Wisdom Books Psalms

Maturing In Discipline

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 137-139 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 458 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የከፍታ መዝሙር ጥናታችን አብቅቷል ፡፡ መዝሙር 137 ስለ ባቢሎን ምርኮኝነት ነው ፤ በምርኮ ሕዝቡ ቀድሞ በእስራኤል የነበረዉን መልካም ቀን አስታወሱ ፡፡ የመዝሙር 137 ፀሀፊ የማይታወቅ ነው ፤ የመዝሙሩ ርዕስ በቀላሉ “ የስደተኞቹ ኃዘን “ ፤ ዋይርስቤ በመዝሙር 137 ዘጠኝ ቁጥሮች ላይ “ አስታዉስ “ እና “ እርሳ “ የሚሉት ቃላት አምስት ጊዜ ጥቅም ላይ እንደዋሉ አመልክቷል ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (137፡ 1-4)፡ ማክአርቱር የመጀመሪያዎቹን አራት ጥቅሶች እንደ ኃዘን አስቀምጧቸዋል ፡፡ ምርኮኞቹ በባቢሎን በወንዞች አጠገብ ተቀመጡ - በጢግሮስና በኤፍራጠስ አጠገብ - እንዲሁም ከፂዎን ላይ ትዝታቸዉን አጠፉ ፡፡ የእግዚአብሄርን መገኘት የሚወክለዉ ቤተ መቅደሱ በፂዎን ስለ ነበር ምናልባት ስደተኞቹ ከእግዚአብሄር ጋር ለመገናኘት እንደማይችሉ የመጥፋት ስሜት እየተሰማቸዉ ነበር ፤ ግዞቱ ካበቃና ቤተ መቅደሱ መልሶ ከተሰራ በኋላም እንኳን ሕዝቡ አሁንም ይህ ስሜት ነበራቸው፡ “ ዋላ ወደ ዉኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ አቤቱ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች ፡፡ ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች ፤ መቼ እደርሳለሁ ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ ? ዘወትር ፡፡ አምላክህ ወዴት ነው ? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ “ (መዝ 42፡ 1-3) ፡፡ ስደተኞቹ በወንዙ አጠገብ ተቀመጡ ምክንያቱም መቀመጥ የኃዘን ግልፅ ቁመና ስለ ነበር ፡፡

በወንዞቹ አጠገብ ሲቀመጡ እስራኤላዊያን መሳሪያቸዉን አርቀዉ አስቀመጡ ምክንያቱም ባቢሎናዊያን “ የፂዎንን መዝሙር “ (ቁጥር 3) እንዲዘምሩላቸዉ አፎዙባቸው ፡፡ ሙዚቃ የእስራኤል አምልኮ የደስታ መግለጫ ማለት ነው፡ “ በረድኤታችን በእግዚአብሄር ደስ ይበላችሁ ለያዕቆብ አምላክ እልል በሉ ፡፡ ዝማሬዉን አንሱ ከበሮንም ስጡ ደስ የሚያሰኘዉን በገና ከመሰንቆ ጋር ፤ በመባቻ ቀን በከፍተኛው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ “ (መዝ 81፡ 1-3) ፡፡ በሰዓቱ በምርኮ እስራኤላዊያን ለደስታ ምንም ምክንያት አልታያቸውም በተለይም ማራኪዎቻቸዉ የአምላካቸዉን መዝሙር በአሽሙር/በሽሙጥ ሲጠይቋቸዉ ፡፡ ለእስራኤላዊያን እግዚአብሄርን ለማመስገን አቀማመጣቸዉ ሙሉ ለሙሉ ከስፍራ ዉጪ እንደሆነ ይመስላል ፤ አመለካከታቸዉ በቁጥር አራት “ የእግዚአብሄርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን ? “ በማለት አጠቃለዉት ነበር ፡፡

