Wisdom Books Psalms

Delight in God's Word

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 119 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 449 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙር 119 አዝናኝ መዝሙር ነው ፡፡ መቼም ቢሆን በመንገድ ላይ አንድ መዝሙር ስጠቅስ ሁልጊዜ መዝሙር 119 ነዉ የሚሆነው ፡፡ መዝ (119፡ 105) ከምወዳቸዉ ጥቅሶች ዉስጥ አንዱ ነው፡ “ ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው “ ፤ ይህ በህይወት ዉስጥ እየሄደ ስላለዉ ነገር መልስ ነው ፡፡ ቃሉን ማጥናት ቀጣዩን እርምጃ ይሰጣችኋል - ለመንገዳችሁ ብርሃንን ይሰጣችኋል ፡፡ ቁጥር 105 የጠቅላላ መዝሙሩ ማጠቃለያ ነው ፤ ፀሀፊዉ አይታወቅም ነገር ግን መዝሙሩ በመገደድ ስር ሆኖ የተፃፈ እንደ ነበር ይታወቃል (ቁጥር 42, 134, 153) ፡፡ በመዝሙሩ ዉስጥ ወደ ዚህ የመገደድ ስሜት የሚያመለክቱ ብዙ ጥቅሶች አሉ ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (119፡ 1-76)፡ መዝሙሩ እንደ ተመሳሳይ ቃል/ትርጉም የተፃፈ ነበር ፤ እያንዳንዳቸዉ ስምንት መስመሮች 22 ክፍሎች አሉት ፤ ሁሉም የመጀመሪያዎቹ ስምንት መስመሮች በዕብራዊ ቅደም ተከተል በመጀመሪያ ፊደል ይጀምራሉ ፤ ከዚያም እያንዳንዱ ክፍል በዕብራዊያን ቅደም ተከተል ይከተላል ፡፡ እነዚህን ክፍሎች ቶማስ ኮንስታብል እንደሚከተለዉ ይከፋፍላቸዋል፡

  1. የእግዚአብሄርን ቃል የመታዘዝ በረከቶች (ቁጥር 1-8) ፡፡
  2. የእግዚአብሄር ቃል የማንፃት ኃይል (ቁጥር 9-16) ፡፡
  3. ለእግዚአብሄር ቃል አድናቆት (ቁጥር 17-24) ፡፡
  4. ለታላቅ ማስታዋለ/መረዳት መፀለይ (ቁጥር 25-32) ፡፡
  5. ለእግዚአብሄር ቃል ትክክለኛ መሰጠት (ቁጥር 33-40) ፡፡
  6. የእግዚአብሄር ቃልና ማዳን (ቁጥር 41-48) ፡፡
  7. የእግዚአብሄር ቃል እንደ ተስፋ ምንጭ (ቁጥር 49-56) ፡፡
  8. ለእግዚአብሄር ቃል ኃይለኛ መሰጠት/መታዘዝ (ቁጥር 57-64) ፡፡
  9. በእግዚአብሄር ቃል ልበ ሙሉነት (ቁጥር 65-72) ፡፡
  10. የእግዚአብሄር ቃል እንደ ተስፋ አላማ/ግብ (ቁጥር 73-80) ፡፡
  11. የእግዚአብሄር ቃል አስተማማኝነት (ቁጥር 81-88) ፡፡
  12. የእግዚአብሄር ቃል ዘላቂነት (ቁጥር 89-96) ፡፡
  13. የእግዚአብሄር ቃል ጣፋጭነት (ቁጥር 97-104) ፡፡
  14. የእግዚአብሄር ቃል የሚሰጠው ብርሃን (ቁጥር 105-112) ፡፡
  15. የእግዚአብሄር ቃል የሚያነሳሳዉ አምልኮ (ቁጥር 113-120) ፡፡
  16. የእግዚአብሄርን ቃል የሚጠብቁት ነፃ መዉጣት (ቁጥር 121-128) ፡፡
  17. የእግዚአብሄር ቃል ድንቅ ስራ (ቁጥር 129-136) ፡፡
  18. የእግዚአብሄር ቃል የፅድቅ ባህሪይ (ቁጥር 137-144) ፡፡
  19. የእግዚአብሄር ቃል እዉነት (ቁጥር 145-152) ፡፡
  20. ለእግዚአብሄር ቃል ያለ ፍቅር (ቁጥር 153-160) ፡፡
  21. በእግዚአብሄር ቃል መደሰት (ቁጥር 161-168) ፡፡
  22. በእግዚአብሄር ቃል መዳን (ቁጥር 169-176) ፡፡

