- መዝሙር 146:5–6 — “ የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምስጉን ነው ፤ እርሱም ሰማይንና ምድርን ባሕርንም፥ በእነርሱ ያለውንም ሁሉ የፈጠረ፤ እውነትን ለዘላለም የሚጠብቅ “
- ያዕቆብ 4:13–14 — “ አሁንም፦ ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና ። ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።