A Cry From Help
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 143-145 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እነዚህ ሰዎስቱም መዝሙሮች የዳዊት መዝሙር ቢሆኑም በመዝሙር 143 ዉስጥ እንጓዛለን ፡፡ በህይወቱ የሆነ ስፍራ ላይ ዳዊት ስለ ሁኔታዎቹ ዘግቧል ፡፡ የፃፈዉ ይህ መዝሙር እንደ አንድ የፀፀት መዝሙር የታዬ ነው ምክንያቱም በእግዚአብሄር ፊት በፀፀት ተንበርክኮ ስለ ነበር ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (143፡ 1-6)፡ ዳዊት ፀሎቱን እንዲሰማ እግዚአብሄርን በመጠየቅ ጀመረ ፡፡ እንደ ዋረን ዋይርስቤ ገለፃ ስትፀልዩ “ ለእግዚአብሄር ሁኔታችሁን መናገር “ አለባችሁ ፡፡ ይህ የዳዊት ሰባተኛዉና የመጨረሻዉ “ የይቅርታ “ መዝሙር ነበር በእዉነቱ በመምጣት “ ይቅርታ “ አላለም እንጂ ፡፡ ዳዊት “ ጌታ ሆይ ፀሎቴን ስማ “ ብሎ ሲፀልይ እንኳን የእግዚአብሄርን ታማኝነት እና ፅድቅን በመጥራት ጀመረ (ቂጥር 1) ፡፡ እግዚአብሄር ታማኝና ፃድቅ ስለሆነ ዳዊት እግዚአብሄር ፀሎቱን እንደሚመልስለት በማሰብ ወደ እግዚአብሄር መጣ ፡፡ እግዚአብሄር ለልጆቹ የሚጠነቀቅ የፍቅር አባት ነው (ማቴ 7፡ 11) ፤ እኛ ደግሞ በይበልጥ ወደ እግዚአብሄር በልበሙሉነት መምጣት እንችላለን ምክንያቱም ቃሉን በማጥናት ዉስጥ እሱንና ባህሪዉን ስለምናውቅ ፡፡
ዳዊትም እግዚአብሄር እንዳይፈርድበት ጠየቀው ምክንያቱም “ ሕያው ሁሉ በፊትህ ጻድቅ አይደለምና “ (ቁጥር 2) ፤ ይህ ሀረግ ዳዊት ስቶ እንደ ነበረ የሚያመለክት ይመስላል ነገር ግን ሁሉም ሌሎቹም ነበሩ ፡፡ እንደ ዮሐንስ ማክአርቱር አገላለፅ “ ዳዊት ፃድቅ እንዳልነበር በማመን ስለ ፅድቅ የተፈወሰ መሆን እንዳለበት አስተዋለ ይህም በእርሱ ሳይሆን በእግዚአብሄር ፅድቅ ምክንያት ይሆናል “ ፤ ነገር ግን የኔልሰን ማብራሪያ ዳዊት አድርጎት ስለ ነበረዉ ነገር ይቅርታ ብሎ እንዳልነበር ያመለክታል ፡፡ የዳዊት ንግግርማንም ፍፁም አይደለም የሚለዉ በሌላ የመፅሀፍ ጥቅሶች የተደገፈ ነው ፤ ሮሜ (3፡ 23) “ ሁሉ ኃጢዓትን ሰርተዋልና የእግዚአብሄርም ክብር ጎድሎአቸዋል “ ይላል ፡፡ ኢሳ (64፡ 6) ሁላችንም በእግዚአብሄር ፊት እንደ እርኩስ ነን ይላል ፡፡
ዳዊት ጠላቶቹ እየተከታተሉ አድቅቀዉት/ሰብረዉት ስለ ነበር በጨለማ ኖርኩኝ አለ ፡፡ እንደ ኔልሰን ማብራሪያ አገላለፅ “ የብርሃንና የጨለማ መፅኀፍ ቅዱሳዊ አነጋገር በዘፍ (1፡ 2-3) ይጀምራል ፤ በጨለማ መኖር በጉድጓድ ዉስጥ ከመሆን ጋር የሚመሳሰል ነው (ቁጥር 3) “ ፡፡ የዳዊት መንፈስ ደካማ ስለ ነበርበጭንቀት የተሸነፈ ነበር (ቁጥር 4) ፤ ዳዊት ምንም የቀረ ነገር አልነበረኝም አለኝ - ተስፋም አልነበረዉም ፡፡
ይሁን እንጂ ዳዊት “ ያለፉትን ቀናቶች “ በማስታወስ እግዚአብሄር ያደረገለትን ሁሉ አሰላሰለ (ቁጥር 5) ፤ ዳዊት የጨለማ ዘመኑን እግዚአብሄር ያደረገለትን ነገር ሁሉ በማሰብ ተዋጋው ፡፡ ዳዊት ለእርሱ ሙሉ ለሙሉ መማረኩን በማመልከት እጆቹን ወደ እግዚአብሄር “ ዘረጋ “ (ቁጥር 6) ፡፡ በደረቅ ወቅት በምትጓዙ ጊዜ ከእግዚአብሄር ጋር ማዉራትን ታገኛላችሁ ፡፡ እንደ ማክአርቱር አገላለፅ “ አንድ ድርቅ ምድሪቱን ህይወት ሰጪ ዉኃ እንድትናፍቅ ስለመታት የዳዊት ናፍቆት ህይወት ሰጪ ነፃ አዉጪዉ ጋር ተሰደደ “ ፡፡ በተራራዉ ስብከት ላይ ኢየሱስ “ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው ይጠግባሉና “ አለ ፡፡ እግዚአብሄርን በደንብ መቅመስ ከጓጓችሁ እንደሚሞላችሁ ተስፋን ይሰጣችኋል ፡፡ የደረቀ ሰዉነታችሁ የተሞላ እንዲሆን ሁኔታችሁን ለእግዚአብሄር በመናገር መልስን መጠየቅ አለባችሁ ፡፡ ተመልሰን ቁጥር 5 ስንመለከት ዳዊት ስለ እግዚአብሄር የሚያውቀውን ተናገረ ፤ እኛም ደግሞ እግዚአብሄር ስላደረገው ነገር ሁሉ ተመልሰን መመልከት እንችላለን፡ “ ስለ ፍጥረቱ፣ ስለ አብርሃም መጠራት፣ ስለ ያዕቆብ ጉዞ እና ስለ ዮሴፍ ህይወት እና ከግብፅ ስለ መዉጣት እና ከነዓንን ስለ መያዝ “ ፡፡
ዳዊት እግዚአብሄር አድርጎት ስለ ነበረዉ ነገር አንፀባረቀም አሰላሰለም ፡፡ በሆነ ነገር ላይ እንዴት ታንፀባርቃላችሁ/ምላሽ ትሰጣላችሁ ? ትፅፉታላችሁ ትመለከቱታላችሁስ ? ዘግቡት ? ሳሉት ? ወደፊት የሚያመጣዉን ማንኛዉንም ነገር በማድረግ በነገሩ ላይ ማሰብ ትችላላችሁ ፡፡ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሄር የመስጠት አስተሳሰብ ለማሳደግ ምን ማድረግ ያስፈልጋችኋል ? 1ጴጥ (5፡ 7) “ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት “ ይላል ፡፡
መዝሙር (143፡ 7-12)፡ ስለ ሁኔታዎቻችን እግዚአብሄርን በማናገር እንዲመልስልን መጠየቅ ፤ ከዚያም እንደ ዋይርስቤ አገላለፅ “ ከዚያ በኋላ በተስፋ መልስ እንጠብቃለን “ ፡፡ ዳዊት መንፈሱ እየወደቀ ስለ ነበር እግዚአብሄር ቶሎ እንዲመልስለት ጠየቀው (ቁጥር 7) ፤ ችሎታ፣ ትጋት እና ፀንቶ ለመቀጠል ፅናት እንዳለን ካላወቅን አሁን እንዲመልስል እግዚአብሄር ያስፈልገናል ፡፡ ዳዊትም ትንሽ ጠንከር ባለ ንግግር እግዚአብሄር ፊቱን ከሰወረበት “ ወደ ጉድጓድ/ሞት የሚወርዱትን እመስላለሁ “ (ቁጥር 7) አለ ፤ ከእግዚአብሄር መልስ ዉጪ ዳዊት እየሞተ እንደ ነበር እንደሚሰማዉ ተናገረ ፡፡ ዋይርስቤ ዳዊት ዛሬ እኛ ከምንፈለገዉ ጋር ተመሳሳይ መልስ እንደፈለገ አሳይቷል ፡፡ የእግዚአብሄርን ፊት ማየት ፈለገ (ቁጥር 7) ፤ የእግዚአብሄርን ቃል መስማት ፈለገ (ቁጥር 8) ፤ የእግዚአብሄር ጥበቃ በረከትን ማግኘት ፈለገ (ቁጥር 9) ፡፡ በፀሎት ህይወቱ ዉስጥ ዳዊት ከእግዚአብሄር ምን እንደሚጠይቅ በጣም የተለዬ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄርን ፍቃድ ማወቅ ፈለገ (ቁጥር 10) ፤ ዳዊት እግዚአብሄርን ፊት ለፊት ማየት፣ ድምፁን መስማት፣ ጥበቃዉን/ከለላዉን መቀበል እና ፍቃዱን ለማወቅ ፈለገ ፡፡ በመጨረሻም ዳዊት ለእግዚአብሄር ታላቅ ስም ክብርን ማምጣት ፈለገ (ቁጥር 11-12) ፡፡ ዳዊት በአስቸጋሪ ስፍራ ሁኔታ ነበር በዚያ ዉስጥም ሆኑ እንዴት ከእግዚአብሄር ጋር እንደምናወራ ሞደል ሆነን ፤ በአንዳንድ መንገዶች ላይ እንደሳተ እያመነ ወደ እግዚአብሄር ጮኸ ፡፡