መፅሀፍ “ ቃል ስጋ ሆነ “ ስለሚል እነዚህ ሁሉ ወደ መጨረሻዉ የክብር ንጉስ ኢየሱስ ያመለክታሉ (ዮሐ 1፡ 1, 14) ፡፡

በመዝሙሩ ዉስጥ ለእግዚአብሄር ቃል እንደ ተመሳሳይ ስምንት ቃላቶች ጥቅም ላይ ዉለዋል፡ ህጉ (አምስት ጊዜ ተጠቅሟል)፣ ምስክርነት (23 ጊዜ ተጠቅሟል)፣ ትዕዛዝ (21 ጊዜ ተጠቅሟል)፣ መመሪያ (21 ጊዜ ተጠቅሟል)፣ ኦሪት (22 ጊዜ ተጠቅሟል)፣ ፍርድ (19 ጊዜ ተጠቅሟል)፣ ቃል (39 ጊዜ ተጠቅሟል) እና ሕግጋት (23 ጊዜ ተጠቅሟል) ፡፡

ዋይርስቤ የእግዚአብሄርን ቃል ያልተቀበሉ ሰዎስት አይነት ሰዎችን ያመለክታል፡

ላልዳኑ ኃጢዓተኞች ህጉ ጠላታቸዉ ነዉ ምክንያቱም ፍርዳቸዉን ስለሚያሳዉቃቸዉ እና ሊያድናቸዉ ስለማይችል፡፡ ለህጋዊ/ቀኖናዊ/ስርዓታዊ አማኞች ህጉ ነፃነታቸዉን የሚያለብሳቸዉ ጌታቸዉ ነው ፤ ነገር ግን መንፈሳዊ ባለዓዕምሮ ለሆኑ አማኞች ህጉ የእግዚአብሄርን ባህሪይ እና የክርስቶስን ስራ እንዲያዩ የሚረዳ አገልጋይ ነው ፡፡

መደምደሚያ

የእግዚአብሄር ቃል ለእኛ ምን ያደርጋል ? ዋይርስቤ የሚያመለክተው፡

የእግዚአብሄር ቃል የተሰጠ ህይወት ባላቸዉ አማኞች ብዙ አስደናቂ አገልግሎቶቹን ያደርጋል ፡፡ ንፁህ ያደርገናል፣ ደስታን ይሰጠናል፣ ይመራናል፣ ጥቅሞችንም ይመሰረትልናል ፡፡ ቃሉ በሚገባ እንድንፀልይ ይረዳናል እንዲሁም ተስፋ፣ ሰላምና እና ነፃነት ይሰጠናል ፤ ቃሉን መዉደድ ወደ ህይወታችን የእግዚአብሄርን አላማ እንድናገኝና እንድንፈፅመዉ የሚረዱ እና ለምስክርነት የሚያበረቱንን ምርጥ ወዳጆች ያመጣልናል ፡፡ “ ምስኪን “ እንደሆንን በምናስብ ጊዜ ቃሉ በማነቃቃት መልሶ በእግራችን ላይ ያቆመናል ፡፡

ወደ እግዚአብሄር ቃል በምንሄድ ጊዜ ወደ እኛ አዲስ ህይወትን ይናገራል ፤ ይሁን እንጂ መዝሙረኛዉ መዝሙር 119፡ “ እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ ፤ ትዕዛዛትህን አልረሳሁምና ባሪያህን ፈልገው “ በሚለዉ ንግግር ያበቃል (ቁጥር 176) ፡፡ ስለ እግዚአብሄር ቃል የሚያዉቃቸዉ ሁሉ እያሉና ለመከተል ቢፈልግም መዝሙረኛው አሁንም ኃጢዓተኛ እንደሆነ እዉቅና ሰጠ ፡፡ እግዚአብሄር ለእግራችን እንደ መብራትና ለመንገዳችን እንደ ብርኃን ያስፈልገናል ፡፡

  1. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 680.

  2. Thomas Constable, Dr. Constable’s Bible Expository Study Notes: Psalms, pp. 412-432; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.

  3. Constable, pp. 409–410.

  4. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 310.

