Wisdom Books Psalms

Protection From Sin And Sinners

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 140-142 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 459 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዛሬ የምንሸፍናቸዉ ሰዎስት ምዕራፎች ቢኖሩንም በአንዱ ላይ ብቻ እናተኩራለን ፡፡ መዝሙር 140 አስደናቂ መዝሙር ነው ፡፡ ይህ ፀሀፊው “ እግዚአብሄር በክፉዎች ላይ በተለይም እርሱን በጎዱት/በስርዓት ባልተመለከቱት ላይ ቅጣትን ወይም ጥፋትን በማምጣት ፍትህን እንዲያደርግ በመጠየቁ “ የእርግማን/የቁጣ የመጨረሻ መዝሙር ነው፡፡ መዝሙር 142 በዋሻዉስጥ እንደ ነበር በዳዊት የተፃፈ ስለመሆኑ የተለዬ መግለጫ አለው ፡፡ ቻርለስሀደን ሱፐርገን “ ዋሻዎች ለፀሎት መልካም ሽፋንን ይሰራሉ ፤ ደብዛዛ ብርሃናቸው እና ጭርታቸው በሚገባ መሰጠትን/ትኩረትን ለመተግበር የሚረዱ ናቸው ፡፡ ዳዊት በዋሻዉ ዉስጥ እንዳደረገዉ በቤተ መንግስቱ ጸልዮ ነበር ባለፉትም ጊዜዎቹ መከራዎችን ወደ ሚያመጡበት ተግባራት በፍፁም አልወደቀም “ ብሎ ተናግሯል ፡፡ ነገር ግን ዛሬ ከኃጢዓተኞችና ከኃጢዓት ስለ መዳን በመዝሙር 141 ላይ እናተኩር ፡፡ ወደ ሀሳቡ በምንመጣ ጊዜ እንዴት እንደምንፀልይ ካላወቅን መዝሙር 141 ለመጀመር መዋቅሩን ይሰጠናል ፡፡

ትምህርት

ዮሐንስ ክርይሶስቶም 300 ከክርስቶስ ሞት በኋላ ዘግይቶም የኮንስታቲኖፖል(ዱሮ ጥልቅ የቱርክ ከተማ) ሊቀ ጳጳስ አማኞች ሁልጊዜ ምሽት ይህን መፀለይ አለባቸው ብሏል፡ “ አባቶቻችን ይህን መዝሙር…… ዝርዝሩን እንደ ሚያድን መድኃኒት እና ኃጢዓትን እንደሚያነፃ ስላዘዙት ምንም ይሁን በቀን ዉሏችን ዉስጥ የሚደርስብንን መከራ - በዉጪ፣ በቤትም እና ጊዜ በምናሳልፍበት ማንኛዉም ስፍራ - በዚህ መንፈሳዊ አይር በምሽት ዉስጥ እንሰረዘዋለን/እናጠፋዋለን ፤ እነዚህን ሁሉ እድፎች እንደሚያስወግድ እንደ አንድ መድኃኒት ታዩታላችሁ “ ብሏል ፡፡

መዝሙር (141፡ 1-2)፡ ይህን መዝሙር ለመግለፅ የምንጠቀምበት ርዕስ ከፓስተር ስቴቨን መጋቢ በመዝሙር 141 ላይ ከተጠቀመዉ ላይ የመጣ ነበር ፡፡ “ ጌታ ሆይ ፀሎቴን አድምጥ/ስማ “ በማለት እንጀምራለን ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን ጌታ ሆይ ስማኝ እኔን ለመርዳትም ፍጠን በማለት ተጠራ ፡፡ ስንፀልይ የምንጠቀመዉ ቃል ብቻ አይደለም በድምፃቸንን የሚገለፅም እንጂ ፡፡ በመፅኀፍ ብዙጊዜ እጣን ከፀሎት ጋር የተዛመደ/የተገናኘ ነው ፤ በራዕ (5፡ 8) ዮሐንስ እጣን የሞላባቸዉን ሳሕኖች ገልጧል - የእግዚአብሄር ሰዎች ፀሎት የሆነዉን ፡፡ በታቦቱ ድንኳን እና በቤተ መቅደሱ የሕዝቡ ፀሎት በቅዱሱ ስፍራ ዉስጥ እንደ እጣን ጭስ ወደ እግዚአብሄር አረገ ፤ በዘጸ (30፡ 34) እግዚአብሄር ሙሴን በእጣኑ አደራረግ/አሰራር ስለሚይዘዉ ነገር ነገረው ፡፡ እንደ www.templeinstitute.org አገላለፅ እጣኑ ቀጥ ባለ ምሰሶዎች ጭሱ ወደ ሰማይ እንዲወጣ ምክንያት የሚሆን የተለዬ እጽ እንዳካተተ ይናገራል ፤ የመሰዊያዉ እጣንም የክርስቶን ምልጃ እንደ መልክ ሊታይ ይችላል ፡፡ ከኪዳኑ ታቦት የስርየት መቀመጫ ፊት ሲቀመጥ መሰዊያው በእግዚአብሄር ፊት ጠበቃችንን ስሎታል (ዕብ 7፡ 25, 9፡ 24) ፡፡

