David and Zion Were Chosen
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 132-133 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዚህ ሳምንት በመዝሙር መፅሀፍ ጥናታችንን እንጨርሳለን ፡፡ የመዝሙር ጥናት በብዙ ከጨረስናቸው የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍት ከማንኛዉም በጣም ረጅም ተከታታይ ትምህርት ነዉ ለኔም ታላቅ ጥናት ነው ፡፡ በመዝሙር ዉስጥ ከፍ እና ዝቅ ባለዉ የስሜት ንግግሮች እርግጠኞች አልነበርኩም ነገር ግን ለእኔ እንደተደጋገመ አልተሰማኝም፡፡ ለመዝሙር መፅሀፍ ሀረጋችን የክብር ንጉስ ነው ነገር ግን ያስገረመኝ የተሰመረበት ጭብጥ የክብርንጉስ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመጣ ነው ፡፡ ከመዝሙር አብዛኛዎቹ ወደ ኢየሩሳሌም ያመለክታሉ - በዚያ ስላለ አምልኮ ለማክበር፣ በዚያ ወዳለዉ ወደ እግዚአብሄር መገኘት እና ወደፊት በዚያ ወዳለዉ ስራ ፡፡ መዝሙር 132 ከሰዎስት ምድቦች ጋር ይገጣጠማል፡ ንጉሳዊ መዝሙር ነው፣ የከፍታ/ወደ ላይ የመዉጣት መዝሙር ነው እና መሲሀዊ መዝመር ነው ፡፡ ይህ ከከፍታ መዝሙሮች ረጅሙ ነው ፡፡
በመዝሙር 132 ወደ እግዚአብሄር ማደሪያ ስፍራ ወደ ኢየሩሳሌም የመሄድ ስሜት ነው (ቁጥር 7) ፤ አይሁዶች ኢየሩሳሌም የእግዚአብሄር ከተማ እንደነበረች ተረድተዋል ፡፡ መዝሙር 132 ከመዝሙር 89 ጋር ተመሳሳይ ነው ፤ ሁለቱም መዝሙሮች የተቀባዉን ንጉስ ሲጠቅሱ ያም ተፅፎበት የነበረዉን እና የወደፊቱ የክብር ንጉስ ጊዜ ላይ በሁለቱም ይተገበራል ፡፡ ከተቀባዉ ንጉስ ጎን ለጎን ሁለቱም መዝሙሮች የሚገጥመዉን ጠላት አቅርበዋል ፤ ሁለቱም መዝሙሮች ወደ መዳን ራስ እና ሁፋን ያመለክታሉ ፡፡ ማክአርቱር መዝሙር 132 “ ለዳዊት ንጉሳዊ ዘር እስከ መሲሁ ድረስ እንኳን ስለቀደመዉ የብሄራዊ ፀሎትን እንደያዘ “ ይገልፃል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (132፡ 1-5)፡ ያልታወቀዉ መዝሙረኛ እግዚአብሄር ዳዊት ችሏቸዉ የነበሩትን አስቸጋሪ ነገሮች (ቁጥር 1) “ ለያዕቆብ አምላክ “ እንዴት መሀላ ምሎ እንደ ነበር (ቁጥር 2) እንዲያስብ ጠየቀው ፡፡ ይህ መጀመሪያ በያዕቆብ ጥቅም ላይ የዋለ ብዙም የማይባል የእግዚአብሄር ስያሜ ነው (ዘፍ 49፡ 24-25) ፡፡ ኢሳ (1፡ 24) “ የእስራኤል አምላክ “ የሚለዉን ቃል ይጠቀማል ፡፡ እስራኤል እግዚአብሄር ለያዕቆብ የሰጠዉ ሁለተኛ ስሙ ነበር ፤ ሁለቱም ሀረጎች በችግር ጊዜ እግዚአብሄር