Having A Heart Connection
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 130-131 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በመዝሙር ዉስጥ ጥናታችንን ስንቀጥል በመፅኀፉ ዉስጥ መሲሁ እንዴት እንደ ክብር ንጉስ እንደቀረበ እናስታዉሳለን ፡፡ መዝሙር 130 በመዝሙር (107-150) አምስት መፅሀፎች ዉስጥ ሲሆን ወደ ላይ ከመዉጣት መዝሙር (120-134) ደግሞ አንዱ ነበር ፡፡ መዝሙሩ ስሜት ቀስቃሽ ትስስርን በመስጠት ቀድሞ ምን እየሆነ እንደ ነበር የኋላ ትዉስታን ሊያመጣልን ይችላል ፤ ለምሳሌ ብዙ አሳ ለመያዝ የቅርብ ጓደኛዬን አዳምን ተጠቅሜአለሁ ፡፡ በዉሃዉ አናት ላይ የሚደነስ “ ናንሲይ ዳንስ “ ተብሎ የተጠራ አሳ መያዣ ዘዴ ነበረኝ ፡፡ አሳ ስናጠምድ ሙዚቃ እያዳመጥን ነበር በተለይም ለእኔ በመደነስ ዘዴ የማገኝበት ትክክለኛ ሪትም የነበረው “ የልጅቷ ስም ተነሳ “ የሚለዉ መዝሙር ነበር ፤ መቼም ቢሆን ያን መዝሙር ስሰማ በፀሀይ በጀልባዋ ላይ በመቆም የማጥመጃ ዘዴ ዳንስን በማድረግ ከቅርብ ጓደኛ ጋር አሳ የማጠምድበትን ያን ቀን አስታዉሳለሁ ፡፡ ከዚያ መዝሙር ጋር ስሜታዊ ግንኙነት/ትስስር አለኝ ፡፡ በተመሳሳይም እነዚህ ወደ ላይ የመዉጣት/የከፍታ መዝሙሮች ለፀኀፊዉ እና ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ ከሚዘምሩት ሰዎች ጋር ስሜታዊ/የጠለቀ ትስስር ለመፍጠር የተፃፉ ነበሩ ፡፡ በተጨማሪም እነዚህ መዝሙሮች ለእኛ መፅሀፉን ከማንበብ በበለጠ እስከ ልብና ነፍስ ትስስር ድረስ በጥልቀት ስናጠናው ከእኛም ጋር ስሜታዊ/የጠለቀ ትስስርን መፍጠር ይችላል ፡፡
መዝሙር 130 በምህረት በመጀመር ወደ መታመን በመቀጠል ከዚያም ወደ ተስፋ የሚመራ ለመጨረሱ መዋጀት ክርክርን/ጉዳይን ይገነባል ፡፡ መዝሙሩ በሰዎስት ክፍሎች ሊዘረዘር ይችላል፡ ስለምህረት ተስፋ የመቁረጥ ፀሎት (ቁጥር 1-2)፣ የመታመን ኃይለኛ መግለጫ (ቁጥር 3-4) እና ለተስፋ የታወቀ/የታሰበበት ዉሳኔ (ቁጥር 5-8) ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (130፡ 1-2)፡ መዝሙረኛው ከነፍሱ ጥልቀት ተጣራ/ጮኸ (ቁጥር 1) ፡፡ ይህ እንዴት ጥልቅ ሊሆን ይችላል ? የክብር ንጉስ ወደ እርሱ ስንጮኸ ለመጠበቅ ዝግጁ ነው ፡፡ ከነፍሳችሁ ጥልቀት ጮኻችኋል ? በራሴ ህይወት በዚያ ዉስጥ ነኝ ፡፡ ሳላምን በፊት ነበር ያገባሁት እናም ነገሮች በጥሩ እየሄዱ አልነበረም ፤ በምክር ዉስጥ ነበር በዚያ ዉስጥ እንድናልፍ ኃይል እንዲኖረን አማኝ ሳልሆን በፊት እንኳን እየፀለይኩኝም ነበር ፡፡ ከዚህ በላይ ምንም ነገር ማድረግ ሳልችል ወደ እግዚአብሄር ጮኩኝ/ተጣራሁ ፡፡
መዝሙረኛዉ ስለ ምህረት ጮኸ እግዚአብሄርም ይሰማዋል (ቁጥር 2) ፡፡ እግዚአብሄር ኃይል እና በሁሉም ላይ የበላይነት ስላለዉ ወደ እርሱ መጮኽ እንችላለን ይሰማናልም ! ምህረት የሚለዉ ቃል ትርጉሙ “ በአንድ ኃይል ስር ለመቀጣት ወይም ለመጎዳት ወዳለ ሰዉ የሚደረግ ይቅርታና ርህራሄ ነው “ ፡፡ በተፈጥሮ እግዚአብሄር ድምፃችንን እንደሚሰማ እናዉቃለን ! አንዳንድ ጊዜ በስጋዊ መስተጋብሮቻችን የሆነ ሰዉ እያዳመጠን እንጂ እየሰማን እንዳልሆነ እርግጠኞች መሆን እንፈልጋለን ፡፡ መዝሙረኛዉ እግዚአብሄር እንዲያደምጠዉ ለመነው - የእግዚአብሄር ጆሮዎች በትኩረት ወደ ልመናዉ እንዲሆኑ ፡፡
መዝሙር (130፡ 3-4)፡ እነዚህ ጥቅሶች በእግዚአብሄር ላይ መታመንን ይናገራሉ ፤ በቁጥር 3 መዝሙረኛው እግዚአብሄር ኃጢዓቱን ቆጥሮ ቢሆን የሚገባዉን ፍርድ ለመጋፈጥ በእርሱ ፊት መቆም እንደማይችል ገለፀ (ሮሜ 5፡ 8) ፡፡ በእዉነታው ከእግዚአብሄር የሚለየንን አንድ ኃጢዓት ብቻ ይወስዳል ፤ ያም ሊቆጥረዉ ያስፈለገዉ ሁሉ ነው ፡፡ አንድ ነው ፤ ነገር ግን በእግዚአብሄር ምህረት አለ (ቁጥር 4) ፡፡ “ መፍራት “ የሚለዉ ቃል በቁጥር 4 እንደ “ አክብሮታዊ ፍራት “ መረዳት ይቻላል ፡፡ የኃጢዓታችን ክብደትና ከእግዚአብሄር የመለየታችን ክብደት በጣም ከፍተኛ ነው ፤ ነገር ግን ሁሉን ቻዩ እና ኃይለኛዉ እግዚአብሄር ያን ኃጢዓት ወደ ጎን የምንልበትን መንገድ ይሰጠናል - ይቅር ስለሚለን ከእርሱ ጋር በትስስር/በግንኙነት መሆን እንችላለን ይህ ከሆነም በኋላ ለኑሮአችን /ለህይወታችን አላማዉን መረዳት ስለምንችል ያን አላማ ለመኖር ወደ ኃይሉ ዉስጥ ልንጠለፍ/ልንተሳሰር እንችላለን ፡፡ በእግዚአብሄር ምህረትና ቸርነት መታመን እንችላለን ፡፡
መዝሙር (130፡ 5-8)፡ መዝሙረኛዉ እግዚአብሄርን በመጠበቅ ተስፋዉን በእግዚአብሄር ቃል ላይ አስቀመጠ (ቁጥር 5) ፡፡ ዘበኞች/ጥበቆች ቅያሬ ጥዋት እስኪመጣላቸዉ ድረስ ምሽቱን ከሚጠብቁበት ጉጉት በላይ እግዚአብሄርን ጠበቀው (ቁጥር 6) ፤ ጥበቃዎች የሰዎችን ደህንነት ለመጠበቅ በምሽት አይኖቻቸዉን በአካባቢዉ ላይ ከፍተዉ የሚከታተሉ/የሚጠብቁ ነበሩ ፡፡ በጨለማ ነገሮችን መመልከት ብዙ ጫናዎች ነበሩት ፡፡ የማለዳ ብርሃን ሲመጣ ፈታ ማለቱን/ቅለቱን አስቡት ፤ ለመስራት እግዚአብሄርን ስንጠብቅ ያ ተስፋ/ጉጉት ሊኖረን ይገባል ፡፡
መዝሙረኛው በእግዚአብሄር ተስፋ ለማድረግ የታሰበበትን ዉሳኔ ገለፀ (ቁጥር 7) ፡፡ በእግዚአብሄር መጠራት ላይ፣ በእግዚአብሄር መታመን ላይ እና ተስፋን በእግዚአብሄር ማስቀመጥ ላይ ታስቦበት የሚሆን ነገር አለ ፤ የሚሰራና አላማ መር ነው ፡፡ ነፍሳችን ከሆነ ነገር ጋር ለመገናኘት በመጠበቅ ላይ ነው….. በመገናኘት ለመሙላት ፡፡ ሰዎች ነፍሳቸዉን መሙላት ለመሞከር ሌሎች መንገዶችን ያገኛሉ - ሰዎችን፣ ምርቶችን፣ ስፍራዎችንና ሙያዎችን ነገር ግን ከጌታ ብቻ የሚመጣ ነው ፡፡ በቅርቡ ኃይለኛ ተቀባይነት ያልነበራትና ከቤተሰቧ ምርጥ ፍቅር ካላገኘች አንዲት ሴት ቀጥሎ በአንድ ፕሌን ላይ ተቀመጥሁ ፤ ወደ አንድ ቤተ ክርስቲያን ስፍራ በመሄድ ተሞልታ ነበር ነገር ግን ከዚያ በኋላ አብራት የተጓዘ ማንም አልነበረም ፡፡ መልካም ሴት ነበረች ይህ ሌሎችን ወደ መዉደድ ማድረግን ያለክታል ነገር ግን አሁንም ከነፍሷ ጋር ወደ ትስስር እንዲመጣ ያን ትስስር እየተመለከተች እንደሆነ ግልፅ ነበር ፤ ያም ኢየሱስ እንደሆነ እናዉቃለን ፡፡ በኑሮአችሁ ምን ያክል ሰዎች “ እግዚአብሄርን አዉቀዉ “ ቢገባ ኢየሱስን አያዉቁትም ? በእግዚአብሄር ያምናሉ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ያለዉን ኃይል ስተዋል ፡፡ ይቺ ሴት እንደ አንድ ጥበቃ/ዘበኛ ነፍሷ ከእግዚአብሄር ጋር የሚገናኝበትን ክስተት እየተመለከተች ነበር ፡፡