ዳዊት በፀሎት እጆቹን አነሳ ፤ በእነዚህ መዝሙሮች ቢያንስ ሰባት ጊዜ መዝሙረኛዉ እጆቹን በፀሎት አንስቷል ፡፡ በ 2ዜና (6፡ 12-13) ሰለሞን ቤተ መቅደሱን በቀደሰ ጊዜ እጆቹን ወደ ሰማይ በመዘርጋት ፀለዬ ፤ በ 1ጢሞ (2፡ 8) ጳዉሎስ ወንዶችን “ የተቀደሱ እጆቻቸዉን በማንሳት “ እንዲፀልዩ አሳሰባቸው ፡፡ እንደ ሳም ስቶርም አገላለፅ እጆቻችንን በማንሳት መፀለይ ስለ ነፍሳችን/ ስለ ልባችን በእግዚአብሄር ፊት ብዙ ነገሮችን ሊያሳይ ይችላል፡ ለሚበልጥ ስልጣን በመማረክ እጆቻችንን ማንሳታችንን፣ ደካማነትን እንደ መግለጫነት፣ ለጥገኝነት/ለመደገፍ እንደ ምልክት፤ ስጦታን ለመቀበል እንደ ተስፋ፤ ትኩረትን ከራስ ወደ አዳኙ ዞር ማለቱን ወይም ደግሞ የእግዚአብሄር ወዳጅ መሆንን ያሳያል ፡፡

መዝሙር (141፡ 3)፡ ዳዊት “ ለአፌ ጠባቂ አኑር “ በማለት ፀለዬ ፤ የሚያስደንቅ ፀሎት ! ብዙጊዜ እንዴት እግዚአብሄር አፋችን እንዲዘጋ እንጠይቀዋለን ? ያዕ (3፡ 5-6) ምላስ ልክ እንደ እሳት እንደሆነ ያመለክታል ፡፡ ከአፋችን የሚወጣዉን እንዲጠብቅ እግዚአብሄርን እንጠይቅ ምክንያቱም የምንለዉ እርሱ ላይ ስለሚንፀባረቅ/እርሱን ሌላ መልክ ስለሚሰጥብን ፡፡

መዝሙር (141፡ 4)፡ ዳዊት “ ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰዉ “ በማለት ፀለዬ ፤ ልቤ ክፉ ወደ ሆነ ነገር እንዲሳብ እና ከህይወቴ ክፉ የሆነ ነገር እንዳይወጣ አታድርግ/አትፍቀድ ፡፡ በ 2ጢሞ (2፡ 22) ጳዉሎስ “ ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል “ አለ ፡፡

መዝሙር (141፡ 5)፡ ዳዊትክፉዎችን ካለመቀበል “ ገስፀኝ “ ከሚለዉ የፅድቅ ጸሎት ከሚመጣው መስተካከልን ወደ መያዝ ተሸጋገረ ፡፡ ሱፐርገን “ በዚህ መሰረት ስህተታችሁን የሚነግራችሁ ሰዉ ምርጥ ጓደኛችሁ ነው ፤ ይህ ለማድረግ ለእርሱ አስደሳች ነገር ላይሆን ይችላል እንዲሁም ጓደኝነታችሁን እንደምታጡ እያደረገ እንደሆነ ያውቃል ነገር ግን እዉነተኛና ታማኝ ጓደኛ ስለሆነ ስለማስተካከያዉ በማመስገን በሚነግራችሁ ነገር እንዴት እንደምትስተካከሉ ተማሩ “ ብሎ ተናግሯል ፤ ሱፐርገን “ የዘይት መደለያ መልካም እንዳልሆነ “ አክሏል ፡፡ እግዚአብሄር እንዲቀጣችሁና እንዲያጠነክራችሁ መፍቀድ አስፈላጊ ነው ፡፡ ኤፌ (4፡ 15) “ እዉነትን በፍቅር የመናገር “ ጥቅምን አፅዕኖት ይሰጣል ፡፡ ዕብ (12፡ 7-11) እግዚአብሄር እንደ ልጆቹ ስለሚቀጣን በቅዱስነቱ ተካፋዮች መሆን እንደምንችል ይናገራል ፤ ይህ ቅጣት ያም ይሆናል ነገር ግን ሰላምንና ፅድቅን ያደርጋል ፡፡

መዝሙር (141፡ 5-7)፡ ዳዊት በመቀጠልም እግዚአብሄርን “ ክፉን እንዲግልጥ “ ጠየቀው ፡፡ ዋናዉ ነገር - ክፋታቸዉ ምን እንደሆነ የታዬ እንዲሆን መፍቀድ ነው ፡፡ ይህ ከአንድ ገደል በኩል ላይ የተወረወረ የመሆን እይታ አሳዛኝ እና ኃይለኛ ነው ምክንያቱም በእስራኤል አንዳንድ አስደናቂ ገደሎች ስላሉ ፡፡ ዳዊት በክፉዎች ላይ ብዙ ፍርዶች እንዲመጡ ፀለዬ ፤ ሰዎች ክፉ ሲመራቸዉ በሚያዩ ጊዜ ወደ እዉነትና የፅድቅ ቃል ይመለሳሉ ፡፡ በማቴ (7፡ 4-5) ኢየሱስ ተከታዮቹን “ አስቀድመዉ ከአይናቸዉ ምሰሶዉን እንዲያወጡ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ/ታያላችሁ “ በማለት ነገራቸው ፡፡ አስታዉሉ ዳዊት መጀመሪያ ስለ ቅጣትና እርማት /ማስተካከያ ከዚያ በመቀጠል ክፉን እንዲገልጥ ፀለዬ ፡፡ የዳዊት ፀሎት ኢየሱስ ወደ ሚያስተምራቸዉ ሁሉም ነገሮች ይመራል ፡፡

መዝሙር (141፡ 8-10)፡ የዳዊት ፀሎት “ አይኖቼ ወደ አንተ ይመለከታሉ “ በማለት አበቃ ፡፡ ዳዊት ስለ ትኩረት ጠየቀ - ለጥበቃና ለመፅናናት ወደ እግዚአብሄር ስለ መመልከት ፤ በመዝሙሩ ዉስጥ ትኩረት ሌለኛዉ የተለመደ ጭብጥ ነው ፡፡ የመዝሙረኛዉ ፀሎት አይኖቹን በእግዚአብሄር ላይ ለማድረግ እና እግዚአብሄርን ለመፈለግ ነው (መዝ 16፡ 8, 25፡ 15, 119፡ 37) ፡፡ ዳዊት በእግዚአብሄር ላይ ሙሉ ለሙሉ ተደግፎ የቀጠለ ለመሆን ስለ ትኩረቱ ስለ ፀለዬ በለዉጥ ላይ መቆም ይችላል ፡፡ ከእግዚአብሄር በተለዬን/ከኃሳቡ በሸሸን ጊዜ ችግር ዉስጥ እንገባለን ፡፡ ዳዊት እርሱ “ ብቻዉን በደህና እስኪያልፍ “ ድረስ ጠላቶቹ “ በራሳቸዉ መረብ ዉስጥ እንዲወድቁ “ ፀለዬ (ቁጥር 10) ፡፡ የዳዊት እምነት በእግዚአብሄር ላይ እርሱን ሊያጠፉት በተመለከቱት ላይ ራሳቸዉ እንዲጠፉ በተደጋጋሚ የተረጋገጠ ነበር ፡፡ የእነዚህን ቁጥሮች ተመሳሳይነት ከዕብ (12፡ 1-3) ጋር አስታዉሉት ፤ አይኖቻችንን በእግዚአብሄር ላይ ማድረግ አለብን ፡፡

መደምደሚያ

መዝሙር 141 ለፀሎት የሚያስደንቁ ዝርዝሮችን/ጭብጦችን/ፍሬ ነገሮችን ይሰጠናል፡ “ ጌታ ሆይ በራሴ ስቆም ፀሎቴን ስማ ፤ ስለ ምታስፈልገኝ ከጭንቀቴ ዉስጥ ወደ አንተ ስጮህ ፀሎቴን ስማ ፤ ወደ አንተ ስፀልይ አፌን/ንግግሬን ጠብቅ ፤ ስለ አንተ ስመሰክር አፌን/ንግግሬን ጠብቅ ፤ ስናገር አፌን/ንግግሬን ጠብቅ በአንተ ላይ ስለሚናገር ፤ ልቤንም ጠብቅ - ወደሌላ በኩል እንዳይገፋው ወይም ለሌላ ነገር እንዳይሰጥ ፤ ምናልባት ይህ ሁልጊዜ ለእናንተ ብቻ ይሆናል ፡፡ ጌታ ሆይ ቅጣኝ አንፃኝም ፤ በፍቅር ለነፍሴ እዉነትን ተናገራት ለአንተም እጠነክራለሁ ፤ ስለዚህ ጌታ ሆይ በዚሪያዬ ያለዉን ክፉ ግለጥ ፤ ምክንያቱም በአንተ ላይ ስላተኮርኩኝ ምን እንደሆነ ማሳዬትና መግለጥ እችላለሁ ፡፡ አይኖቼን በአንተ ላይ ስታደርግ በዚህ አስደናቂ የህይወት ጉዞ ዉስጥ መጓዝ እችላለሁ “ ፡፡

  1. Robert L. Deffinbaugh, “Psalm 109: A Prayer for the Punishment of the Wicked”; available from https://bible.org/seriespage/psalm-109-prayer-punishment-wicked.

  2. Charles Haddon Spurgeon, A Treasury of David, vol. iii (McLean, VA: MacDonald Publishing, n.d.), p. 323.

  3. Robert C. Hill, St. John Chrysostom: Commentary on the Psalms, vol. 2 (Brookline, MA: Holy Cross Orthodox Press, 1998), p. 276.

  4. Steve Shepherd, “Lord, Come Quickly”; available from https://www.sermoncentral.com/sermons/lord-come-quickly-steve-shepherd-sermon-on-christian-life-181481.

  5. Sam Storms, “10 Things You Should Know About the Lifting of Hands in Worship;” available from https://www.samstorms.com/enjoying-god-blog/post/10-things-you-should-know- about-the-lifting-of-hands-in-worship.

  6. Spurgeon, p. 309.

ጥያቄዎች

  1. መዝ (140፡ 3) ከአፋችን ስለሚወጣዉ ቃል ኃይል ምን ይላል ? በንግግር በአንድ ሰዉ/በሆነ ሰዉ ተጠቅታችሁ ታዉቃላችሁ ? በንግግራችሁ የተመረዙ ክፉዎች ገጥመዋችሁ ያውቃሉ ? መፅሀፍ ቅዱስ ስለዚህ ምን ይላል ? (ምሳ 10፡ 20, 31, 18፡ 21)
  2. በመዝ (141፡ 2) መሰረት መዝሙረኛዉ ወደ እግዚአብሄር መገኘት እንዴት እንደገባ ምን ታስባላችሁ ? ለፀሎትና ለአምልኮ ጊዜ አችሁ እንዴት ትዘጋጃላችሁ ? እግዚአብሄር እንዴት እንዲቀበላችሁ ትፈልጋችሁ ?
  3. እንደ አንድ ክርስቲያን መዝሙረኛው በመዝ (141፡ 9) እንደ ገለፀው ክፉዎች ሊያጠምዷችሁ እንደተቀመጡ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? ያን እንዴት ታሸንፋላችሁ ?
  4. መዝሙር 142 ዳዊት ከሳዖል በዋሻ ዉስጥ ተሸሽጎ በነበር ጊዜ የዘመረዉ መዝሙር ነበር ፤ በህይወታችሁ ጥቂት “ የዋሻ “ ክስተቶችን አስቡ ፤ ዳዊት በዚህ መዝሙር እንደጮኸዉ ወደ እግዚአብሄር ጮኻችኋል ወይስ በጭንቀትና በፍራት ተሸንፋችሁ ነበር ? ዉጤቱ ምን ነበር ?
  5. በመዝሙር (140-142) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 141:1–3

“LORD, I call on You; hurry to help me. Listen to my voice when I call on You. May my prayer be set before You as incense, the raising of my hands as the evening offering. Lord, set up a guard for my mouth; keep watch at the door of my lips.”

ከቀን ወደ ቀን ዳዊት በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ተመለሰ ፡፡ የእርሱ የጸሎት ህይወት ለአንተ ምሳሌ ነው ፡፡ ምን እንደምትል ሳታውቅ እርሱን ለመፈለግ ወደ እግዚአብሔር የተመለስክባቸው ጊዜያት አሉን ? ዛሬ በጸሎት እግዚአብሔርን ስትፈልግ መዝሙር 141 እንደ መመሪያ ተጠቀመው ፡፡ የዳዊት እውነተኛ ቃላት በልብህ ውስጥ ያስተጋባሉ ፡፡

መጸለይ ስትጀምር እግዚአብሔርን ተጣራ እናም ይሰማህ ዘንድ ለምነው ፡፡ ራስህን አሳልፈህ እንደሰጠህ በሚያሳይ መልኩ ደግሞም ደካም እንደሆንክ እናም ለእግዚአብሔር ታማኝ በመሆን ለአምልኮ በእግዚአብሔር ፊት እጆችህን አንሳ ፡፡ ቀጥሎ እግዚአብሔር አፍህን ይጠብቅ ዘንድ ጸልይ ከንፈሮችህንም ጠብቅ ፡፡ በመከራ ውስጥ ሳለህ ምን ያህል ጊዜ የስጋህ የመጀመሪያ እርምጃ የጥላቻ ፣ የቅናት ወይም የቁጣ ቃልን እንድትናገር አድርጎሃል ? እግዚአብሔር የምላስህን የንግግርህን ኃይል ያውቃል ፡፡ ስለዚህ በአፍህ ላይ ጠባቂን እንድያደርግ ጸልይ ፡፡ እግዚአብሔርን ወዳለህበት ሁኔታ ስትጋብዘው ፣ እርሱ ይመልስልሃል ፡፡ እርሱ ይጠብቅሃል ፣ ያንጽሃል እንድሁም ክፉውን ያስወግድልሃል ፡፡ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ተመለስ ፡፡ እርሱ ታማኝ ነው ፤ ተስፋዎቹም በየቀኑ እውነት ናቸው ፡፡

“ አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፤ ስማኝ፤ ወደ አንተ ስጮኽም የልመናዬን ቃል አድምጥ ። ጸሎቴን በፊትህ እንደ ዕጣን ተቀበልልኝ፥ እጅ መንሣቴም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትሁን ። አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ ። “ - መዝሙር 141፡1-3

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ዕዝራ 9:5 — “ በሠርክም መሥዋዕት ጊዜ ልብሴና መጐናጸፊያዬ እንደ ተቀደደ ሆኖ ከመዋረዴ ተነሣሁ፤ በጕልበቴም ተንበርክኬ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር እጄን ዘረጋሁ ። “
  • ኤፌሶን 4:29 — “ ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ ። “
  • ያዕቆብ 3:5–6 — “ እንዲሁም አንደበት ደግሞ ትንሽ ብልት ሆኖ በታላላቅ ነገር ይመካል። እነሆ፥ ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል ። አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል። “