በአስቸጋሪ ሁኔታ ዉስጥ ምናልባትም በጭንቀት ዉስጥ በምንሆን ጊዜ ምናልባትም የሚዘወተር ልምምድ ከሆነ- መንፈሳዊ ድርቀት - የብቸኝነት ጊዜ ዉስጥ ከሆናችሁ፣ ምንድነዉ ማድረግ ያለባችሁ ?ቤትስይ ዘክሩዝ ከዘወትር ልምምድ እንዴት እንደ ገና በእግዚአብሄር ወደ እምነት እንደሚኬድ ጥናት አድርጋለች ፤ ተስፋ ከመቁረጥ ጉድጓድ ወደ እግዚአብሄርን መፍራት ፡፡ አስር ነገሮችን አቅርባለች፡
- በድብርት ስፍራ እንድትሆኑ ካደረጋችሁ ጥፋት መለየት/መሄድ (መዝ 42፡ 5) ፡፡
- ለሌሎች በመናገር ማድረስ (ያዕ 5፡ 16 ሰዎች ለእናንተ እንዲፀልዩላችሁ የመጠየቅን ሂደት ይገልፃል ) ፡፡
- ሙያዊ እርዳታ ማግኘት ፤ ወይም ምክርን እና ጥበብን ከሌሎች መፈለግ (ምሳ 11፡ 14) ፡፡
- ወደ እግዚአብሄር ለመቅረብ በመሳብ በእርሱ እዉነትን ማግኘት ( መዝ 34፡ 18) ፡፡
- እግዚአብሄር ቃል ላይ መጣበቅ (መዝሙር 23, ሮሜ 5፡ 1-8, 1ዮሐ 4፡ 9-10) ፡፡
- የግላችሁን የደስታ ፕሮጀክት መጀመር ፤ ደስታ የሚያመጡላችሁን ነገሮች ማድረግ ፡፡
- ሌሎችን መርዳት ፤ አይናችሁን ከራሳችሁ ላይ በማንሳት ሌሎችን እንድትወዱ የሚያደርጋችሁን ነገር ማድረግ ፡፡
- በአምልኮ ዉስጥ መቆየት/መያያዝ (መዝ 59፡ 16-17) ፤ የእግዚአብሄር ቃል በሙዚቃ ዉስጥ እንዲያገለግላችሁ መፍቀድ ፡፡
- ፈጠራ የሆነ ነገር ማድረግ ፤ እራሳችሁን በመግለጣችሁ ለመሳሳት ነፃነትን ይሰጣችኋል ፡፡
- አመለካከታችሁን/እይታችሁን መጠበቅ ፤ መዝ (30፡ 5) “ ልቅሶ ማታ ይመጣል ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል “ ፡፡
መደምደሚያ
በልምምድ/በዘወትር ልማድ ዉስጥ ከሆናችሁ እና በዚህ ሂደት ዉስጥ መጓዝ ከጀመራችሁ ደስታ በማለዳ ይመጣል ፤ ስለ ዳዊት የምወደዉ ነገር ያ ነው - ዳዊት የትም ስፍራ ቢሆንም አይኖቹ በእግዚአብሄር ላይ ነበር ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 1043.
John MacArthur, The John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 691.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 740.
Nelson’s Commentary, p. 740.
MacArthur, p. 691.
Wiersbe, p. 1043.
Wiersbe, p. 1043.
Wiersbe, p. 1043–44.
Betsy de Cruz, “10 Ways Christians Can Fight Depression”; available from https://www.crosswalk.com/slideshows/10-ways-christians-can-fight-depression.html.
ጥያቄዎች
-
መዝ (143፡ 5) “ የቀደመዉን ዘመን አሰብሁ ስራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ ፤ የእጅህንም ስራ ተመለከትሁ “ ይላል ፤ በእግዚአብሄር የእጅ ስራዎች ላይ እንዴት ታሰላስላላችሁ ? በእግዚአብሄር ፍጥረቶች እና በሰራዉ ሁሉ ላይስ ? አምላካችሁ እንዴት ትልቅ ነው ?
-
መዝሙረኛው በመዝ (143፡ 8) “ የምሄድበትን መንገድ አስታዉቀኝ “ በማለት እንደፀለየዉ በመፀለይ እግዚአብሄር የነገራችሁን ሳታዳምጡ ቀርታችሁ ታውቃላችሁ ? አዎ ከሆነ ለምን ዉጤቱስ ምን ነበር ?
