Wisdom Books Psalms

A Prayer For Jerusalem

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 122-123 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 451 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ ወደ ላይ የመዉጣት ሰዎስተኛዉ መዝሙር ስለሆነ ሰዎች ከሁሉም አገሪቱ ክፍል በመምጣት ወደ ኢየሩሳሌም እየወጡ ናቸው ፤ ይህን በአንድ አመት ዉስጥ ሰዎስት ጊዜ ያደርጉ ነበር (ዘጸ 23፡ 13-17) ፡፡ ለምን ኢየሩሳሌም (ፂዎን) ? መዝ (132፡ 13-14) ምክንያቱ እግዚአብሄር ስለመረጣት እና ቤቱ እንድትሆን ስለፈለጋት ነዉ ይላል ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (122፡ 1-2)፡ ዋይርስቤ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ቁጥሮች “ ለእግዚአብሄር ልብ ስለ መኖር “ በማለት ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ኮንስታብል እነዚህን ቁጥሮች የዳዊትን “ የአምልኮ ደስታ የሞላዉን ተስፋ “ እንደሚያሳዩ ፅፏል ፤ “ የእግዚአብሄር ቤት “ የእግዚአብሄርን የታቦት ማደሪያ በቋሚነት በዚያ የተቀመጠዉን አመልክቷል / ጠቅሷል ፡፡ ለማምለክ ወደ እግዚአብሄር መገኘት/ፊት መሄድ የዳዊት ልምድ ነበር (2 ሳሙ 12፡ 20) ፤ ዳዊት በአካላዊ ችግራቸዉ ምክንያት እና በሀገራዊ ስደት ምክንያት ወደ እግዚአብሄር ቤት መሄድ የማይችሉ ሰዎች እንዳሉ ያዉቅ ነበር (መዝ 42፡ 1-3, 137፡ 1-3) ፡፡ ከግል ልምዴ እስራኤል ደርሳችሁ ኢየሩሳሌም ስትቀርቡ የእግዚአብሄር መገኘት ኃይለኛ እንደሆነ እንደሚሰማ መናገር እችላለሁ ፡፡ ዳዊት ተደሰተ ምክንያቱም በማደሪያዉ ስፍራ እግዚአብሄርን ስላመለከ - በኢየሩሳሌም በሮች ላይ መቆም ስለቻለ (ቁጥር 2) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ በእነዚህ ቃላቶች የህፃን ልጅ የሚመስል መጓጓት እንዳለ ፤ እዉነት ወዳልሆነ የቀረበ የማደግ ሁኔታ ስሜት “ እንደሆነ ያመለክታል ፡፡

ለእስራኤል ጥሩ ልብ/መልካም አሳብ ከሌላችሁ አንዴ እንዲሰጣችሁ እግዚአብሄርን ጠይቁት ፤ ጳዉሎስ በሮሜ (15፡ 27) እንዳመለከተዉ አሕዛቦች ነን፡ “ ወደዋልና የእነርሱም ባለ ዕዳዎች ናቸው ፤ አሕዛብ በእነርሱ መንፈሳዊ ነገርን ተካፋዮች ከሆኑ በስጋዊ ነገር ደግሞ ያገለግሉአቸዉ ዘንድ ይገባቸዋልና “ ፡፡ አይሁዶችን ልንጠነቀቅላቸዉ ታዘናል ምክንያቱም አይሁድ በነበረዉ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድነትን ስለተቀበልን ፡፡