  5. Wiersbe, p. 311.

ጥያቄዎች

  1. መዝ (119፡ 11) “ አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ ሰወርሁ “ ይላል ፤ ጥቂት እትሞች “ ያዘ/ሰወርሁ “ በሚለዉ ፋንታ “ ደበቅሁ “ ይላሉ ፤ በልባችሁ የሆነ ነገርን እንዴት ትደብቃላችሁ/ትሰዉራላችሁ (ዘዳ 6፡ 4-8) ? በእግዚአብሄር ላይ ኃጢዓት እንዳትሰሩ የእግዚአብሄርን ቃል በልባችሁ እንዴት መደበቅ/መሰወር ትችላላችሁ ?
  2. በመዝ (119፡ 37) እንድታደርጉት የሚላችሁን ለማድረግ ለእናንተ እንዴት ቀላል ነው ? ከንቱ ወይም ዋጋ የሌለዉ ነገር በእግዚአብሄር ላይ ከመታመን እንዴት ሊወስዳችሁ ይችላል ? ከእርሱ ጋር ግንኙነታችሁ እንዴት ነው ? (ምሳ 11፡ 2, 16፡ 18, 29፡ 23, ያዕ 4፡ 1-4)
  3. በመዝ (119፡ 45) እንደሚለው የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ በመፈለግ በመብት ወይም በነፃነት እንዴት ልንጓዝ እንችላለን (ዮሐ 1፡ 14፣ 8፡ 36) ? የእግዚአብሄር ህግ ከሰዉ ህግ እንዴት ይነፃፀራል /ይወዳደራል ? (መዝ 19፡ 7)
  4. ዛሬ በመዝ (119፡ 73) ላይ “ እጆችህ ሰሩኝ አበጃጁኝም “ ብሎ ከተፃፈው አለም የተለዬ ምን ታስተምራለች (ዘፍ 1፡ 26-27, ኤር 1፡ 5) ? የአለም እይታ እንዴት አደገኛ ሊሆን ይችላል ?
  5. በጣም የሚታወቀዉ የመፅሀፍ ጥቅስ መዝ (119፡ 105) ነው “ ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው “ ፤ ይህ ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? በህይወታችሁ ይህ ጥቅስ በትክክል የሆነበትን / የቆመበትን የተለዬ ሁኔታ ወይም ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ?
  6. መዝ (119፡ 130) “ የቃልህ ፍቺ ያበራል ሕፃናትንም አስተዋዮች ያደርጋል “ ይላል ፤ አስተዋዮቹ/ቀላሎቹ እነማን ናቸው ? አንዳንድ ጊዜ ለአስተዋዮች የእግዚአብሄርን ቃል ለማስታዋል ለምን ቀላል እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ? (ኢሳ 55፡ 9, ሉቃ 18፡ 16-17)
  7. በመዝ (119፡ 165) መሰረት የእግዚአብሄርን ሕግ የሚወዱ ታላቅ ሰላም እንደሚኖራቸዉ ይገልፃል ፤ በራሳችሁ ህይወት ይህ አዉነት ሆኖ አግኝታችሁታል ? በሌሎች ሰዎች ህይወትስ ? የትኛዉ የእግዚአብሄር ሕግ ክፍል ከብዙዎች ጋር ይታገላል ? እግዚአብሄር ብዙ ሰላም እንዲሰጣችሁ ያ ይማርካችኋል ?
  8. በመዝሙር 119 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 119:105

“Your word is a lamp for my feet and a light on my path.”

እስኪ ደቂቃ ውሰድና እራስህን በማታውቀው መንገድ ላይ እየተጓዝክ እንደሆነ አድርገህ ሳል ፡፡ መቼ ወይም የት ቦታ ላይ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ላይ መታጠፍ እንዳለብህ ወይም መቼ ላፍታ ያክል እንደምትቆም አታውቅም ፡፡ ጨለማ ነው ፡፡ ነገር ግን እንደ አድል ሆኖ በፊትህ ያለውን መንገድ ለማብራትና እግሮችህን ለመምራት ፣ መብራት አለህ ፡፡ ሆኖም ግን ሊያበራልህ የሚችለው እስከ ቀጣዩ እርምጃህ ያለውን ርቀት ስለሆነ በየጊዜው አንድ እርምጃ እንድትራመድ ያስገድድሃል ፡፡

መብራቱ የእግዚአብሔርን ቃል ይወክላል ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በጨለማው ላይ ብርሃንን ያደርጋል ፡፡ ቃሉ የህይወት መንገድህን ይገልጥልሃል ፡፡ ምናልባት የአምስት አመት እቅድህን ወይም ደግሞ የእያንዳንዷን እርምጃ ገፅታ ላይገልፅ ይችላል ፤ ነገር ግን ቀጣይ እርምጃህን ይገልጥልሃል ፡፡ ቃሉ ይመራሃል ፣ ያግዝሃል ደግሞም ይሸፍንሃል ፡፡ ቃሉ በአፍህ ከማር ይልቅ ይጣፍጣል ፤ ተስፋንና እውቀትንም ይሰጥሃል ፡፡ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ምንድን ነው የምታደርገው ? እሁድ ጠዋት ብቻ ነው ቃሉን የምታነበው እናም በዚያች ሰዓት ብቻ ስላሰብከው የሳምንቱን እርምጃህን ይመራሃልን ? እንደዛ አይደለም እግዚአብሔር የሚፈልገው ፡፡ የእርሱ ፍለጋ ቃሉን በየቀኑ እንድትገልጥ ነው ፡፡ አዎን ፣ በየቀኑ ፡፡ በጉዞህ መንገድህን በየቀኑ ያበራልሃል ፡፡ ዛሬ መጽሀፍ ቅዱስህን ግለጥና ቃሉን አንብብ ፡፡

“ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው ። “ - መዝሙር 119፡105

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 16:11 — “ የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ ። “
  • መዝሙር 119:103–104 — “ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው፤ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ ። ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ፤ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ ። “
  • ዮሐንስ 1:1 ፤ 1፡14 — “ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ……… ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን ። “