His Love Is Eternal
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 134-136 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የዛሬዉ ምዕራፍ ሁለት ግልፅ የሆኑ ፍሬ ነገሮች አሉት፡ ስም እና ፍቅር ፡፡ መዝሙር 134 ከሚጠበቅባቸዉ ከሰዎስቱ በአንዱ በዓል ላይ (ዘዳ 16፡ 16) ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ በመንፈሳዊ ተጓዦቹ ከተዘመሩት 15 የከፍታ መዝሙሮች ዉስጥ የመጨረሻዉ ነው ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (134፡ 1-3)፡ መዝሙረኛዉ “ በምሽት በእግዚአብሄር ቤት የሚቆሙትን ! “ ሰዎች ጠቀሰ ፤ የዚህ ምሳሌ አንዱ ሐና ነበረች፡ “ ከአሴር ወገንም የምትሆን የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይ ነበረች ፤ እርስዋም ከድንግልናዋ ጀምራ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ኖረች ፤ እርስዋም 84 አመት ያህል መበለት ሆና በጣም አርጅታ ነበር ፤ በጾምና በጸሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም ነበር “ (ሉቃ 2፡ 36-37) ፡፡ ሄነሪ ማቴዎስ “ ከእነርሱ ዉስጥ አንዳንዶቹ በእግዚአብሄር ቤት በማታ ቅዱስ እቃዎችን የማይንቁ የቤተ መቅደሱን ቅዱስ ነገሮች እና ሊሰርቋቸዉ የማይችሏቸዉን ዉድ ነገሮችን በመጠበቅ እንዳገለገሉ ፤ ታቦቱ በመጋረጃዉ ዉስጥ ስለ ነበር የበለጠ ጥበቃ ያስፈልገዉ እንደ ነበር ፤ በመሰዊያዉ ላይ ያለዉ እሳት እና በመቅረዙ ላይ ያለዉ መብራት አለመጥፋቱን ለማየት በተመሳሳይ በዚያ እንደሚገኙ “ ፅፏል ፡፡
ፀሎትን የሚገልፁ ሌሎች ጥቅሶች፡
1ጢሞ (2፡ 8)፡ “ እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቁጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሱ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ “ ፡፡
1ጴጥ (2፡ 9)፡ “ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትዉልድ የንጉስ ካህናት ቅዱስ ሕዝብ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ “ ፡፡
ዘኁ (6፡ 24-26)፡ “ እግዚአብሄር ይባርክህ ይጠብቅህም ፤ እግዚአብሄር ፊቱን ያብራልህ ይራራልህም ፤ እግዚአብሄር ፊቱን ወደ አንተ ያንሳ ሰላምንም ይስጥህ “ ፡፡
መዝሙር (135፡ 1-4)፡ በእያንዳንዳቸዉ በመዝሙር 134 እና በመዝሙር 135 የመጀመሪያዉ ቁጥር በተመሳሳይ ለምስጋና “ ሃሌ ሉያ ! የእግዚአብሄርን ስም አመስግኑ ፤ እናንተ የእግዚአብሄር ባሪያዎች ሆይ አመስግኑት “ (ቁጥር 1) ብሎ በመጣራት ይጀምራል ፡፡
መዝ (100፡ 4) “ ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ ፤ አመስግኑት ስሙንም ባርኩ “ ይላል ፡፡ በእግዚአብሄር ፊት በምስጋናና በታላቅ አመስጋኝ ልብ ስንመጣ ጠላታችን ኃይሉ ይወሰዳል ፡፡
መዝሙረኛው ያህዌ/እግዚአብሄር “ ያዕቆብን ለራሱ “ እንደመረጠው ተናገረ ፤ ክርስቲያን ይህን ንግግር ግላዊ ሲያደርጉት/ወደ ራስ ሲያመጡት ይህ እግዚአብሄር እስራኤልን በመምረጡ እንዴት ዋስትና እንደሚኖረን ያደርጋል ፡፡ በዚህ ዋስትና የኖረን ጠቅላላ ምክንያቱ እግዚአብሄር እስራኤልን “ ለመዝገቡ ስለመረጠው /ኃብቱ ስላደረጋት “ (ቁጥር 4) ፡፡
መዝሙር (135፡ 5-7)፡ ቁጥር 5 ከመዝ (136፡ 2-3) ይመሳሰላል፡ “ የአማልክትን አምላክ አመስግኑ ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነዉና ፡፡ የጌቶችን ጌታ አመስግኑ ፤ ምህረቱ ለዘላለም ነዉና “ ፡፡
ቁጥር 6 ከመዝ (136፡ 4-6) ይመሳሰላል፡ “ እርሱ ብቻዉን ታላቅ ተኣምራትን ያደርግ ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነዉና ፤ ሰማያትን በብልሃት የሰራ ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነዉና ፤ ሰማያትን በብልሃት የሰራ ምሕረቱ ለዘላለም ነዉና ፤ ምድርን በዉኃ ላይ ያጸና ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነዉና “ ፡፡
ቁጥር 7 ከመዝ (136፡ 7-9) ይመሳሰላል፡ “ ብቻዉን ታላላቅ ብርሃናትን የሰራ ፤ ምህረቱ ለዘላለም ነዉና ፤ ለፀሐይ ቀንን ያስገዛው ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነዉና ፤ ለጨረቃና ለከዋክብትም ሌሊትን ያስገዛቸው ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነዉና “ ፡፡
መዝሙር (135፡ 8-12)፡ ቁጥር (8-9) ከመዝ (136፡ 10-12) ይመሳሰላል፡ “ ከበኩራቸው ጋር ግብጽን የመታ ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነዉና ፤ እስራኤልንም ከመካከላቸው ያወጣ ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነዉና ፤ በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነዉና “ ፡፡
መዝሙር (135፡ 13)፡ “ አቤቱ ስምህ ለዘላለም ነው ዝክርህም ለልጅ ልጅ ነዉና “ ይላል ፡፡
መደምደሚያ
እነዚህ ምዕራፎች ለእግዚአብሄር ብዙ ስሞችን ይጠቀማሉ፡
- ጌታ ሆይ - አዶናይ “ የኔ ጌታ “ ማለት ነው ፡፡
- እግዚአብሄር - ኤሊሆም በአጭር “ አምላክ “ ማለት ነው ፡፡
- እግዚአብሄር - ወይም ያህዌ ትርጉሙ እኔ የሚል ሲሆን ለሰማይና ምድር ፈጣሪ ለእግዚአብሄር ብቻ የተሰጠ ስም ነው፡ “ ሙሴም እግዚአብሄርን ፡፡ እነሆ እኔ ወደ እስራኤል ልጆች በመጣሁ ጊዜ ፡፡ የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ላከኝ ባልሁም ጊዜ ፡፡ ስሙስ ማን ነው ? ባሉኝ ጊዜ ምን እላቸዋለሁ ? አለው ፡፡ እግዚአብሄርም ሙሴን ፡፡ ያለና የሚኖር እኔ ነኝ አለው ፤ እንዲህ ለእስራኤል ልጆች ፡፡ ያለና የሚኖር ወደ እናንተ ላከኝ ትላለህ አለው ፡፡ እግዚአብሄርም ደግሞ ሙሴን አለው ፡፡ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ ፡፡ የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሄር ወደ እናንተ ላከኝ ፤ ይህ ለዘላለሙ ስሜ ነው እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው “ (ዘጸ 3፡ 13-15) ፡፡
የእግዚአብሄር ፍቅር ዘላለማዊ ነው ፤ ስሙም ለዛላለም ነው ፡፡ ይህ ሁሉ የእግዚአብሄር መንግስት ሙሉ ለሙሉ የሚስተዋልበትና በፂዎን ሁላችንም ከአባታችን ጋር እንደምንገናኝ የወደፊቱን መገለጥ ያመለክታል ፡፡ ከአምላካችን ጋር በመሆንበማያልቀዉ የዘላለም ፍቅሩ እንደሰታለን !
Matthew Henry, Zondervan NIV Matthew Henry Commentary (Grand Rapids: Zondervan, 2010) “Psalm 134”. Available at https://www.biblestudytools.com/commentaries/matthew-henry-complete/psalms/134.html.
ጥያቄዎች
-
መዝ (134፡ 2) “ በቤተ መቅደስ ዉስጥ እጆቻችሁን አንሱ እግዚአብሄርንም ባርኩ “ ይላል ፤ እግዚአብሄርን ለመባረክ እጆቻችሁን ታነሳላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አታነሱም ? እንዲህ አይነት አምልኮ በሰማይ ይሆናል ?
-
በራሳችሁ አገላለፅ/ቋንቋ መዝ (135፡ 16-18) ምን ማለት ነው ? አሁንም እንደነዚህ አይነት ጣዖቶች ዛሬም አሉ ? እነርሱን የሰራቸዉ አንዱስ ? ልትተዋቸዉ የሚያስፈልጉ ጣዖቶች በሕይወታችሁ አሉ ?
-
ለእናንተ “ ፍቅሩ ዘላለማዊ ነው “ (መዝሙር 136) ማለት ምን ማለት ነው ? በዚያ ሐረግ ላይ እንዴት ሕይወታችሁ ላይ ተፅዕኖ እንደሚያደርግ በማሰላሰል ጥቂት ደቂቃ ዉሰዱ ፡፡
-
በመዝሙር (134-136) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 136:3–4
“Give thanks to the Lord of lords. His love is eternal. He alone does great wonders. His love is eternal.”
መዝሙረኛው ከፍጥረት ጀምሮ እስራኤላውያን በከነዓን ምድር እስከተቀመጡበት ጊዜ ድረስ ያለውን የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ፍቅር ይገልጻል ፡፡ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ፍቅር የዘለቀው በታአምራዊ አጋጣሚዎች ደግሞም በታማኝነት ጊዜያቶች ብቻ አልነበረም ነገር ግን በአስቸጋሪ ጊዜያቶችና በቁጣ ወቅቶችም ጭምር እንጅ ፡፡ በእያንዳንዷ የህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር ዘላለማዊ ፤ ምህረቱም ለዘላለም እንደሆነ ደግሞም ፍቅሩ ፈጽሞ እንደማይቆም መዝሙረኛው አውቋል ፡፡
ዛሬ ዘላለማዊ በሚለው ቃል ላይ አትኩር ፤ ዘላለማዊ ፡- ለዘላለም የሚዘልቅ እንድሁም መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ፡፡ እግዚአብሔር ስለሚወድህ ፣ ከሞት ያድንህ ዘንድ እናም አንተ ለዘላለም ከእርሱ ጋር መኖር እንድትችል ልጁን ኢየሱስን ላከው ፣ ይህ ዘላለማዊ ፍቅር ነው ፡፡ አሁን ዜግነትህ ሰማያዊ ነው ፡፡ በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ባለፍ ጊዜ እንኳ የእግዚአብሔር ፍቅር ከአንተ ጋር ነው ፡፡ ምህረቱም በየማለዳው አዲስ ነው ፡፡ በፈተናዎችህና በድካሞችህ ጊዜ ሳይቀር የእግዚአብሔር ፍቅር በርህራሄ እንደተሞላ ነው ፡፡ እርሱ መኃሪ ፣ ለቁጣ የዘገየ ነው ደግሞም በታማኝነትና በእውነት የተሞላ ነው ፡፡ ፍቅሩ በአንተ ላይ ከመፍሰስ አይቆምም ፡፡ ተቀበለው ፡፡ እሺ በለው ፡፡ በእርሱ እረፍ ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ የእግዚአብሔር ፍቅር ለአንተ ዘላለማዊ ነው ፡፡
“የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና ፤ እርሱ ብቻውን ታላቅ ተኣምራትን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና “ - መዝሙር 136፡3-4
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 86:15 — “ አቤቱ፥ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ መዓትህ የራቀ ምሕረትህም እውነትህም የበዛ “
- ዮሐንስ 3:16 — “ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ። “
- ሮሜ 8:35–37 — “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን ? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው ። በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።