Zion's Restoration
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 126-127 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዚህ ሳምንት የእግዚአብሄር ቃል በህይወታችን እንዴት እንደሚሸከመን የሚያተኩረዉ ረጅሙን መዝሙር ስለ መዝሙር 119 አዉርተናል ፡፡ ከመዝሙር 120 እስከ መዝሙር 134 የእስራኤል ህዝቦች ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ እግዚአብሄር ስላደረገላቸው ነገር የሚዘምሯቸው የከፍታ መዝሙር ናቸው ፡፡ መዝሙር 126 ሰባተኛዉ የከፍታ መዝሙር ነው ፡፡ ፀኀፊዉን ባናዉቀዉም የኔልሰን ማብራሪያ “ መዝሙሩ ከባቢሎናዊያን ምርኮ በመከተል ወደ ኢየሩሳሌም በመታደስ ጊዜ የመጣ እንደሆነ “ ይናገራል፣ በብዛት በነህምያና በዕዝራ ጊዜ የሆነ ይመስላል ፡፡ ዕዝ (2፡ 1), ነህ (7፡ 6) እና ኢሳ (10፡ 22) ጥቂት የአይሁዶች ቡድን ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱበትን ጊዜያት ይገልፃሉ ፡፡
መፅሀፍ ሰዎስት የተለዩ መመለሶችን ይገልፃል ፤ የመጀመሪያው በግምት 538 ከክርስቶስ ልደት በፊት በዘሩባቤል ተመርቶ የነበረው በዕዝራ (1-6) የሚገኝ ሲሆን ፤ ሁለተኛው በ458 ከክርስቶስ ልደት በፊት በዕዝራ ተመርቶ የነበረው በዕዝራ (7-10) ተገልጾአል ፤ ሰዎስተኛውበነህምያ (1-2) እንደተገለፀው 445 ከክርስቶስ ልደት አካባቢ ሌላ የአይሁዶች የመመለስ ማዕበል ከነህምያ ጋር ነበር ፡፡ ከ70 አመት ምርኮ በኋላ አይሁዶች ወደ ቤታቸዉ/ወደ ምድራቸዉ እየመጡ ነበር ! ይህ መዝሙር ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ቤታቸዉ በመመለስ ደስታቸዉን ይናገራል - እግዚአብሄርን ያመኑ ወደ ሚሆኑበት ቤታቸው ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (125፡ 1-3)፡ እስራኤላዊያን ቀምሰዉት/አግኝተዉት የነበረዉ ያልተጠበቀ ነገር ነበር ከእዉነት ይልቅ ሕልም ይመስላል ፤ እግዚአብሄር እንደሚሰጣቸዉ ተናግሮት ወደ ነበረዉ ምድራቸዉ ተመለሱ ፡፡ ዋረን ዋይርስቤ እነዚህን ጥቅሶች፡ “ በእኛ ዉስጥ ነፃ የመዉጣት ደስታ እንዳለ “ ይገልፃቸዋል ፡፡ መዝሙር 126 ዛሬ ሰዎች በመዳን ዉስጥ የሚገጥማቸዉን ይገልፃል ፡፡ በባርነት ከሆናችሁ ነፃ ስትወጡ የጌታን ደስታ ትቀምሱታላችሁ ፤ ካጣበቃችሁ/ከተጣበቀባችሁ ማንኛዉም ነገር( ከትዕቢት፣ ከሱስ፣ ከዝሙት፣ ማንኛዉንም የተለመደ ነገር ከመብላት) ነፃ የሚያወጣችሁን የክብር ንጉስን ኢየሱስ ክርስቶስን ስታገኙት ያ ክብደት ወይም ህመም አይኖራችሁም ፡፡ በመጨረሻም በእዉነት ህልም የሆነዉን ነፃነትና ድንቅ ትቀምሳላችሁ ፡፡
