Delight in the Journey
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 120-121 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መዝሙር (120-134) ወደ ላይ የመዉጣት/ከፍ የማለት መዝሙርን ይይዛሉ ፤ እነዚህ አይሁዶች ከተራራዉ ላይ እስከ ኢየሩሳሌም በሚሄዱበት መንገዳቸዉ ላይ ከዘመሩት ከመንገድ ጉዞ መዝሙሮች ጋር የሚመሳሰሉ ነበር ፡፡ ዳዊት አራት የከፍታ/ወደ ላይ የመዉጣት መዝሙር ፅፏል (122, 124, 131, 133)፣ ሰለሞን አንድ ፅፏል (127) እና ቀሪዉ አስሮቹ ስማቸዉ ባልታወቀ የተፃፉ ነበሩ ፤ መዝሙር 121 ማንነቱ በማይታወቅ ነበር የተፃፈው ፡፡ መዝ (120፡ 5) የዚህ ቡድን ተጓዦች ኢየሩሳሌም ለመድረስ ረጅም ጉዞ ይጓዙ እንደ ነበር ያመለክታል ፡፡
በመዉጣት/ከፍ በማለት መዝሙር ላይ ማንኛዉም ማጣቀሻን “ መመልከት “ ቤተ መቅደሱን ለማየት የተስፈኝነትን መግለጫ እንደሚሆን የሚያስገነዝብ ይሆናል (መዝ 134፡ 1-2) ፡፡ እስራኤላዊያን በአመት ዉስጥ ለበዓላት ወደ ኢየሩሳሌም ሰዎስት ጊዜ መሄድ ይጠበቅባቸዉ ነበር፡ “ በዓመት ሶስት ጊዜ በዓል ታደርግልኛለህ ፡፡ የቂጣን በዓል ጠብቅ ፤ በአቢብ ወር ከግብፅ ምድር ወጥታችኋልና በዚህ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላለህ ፤ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ ፡፡ በእርሻም የምትዘራትን የፍሬህን በኩራት የመከር በዓል ዓመቱም ሳያልቅ ፍሬህን ከእርሻ ባከማቸህ ጊዜ የመክተቻዉን በዓል ጠብቅ ፡፡ በዓመት ሶስት ጊዜ በአንተ ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በጌታ በእግዚአብሄር ፊት ይታይ “ (ዘጸ 23፡ 14-17) ፡፡ ይህ መዝሙር እግዚአብሄር የግል አምላኪዎችን እና እስራኤል እንደ አጠቃላይ በደህና እንደሚጠብቅ የማረጋገጫ ትርጉምን ያስተላልፋል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (121፡ 1-2)፡ ማክአርቱር እነዚህን ቁጥሮች እግዚአብሄር እንደ እረዳት ይገልፃቸዋል ፤ መዝሙረኛው እግዚአብሄር አምላክን ለማምለክ ወደ ኢየሩሳሌም ለረጅም ጉዞ ሲነሱ የሚያስፈልጋቸዉን ማንኛዉንም እንደሚረዳቸዉ ሙሉ እምነት ነበረው ፡፡ ሁኔታቸዉ ምንም ቢሆን እግዚአብሄር ሊረዳቸዉ ሁሉም ኃይል ነበረዉ ምክንያቱም የሰማይና የምድር ሰራተኛ እንደሆነ ስለሚያውቁ ፡፡መዝ (89፡ 11-13) “ ሰማያት የአንተ ናቸው ምድርም የአንተ ናት ፤ ዓለምንና ሞላዉም አንተ መሰረትህ ፡፡ ሰሜንና ደቡብን አንተ ፈጠርህ ፤ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል ፡፡ ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው ፤ እጅህ በረታች ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች “ ይላል (መዝ 89፡ 11-13) ፡፡
መዝሙር (121፡ 3-4)፡ ማክአርቱር መዝሙረኛዉን እግዚአብሄርን እንደ ጠባቂዉ እንዳየዉ ተመለከተ ፤ መዝ (91፡ 11-13) ተመሳሳይ ሀሳብ ገልፆአል፡ “ በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና ፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሱሃል ፡፡ በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ ፤ አንበሳዉንና ዘንዶዉን ትረግጣለህ “ ፡፡ መዝ (31፡ 8) “ በሰፊም ስፍራ እግሮቼን አቆምህ “ ይላል ፡፡
መዝሙረኛው (121፡ 5-6)፡ ማክአርቱር እግዚአብሄር እንደ ጠባቂ መገለፁን አዬ ፡፡ ኢሳ (25፡ 4) “ የጨካኞችም ቁጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ ዐዉሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ ለድሀዉ መጠጊያ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መጠጊያ ከዉሽንፍር መሸሸጊያ ከሙቀትም ጥላ ሆነሃል “ ይላል ፤ ኢሳ (49፡ 2) “ አፌንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድርጎአል በእጁ ጥላ ሰዉሮኛል ፤ እንደ ተሳለ ፍላጻም አድርጎኛል በሰገባዉም ዉስጥ ሸሽጎኛል “ ይላል ፡፡ እግዚአብሄር በሁሉም ሁኔታ ዉስጥ ሁሉንም ቀን ህዝቡን ይጠብቃል ፤ በፍፁም አንድም ቀን አይተዉም ፡፡ ይጠብቃችኋል ፡፡
መዝሙር (121፡ 7-8)፡ ማክአርቱር እግዚአብሄርን እንደ ጠባቂያችን ገልፆታል ፡፡ እግዚአብሄር ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዙ በጉዞአቸዉ ላይ ከሕዝቡ ጋር ይሆናል ነገር ግን “ አሁን እና ለዘላለም ከመምጣትና ከመሄዳቸዉ “ (ቁጥር 8) ጋር ሁሉንም ጊዜ አብሮአቸዉ እንደሚሆንም ቃል ገብቶላቸዋል ፡፡ በኢየሩሳሌም ያሉ ቤቶች ለዘዳ (6፡ 9-12) በመታዘዝ ከቤቱ በር ቋሚዎች ጋር የተጣበቀ ጥቂት የመፅኀፍ ጥቅል ሙዝሀዎች አሉት፡ “ በቤትህም መቃኖች በዳጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው ፡፡ አምላክህ እግዚአብሄር ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ባገባህ ጊዜ ፤ ያልሰራኃቸዉም ታላቅና መልካም ከተሞች ፤ ያልሞላሃቸዉንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች ያልማስሃቸዉንም ወይንና ወይራ በሰጠህ ጊዜ በበላህና በጠገብህም ጊዜ ፤ በዚያን ጊዜ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን እግዚአብሄርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ “ ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤልን ይደግፋል ነገር ግን ለእነርሱ እግዚአብሄር አድርጎላቸዉ የነበረው ሁሉ አዉቀዉ ራሳቸዉን ያነቃሉ ፡፡ ዘዳ (11፡ 20-21) “ እርስዋንም እንዲሰጣቸው እግዚአብሄር ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር እንደ ሰማይ ዘመን በምድር ላይ ዘመናችሁ የልጆቻችሁም ዘመን ይረዝም ዘንድ በቤትህ መቃኖችና በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው “ ይላል ፡፡ የእግዚአብሄር ቃል ሕዝቡ ለሚያስፈልጋቸዉ ሁሉም ነገር ነበር ፡፡
መደምደሚያ
ስቴቨን ኮል ስለ እግዚአብሄር የጥበቃ/የመከላከል እጅ አራት እዉነታዎችን አስቀምጧል፡
- ንፁህ ህሊና ካለን ሀሜተኞች ወይም የሌሎች ተቃዉሞች እያሉ እግዚአብሄር ለእኛ እንደሆነ ማወቅ እንችላለን ፡፡ “ እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን ? እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል ? ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም ? እግዚአብሄር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል ? የሚያጸድቅ እግዚአብሄር ነው የሚኮንንስ ማን ነው ? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሄር ቀኝ ያለዉ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልድው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው “ (ሮሜ 8፡ 31-34) ፡፡ የእግዚአብሄርን ጥበቃ ለመረዳት ወደ እግዚአብሄር በንፁኅ ፅላት መምጣት አለብን ፡፡
- የእግዚአብሄርን ሉዓላዊነት ካወቅን በአላማዉ መሰረት እንደሚከላከልልንና እንደሚጠብቀን እርሱን መታመን እንችላለን ፡፡
- በመስቀሉ ላይ በግላችን ምህረቱን ከተቀበልን ሁሉንም ችግሮች እንዴትም ቢያስፈራሩ ችግር እንደሌላቸዉ የእግዚአብሄርን ምህረት ለማዉራት እንደ እድል እናያቸዋለን ፡፡ “ ወንድሞች ሆይ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግስትን እንዲያደርግላችሁ አዉቃችሁ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት ፤ ትዕግስትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሉዓን ትሆኑ ዘንድ ስራዉን ይፈጽም “ (ያዕ 1፡ 2-4) ፡፡ የእግዚአብሄርን ጥበቃ በምናዉቅ ጊዜ እግዚአብሄር በብዙ እርሱን እንድንመስል ለማድረግ ነገሮችን እንድንቀምሳቸዉ እንደሚፈቅድልን እንረዳለን ፡፡
- ለእኛ ህይወቱን ዝቅ አድርጎ ያስቀመጠዉን አዳኛችንን ስንከተል ለእርሱ መሰጠታችንን ዋጋዊን ለመክፈል ዝግጁና ፍቃደኞች መሆን አለብን ፡፡
እግዚአብሄር ሉዓላዊ እንደሆነ ለማወቅ ወደ ግብዣዉ/ገበታው በንፁኅ ህሊና፣ በንፁህ አይምሮ መምጣት ያስፈልገኛል ፤ እግዚአብሄር ሁሉም በቁጥጥሩ ነው ፡፡ ሁኔታዉ ታላቅ ባይሆንም እንኳን ሁሉም ነገር በብዙ እርሱን እንድመስል ለማድረግ እድል ነው ፡፡ ሌሎች እርሱን እንዲያዩ ህይወቴን ለመሰዋት ፍቃደኛ ነኝ ? ምንም ይሁን እግዚአብሄር ኋላችሁን ስላገኘው በማወቅ መንገድ ላይ የሚዘመር የመንገድ ጉዞ ነው ፡፡
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 682.
MacArthur, p. 682.
MacArthur, p. 682.
MacArthur, p. 682.
MacArthur, p. 682.
Steven Cole, “Lesson 65: God’s Protective Hand (Acts 25:1–12),” www.bible.org; accessed at https://bible.org/seriespage/lesson-65-god-s-protective-hand-acts-251-12.
ጥያቄዎች
-
መዝ (120፡ 1) አንብቡ ፤ ብዙጊዜ ወደ እግዚአብሄር በመጮህ መልስ እስከማዳመጥ ድረስ ችግር ዉስጥ እስክትገቡ ትጠብቃላችሁ ? ወይስ ሁል ጊዜ የእርሱን ድምፅ ለመስማት ጊዜ ትወስዳላችሁ ? ያ ምን ይመስላል ?
-
በመዝ (120፡ 7) ልክ እንደ መዝሙረኛው ሰላምን ፈልጋችሁ ነገር ግን በዙሪያችሁ ያሉት እንዳልተስማሙ ተሰምቷችሁ ያውቃል ? ያን ሁኔታ ለመቆጣጠር ምርጡ መንገድ ምን እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
-
እግዚአብሄር እንደማይተኛም እንደማያንቀላፋም በማወቅ እንዴት ምቾት ልታገኙ ትችላላችሁ ? (መዝ 121፡ 3-4)
-
“ እግዚአብሄር በቀኝ አጃችሁ ላይ ጥላችሁ ነው “ ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? (መዝ 91፡ 1-2, 121፡ 5)
-
የመዝሙር 121 ፀሀፊ “ እግዚአብሄር ከክፉ(ከሚጎዳ) ሁሉ ይጠብቅሀል “ ይላል ፤ ክፉ ወይም አስፈሪ ነገር በአማኞች ላይ ለምን እንደሚሆን እንዴት ትገልፁታላችሁ ? (መዝ 34፡ 17-19)
-
በመዝሙር (120-121) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 121:1–2
“I lift my eyes toward the mountains. Where will my help come from? My help comes from the LORD, the Maker of heaven and earth.”
በጉዞ ላይ የነበርክበትን ጊዜ አስብ ልክ ፡- የመንገድ ጉዞ ፣ የተራራ መውጣት ጉዞ ወይም የባህር ማዶ ተልዕኮ ጉዞ ፡፡ ምናልባትም በሆነ የህይወት አጋጣሚ ውስጥም አልፈህ ይሆናል ልክ ፡- ህመም ፣ የጉርምስና መጀመሪያ አመታት ፣ ስራ ማጣት ፣ አስቸጋሪ ከሆነ ወዳጅነት መላቀቅ ወይም ስለ ሚወዱትን ሰው ሞት ማዘን ፡፡ ጉዞ የሚለውን ቃል ስትሰማ ወደ ጭንቅላትህ የሚመጣው ምንም ይሁን ነገር ግን እግዚአብሔር እስራኤላውያን ወደ ኢየሩሳሌም ባደረጉት ጉዞ አብሮአቸው እንደነበር ሁሉ ከአንተም ጋር እንደሆነ አድርገህ አስብ ፡፡
እግዚአብሔር ረዳትህ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ጋሻህ ነው ፡፡ እግዚአብሔር መሸሸጊያህ ነው ፡፡ የሰማይና የምድር ፈጣሪ ያውቅሃል ፡፡ እርሱ ከአንተ ጋር ይሄዳል ፡፡ ዛሬ ከፊትህ ያለው ምንም አይነት ጉዞ ይሁን ፣ አይኖችህን ወደ ኢየሱስ አንሳ ፡፡ ብቻህን አይደለህም ፡፡ ቀንና ማታ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው ፤ ምክንያቱም የሚጠብቅህ እግዚአብሔር አምላክ አይተኛም ! እርሱ ከፊትህ ያለውን ጊዜ እንድሁም ዘላለምህን ይጠብቃል ፡፡ ዉዱ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ፣ አይኖችህን አንሳ ፡፡ በዛሬው ጉዞህ ላይ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው !
“ ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ ? ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው ። “ - መዝሙር 121፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 121:3–4 — “ እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም ። እግርህን ለመናወጥ አይሰጠውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም ። “
- ኢሳይያስ 41:10 — “ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ ። “
- ኤርምያስ 29:11 — “ ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።