መዝሙር (122፡ 3-5)፡ ዋይርስቤ ቁጥር 3-5 “ የአመስጋኝ ልብ ስለ መኖር “ ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ቁጥር 3 ኢየሩሳሌምን “ እንደ ተገጠገጠች ከተማ “ ተገልፃለች ፡፡ ዳዊት በዉጊያ/በጦርነት ከኢያቡሳዊያን የኢያቡሳዊያንን ከተማ በመያዝ፣ ንብረቱን ወሰደ እንዲሁም መከላከያዉን እና ቅጥሩን አጠናከረ ፤ ከዚያም ዳዊት ኢየሩሳሌም ብሎ ሰየማት (2ሳሙ 5፡ 6-10) ፡፡ ከተማዋ የ12 ነገድ ለመሄድ የሚታዘዙበትና በአመት ሰዎስት ጊዜ ለእግዚአብሄር ሕዝባዊ የምስጋና አዋጅ ማድረጊያ ስፍራ ሆነ (ቁጥር 4) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ እነዚህን ጊዜያት “ በህይወታቸዉ ስለ ቸርነቱ የእግዚአብሄር ሰዎች እግዚአብሄርን እንደሚያመሰግን ፤ የድምፅ ምስጋናቸው የእንስሳት፣ የእህልና፣ የወይን እና የዘይት መስዋዕትን እንደሚይዝ “ ይገልፃል ፡፡ ኢየሩሳሌም ለአምልኮ የሕዝቡ እምብርት እና “ በእግዚአብሄር ህግ በቅርርብ የሚተሳሰሩበት” (ቁጥር 5) “ ሲቪል ፍርድ እና ዉሳኔዎች ይደረጉባት ነበር “ ፡፡ ዛሬ ሕዝቦች ለኢየሩሳሌምና ለእስራኤል ምድር ይዋጋሉ ፡፡

መዝሙር (122፡ 6-9)፡ ዋይርስቤ ቁጥር 6-9 “ የፀሎት ልብ ስለ መኖር “ ያጠቃልላቸዋል ፡፡ ቁጥር 6-7 ለኢየሩሳሌም የዳዊትን ፀሎት መዝግቧል፡ “ ለኢየሩሳሌም ሰላምን ለምኑ ፤ አንተንም ለሚወድዱ ልማት ይሁን ፡፡ በኃይልኅ ሰላም በጌጠኛ ቤትህም ልማት ይሁን “ ፤ ያ ፀሎት አሁንም የአለም ህዝቦች ከተማዋን እና የቤተ መቅደሱን ተራራ ለመቆጣጠር ሲፈልጉ ዛሬም ይቆማል ፡፡

ስለ ሰላም የዳዊት ፀሎት እንደ ጦርነት በኢየሩሳሌም ዉጊያ ከተካሄደ በኋላ ትንቢታዊ ነበር - በሳዖልና በዳዊትን በኃያላኑ ሰዎቹ መካከል (2ሳሙኤል 8)፣ የአሞናዊያን አመፅ (2ሳሙ 12፡ 26-31)፣ የአቤሴሎም አመፅ (2 ሳሙኤል 18)፣ የሳቤኤ አመፅ (2ሳሙኤል 20) እና ዳዊት በገባዖንም በተበቀለ ጊዜ ፤ እነዚህ ሁሉ በኢየሩሳሌም አልነበሩም ነገር ግን በኢየሩሳሌም ዙሪያ ኢየሩሳሌም ለመቆጣጠር ተዋግተዋቸዉ የነበሩ ናቸው ፡፡ እነዚህ ዉጊያዎች በተከፈሉት በእስራኤልና በይሁዳ መንግስት መካከል በተደረጉ ዉጊያዎች ተከተልዉ የሆኑ ዉጊያዎችም ነበሩ ፡፡ ዛሬ ዉጊያዉ ለኢየሩሳሌም ነው ፤ በመልካምና በክፉ መካከል ዉጊያዉ በኢየሩሳሌም ይረጋጋል/ያቆማል ፡፡

በምፀት ጊዜ ኢየሩሳሌም የሚለዉ ስም “ የሰላም ከተማ ማለት “ ነው ነገር ግን በአለም ላይ ከሌላ ከተማ በላይ ዉጊያ ያለበት ነው ፡፡ ዛሬ ዉጊያዉ እየሄደ ያለዉ ፡፡

  • 1947-1949፡ የእስራኤል ዉጊያ ለነፃነት በማካሄድ በ1948 እንደ ነፃ ህዝብ ማንነታቸዉንአወጁ ፡፡
  • ሰኔ 1967፡ በእስራኤል እና በግብፅ፣ በጆርዳን እና በሶሪያ መካከል የስድስት ቀን ጦርነት ተካሄደ ፤ በዚህም እስራኤል ጋዛን በመቆጣጠር የመሬት ይዞታዋን ሰዎስት እጥፍ አደረገች ፡፡
  • 1967-1970፡ እስራኤል በሲዊዝ ካናል ላይ በጦርነት ላይ ነበረች ፡፡
  • 1973፡ ግብፅ እና ሶሪያ በፆም አመት ጦርነት ላይ እስራኤልን አጠቁ ፤ ሌሎች የአረብ አገራትም ግብፅን እና ሶሪያን በገንዘብ፣ በመሳሪያ እና በወታደሮች ደገፉአቸው ፡፡
  • 1978፡ እስራኤል በፍልስጤም ነፃ አዉጪ ድርጅት ተጠቅታ ነበር ፤ እስራኤልም ሊባኖስን በመዉረር ምላሽ ሰጠች ፡፡
  • 1981-1982፡ እስራኤል በሊባኖስ የፍልስጤም ነፃ አዉጪ ድርጅት ማዘዣን በማጥቃት በእንግሊዝ በእስራኤል አምባሳደር ላይ የግድያ ሙከራ ከተደረገ በኋላ ሊባኖስን ወረረች ፡፡
  • 1987፡ ፍልስጤማዊያን በእስራኤል ላይ አመጽ አደረጉ ፡፡
  • 2000፡ ሁለተኛ ፍልስጤማዊያን በእስራኤል ላይ አመጽ አደረጉ ፡፡
  • 2006፡ እስራኤል በሊባኖስና በጋዛ አማፂዎችን ተዋጋች ፡፡
  • 2008-2009፡ እስራኤል ከሀማስ ጋር ተዋጋች ፡፡
  • 2012፡ እስራኤል ከሀማስ ጋር ተዋጋች ፡፡

መደምደሚያ

ዳዊት ስለ ኢየሩሳሌም ሰላም ፀለዬ ፤ እግዚአብሄር “ የሚባርኩህን እባርካለሁ “ ካለበት ከዘፍ (12፡ 3) የሚመስል ነው ፡፡ ለመዝሙር መፅኀፍ ሀረጋችን የክብር ንጉስ ነው ፤ በመዝሙር መፅሀፍ ዉስጥ ቃሎቹ ወደ ሚመጣዉ መሲህ እንደሚያመለክቱ እናምናለን ፡፡ የሰላም ልዑል ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣል (ኢሳ 9፡ 6) ፤ ኢየሱስን እንደ ሰላም ልዑል እንዴት ልንታመንበት እንችላለን ?

“ ሰላምን እተዉላችኋለሁ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም “ (ዮሐ 14፡ 27) ፡፡

“ አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሄር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል “ (ፊል 4፡ 7) ፡፡

“ በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ ! “ (ቆላ 3፡ 15)፡፡

“ እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሄር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ “ (ሮሜ 5፡ 1) ፡፡

ለኢየሩሳሌም ከተማ እግዚአብሄር መልካም/የሚያስብ ልብን ይሰጣችኋል !

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 338.

  2. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Study Notes: Psalms, p. 433; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 730.