ከለላና በረከትን እንደሚሰጥ ለማሳየት ጥቅም ላይ የዋሉ ነበሩ ፡፡ በቁጥር (3-5) ዳዊት ለእግዚአብሄር እና ለታቦቱ ማደሪያን ስፍራ ለማግኘት በፍላጎቶ የተነሳ ነበር (2ሳሙ 7፡ 1-2) ፤ ይህ ለዳዊት አስቸጋሪ ነገር ሆነ (2ሳሙኤል 24) ምክንያቱም ታቦቱን ወደ ምድሪቱም ቢያመጣዉም እንኳን እንዲገነባ ስላልተፈቀደለት ፡፡ እግዚአብሄር ዳዊትን ልጁ ሰለሞን እንደሚገነባዉ ነገረው ፡፡
መዝሙር (132፡ 6-7)፡ መዝሙረኛዉ ከዳዊት አስቸጋሪ ነገር ወደ ዳዊት ዘር ተጓዘ ፤ ኤፍራታ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ቤተልሄም አካባቡ ታቦቱ እንደደረሰ ሰሙ በዱር (ቂርያትይዓሪም ተብሎ በሚታወቀዉ ) ማሳም ላይ አገኙት ፡፡ ታቦቱ ወደ ኢየሩሳሌም ከመወሰዱ በፊት (2ሳሙ 6፡ 1-5) ለ20 አመት በቂርያትይዓሪም ነበር (1ሳሙ 7፡ 1-2) ፡፡ ማክአርቱር “ የእግዚአብሄር ዙፋኑ በሰማይ እና የእግር መረገጫዉ ደግሞ ምድር ላይ እንደሆነ “ ይገልፃል ፤ በዚህ አገላለፅ “ የእግሮቹ መረገጫ/መቆሚያ “ በቁጥር 7 “ በምድር ላይ በኪዳኑ ታቦት ላይ ማምለክ “ የሚለዉን ያመለክታል ፡፡ ኮንስታብል ወደ ኢየሩሳሌም በታቦቱ መመለስ ጉዞ ላይ ምላሹን ይገልፃል ፡፡
የእስራኤል መንፈሳዊ ተጓዦች እዚህ ጋር እንደ “ እግዚአብሄር እግር መቆሚያ “ በተጠቀሰው ታቦቱ ወደ ተቀመጠበት (ቁጥር 7) ወደ ኢየሩሳሌም ስፍራ ወደ ፂዎን ተራራ ላይ እግዚአብሄርን ለማምለክ ሲሄዱ ይህን መዝሙር ዘመሩ ፡፡ ያ እግዚአብሄር በአካባቢያዉ መንገድ በሕዝቡ መካከል ያድርበት ነበር ፤ ምድራዊ ዙፋኑ ነበር ፡፡ ከእነርሱ ጋር ለመገናኘት እግዚአብሄርን በዚያ ይጣራሉ ፤ “ የእግዚአብሄር ታቦት ኃይልን “ ተናገሩ ምክንያቱም በቀደሙት የእስራኤል ዉጊያዎች የእግዚአብሄርን ኃይል ስለሚወክል ፡፡
ታቦቱ በብዙ ነገሮች ዉስጥ ነበር በምድረበዳ ከህዝቡ ፊት መሄዱን እና ወደ ተስፋይቱ ምድር ዮርዳኖስን እንዲሻገሩ መምራቱን ያካትታል ፡፡
መዝሙር (132፡ 8-10)፡ እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን “ ጌታሆይ….አንተና ኃይለኛዉ ታቦቱ ተነሳ “ በማለት ተጣሩ (ቁጥር 8) ፤ የኔልሰን ማብራሪያ ተስፋ ገብቶ እንደ ነበረው ለእነርሱ የተቀባዉን እንዲልክላቸዉ እየጠየቁት እንደሆነ ያመለክታል ፡፡ መዝሙረኛው እግዚአብሄርን ሁሉንም ነገር በከተማዉ በስፍራዉ ላይ እንዲያስቀምጠዉ ጠየቀው - ታቦቱን፣ ንጉሱን፣ ካህናቱንና በአምልኮ የእግዚአብሄር የሆኑትን ሰዎች እንዲያስቀምጥ (ቁጥር 8-9) ፡፡ መዝሙረኛው እግዚአብሄር ከእነርሱ እንዳይመለስ/ፊቱን እንዳያዞር ለመነው ምክንያቱም ለዘላለም የተቀባዉን ተስፋ ገብቶላቸዉ ስለ ነበር (ቁጥር 10) ፡፡