መዝሙር (137፡ 5-6)፡ ማክአርቱር ከለቅሶ ወደ ሁኔታ ሽግግሩን ተመልክቷል ፡፡ እስራኤላዊያን ኢየሩሳሌምን ሳሏት ምክንያቱም ካሉበት ስፍራ የተሸለች ስፍራ ስለነበረች ፡፡ በጭንቀታቸዉ መካከል ላይ እስራኤላዊያን ከየት መጥተዉ እንደ ነበርና ደስታቸዉ የት እንደ ነበር በማሰብ አስታወሱ ፤ ለማስታወስ ፍላጎታቸው “ ቀኛቸዉ ረስቷቸዉ “ (ቁጥር 5) እንደ ነበር እና ኢየሩሳሌም በፍፁም ከረሷት ምላሳቸዉ ከላይኛዉ አፋቸዉ ጋር እንደሚጣበቅ (ቁጥር 6) እግዚአብሄርን መጠየቅ ነበር ፡፡ ኢየሩሳሌምን መርሳት እግዚአብሄርን ከመርሳት ጋር ተመጣጣኝ ስለሆነ እስራኤላዊያንአይናቸዉን በኢየሩሳሌም ላይ ለማድረግ ሰሩ ፡፡

እስራኤላዊያን መከራ እየደረሰባቸዉ እንደ ነበር እንኳን በመከራ ዉስጥ እንዴት እንደሚሰሩ እየተማሩ ነበር ፡፡ በግዞት ዉስጥ ስለነበሩ በጥሩ ሁኔታ ዉስጥ አልነበሩም ፤ ይሁን እንጂ በችግራቸዉ መካከል ላይ አይናቸዉን በእግዚአብሄር ላይ ማድረግ እየተማሩ ነበር ፤ በዚህ መንገድ አይናቸዉን በእግዚአብሄር ላይ ማድረግ ለእስራኤላዊያን የማይመች እንደሆነ ይሰማል ነገር ግን መዝ (9፡ 11) ለመኖር እየሞከሩ ነበር “ በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሄር ዘምሩ በአሕዛብም መካከል አደራረጉን ንገሩ “ ፡፡ እስራኤላዊያን በእግዚአብሄርየተጣሩ/የነፁ ነበሩ ፡፡ በችግራቸዉ መካከል ላይ እና ነገሮች እንደሚገምቷቸዉ በማይሰሩበት ጊዜ በእግዚአብሄር ባላቸዉ እምነት እንዴት እንደሚፀኑ እየተማሩ ነበር ፡፡

መዝሙር (137፡ 7-9)፡ ይህ መዝሙር በኃዘን በመጀመር ቀጥሎ ወደ ሁኔታ ከተጓዘ ከቁጥር ሰባት እስከ ዘጠኝ እርግማኖችን ይይዛሉ ፡፡ እርግማን ለጠላቶች ጥላቻን ይገልፃል ፡፡ መዝሙረኛው ወደ ስደት እንዲሄዱ ምክንያት የሆኗቸዉን የእስራኤል ጠላቶች ለመቅጣት እግዚአብሄር እንዲራመድ ፍላጎቱን ገለፀ ፤ ትርጓሜዉም እስራኤላዊያን በራሳቸዉ ለማድረግ ኃይል ስለሌላቸዉ እግዚአብሄር የእስራኤልን ጠላቶች ለመዋጋት የእርግማን ንግግሮቹ ፍላጎቱ እንዲሆን ነው ፡፡

በኢየሩሳሌም መጥፋት ላይ ኤዶማዊያን ከባቢሎናዊያን ጋር ህብረት ነበራቸው፡ “ በጾም ምድር የምትኖሪ የኤዶሚያስ ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ሐሴትም አድርጊ ፤ ጽዋዉ ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋል አንቺም ትሰክሪአለሽ ትራቆቻለሽም ፡፡ የጽዮን ልጅ ሆይ የበደልሽ ቅጣት ተፈፀመ ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አያስማርክሽም ፡፡ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ በደልሽን ይቀጣል ፤ ኃጢዓትሽን ይገልጣል “ (ሰቆ.ኤር 4፡ 21-22) ፡፡ ኤዶምያስ በኢየሩሳሌም መፈራረስ ስለተደሰተች እስራኤል እግዚአብሄርን በኃጢዓታቸዉ ምክንያት በተመሳሳይ ቁጣ እንዲከፍላቸዉ ጠየቀች ፡፡ እስራኤላዊያን በኃጢዓታቸዉ ምክንያት የእግዚአብሄርን ቅጣት ቀምሰዋል ፡፡ ኮንስታብል “ ስለኃጢዓታቸዉ የእግዚአብሄርን ቅጣት የቀመሱ አማኞች ታላቅ ኃዘን ይሰማቸዋል ፤ አንዳንድ ጊዜ ቅጣት ከህብረት አምልኮ በረከትና ከሚመጣዉ ደስታ ያስወጣናል ፤ ሁልጊዜ ለተስፋዉ የታመን ለመሆን እግዚአብሄርን መጠየቅ ተከጊ እንደሆነ “ ፅፏል፡፡