መደምደሚያ
ኢሪክ እና እኔ ተጋብተን በነበረበት ጊዜ ካይል እንዴት ሊፀልይልን እንደሚችል ሲጠይቀን አስታዉሳለሁ ፤ ልክ እንደ አቅላና ጵርስቅላ መኖር እንድንችል እንዲፀልይልን ነገርኩት ፡፡ እግዚአብሄርን በማያዉቁት ወይም ከእርሱ ጋር የጠበቀ ቅርርብን አሳድገዉ ባልነበሩት ሰዎች ጎን ለመሄድ እንፈልጋለን ፡፡ በሐዋሪያት ስራ 18 ላይ አቅላና ጵርስቅላ በመጥምቁ ዮሐንስ ስለ ጌታ ብዙ በሚያዉቀዉ ነገር ግን ከእግዚአብሄር ጋር ጥልቅ ዝምድናን/ትስስርን ቀምሶ ባልነበረው በአጵሎስ ተወሰዱ ፤ አጵሎስን በእግዚአብሄር ማመን ምን ማለት እንደሆነ በማሳየት ተስፋዉን በጌታ እንዲያገኝ ረዱት ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ስሜቱ የጠለቀ ነፍስ ድረስ የሆነ ግንኙነት እንዲያደርግ ረዱት ፤ አቅላና ጵርስቅላ ከአጵሎስ ጎን/አጠገብ ከሄዱ በኋላ በሙሉ ድፍረት ማስተማር የቻለ ነበር (ሐዋ 18፡ 24-28) ፡፤
ከእግዚአብሄር ጋር ያን ስሜት የሚያነሳሳ ትስስር እየፈለጉ ከነበሩ ሰዎች ጎን መሄድ እንፈልጋለን ፤ ሁሉንም እሁድ ለራት ወደ ቤታችን ክፍት የራት ግብዣ አለን ፡፡ ሰዎችን ያለምንም አጀንዳ በመምጣት የአምላካቸዉን ታሪክ በማዉራት፣ በማበረታታት እና በመማማር ጊዜ እንድናሳልፍ እንጋብዛቸዋለን ፡፡ ጥቂት ምሽቶችን ወንጌልን ስለ መስበክ ወይም ደግሞ ለጠፉት ስለ ክርስቶስ ፍቅር በማዉራት ጊዜ እናሳልፋለን ፤ በማዉራትና በመናገር ሂደቱ ዉስጥ በህይወታቸዉ ዉስጥ እንዴት እንደምንነግራቸዉ ለማወቅ ስለመለየት፣ እንዴት ልንባርካቸዉ እንደምንችል እና እንዴት ልባቸዉን ከእርሱ ጋር መገናኘት እንዲችል እንዴት እንደምንረዳቸዉ እግዚአብሄርን እንጠይቃለን ፡፡ ብዙጊዜ ታሪካቸዉን ሲነግሩን በኑሮአቸዉ ዉስጥ የእግዚአብሄርን እንቅስቃሴ/ነዉጥ በመጣራት እየተራዳን ነው ፡፡
በአዲስ ኪዳን ዉስጥ በአገልግሎታቸዉ የተጠቀሱት ሁለቱ የታጋቡት ጥንዶች አቅላና ጵርስቅላ ላይ ሁላችንም መመልከት እንችላለን፣ እንዲሁም ወደ ሚፈልጉት ወደ ሌሎች ለማፍሰስ እንዴት ሊጠቀምብን እንደሚችል እግዚአብሄርን መጠየቅ ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሄርን ወደ ሚፈልጉት እና ከክርስቶስ ጋር ያለዉ ትስስር ምን ሊሆን እንደሚችል ሙሉ ለሙሉ እስካሁን ወዳልቀመሱት ማገልገል እንችላለን ፡፡ በመጨረሻም ልባቸዉ ከእርሱ ጋር ሙሉ ትስስር እንዲኖረዉ እንፈልጋለን ፡፡
ጥያቄዎች
-
መዝሙር 130 አስቸኳይ በሚመስል ፀሎት ይጀምራል ፤ በዚህ ስሜት ወይም በአስቸኳይ ሁኔታ ወደ እግዚአብሄር የጮኻችሁበትን ጊዜ አስቡ ፤ የፀሎታችሁ ዉጤት ምን ነበር ? አስቸኳይ ፀሎታችሁ አሁንም እየቀጠለ ከሆነ ወደ እርሱ ልባችሁን ማፍሰሳችሁን ቀጥሉበት ፡፡
-
በመዝ (130፡ 5) መዝሙረኛዉ ተስፋዉን ለምን በእግዚአብሄር ቃል ላይ አስቀመጠ (መዝ 119፡ 89፣ ማቴ 5፡ 18፣ ሉቃ 16፡ 17፣ ዮሐ 10፡ 35) ? ይህ ከመዝ (130፡ 7) ጋር እንዴት ይመሳሰላል ?
-
በብሉይ ኪዳን እግዚአብሄር ሕዝቡን እንዴት ዋጀ/ተቤዠ ? ዛሬ ለአማኞች የዚህ መቤዠት/ቤዛነት መፈፀም ምንድን ነው ? (ሮሜ 8፡ 18-30, ገላ 3፡ 13)
-
መዝ (115፡ 3) “ የፈቀደዉን ሁሉ ያደርጋል “ የሚለዉ እግዚአብሄር መልካም እንደሆነ ሙሉ እምነት ከሌላቸው በመረበሽ ያስፈራችኋልን ?
-
በመዝሙር (130-131) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 130:5–6
“I wait for Yahweh; I wait and put my hope in His word. I wait for the the Lord more than watchmen for the morning—more than watchmen for the morning.”
ጸሀይ በአድማሱ ላይ ስትወጣ ፣ ጠባቂ ፈታ እረፍትን ያገኛል ፡፡ የጠዋት ብርሃን መጥቷልና የለሊቱ ጨለማ እንድሁም ማንኛውም አይነት አደጋ በንጋቱ ጅማሮ ምክንያት ያበቃል ፡፡ የጸሀይ ብርሃን ደርሷልና ጠባቂ ለአድስ ቀን ተስፋን ያጭራል ፡፡
ዛሬ ስራን ፣ ልጅን ፣ ደስታን ፣ ፈውስን ፣ ገንዘብን ወይም ሌላ ነገርን ለማግኘት ሰትጠብቅ ፣ ደስታህን በጌታ አድርግ ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ መጥቷል ፡፡ እርሱ ብርሃንህ ነው ፤ የእርሱ ቃል ፈውስን ፣ እውነትን ፣ ደስታን እና ድነትን ያስገኛል ፡፡ ልክ ጠባቂ ነቅቶ እንደሚጠብቅ ሁሉ አንተም እግዚአብሔር በህይወትህ እንድሰራ ነቅተህ መጠበቅ አለብህ ፡፡ ራስህን በአድማስ ላይ የሚወጣው ብርሃን እንድያገኝህ አድርገህ አስቀምጥ ፡፡ እርሱ ከአንተ ጋር ነው ፡፡ የእርሱን ፍቅር አውጅ ፡፡ የእርሱን ብርሃን አውጅ ፡፡ በእርግጥ በጨለማ ውስጥ ሁኖ መጠበቅ ከባድ ሊሆን ይችላል ……. ነገር ግን በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ላይ ተስፋን በማድረግ ጠብቅ ፡፡ በጌታ ላይ ተስፋን በማድረግ ጠብቅ ፡፡
“አቤቱ፥ ስለ ስምህ ተስፋ አደረግሁህ፤ ነፍሴ በሕግህ ታገሠች ። ከማለዳው ሰዓት ጀምሮ እስከ ሌሊት ነፍሴ በእግዚአብሔር ታመነች ። “ መዝሙር 130፡5-6
ተጨማሪ ጥቅስ
- ኢሳይያስ 52:7–8 — “ የምስራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፦ አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው ። እነሆ፥ ጕበኞችሽ ጮኸዋል፤ እግዚአብሔር ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዓይን በዓይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፥ በአንድነትም ይዘምራሉ ። “
- ሕዝቅኤል 3:17 — “ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጌሃለሁ፤ ስለዚህ የአፌን ቃል ስማ ከእኔም ዘንድ አስጠንቅቃቸው ። “
- ሚክያስ 7:7 — “ እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አምላኬም ይሰማኛል ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።