Wisdom Books Psalms

Psalms 124-125

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 124-125 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 452 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙር 124 ወደ ላይ የመዉጣት በመባል የሚታወቅ መዝሙር ክፍል ነው ፡፡ ሕዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም መንገዳቸዉ ላይ በነበሩ ጊዜ እነዚህን መዝሙሮች ዘመሯቸው ፤ በምን ዉስጥ አልፈዉ ስለ ነበረዉ ነገር በመዘመር ሕዝቡ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡ ጊዜ ትክክለኛ የአይምሮ መዋቅር ዉስጥ ነበሩ ፡፡ መዝሙር ለእኛ የልብ ትስስር መፍጠር የሚችል ችሎታ ያለዉ ስለሚመስል የዜማ ወይም መዝሙር ፍላጎት የስሜት ግንኙነት መፍጠር ነው ፡፡ መዝሙር 124 ቢሆን የሚል ንግግር ስርዓትን ይይዛል - “ ከሆነ/ይህ ይሆናል “ የሚል ንግግር አስቀምጧል ፤ በቀላሉ የሆነ ነገር እዉነት ከሆነ ዉጤቱ ይህ ይሆናል ማለት ነው ፡፡

መዝሙር 124 ወደ ሁለት ክፍል ወይም ቁብ ነገር ሊከፈል ይችላል ፤ ቁጥር 1-5 ነፃ ስለመዉጣት ይናገራል ፤ ይህ ዳዊታዊ መዝሙር ስለሆነ ዳዊት ነፃ መዉጣትን ባገኘ/በገጠመዉ ጊዜ ስለጊዜዉ ፃፈው ፡፡ ቁጥር 6-8 ነፃ ስለመዉጣት አመስጋኝነትን ይገልፃል ፡፡ ሁለቱ ጭብጥ/ፍሬ ነገሮች በሚቀያየሩ ንግግሮች ሊገናኙ ይችላሉ፡ ነፃ የወጣችሁ ከሆነ አመስጋኝነት ምላሻችሁ መሆን አለበት ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (124፡ 1-2)፡ በመዝሙሩ “ ከሆነ “ የሚለዉ ቃል እንደ መጀመሪያ ቃል ይከሰታል ፤ “ ከእኛ ጋር የነበረዉ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ “ የሚለዉ የመጀመሪያ ሁኔታ ነበር ፡፡ ቁጥር 2 (ኒዉ ኪንግ ጀምስ እትም) “ ሰዎች በእኛ ላይ በተነሱብን ጊዜ “ የሚል መነሻ ጨምሯል ፤ ይህ የዳዊት መዝሙር ስለሆነ ብዙ ሰዎች ፍልስጤም እስራኤልን ባጠቃች ጊዜ ከ 2ሳሙ ( 5፡ 17-19) ጋር ያገናኙታል ፡፡ በጉዳዮች ዉስጥ በመሄድ ፈተናዎቹን በሚገጥሙ ጊዜ ነፃ መዉጣትና ጥበቃ ያስፈልገናል፣ እንዲገለጥልን በሚያስፈልገን ጊዜ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር እንደሆነ ማወቅ እንችላል ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን ወደ ዉጊያው ጋበዘው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ወደ ዉጊያችን እንዲገባ እግዚአብሄርን መጋበዝ እንረሳለን - ትልቅ ወይም ትንሽ ዉጊያ ዉስጥ ፡፡ እግዚአብሄር ወደ ጦርነታችሁ ዉስጥ የተጋበዘ ሲሆን በትልቅ መንገድ ሊያሳየየን ይችላል ፡፡