መደምደሚያ

“ ከኃጢዓት ጋር እየተጋደላችሁ ገና ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም ፤ እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር ፡- ልጄ ሆይ የጌታን ቅጣት አታቅልል በሚገስጽህም ጊዜ አትድከም ፤ ጌታ የሚወደዉን ይቀጣዋልና የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረዉን ምክር ረስታችኋል ፡፡ ለመቀጣት ታገሱ ፤ እግዚአብሄር እንደ ልጆቹ ያደርጋችኋልና ፤ አባቱ የማይቀጣዉ ልጅ ማነው ? ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም ፡፡ ከዚህም በላይ የቀጡን የስጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸዉም ነበር ፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን ? እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና እነርሱ ግን ከቅድስናዉ እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል ፡፡ ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል “ (ዕብ 12፡ 4-11) ፡፡

ቺፕ ኢንግራም ከዚህ ፅሁፍ በዕብራዊ አምስት የመፅኀፍ ቅዱሳዊ ቅጣቶች ባህሪያትን ዘርዝሯል፡

  1. የቅጣት አስፈላጊነት ጥፋትን ለማራቅ ነው (ዕብ 12፡ 4) ፡፡
  2. የቅጣት አይነቶቹ ድርጊት ወይም ቃል ነው (ዕብ 12፡ 5) ፡፡
  3. የቅጣት መነሳሳት/ፍላጎት ፍቅርን ለመግለፅ ነው (ዕብ 12፡ 6-8) ፡፡
  4. የቅጣት ግቡ መታዘዝን ለማስተማር/ማስተማር ነው (ዕብ 12፡ 9) ፡፡
  5. የቅጣት ዉጤት የአጭር ጊዜ ህመም እና የረጅም ጊዜ ጥቅም ነው (ዕብ 12፡ 10-11) ፡፡

መዝሙር 137 ላይ ስትመለከቱ እግዚአብሄር ያደረገዉን ለምን እንዳደረገዉ በዕብራዊ 12 ላይ በመመልከት ትረዳላችሁ ፤ እንደተማርን እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል ፡፡ የማጥሪያ ሂደት ነው በማጣራቱ ዉስጥ በብዙ ኢየሱስን መምሰል ትጀምራላችሁ ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 363.

  2. John MacArthur, The John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 689.

  3. Wiersbe, p. 363.

  4. Wiersbe, p. 363.

  5. MacArthur, p. 689.

  6. MacArthur, p. 689.

  7. MacArthur, p. 689.

  8. Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes: Psalms, p. 465; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

  9. Chip Ingram, “Five Characteristics of Biblical Discipline”; available at https://www.focusonthefamily.com/parenting/effective-biblical-discipline/effective-child-discipline/five-characteris- tics-of-biblical-discipline.

ጥያቄዎች

  1. በመዝሙር 137 ሕዝቡ እያለቀሱ የነበሩት ለምን ነበር ? በግዞት ወይም በሆነ ነገር/ሰዉ በባርነት እንደ ነበራቸዉ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? አዎ ከሆነ አብራሩት
  2. መዝ (138፡ 6) አንብቡ ፤ “ ወደ ችግረኞች ይመለከታል “ የሚለዉን ንግግር ግለፁ ፤ “ ትዕቢተኞችን ከሩቅ ያውቃል “ ማለትስ ምን ማለት እንደሆነ ግለፁ ?
  3. በመዝሙር 139 ዳዊት እግዚአብሄር ስለ እኛ ሁሉንም ነገር እንደሚያዉቅ እና ከእርሱ መሸሽና መደበቅ እንደማንችል አካፍሏል/ተናግሯል ፤ ዳዊት ስለ እነዚህ እዉነቶች እንዴት የተሰማዉ መሰለ ? እናንተስ ? ስለ እግዚአብሄር እነዚህን ነገሮች ማወቅ እንዴት እንዲሰማችሁ ያደርጋችኋል ?
  4. በመዝ (139፡ 16) መሰረት ዳዊት ከመወለዱ በፊት እንኳን ሁሉም የተፈጠሩት ቀኖች በእግዚአብሄር በመፅሀፉ ላይ የተፃፉ ነበሩ ፤ ለእኛም ለእያንዳንዳችን ይህ እዉነት ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታስቡም ?
  5. በመዝ (139፡ 23) ዳዊት እግዚአብሄርን ልቡን እንዲመረምር ጠየቀው ፤ በቀደመዉ ምዕራፍ ዳዊት እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር እንዴት እንደሚያዉቅ ከገለፀ በኋላ ዳዊት ጥያቄዉን በዚህ መንገድ ለምን ጠየቀ/ፃፈ ?
  6. በመዝሙር (137-139) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 139:13–14