-
መዝሙረኛው በመዝ (143፡ 10) እንዲያስተምረዉ እግዚአብሄርን እንደጠየቀዉ ለህይወታችሁ የእግዚአብሄርን ፍቃድ ታውቃላችሁ (ኤፌ 5፡ 15-20) ? አዎ ከሆነ እንድታደርጉት በሚመራችሁ ላይ እየተከተላችሁ ነው ? አይደለም ከሆነ እንድታደርጉ የሚፈልገዉ ምን እንደ ሆነ ለመጠየቅ ጥቂት ክስተቶችን/እንቅስቃሴዎችን ዉሰዱ
-
መዝሙር 144 ብዙ የተለያዩ ስሞችን በመጠቀም እግዚአብሄርን ይገልፀዋ፡ አለት፣ ምሽግ፣ እንደ ጥብቅ ስፍራ፣ እንደ ነፃ አዉጪና እንደ ጋሻ ፤ ለእግዚአብሄር ሌሎች ጥቂት ስሞች ምንድናቸዉ ? አንድ መዝሙር ከፃፋችሁ በህይወታችሁ እግዚአብሄር ባደረገላችሁ መሰረት ለእግዚአብሄር ምን ስም ተጠቀማችሁ ?
-
በመዝሙር (143-145) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 143:1, 4
“LORD, hear my prayer. In Your faithfulness listen to my plea, and in Your righteousness answer me . . . My spirit is weak within me; my heart is overcome with dismay.”
ጓዳኞች ብዙውን ጊዜ “ እንደምን አለህ ? “ በመባባል ሰላምታን ይለዋወጣሉ ፡፡ ብዙዎቹም ፈገግ በማለት “ ደህና ነኝ “ ብለው ይመልሳሉ ፡፡ ነገር ግን የሆነ ቀን ደህና ባትሆንስ ? እናም በዚያ ቀን የሆነ ሰው እንዴት እንደከረምክ ሲጠይቅህ “ ነፍሴ በውስጤ አለቀችብኝ፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ “ ብትል ፡፡ ዳዊት ይህንን ሀቅ ይህንን እውነት ለእግዚአብሔር ይነግረዋል እናም በተጨማሪ “ ፈጥነህ መልስልኝ “ ይለዋል ፡፡ የዳዊት መንፈስ ደክሞ ነበር ደግሞም በቃ ከዚያ በኋላ ዳግም ወደ ጉድጓድ ውስጥ መግባት አይፈልግም ነበር ፡፡
ከዚህ የተስፋ መቁረጥ ፣ የብቸኝነት እና የድብርት ስሜት ጋር ትቆራኛለህን ? የሚሰማህን ስሜት ለእግዚአብሔር ተናገር የትኛውንም አይነት ሀፍረትና የሀጢአተኝነት ስሜት ከአንተ አርቅ ፡፡ እናም ሂድና ጥበብን በመሻት ለሆነ ሰው ተናገር ፡፡ አስታውስ ብቻህን አይደለህም ፡፡ በዚህ የተስፋ መቁረጥ ስፍራ ውስጥ መቆየት የለብህም ፡፡ ሌሎችም ከአንተ ጋር ይወዳጃሉ ፡፡ ዛሬ እነዚህን ተስፋዎች ከእግዚአብሔር ተቀበል እናም እመን ፡- እግዚአብሔር ይወድሃል እናም ለአንተ ያስባል ፡፡ እርሱ አለትህ ፣ መሸሸጊያህ ፣ አዳኝህና ጋሻህ ነው ፡፡ እርሱ መኃሪ ፣ ሩህሩህ ፣ ለቁጣ የዘገየ እናም በታማኝ ፍቅሩ ታላቅ ነውና በእርሱ ተሸሸግ ፡፡ እናም ዛሬ መንፈስህ ደክሞ ልብህም በተስፋ መቁረጥ ተሞልቶ ከሆነ ፣ ዛሬ እርዳታን ፈልገህ የምትጸልየውን ጸሎት እግዚአብሔር ይሰማል ፡፡
“አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማ፤ በእውነትህ ልመናዬን አድምጥ፥ በጽድቅህም መልስልኝ ………ነፍሴ በውስጤ አለቀችብኝ፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ ። “ - መዝሙር 143፡1 ፣ 143፡4
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 143:7–8 — “አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፤ ነፍሴ አልቃለች፤ ፊትህን ከኔ አትመልስ፥ ወደ ጕድጓድም እንደሚወርዱ አልሁን ። አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አስታውቀኝ ። “
- መዝሙር144:2 — “ መሓሪዬና መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና መድኃኒቴ፤ ረዳቴና መታመኛዬም፤ ሕዝቤንም ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ ። “
- 1ኛ ጴጥሮስ 5:6–7 — “እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ፤ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።