መዝሙር (124፡ 3-5)፡ ዳዊት እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር ባይሆን ኖሮ ምን እንደሚሆን ገለፀ፡ “ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር ….. በዚያን ጊዜ የጎርፍ ዉኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር “ (ቁጥር 3-5) ፡፡ እግዚአብሄርን ከእነርሱ ወገን ባይሆን ኖሮ ጎርፍና ፈሳሾች በላያቸዉ ላይ ይፈስሱ ነበር ፤ ነገር ግን 2ሳሙ (5፡ 20-25) እግዚአብሄር በፍልስጤማዊያን ላይ ጣልቃ ስለ ገባ ዳዊት ያን ዉጊያ እንዳሸነፈ ገልጧል፡ “ ዉኃ እንዲያፈርስ እግዚአብሄር ጠላቶቼን በፊቴ አፈረሳቸዉ አለ “ (2ሳሙ 5፡ 20) ፡፡ ወደ ጦርነታችን እግዚአብሄርን ከጋበዝነዉ የማሸነፍ የተሸለ እድል አለን ፤ ይህ ዘይቤአዊ አነጋገር እንደሆነ ስታስታዉሱ ወደ ዉጊያዉ እግዚአብሄርን ስንጋብዘዉ ሁልጊዜ እናሸንፋለን ? ሁልጊዜ አይሆንም ፡፡ ሮሜ (5፡ 3-4) እግዚአብሄር በዉጊያ ዉስጥ ለሆነ ጊዜ ስለሚጠብቀን ማደግ እንችላለን ፡፡ ያዕ (1፡ 12) እግዚአብሄር በመከራዉ ዉስጥ የፀናን እንድንሆን በመጠየቅ ሊያጠራን በዉጊያ ዉስጥ እንደሚያደርገን ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄርን ወደ ዉጊያዉ ዉስጥ ጋብዘነው እንዳልታዬ ካሰብን በማቆም በጦርነቱ ዉስጥ እግዚአብሄር ምን ሊያስተምረን እየሞከረ እንዳለ ራሳችንን መጠየቅ ያስፈልገናል ፡፡ እግዚአብሄር ነፃ ቢያወጣንም ወይም በዚያ ዉስጥ ቢያደርገንም እርሱ ከእኛ ጋር እንደ ሆነ ማወቅ እንችላለን ፡፡

ሕዝቡ ይህን መዝሙር ወደ ኢየሩሳሌም በሚሄዱበት መንገድ ላይ እየዘመሩ እንደ ነበር እናስታዉሳለን ስለዚህም እግዚአብሄር ለእነርሱ አድርጎላቸዉ የነበረዉን ያስታዉሳሉ (ቁጥር 1-5) ፡፡ ቀሪዎቹ ጥቅሶች ለእግዚአብሄር ምስጋናቸዉን ይገልፃሉ (ቁጥር 6-8) ፡፡

መዝሙር (124፡ 6)፡ ዳዊት ነፃ ስለመዉጣታቸዉ እግዚአብሄርን አመሰገነ፡ “ እግዚአብሄር የተባረከ ይሁን “ ፤ “ እግዚአብሄር ሲባረክ “ በምትሰሙ ጊዜ እግዚአብሄር የእናንተን ባርኮት አይፈልግም ከሚለዉ መረዳት ጋር እንዴት ታስታርቁታላችሁ ? ዘዳ (8፡ 10) “ ትበላማለህ ትጠግብማለህ ስለሰጠህም ስለመልካሚቱ ምድር አምላክህን እግዚአብሄርን ትባርካለህ “ ይላል ፤ በዚህ አነጋገር እግዚአብሄርን መባረክ ማለት ለእርሱ ምስጋና መስጠት ማለት ነው ፡፡

መዝሙር (124፡ 7)፡ ዳዊት ከወጥመድ የማምለጡን አሳብ በአዳኝና በታዳኝ የቃልመልክ ስሎታል ፡፡ ትንሽ ታዳኝን ለመያዝ እንደ መያዣ ወጥመድ በቀጭን ገመድ ወይም የአሳ መያዣ ቀለበት አይነት ነገር ታደርጋላችሁ ፤ እንስሳዉ ገመዱን በጎበኘዉ/በነካዉ ጊዜ ቀለበቱ እንስሳዉን ይይዘዋል ፡፡ ወጥመዶች እንደ አካባቢዉ አካል ለመቀየጥ የተቀመጡ ናቸው ፡፡ ስለ ኑሮአችን እና ሊያደምጡን ስለሚፈልጉ ጠላቶቻችን በምናስብ ጊዜ ወጥመዶቹ በአካባቢያችን ዉስጥ ለመቀላቀል/ለመቀየጥ በመንገዳችን ሁሉ ላይ የተቀመጡ ናቸው ፤ በብዙ በቀረብናቸዉ ጊዜ ይይዙናል ፡፡ በዚህ አገላለፅ ወጥመዱ ወፏን ይይዛት ይሆናል ነገር ግን ወፏ ማምለጥ ትችል ነበር ፡፡ ወጥመዱ ከተሰበረ እግዚአብሄር ፍጥረቱን ከዚያ ወጥመድ ነፃ አወጣቸው ፡፡ ስለዚህ አመስጋኝነት አስተሳሰብ ስናስብ ጠላታችን ሊያዘን ወይም ሊያጠምደን ካስቀመጠው ነገር ማምለጥ በምናስብ ጊዜ እንዴት ማመስገን አለብን ?