“For it was You who created my inward parts; You knit me together in my mother’s womb. I will praise You because I have been remarkably and wonderfully made. Your works are wonderful, and I know this very well.”

የሰማይና የምድር አምላክ በእናትህ መህጸን ውስጥ ፈጠረህ ፡፡ አርሱ አንድ አድርጎ አያይዞሃል ፡፡ ውብና ድንቅ ሆነ የተፈጠረ ብሎ ጠርቶሃል ፡፡ እርሱ የአይንህን እይታ ፣ ቁመትህን ፣ የራስ ጸጉርህን ቁጥር እንድሁም አሳብህን ጭምር ያውቃል ፡፡ ከእርሱ ምንም የተደበቀ ነገር የለም ፡፡ ቀናቶችህ በሙሉ ከእነርሱ አንዳቸው እንኳ ለአንተ ሳይጀምሩ በእርሱ መጽሀፍ ተጽፈው ነበር ፡፡ አይገርምም ? ከፍጥረትህ ከመታሰብህ ጀምሮ ፣ እርሱ አንተን በማሳደግ እናም ወደ እርሱ ምስል እርሱ ወደ ሚፈልገው ማንነት አንተን በማሰልጠን ላይ ነው ፡፡

ሁሉን አዋቂው እግዚአብሔር ብቻ አይደለም ነገር ግን እንድትበረታ እንድሁም ወደ መብሰል እንድትሄድ መገኘቱም ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነው ፡፡ እርሱ ከአንተ ጋር የማይሆንበት እናም አንተ በራስህ የምትሄድበት ምንም መደበቂያ ቦታ የለም ፣ ማምለጥ የምትችልበት ምንም አይነት ርቀት የለም ፣ የማይደረስበት ከፍታ የለም ፣ በጣም ጥልቅ የሚሆንም ነገር የለም ፡፡ እጁም ትመራህና ትይዝህ ዘንድ ዘወትር በዚያ ነች ፡፡ በዛሬዋ ቀን ውስጥ ስትመላለስ ከእግዚአብሔር የሆኑትን እነዚህን እውነቶች እመን ፡- ታውቀሃል ፡፡ እግዚአብሔር ለአንተ አሳብና እቅድ አለው ፡፡ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ወብና ፍጹም ሆነህ ተፈጥረሃል ፡፡ እግዚአብሔር ቀርጾሃል ሰርቶሃል እናም ለአንተ የተለየ እቅድ አለው ! በእነዚህ ለህይወትህ በጎ ተፅእኖ ባላቸው ተስፋዎች ላይ ተጣበቅ ፡፡

“አቤቱ፥ አንተ ኵላሊቴን ፈጥረሃልና፥ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛል ። ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች ። “

  • መዝሙር 139፡13-14

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 139:1–5 — “አቤቱ፥ መረመርኸኝ፥ አወቅኸኝም ። አንተ መቀመጤንና መነሣቴን አወቅህ፤ አሳቤን ሁሉ ከሩቅ አስተዋልህ ። ፍለጋዬንና ዕረፍቴን አንተ መረመርህ፤ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ ፥ የዓመፃ ቃል በአንደበቴ እንደሌለ ። አቤቱ፥ አንተ እነሆ የቀድሞውንና የኋላውን አወቅህ፤ አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ ። “

ኤፌሶን 2:10 — “ እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን ። “

1ኛ የጴጥሮስ 2:9 — “ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ ፡፡ “