  4. Wiersbe, p. 338.

  5. Nelson’s Commentary, p. 730.

  6. Nelson’s Commentary, p. 730.

  7. Wiersbe, p. 339.

ጥያቄዎች

  1. በመዝ (121፡ 1) ዳዊት “ ወደ እግዚአብሄር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ “ ደስ አለኝ አለ ፤ ወደ እግዚአብሄር መገኘት ስትገቡ በዚህ መልኩ ይሰማችኋል ? ለእናንተ “ የእግዚአብሄር ቤት “ ህንፃው መገኘቱን የሚሰማችሁበት የተለዬ ስፍራ ነዉ ወይስ ሌላ ስፍራ ነው ?
  2. ስለ ኢየሩሳሌም ሰላም ለመፀለይ ዕንደተገደዳችሁ ይሰማችኋል (መዝ 122፡ 6) ? ለምን ወይስ ለምን አልተሰማችሁም ?
  3. ዘማሪዎቹ ለእነርሱ መሀሪ/ቸር እስኪሆን (ምህረትን ወይም ሞገስን እስኪያሳያቸው) ድረስ ወደ እግዚአብሄር ተመለከቱ (መዝ 123፡ 2) ፤ እግዚአብሄር ለእኛ መሀሪ ወይም ቸር ያልሆነበት ጊዜ አለ ? መልሳችሁን አብራሩ
  4. መዝሙር (122-123) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 122:6–8

“Pray for the peace of Jerusalem: ‘May those who love you prosper; may there be peace within your walls, prosperity within your fortresses.’ Because of my brothers and friends, I will say, ‘Peace be with you.’”

ሰላም የሽብርና የብጥብጥ ተቃራኒ ነው ፡፡ በጦርነት ጊዜያት ሰዎች “ ጦርነትን ሳይሆን ሰላምን እንሻለን “ ይላሉ ፡፡ ለአንተም ህይወት ይህ እውነት ነው ፡፡ አንተም ሽብር ሳይሆን ሰላም እንድኖርህ ትሻለህ ፡፡ ልብህ ዕረፍት ፣ ደህንነት እና ፅጥታ እንድሰማው ይሻል ፡፡ አለም ዘላቂ ሰላምን ሊያስገኝም ሊያቀርብም አይችልም ፡፡ ዳዊትና ኢሳይያስ በኢየሩሳሌም ሰላም ይሆን ዘንድ ተንብየዋል ጸልየዋልም ፡፡ እናም ኢየሱስ የሰላም ልዑል ሆኖ መጣ ፡፡ የኢየሱስ ሰላም ልብህን ይቆጣጠራል ደግሞም አምሮህን ይጠብቃል ፡፡

ገደብን ፣ ፈተናን ፣ ፍርሃትን እና ሌሎችንም ስትተው ፣ ወደ ህይወትህ የክርስቶስን ሰላም ትቀበላለህ ደግሞም አዕምሮን ሁሉ የሚያልፍ ሰላም ይኖርሃል ፡፡ ስለ ግንኙነት ፣ ስለ ፈተና ፣ ስለ ህክምና ቀዶ ጥገና ወይም ስለ ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያ የሚያስጨንቅህን አሳብ ለጌታ ተወው ፡፡ ጮኸኽ እንድህ በል “ ይህን ለአንተ ትቼዋለሁ ጌታሆይ ፡፡ “ ስትተወው እናም ይህን ጭንቀት ከጌታ በሆነ ሳላም ስትተካው ፣ ጌታን ከፊትህ እንደሚቀድም እመነው ፡፡ ልብህንና አዕምሮህን እንድቆጣጠር ስትፈቅድለት ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምህ ነው ፡፡ በራስህ ብርታትና ችሎታ ላይ ሳይሆን በእርሱ ላይ ታመን ፡፡ እናም ለክርስቶስ ዳግም መምጣት ስትዘጋጅ ፣ በኢየሩሳሌም ሰላሙ ይሆን ዘንድ ጸልይ ፡፡

“ ለኢየሩሳሌም ሰላምን ለምኑ፤ አንተንም ለሚወድዱ ልማት ይሁን ። በኃይልህ ሰላም፥ በጌጠኛ ቤትህም ልማት ይሁን ። ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀሮቼም፦ በውስጥሽ ሰላም ይሁን አልሁ ። “

  • መዝሙር 122፡6-8

ተጨማሪ ጥቅስ

ኢሳይያስ 9:6 — “ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል ። “

ፊልጵስዩስ 4:7 — “ አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል ። “

ቆላስይስ 3:15 — “በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ ። “