Wisdom Books Psalms

Protection Of The Oppressed

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 128-129 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 454 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በሪቫይቭ ት/ቤት መፅኀፍ ቅዱስን በማጥናት በዚህ ጉዞ ላይ ከአንድ አመት በላይ ሆነን ፡፡ ስለ ዛሬ ምን እንደምናወራ ንግግሩን ባስቀመጡት በአሪት በአምስቱ የመጀመሪያ የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍ ጀምረን ፡፡ መዝሙረኛው በአሪት እና በታሪክ መፅኀፍት መካከል ስለሆኑት ሁሉም ነገር ይፅፋል ፤ ይህ እስራኤላዊያን አልፈዉበት በነበረዉ ነገር ሁሉ እንዴት ይቋቋሙት እንደነበር የሚያንፀባርቅ አንድ መዝሙር ነው ፡፡

አሁንም ወደ ላይ የመዉጣት መዝሙር ላይ ነን ፤ የከፍታ መዝሙር እስራኤላዊያን ወደ ኢየሩሳሌም ለቂጣ በዓል፣ ለመከር በዓል ወይም ደግሞ ለዳስ በዓል ሲሄዱ የዘመሯቸዉ ነበሩ ፡፡ በእያንዳንዱ አመት ሰዎስት ጊዜ እስራኤላዊያን ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ ባደረጉ ጊዜ እየዘመሩ ነበር ፤ በእነዚህ የከፍታ ጊዜያት ሁል ጊዜ ምላሽ የመስጪኛ እና የማመስገኛ ነበሩ ፡፡ ይህ መዝሙር የሀዘን እና የእምነት እንዲሁም በስቃይና በመከራ ላይ እንዴት መተኮር እንዳለበት የሚያሳይ መዝሙር ነው ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (129፡ 1-2)፡ እነዚህ ቁጥሮች እንዴት መከራን እና ስቃይን እንደሚቀበል ይወያያሉ ፤ እነዚህ ቁጥሮች በመሰረታዊነት ተመሳሳይ ናቸዉ ነገር ግን ሁለተኛዉ ጥቅስ አጥቂዎች አሸንፈዉ እንዳልነበር ያውጃል ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች የእስራኤላዊያን ቀድሞ እንዴት እግዚአብሄር ነፃ እንዳወጣቸዉ ምላሽ መስጫዎች ናቸው ፡፡ እስራኤል እንዴት በስቃይ እንዳለፉ እንመለከታለን ፡፡

  • ዘፍ (12፡ 1-3)፡ አብርሃም ተጠራ ፤ አብርሃም ሲጓዝ አንዳንድ ሰዎች ይባርኩታል ወይም ይረግሙታል እግዚአብሄርም በረከትን ወይም እርግማንን ይመልስላቸዋል ፡፡ አብርሃም እግዚአብሄር ጥንቃቄን ወስዶለት እንደ ነበር ይረዳል ፤ ይህ መልሶ ቃሉን ታመኑ ወደሚለው ወደ መዝሙር 19 ይወስደናል ፡፡

ዘፍ (21፡ 8-13)፡ ይስሐቅ በእስማኤል ተሰቃዬ/መከራ አዬ ፤ ቆይቶም እስማኤል ይስሐቅን አፌዘበት ፡፡ ሁልጊዜ በመካከላቸዉ ዉጥረት ነበር ፡፡ ይስሐቅ ከወንድሙ የቀጠለን/የማያቋርጥን መከራ በመቀበል ለተወሰነ ጊዜያት ይመጣል ፤ ገላ (4፡ 21-31) ዛሬም በሙስሊሞች (በእስማኤል) እና በአይሁዶች (በይስሓቅ) እና ክርስቲያኖች ግጥሚያ አሁንም የሚሰማንን ዉጥረት ይገልፃል ፡፡ አይሁዶች ከምድረ ገፅ ላይ ስለ አለመጥፋታቸዉ እዉነት አስደናቂ ነገር አለ ፡፡ በመፅሀፍት ላይ ከታሪክ በኋላ ታሪክ አይሁዶችን ከምድረ ገፅ ላይ ለማጥፋት የሞከሩት መሪዎች እና ሀገራት ነው ፤ ይሁን እንጂ አላሸነፏቸዉም ፡፡

ዘጸ (1፡ 9-14)፡ እስራኤላዊያን በብዙ በተሳደዱ ጊዜ በብዙ በመጨመር ወደ ሕዝብ አደጉ/የሕዝብን ቅርፅ ያዙ ፤ አልጠፉም ፡፡ በመዝ (88፡ 15) እና በሆሴ (11፡ 1) ከችግር ነፃ የመዉጫ ንግግሮችን እናያለን ፡፡

ዘጸ (14፡ 19-31)፡ ግብፃዊያን አይሁዶችን ለማስመጥ/ለማጥፋት ሞከሩ ነገር ግን እግዚአብሄር በዚያ ፋንታ ግብፃዊያንን አሰመጣቸው ፡፡