እስራኤል በደስታ መጮኽ ስትጀምር ሌሎች ሕዝቦች እግዚአብሄር ለእነርሱ አድርጎላቸዉ የነበረዉን ያስታዉላሉ ፡፡ አዎ እግዚአብሄር ከ70 አመት በፊት አስወጥቷቸዉ ነበር ነገር ግን አሁን መልሶ አመጣቸው ፡፡ እግዚአብሄር በእዉነት ከባርነት አዉጥቶ በማምጣት ነፃ ስላደረጋቸዉ ክብርን ተቀበለ ፡፡ በሳቅ የሚሞላ ታላቅ አይደለምን ? በእግዚአብሄር ፍቃድ መካከል ላይ በመሆን ስታዉቁት በጣም የሚያድስ/የሚዝናና ነው ፡፡
ስለዚህ ነገር አማኞች እግዚአብሄርን የሆነ ነገር ማዉራት ሲፈልጉ ከዚያም በሚሆን ጊዜ ይህ በእዉነት ከእግዚአብሄር እንደ ነበር ሲደነቁ ሌላ የት ላይ አይተናል ? ሐዋ (12፡ 6-11) አማኞች ሄሮድስ ምንም እንኳን ያዕቆብን ቢገድለዉም ጴጥሮስን እንዲለቅቀው የፀለዩበተትን ጊዜ ይገልፃል ፡፡ አንድ መለዓክ ጴጥሮስን ከሰንሰለት እና ከያዥዎቹ ነፃ አዎጣው ይህ ቢሆንም እንኳን ጴጥሮስ ግን ራዕይ እያየ እንደ ነበር አሰበ ፡፡ በጴጥሮስ መንገድ ላይ የነበረ ማንኛዉም ወጥመድ እግዚአብሄር ተጠነቀቀላቸው ፡፡ ጴጥሮስ ሆኖ የነበረዉን ባስተዋለ ጊዜ “ እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ “ (ሐዋ 12፡ 12) ፡፡ ስለ ጴጥሮስ መለቀቅ እየፀለዩ ቢሆንም እንኳን በበሩ ላይ መቆሙን ማመን አልቻሉም ነበር (ሐዋ 12፡ 13-17) ፡፡
በመዝሙር 126 እስራኤላዊያን ስለ መለቀቃቸዉ ናፍቀዉ ነበር በሆነም ጊዜ እንደ ህልም የሚሰማ ቢሆንም እንኳን ተደሰቱ አሕዛቦችም እስራኤል በእግዚአብሄር ደስታ እንደተሞላች አስተዋሉ ፡፡ የደስታ ህይወት ትኖራላችሁ ? ቁጥር 3 ለእነርሱ እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረዉን ሌሎችን ነገሯቸው ፡፡ በእዉነት እግዚአብሄር ነፃ እንዳወጣችሁ ስታምኑ በጌታ ደስታ ትጓዛላችሁ ፡፡
መዝሙር (126፡ 4-6)፡ እንደ ዋይርስቤ አገላለፅ እነዚህ ቁጥሮች “ በዙሪያችን የህይወት ተስፋዎች እንዳሉ “ ያሳያል፡፡ የእስራኤል ሰዎች ለእግዚአብሄር ምርኮአቸዉን እንዲመልስ ፀለዩ (ቁጥር 4) ፡፡ “ በነጌቫ ዉሃ መዉረጃዎች “ በእስራኤል በደቡብ በኩል ያለን ወንዝ ያመለክታል ፤ ይህ በመጨረሻ በበጋ ወቅት የሚደርቅ የተወገደው የቤርሳቤህ ደቡብ ክፍል ነጌቫ ተብሎ ተጠራ ነገር ግን ወንዞቹ በፍጥነት በመሙላት በዝናብ ምንጮች ይፈስሳሉ ፡፡ በዚህ ሁኔታ መዝሙረኛው የእስራኤል ምርኮ ወዲያዉኑ ከምንም በፍጥነት እንደሚቀየር ፀለዬ “ ፡፡ በቁጥር 4 ከባቢሎን መንገዶች በእግዚአብሄር ተጨማሪ በረከቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ይህ አስተሳሰብ ነበር ፤ ሕዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ እንደ ጎርፍ ይመለሳሉ - ተጓዦቹ ኢየሩሳሌምን እንደገና እንደሚይዝ የመጀመሪያ ህዝብ ተመልሰዉ ወደ ምድሪቱ ተጓዙ ፡፡ እግዚአብሄርን ከሕዝቡ ጋር እንደገና ይህን ማህበረሰብ ወደ ስፍራዉ መልሶ በማደስ እንዲያፈሳቸዉ እየጠየቁ ነበር ፡፡ በቀረዉ አስተሳሰብ በጥቂት ጀመሩ ነገር ግን እግዚአብሄር እንዲሆኑ እንደሚፈልገው እንዲያድሳቸዉ ጠየቁት ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ በመጨረሻም ይህ በህዝቡ መካከል የእግዚአብሄርን ስራ ስለሚፈፅመዉ ስለ ኢየሱስ መምጣት ጸሎት ነው “ አለ ፡፡
ሰዎስት የህዝብ ማዕበል በዘሩባቤል፣ በዕዝራና በነህምያ ስር ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ ፤ በዚህ የጊዜ መዋቅር ጊዜ ቤተ መቅደሱን መልሰዉ ገነቡት ፡፡ በጊዜዉ ቆይቶም ይህ ቤተ መቅደስ ፈራርሶ ስለነበር ሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ ሐሰተኛዉ ክርስቶስ/አዉሬው ለአይሁዶች መልሰዉ ቤተ መቅደሱን እንዲገነቡ ስምምነት ባደረገ ጊዜ ይገነባል ፡፡ አዉሬዉም ወደ ቤተ መቅደሱ በመምጣት ለችግሮች ምክንያት ይሆናል ነገር ግን በዚህ ሁሉ የክብር ንጉስ ተመልሶ ይመጣል ፡፡ በዚህ ሁሉ አብረን እንደታሰርን በዚያ መልክ እንፅና ፡፡
ኢየሱስ ለመጀመሪያ የመጣ ጊዜ ከባርነት ወደ ነፃነት ታደገን ፡፡ በዮሐ (7፡ 37-38) ኢየሱስ ማንም የተጠማ ከነበር ወደ እርሱ በመምጣት እንዲጠጣ ጋበዘ/ተጣራ ፤ “ በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ዉኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ “ ፤ ስለዚህም መዝ (126፡ 4) ክርስቶስ በመምጣት በዉስጣችን በፃነት በሚፈስስ ዉሃ የመታደሳችን መልክ ነው ፡፡
በሕዝ (47፡ 1-12) ሕዝቅኤል በእነዚህ ጥቅሶች የተገለፁትን በራዕይ አይቷቸዋል/ቀምሶአቸዋል ፤ በቁጥር 3-5 ከእግዚአብሄር መገኘት ከቤተ መቅደስ የፈሰሰዉን ዉሃ ገልፆታል ፤ ከቤተ መቅደስ የሚፈስሰዉ ዉሃ - ከኢየሩሳሌም ከእግሩ እስከ ጉልበቱ እስከ ጭኑ ድረስ ሔደ ፡፡ ወዲያዉኑም ዉሃው ለመዋኘት በበቂነት በጥልቀት በመፍሰስ በእግር መሻገር የማይቻል ወንዝ ሆነ ፤ ከቤተ መቅደስ የሚፈስሰዉ ዉሃ በሁሉም መንገድ ወደ ታች ወደ አረባም “ ወደ ረከሰዉ ዉሃ “ ማለትም ወደ ሙት ባህር ፈሰሰ (ሕዝ 47፡ 6-8) ፡፡ ይህ ንፁህ ዉሃ ወደ ከንቱዉ ዉሃ በሚፈስስ ጊዜ ከንቱዉ ዉሃ ንፁህ/የታደሰ ይሆናል ፤ ዉሃዉ ንጹህ ሲሆን ደግሞ ዉሃ ወደ ሄደበት ስፍራ ሁሉ ህይወት ይሆናል (ሕዝ 47፡ 9) ፤ ይህ ህያዉ ዉሃ ፍሬን ይሰጣል - ምንም አይሞትም ፡፡ እያንዳንዷ ወር ላይ ለምግብና ለፈዉስ ቅጠል ንፁህ/አዲስ ይኖራል ምክንያቱም ዉሃው ከቤተ መቅደስ ስለሚመጣ (ሕዝ 47፡ 10-12) ፡፡