መዝሙር (124፡ 8)፡ ዳዊት እርዳታቸው ሰማይና ምድርን ከሰራዉ በእግዚአብሄር የተገኘ እንደ ነበር አስተዋለ ፡፡ እግዚአብሄርን ወደ ዉጊያዎቻችን ስንጋብዘው ከእኛ ጋር ወደ ዉጊያ ዉስጥ የጋበዝናቸዉን ማስታወስ አለብን ፤ ይህ ሁሉንም ነገር ማድረግ የሚችለዉ እግዚአብሄር ነው ፡፡ በጣም ትልቅ ስለሆነ ሊረዳን ይችላል ፡፡ እግዚአብሄር ማን እንደሆነ ስናስታዉስ በእያንዳንዷ ነጠላ ዉጊያ እና መከራ እና በኑሮአችን በሚገጥሙን ወጥመዶች ሁሉ ልንጋብዘዉ እንፈልጋለን ፡፡ ይህን ስናደርግ አመስጋኞች ያደርገናል - አመስጋኝ ልብን ይሰጠናል ፡፡ በዚያ እንድንኖር እግዚአብሄር ሚተዉብን ጊዜያት አሉ ምክንያቱም ስናድግ ማየት ስለሚፈልግ ፤ ነገር ግን ከገጠመን ከማንኛዉም ነገር ነፃ ሲያወጣን ለማየት በመፈለግ እግዚአብሄር በጣም በብዙ የሚወደን ጊዜያት አሉ ፡፡

ይህ መዝሙር በኢየሩሳሌም መንገድ ላይ በሚዘምሯቸዉ መዝሙሮች ስብስብ ላይ ይህ ወደ ላይ የመዉጣት መዝሙር ላይ ለምን ተጨምሮ እንደ ነበር ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር ያደረገላቸዉን ማስታወስ እግዚአብሄር ከእነርሱ ጎን እንደ ነበር ማስታወሻ ነበር ፡፡ ዳዊትም በዚህ መዝሙር ዉስጥ አመስጋኝነቱን አሳዬ ከዚያም ከሌሎች ከሁሉም ጋር ስለተጋራ በአንድ ላይ ማክበር ቻሉ ፡፡

እግዚአብሄር የክብር ንጉስ ስለሆነ የክብር ንጉሱን በማሳያዉ ላይ የማስቀመጥ ችሎታዉ አለን ፡፡ ተመልሳችሁ ቁጥር 1 እና 2 ላይ ተመልከቱ ፤ ዳዊት ሁሉንም ሌሎቹን በመጥራት ለዳዊት በተለዬ እና ለሕዝቡ ያደረገላቸዉን እንዲያስታዉሱ ጠየቃቸው ፡፡ ሁሉም ሰዉ የአመስጋኝነትን አመለካከት ማሳደግን እንዲያስታዉሱ ፈለገ ምክንያቱም በቀኑ መጨረሻ ላይ ሁላችንም ክብሩን የምናፀባርቅ የእግዚአብሄር ሰዎች ነን ፡፡ እግዚአብሄር የታደገብንን፣ ያዳነብንን፣ ከኛ ወገን የሆነበትን ሁሉንም መንገድ ስናስታዉስ በዙሪያችን ካሉት ከሁሉም ጋር መጋራት/መነጋገር እንችላለን ፡፡ ዳዊትም ይህን በኃይል እንዲሉት ሁሉንም ጠየቀ ፤ ወደ ዉጊያችን ዉስጥ እግዚአብሄርን ለመጣራት በኃይል /ጮኸን ስንናገር ኃይል አለ ፡፡ እግዚአብሄር ማን እንደሆነ በኃይል ስናስታዉስ ኃይል አለ ፡፡