መዝሙር (132፡ 11-18)፡ መዝሙረኛው እግዚአብሄርን ለዳዊት ዘሩ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ እንደሚገዛ ምሎ እንደነበር አስታወሰው (ቁጥር 11-12) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ቁጥር 11 “ የዳዊት ኪዳን ማዕከላዊ ቃል የግጥማዊ እንደ ገና ማስታወስ እንደ ነበር “ ይናገራል (2ሳሙ 7፡ 8-16) ፡፡ በሚያናድድ ሁኔታ ከዳዊት ዘር የነበሩ ነገስታቶች ምንያክሎቹ ክፉ እንደ ነበሩ እናውቃለን ፡፡ “ ለዳዊት የተገባዉ ተስፋ በታመኑት ልጆች ላይ፣ መንገድ በሳቱት ልጆች ላይ ቁጣዉ እና በመጨረሻም ተስፋ በተደረገዉ በሚመጣዉ ልጅ መፈፀም በእግዚአብሄር የተገባ በረከት የተወሰነ ነበር “ ፡፡
እግዚአብሄር ለዘላለም ቤቱና ማረፊያ ስፍራዉ እንድት ሆን ፂዎንን (ኢየሩሳሌምን) መረጠ ፤ ፈለጋት (ቁጥር 13-14)፡፡ እግዚአብሄር በከተማዉ ያሉትን ሕዝቦች ይባርካል፣ ካህናቱን ድነትን ያለብሳል ሕዝቡም “ በደስታ ይጮኻሉ “ (ቁጥር 15-16) ፡፡ “ በደስታ መጮኽ “ ማለት ቃል በቃል “ እስከ መጨረሻዉ መጮህ “ ማለት ሲሆን “ ከልብ የመነጨን የደስታ መዝሙርን “ ለመግለፅ ይጠቅማል ፡፡ በኢየሩሳሌም እግዚአብሄር “ ለዳዊት ቀንድን በማብቀል “ ለሚመጣዉ መሲህ የመብራትን ስልጣን ያዘጋጃል (ቁጥር 17) (ኢሳ 11፡ 1-5) ፡፡ የሚመጣዉ መሲህ ጠላቶቹ ሲያፍሩ እርሱ ዘዉድ ይለብሳል (ቁጥር 18) ፡፡
መደምደሚያ
የከፍታ መዝሙሮቹ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ ዘምረዋቸዉ የነበሩት ለሁላችንም ነበሩ ፡፡ ወደ ሰማይቱ ፂዎን እንሄዳለን (ዕብ 12፡ 22-24) ፡፡ የመሲሁ መንግስት ለዘላለም ይመሰረታል ( ኢሳ 9፡ 7) ጠላቶቹም አይቋቋሙትም ፡፡ የክብር ንጉስ ፍፁም ነው፣ ይህ ለሁላችንም የመዘጋጀት መዝሙር ነዉ ምክንያቱም በእርሱ ጊዜ ሁላችንም ወደ እርሱ ከፍ ስለምንል ፡፡
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 686.
MacArthur, p. 686.
MacArthur, p. 686.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes: Psalms, p. 450; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999) p. 734.
Nelson’s Commentary, p. 734.
Nelson’s Commentary, p. 734.
Nelson’s Commentary, p. 734.
ጥያቄዎች
-
በመዝ (132፡ 3-5) ዳዊት ታቦቱን በማግኘት ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በጣም የጓጓው ለምን ነበር ? (2ሳሙ 6፡ 12)
-
በመዝ (132፡ 12) እግዚአብሄር ለዳዊት ቃል ኪዳንን አደረገ ፤ በመፅሀፍ ሌላ የት ስፍራ ላይ ይህ ቃል ኪዳን ተደርጓል ? (2ሳሙ 7፡ 11-12, መዝ 89፡ 3-4)
-
መዝ (133፡ 1) “ በአንድነት መቀመጥ “ እንዴት መልካም እንደሆነ ይናገራል ፤ በመፅሀፍ ላይ አንድነት እና ሕብረት በአንድ ላይ ብዙ ማሳካት እንደሚችሉ ብዙ ምሳሌዎች አሉ ፤ በመፅኀፍ ላይ እነዚህ የት የተጠቀሱ ናቸው (ዘዳ 32፡ 30, ሮሜ 12፡ 16, 1ቆሮ 1፡ 10, ዕብ 10፡ 25) ? ከወንድሞቻችሁ ጋር በህብረት ተቀምጣችኋል ? አይደለም ከሆነ ተመሳሳይ አስተሳሰብ ካላቸዉ ሰዎች ጋር ጊዜ አችሁን ምን በማድረግ ማሳለፍ ትችላላችሁ ?
-
በመዝሙር (132-133) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 133:1
“How good and pleasant it is when brothers live together in harmony!”
በስፓርት ቡድን ውስጥ አንድነት ሲኖር ፣ ጨዋታው በድል የመጠናቀቁ እድል ይሰፋል ፡፡ በክርስቶስ አካልም ውስጥ አንድነት ሲኖር ፣ በመንግስቱ ውስጥ ለአሸናፊነት ያበቃል ፡፡ ጌታ ህብረትንና አንድነትን ይሻል ፡፡ በክርስቶስ ወንድምና እህት በሆኑት መካከል ህብረትን አንድነትን ሲያዩ አለማውያን በኢየሱስ ያምናሉ ፡፡
እርስ በእርሳችሁ በህብረት ለመኖር እንዴት ነው አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ የምታደርጉት ? ፍቅር ሁሉንም ነገር በፍጹም አንድነት አቅፎ ይይዛል ፡፡ ስለዚህ ፍቅርን ልበሱ ፡፡ ፍቅር የመጣው ከላይ ከሰማዩ አባታችሁ ፍቅር እንደሆነ አስታውሱ ፡፡ ፍቅራችሁ ከእርሱ ከተቀበላችሁት ፍቅር ይፍሰስ ፡፡ ቤተሰባችሁን ውደዱ ፡፡ በክርስቶስ አካል ውስጥ ያሉትን ወንድሞቻችሁንና አህቶቻችሁን ውደዱ ፡፡ በደልን አትቁጠሩ ፡፡ ሌሎችን ይቅር በሉ እናም ለራሳችሁ ይቅርታን ፈልጉ ፡፡ ሌሎችን ስትወዱ ፣ አለም አንድነታችሁን ያያል ደግሞም ይመሰክራል ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ራሳችሁን ክዳችሁ በትህትና ተመላለሱ ፡፡ በወንድምና በእህት መካከል አንድነት አንደሚጎድል ከተሰማችሁ ፣ እርቅ ለማውረድ ጊዜው አሁን ነው ፡፡ ዛሬ እነርሱን እንዴት ልትወዷቸው እንደሚገባ ጌታን በመጠየቅ ጀምሩ እናም ይህንን በመታዘዝ አድርጉት ፣ እርሱም ከአንተ ጋር እንደሚሆን እመኑ ፡፡
“ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው ። “ - መዝሙር 133፡1
ተጨማሪ ጥቅስ
- ዮሐንስ 17:20–23 — “ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ ። እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል ። “
- 1ኛ ቆሮንቶስ 13:4–8a — “ ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም ፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም ፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም ፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል ። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም ፡፡ “
- ቆላስይስ 3:14 — “ በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።