በመዝሙር 126 ሕዝቡ እግዚአብሄርን ደርቆ የነበረዉን ነገር ሁሉ እንዲያደስ ጠየቁት ፤ ከባርነት እየወጡ ስለ ነበር አዲስ ህይወትን መቅመስ ፈለጉ ፡፡ ኢየሱስን ይህን እንዲያደርግልን ስንጠይቀዉ ህያዉ ዉሃን ይሰጠናል ፤ በመጨረሻም ቤተ መቅደሱን እንደገና እናየዋለን፣ በሕዝቅኤል 47 መሰረት ወደ ምድር ህይወትን ያመጣል ፡፡ በእኛ ዉስጥ ልንቀምሰዉ የምንችለዉ የነፃነት ደስታ ነው ፤ ዙሪያችን ክርስቶስ ተመልሶ በመምጣቱና በሰዎስተኛዉ ቤተ መቅደስ የተስፋ ህይወት ነው ፡፡ ዋይርስቤ “ ከፊታችን የስራ ፈተና ይመጣል “ ብሏል ፤ ቁጥር 5-6 “ በእንባ የዘሩ በደስታ ጪኸጽ እንደሚሰበስቡ “ ገልፀዋል ፡፡ በጊዜዉ እርሻ/ግብርና ከባድ/አስቸጋሪ ስራ ነው ፤ መሬትም አስቸጋሪ ነው ፤ ፍሬ ለማየት ስራን ይፈልጋል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ የእስራኤል ህዝቦች ወደ ንስኃ ወደ መራቸዉ ወደ ባቢሎን በእንባ ሄዱ ብሏል ፤ በዚህ ንስሀ ምክንያት 70 አመት መጨረሻ ላይ እጅግ ብዙ ሽልማቶችን አገኙ ፡፡ ጌታ በትክክል ትሁቶቹን እና ይቅር ጠያቂ ሰዎችን ሊታደግ መጣ ፤ ነገር ግን ያ ሽልማት ያለ ስራ አይመጣም - ያለ ይቅርታና ያለ ንስሀ ፡፡
መደምደሚያ
ጌታ የደስታን ምርኮ እንድንሰበስብ ይፈልጋል ነገር ግን ይህ ራሳችንን ለማቅረብ ፍቃደኞች ስንሆንና በባርነት ዉስጥ ከሚያደርጉን ነገሮች ለመዉጣት እግዚአብሄር እንድናደርግ የጠየቀንን ስናደርግ ብቻ ይመጣል ፤ ይህ በመሰረቱ ስራ ይፈልጋል/ይወስዳል ፡፡ ገላ (6፡ 9) ይህን ተስፋ ያረጋግጣል ፡፡ አብዛኞቻችን በዙሪያችን ካለው በህይወታችን ከምናገኘዉ ሽልማት ፊት ዝም ያልነን ፡፡ ስለ እርሱ ብዙ ለመቅመስ/ለማወቅ በዚህ መጓዛችሁን መቀጠል አለባችሁ !
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 732.
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 684.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 344.
Wiersbe, p. 345..
MacArthur, p. 684.
Nelson’s New Illustrated Bible Commentary, p. 732.
Wiersbe, p. 345.
Nelson’s New Illustrated Bible Commentary, p. 732.
ጥያቄዎች
-
አይሁዶች ከምርኮ በተመለሱ ጊዜ ሌሎች ሕዝቦች “ እግዚአብሄር ታላቅ ነገር አድርጎላቸዋል “ አሉ ፤ ሌሎች ሕዝቦች ቀንተዉ እንደ ነበር ታስባላችሁ ? ኢየሱስ ስለ እስራኤልና ስለ ቅናት ምን ብሏል (ሮሜ 11፡ 11-14)? ኢየሱስ ባደረገላችሁ ነገር የሆነ ሰዉ ወደ ህይወታችሁ በቅናት ይመለከታል ? እንዴት አድርጎ ?
-
መዝ (127፡ 1) ምን ማለት ነው ? ማቴ (7፡ 24-27) ይህን ጥቅስ በይበልጥ ይገልፀዋል ወይም ያብራራዋል ብላችሁ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አይገልፀውም ? “ ቤታችሁ “ በጠንካራ መሰረት ላይ የተሰራ ነው ?
-
በመዝ (127፡ 2) በቂ ምግብ እንዲኖር ጠንክሮ መስራት ከንቱ ነዉ አለ ፤ ይህን ሌላ በመፅሀፍ የት ላይ ታዩታላችሁ ? (ማቴ 6፡ 26, ዮሐ 6፡ 27, ፊል 2፡ 16, ቆላ 3፡ 23-24)
-
በመዝሙር (126-127) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 126:1–2
“When the LORD restored the fortunes of Zion, we were like those who dream. Our mouths were filled with laughter then, and our tongues with shouts of joy. Then they said among the nations, ‘The LORD has done great things for them.’”
እግዚአብሔር ከአመታት ግዞት በኋላ ጽዮንን ( የእስራኤልን ትውልድ ) አሰበ ወደ ቦታቸው መለሰ ፡፡ እርሱ ለአንተም ህይወት መታሰብን ወደ ቀድሞው መመለስን ለማድረግ ይፈልጋል ፡፡ መወሰን አለብህ “ አዎ ነጻነትን ፣ ህይወትን ፣ እግዚአብሔርም ለእኔ በእርሱ ውስጥ ያዘጋጀውን የደስታ ሙላት ለመሻት ፍቃደኛ ነኝ ! “
ልክ አትክልተኛ ፡- አረሙን ለማስወገድ ፣ መሬቱን ለማረስ ፣ ዘሩን ለመዝራት እና ዘሩ እስኪያድግ ለመጠበቅ ጊዜን እንደሚወስድ ሁሉ የአንተም ህይወት ከክርስቶስ ጋር እንድሁ ነው ፡፡ መወሰን ትችላለህ ወደ አትክልቱ ስፍራ ለመሄድ ነገር ግን ውበቱን አይተህ ደስ ላለመሰኘት ወይም ፍራፍሬውን ላለመቅመስ በቃ ምንም ላለማድረግ ፡፡ ወይም ደግሞ ስራውን ለመቀበል ፣ ውበትን ለማጎልበት እናም ደግሞ ለፈውስ እግዚብሔርን በንስሃና ራስን በማዋረድ ለመፈለግ መምረጥ ትችላለህ ፡፡ ዛሬ ምርጫህ ምንድን ነው ? እግዚአብሔር በህይወትህ ትልልቅ ነገሮችን ለማድረግ ፍቃደኛ ነው እናም ደግሞ ሙሉ ፈውስን ሊሰጥህ በመጠበቅ ላይ ነው ! እርሱ አፍህን በሳቅና በእልልታ ሊሞላ ደግሞም ምርኮን ሊመልስ ይፈልጋል ፡፡ ጊዜ ይወስድ ይሆናል ነገር ግን ለነጻነት ለመልካም ያደርገዋል ፡፡
“ እግዚአብሔር የጽዮንን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ እጅግ ደስተኞች ሆንን ። በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን፥ አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ፤ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው ተባለ ። “
- መዝሙር 126፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
ኢሳይያስ 61:7 — “ በእፍረታችሁ ፋንታ ሁለት እጥፍ ይሆንላችኋል፥ በውርደታችሁም ፋንታ ዕድል ፈንታችሁ ደስ ይላቸዋል፤ ስለዚህ በምድራቸው ሁሉ እጥፍ ይገዛሉ፥ የዘላለምም ደስታ ይሆንላቸዋል ። “
አሞጽ 9:14 — “ የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፥ የፈረሱትንም ከተሞች ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁንም ይጠጣሉ፤ አታክልትንም ያባጃሉ፥ ፍሬውንም ይበላሉ ። “
ገላትያ 6:9 — “ ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።