ሮሜ (10፡ 9) “ ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሄርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ “ ይላል ፡፡ ሁላችንም እግዚአብሄር ሊያድነን እንደሚችል እናውቃለን ፤ ሁላችንም እግዚአብሄር አለምን እንደፈጠረ እናውቃለን ፤ ሁላችንም እግዚአብሄር የፈለገዉን ሁሉ ማድረግ እንደሚችል እናውቃለን - በመምጣት ለእኔ ዉጊያዬን ይዋጋል ፡፡ ነገር ግን ያ በኃይል ስንናገረው የሚመጣ ኃይል አለ ፤ እግዚአብሄር ኢየሱስ ጌታችን እንደሆነ በኃይል እንድንናገር ይጠይቀናል ፤ ለዚያ ነዉ ከእኛ ጋር ወደ ትስስር የገባው ፡፡ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በኃይል ስትናገሩ እግዚአብሄር ከሞት እንዳስነሳዉ በልባችሁ ማመናችሁን እየተናገራችሁ ነው ፡፡ በኃይል “ ኢየሱስ የህይወቴ ጌታ ነህ “ በማለት በኃይል በምትሉ ጊዜ በእናንተ ላይ የሚመጣዉን ሰላምና ኃይል ይሰማችኋል ፡፡

እንደ አማኝ ስራችን የእግዚአብሄርን ክብር መግለጥ/ማንፀባረቅ ነው ፡፡ በተግባሮቻችን ዉስጥ የእግዚአብሄርን ክብር ማንፀባረቅ እንችላለን ፤ ነገር ግን በኃይል የሚናገር የአመስጋኝ ልብ ሲኖረን ሰዎች ወደ እኛ የሚያዳምጡት የተለያዬ ኃይል አለ ፡፡ ነፃ ወጥታችሁ ከሆነ አመስጋኝ የሆናችሁበትን መንገድ በኃይል ግለፁ ፡፡ በመከራ ዉስጥ ብታልፉም ወይም እግዚአብሄር ሊያጠራችሁ በስፍራዉ የሚያስቀምጣችሁ ቢመስልም እንኳን ይህን የአመስጋኝነት ልብ ስትገልፁ ሁለት ነገሮችን ታደርጋላችሁ ፤ የመጀመሪያው ለጠላታችሁ እግዚአብሄር ከእናንተ ወገን እንደሆነና በእግዚአብሄር በኃይል ፀንታችሁ እንደተቀመጣችሁ እያወጃችሁ ነው ፡፡ ሁለተኛው በዚያ መከራ ዉስጥ ስትሄዱ ለሚያዩአችሁ ሰዎች አመስጋኞች ነን እያላችኋቸው ነው ፤ ያ ሰዎችን በህይወታችሁ ስለ እግዚአብሄር ጉጉዎች ያደርጋቸዋል - ያም በመከራ ዉስጥ ብታልፉም አመስጋኝ እንደሆናችሁ ፡፡