ኢሳያስ (37-38)፡ ሶርያዊያን በከበባ ዉስጥ እስራኤላዊያንን ሊያስርቡአቸዉ ሞከረ እግዚአብሄር ግን ሰራዊታቸዉን አጠፋቸው ፡፡

ዳንኤል 3፡ ንጉስ ናቡከነደፆር (የባቢሎን ገዢ) አይሁዶችን ለማቃጠል ሞከረ እግዚአብሄር ግን ታደጋቸው ፡፡

ዳንኤል 5፡ ብልጣሶር የእስራኤልን አምላክ ቢሳደብና የተቀደሱትን እቃዎች ቢያረክስም በዚያ ምሽት ሜዳናዊዉ እና ፋሬሳዊያን ገደሉት ፡፡

ዳንኤል 6፡ ፋሪሳዊያን ዳንኤልን ወደ አንበሶች ጉድጓድ ወርዉረዉት ነበር ነገር ግን እግዚአብሄር አዳነው በዚህም ፋንታም አዉሬዎቹ ከሳሾቹን ገደሏቸው ፡፡

ከጊዜያት ሁሉ በጣም በሚያስከፋዉ አደጋ ላይ ሂትለር በጋዝ አዳራሽ ዉስጥ ከ6ሚሊዮን በላይ አይሁዶችን ገደለ ነገር ግን በመጨረሻ ተሸነፈ የእስራኤልም ሕዝብ በ1948 ተመሰረተች ፡፡

ሁሉም ሰዎ/ህዝብ ጥቂት ሕዝቦችን፣ አናሳ ቡድኖችን ለማጥፋት ለምንድ ነዉ የሚፈልጉት ? ለምን ? ጠላት ለምን በጣም ያተኩራል ? ማቴዎስ ኢየሱስ ህዝቡን በአንድ ላይ ለመሰብሰብ እንደፈለገ ነገር ግን እምቢ በማለት ብቸኛ ሕዝብ ሆኑ ኢየሱስም ተመልሼ እስክመጣ እና የመረጣቸዉም ሕዝቦቹ “ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው “ (ማቴ 23፡ 37-39) እስኪሉ ድረስ እንደማያዩት በማለት እንደ ጨረሰ ይናገራል ፤ ስለዚህም በዚህ መሰረት የጠላት ምክንያት እስራኤልን ካጠፋት ኢየሱስ ተስፋ እንደገባው ጌታ ተመልሶ መምጣት እንደማይችል ነው ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ምንም ማሳደድ ወይም በጠላትነት ለመምታት ቢሞክርም ችግር የለውም ጠላቶቿ እንዲያጠፋት አይፈቅድላቸዉም ሁልጊዜም እግዚአብሄር ያሸንፋል ፤ እንዲሁም ተመልሶ በመምጣት ቤቱን ያነፃል (ዘካሪያስ 14) ፡፡

መዝሙር (129፡ 3)፡ እስራኤላዊያን የተሳደዱ መሆንን ብቻ አልሆኑም ዋይርስቤ እስራኤላዊያን ከመከራ/ከስቃይ ጥቅምን እንደሚማሩ አመልክቷል ፡፡ ይህ ጥቅስ ብዙ መከራዎችን ይተገብራል /ይገልፃል ፡፡ ማክአርቱር መዝሙረኛው “ በጠላቶቿ በእስራኤል ላይ የደረሰዉን ቁስል ጥልቀት ነገር ግን ሞት የማስከተል እንደሆነ ለመግለፅ የእርሻን ተመሳሳይነትን እንደተጠቀመ……” ይገልፃል ፡፡

መዝሙር (129፡ 4)፡ ኮንስታብል “ በአሁኑ ጊዜ ያለ ገዢ ወይም ነገር እስራኤልን ይዞ የነበረዉ አሁን እንደተቆረጠ “ ፅፏል ፡፡ ይህ ቁጥር መቅሰፍት/ቁጣ እንደቆመ ያሳየናል ፡፡ ለእስራኤላዊያን የደረሰባቸዉን ወደ ታች ለቀጣዩ ትዉልድ ለማስተላለፍ አስፈላጊ ነበር ፡፡

መዝሙር (129፡ 5-8)፡ መዝሙረኛው “ ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ ወደ ኋላቸዉም ይመለሱ “ በማለት ፅፏል ፡፡ እዚህ ጋር ይዋረዱ የሚለዉ ቃል ይፈሩ ማለት ነው ፡፡ ማክአርቱር ማፈር ማለት መሰናከል እና መዋረድ ማለት እንደሆነ ይገልፃል ፡፡ መዝሙረኛው እስራኤልን ያሰቃዩትን እጣ ለመግለፅ የጠወለገን ሳር መልክ አመለከተ ፡፡ ማክአርቱር “ ስራቸዉ ጥልቅ ያልሆነ ሳሮች … በፍጥነት በመጀመሪያው ሙቀት እንደሚደርቅ ክፉዎችንም እንደሚገልጽ “ ፅፏል ፡፡

መደምደሚያ

ሰይጣን እስራኤልን ይጠላል ፡፡ አይሁዶችን ማጥፋት የሚችልበትን ማንኛዉም ነገር ያደርጋል ፤ ነፃ ለመዉጣት መፀለይ የሚያስፈልገን ለዚያ ነው ፡፡ ጠላታችን የተሸነፈ እንዲሆን እንፈልጋለን ፡፡ ድነት ከአይሁድ ነው ፤ ድነት ኢየሱስ ነው (ዮሐ 4፡ 22) ! ኢየሱስ ማለት ነፃነት ነው ፡፡ ሰይጣን ጊዜዉ የተወሰነ እንደሆነ ያውቃል ፡፡ ድነት ለሁሉም የቀረበ ነው ፡፡ ጠላት አያሸንፍም ፡፡

  1. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 350.

  2. Wiersbe, p. 350.

  3. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 685.

  4. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 448; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

  5. MacArthur, p. 685.

  6. MacArthur, p. 685.

ጥያቄዎች

  1. የሆነ ሰዉ ለምን እግዚአብሄርን በመፍራት ደስተኛ ወይም የተባረከ ይሆናል ? እግዚአብሄርን መፍራት ማለት ምን ማለት ነው ?
  2. እግዚአብሄርን ያለመፍራትና በኃጢዓት የመቀጠል ዉጤቱ ምን ሊሆን ይችላል ? (2ሳሙ 12፡ 12, ማቴ 10፡ 26)
  3. እንደ መዝሙር 128 አገላለፅ እግዚአብሄርን ለሚፈሩት በረከቶች ምን እንደሚሆኑ መዝሙረኛው ምን እያለ ነበር ? በቤታችሁ ጌታ የበላይ /የመጀመሪያ ቅድሚያ አለው ?
  4. የመዝሙር 129 ርዕስ “ የተጨቆኑት ከለላ/ጥበቃ “ የሚል ነው ፡፡ ይህን መዝሙር ከመዝ (118፡ 1-4) እና መዝ (124፡ 1-5) ጋር አወዳድሩ ፤ የእግዚአብሄርን ጥበቃና ታማኝነትን እንዴት ታዩታላችሁ ?
  5. የመዝ (129፡ 6) ምስል ኢየሱስ በዘሩ ምሳሌ ላይ እንዴት ተጠቀመው ? (ማቴ 13፡ 5-6, 20-21)
  6. በመዝሙር (128-129) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 129:1–2

“Since my youth they have often attacked me—let Israel say—Since my youth they they have often attacked me, but they have not prevailed against me.”

እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ለአመታት በታማኝነት ጠብቋቸዋል እናም በተመሳሳይ እርሱ አንተንም ለመጠበቅ ቃል ገብቷል ፡፡ አስታውስ በክርስቶስ ህይወት አለ ፡፡ በክርስቶስ ድል አለ ፡፡ በክርስቶስ ነጻነት አለ ፡፡ በአንተ ላይ የተሰራ መሳሪያ አይከናወንም ፡፡ በተደጋጋሚ ጉዳት ሊደርስብህ ይችላል ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ጸንተህ ስትቆም ፣ ድልን ትቀዳጃለህ ፡፡ የጠላት አሳብ አያሸንፍም ፡፡

ምን ይመስላል በመጎዳት ውስጥ ሆኖ መዋጋትን መቀጠል ? በእግዚአብሔር ላይ በእምነት ቁም ፡፡ እግዚአብሔር አሸናፊ እንደሆነ በማመን ፣ በእምነት መጓዝህን ቀጥል ስለዚህም በእርሱ ብቻ ድልን ታገኛለህ ፡፡ ድል የሚገኘው አይኖችህን በኢየሱስ እና በእርሱ ጥበብ ላይ በማድረግ ነው ፡፡ እርሱን ፈልገው ፡፡ ከቃሉ ጋር ጊዜን አሳልፍ ፡፡ ድምጹ እንድመራህ ፍቀድ ፡፡ ነገር ግን እወቅ አንተ እንድሁ ዝም ብለህ ሳለ እንኳ ፣ እርሱ ስለ አንተ ይዋጋል ፡፡ ጠላት አያሸንፍም ፡፡ በክርስቶስ ኑር ፡፡ እርሱ መሸሸጊያህ ነው ፡፡

“ እስራኤል፦ ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ ይበል ፤ ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም ። “ - መዝሙር 129፡1-2

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ኢሳይያስ 54:17 — “ በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፥ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር ፡፡ “
  • ኤርምያስ 1:19 — “ከአንተ ጋር ይዋጋሉ፥ ነገር ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ድል አይነሡህም፥ ይላል እግዚአብሔር ፡፡ “
  • 1ኛ ዮሐንስ 4:4 — “ ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ አሸንፋችኋቸውማል፥ በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና ። “