መደምደሚያ

በዉጊያ ላይ በምትሆኑ ጊዜ እግዚአብሄርን ጋብዙት ፤ ነፃ ከወጣችሁ በአመስጋኝ ልብ አንፀባርቁ ፤ ነፃ ላወጣችሁ ለእግዚአብሄር እንዴት አመስጋኞች እንደሆናችሁ በኃይል ስትናገሩ ለእግዚአብሄር ክብር እያመጣችሁ ነው ፡፡ የማመስገኛ ቃላቶቻችሁን ኃይል በጠላቶቻችሁ ላይ እንደ መሳሪያና ለክብር ንጉስ እንደ ምስክርነት ለመጠቀም ደፋሮች ሁኑ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. መዝሙር 124 “ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ባይሆን ኖሮ ? “ በሚለዉ ጥያቄ ይጀምራል ለጥቂት ደቂቃ በዚያ ሀረግ ላይ አሰላስሉ ፤ እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር ባይሆን ኖሮ የተለዬ ነገር ምን ይሆናል ?
  2. በመዝ (124፡ 7) በሁለተኛዉ ግማሽ ላይ ዳዊት “ ወጥመድ ተሰበረ እኛም ነፃ ወጣን “ አለ ፡፡ በህይወታችሁ ነፃነት ምን ማለት እንደ ሆነ መደነቅ አቁማችሁ ታውቃላችሁ ? በኢየሱስ ምን አይነት ነፃነት አገኛችሁ ?
  3. ዳዊት በእግዚአብሄር የታመኑት “ እንደ ጽዮን ተራራ እንደሚፀኑ “ ጠራቸዉ (መዝ 125፡ 1) ፤ ተራራ እንዴት የሚንቀሳቀስ ሊሆን ይችላል ? ኢየሱስ ስለዚያ ምን አለ (ማቴ 17፡ 20) ? እምነታችሁ እንደ ተራራ የፀና ይሆናል ? ለምን ወይም ለምን አይፀናም ?
  4. በመዝሙር (124-125) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 124:2–3

“If the LORD had not been on our side when men attacked us, then they would have swallowed us alive in their burning anger against us.”

እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነው ፡፡ እርሱ ከጎንህ ነው ፡፡ አዎን የሰማይና የምድር ፈጣሪ ረዳትህ ይሆን ዘንድ ቃልገብቷል ፡፡ እርሱ አምላክህ ነው ፡፡ እርሱ በውጊያ ውስጥ ከአንተ ጋር ነው ፡፡ እርሱ በወጀብና በእሳት ውስጥ ከአንተ ጋር ነው ፡፡ ዛሬ እርሱ ከአንተ ጋር ነው ፡፡ በቀንህ ውስጥ ቆም ብለህ አመስግነኸዋልን ? እግዚአብሔር ለማዳን ደግሞም ተግሳጽንና ምሪትን ለመስጠት ቻይ እንደሆነ እወቅ ፡፡

ከእንቅልፍህ ከተነሳህባት ደቂቃ ጀምሮ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው ፡፡ እርሱን አውራው በቀንህም ላይ ጥራው ጋብዘው ፡፡ ቆም በልና እንድህ በል “ አዎን እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ነው ፡፡ “እግዚአብሔር ውጊያውን ይዋጋልሃል ፡፡ በራስህ መታገሉንና ነገሮችን ለመፍታት መጣጣሩን አቁም ፡፡ በላይህ ላይ ይፈስ ዘንድ እግዚአብሔር የእርሱን ጥበብ ፣ ኃይልና ብርታት እንድሰጥህ ጠይቅ ፡፡ እርሱ ጠላትን ማባረር ይችላል ፤ የታመመን መፈወስ ይችላል ፡፡ እርሱ የጥርጣሬ እና የፍርኃትን መንፈስ ማስወገድ ይቻለዋል ፡፡ ዛሬ ራስህን ዝቅ በማድረግ በቀንህ ላይ እግዚአብሔርን ጥራ ፡፡

“እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ ፥ ቍጣቸውን በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር ፡፡ “ - መዝሙር 124፡2-3

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 2ኛ ሳሙኤል 5:19 — “ዳዊትም፦ ወደ ፍልስጥኤማውያን ልውጣን? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፦ ፍልስጥኤማውያንን በእርግጥ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁና ውጣ አለው ።
  • 1ኛ ዜና 10:13–14 — “እንዲሁ ሳኦል በእግዚአብሔር ላይ ስላደረገው ኃጢአት፥ የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልጠበቀ ሞተ። ደግሞም መናፍስት ጠሪ ስለ ጠየቀ እግዚአብሔርንም ስላልጠየቀ፥ ስለዚህ ገደለው፥ መንግሥቱንም ወደ እሴይ ልጅ ወደ ዳዊት አሳለፈው ። “
  • ሮሜ 8:31 — “ እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል ?