Affection For The Lord
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 116-118 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ ወደ መዝሙር 116 እንገባለን ፡፡ ከመጀመራችን በፊት ስለሌሎቹ ሁለት መዝሙሮች ጥቂት ጣዕሞች/ነገሮች አሉ ፤ መዝሙር 117 ሁለት ቁጥሮች ብቻ ያሉት እና የመፅኀፍ ቅዱስ አጭሩ ምዕራፍ ነው ፡፡ መዝሙር 118 ከአጭሩ መዝሙር በመቀጠል እና ከረጅሙ መዝሙር 119 በፊት ወዲያዉኑ የሚመጣ ነው ፡፡ ስለ መዝሙር 116 የተለየዉ ነገር ከዚያ የሚመጣዉ ለእግዚአብሄር ያለዉ ፍቅር ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከመታወቅ የሚበልጥ ፍቅር ለእግዚአብሄር ያላቸዉን ሰዎች እናገኛለን ፤ በእዉነት ከእግዚአብሄር ጋር የተገናኘ ልብ አላቸው ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (116፡ 1-2)፡ መዝሙረኛው እግዚአብሄር ልመናዉን ስለሰማው እግዚአብሄርን እወደዋለሁ አለ (ቁጥር 1) ፤ ይህ ኪዳናዊ ፍቅር ነው ፡፡ የምንለዉን ለመስማት የተፅዕኖ ሰዎች ለመስማት በሚፈልጉ ጊዜ እንወደዋለን - እዚህ ጋር መዝሙረኛዉ እንደገለፀዉ ማለት ነው ፡፡ ያስደንቃል ! የአለም ፈጣሪ ሁሉጊዜ ወደ እርሱ በምንጣራ ጊዜ ድምፃችንን ይሰማናል ፤ እግዚአብሄር ጆሮቹን ወደ እኛ ያዘነብላል - ከእኛ መስማትን ይፈልጋል ወደ እኛ በማዳመጥም ይደሰታል ፡፡
በዮሐ (10፡ 27) ኢየሱስ “ በጎቼ ድምፄን በመስማት ይከተሉኛል “ አለ ፤ ነገር ግን በዚህ ጥቅስ ላይ ኢየሱስ “ አዉቃቸዋለሁ “ እንዳለም እንዳትረሱ ፡፡ እግዚአብሄር እንዴት ድምፃችሁን እንደሚያዉቀዉ አስቡ - ድምፃችሁ ምን እንደሚመስል በትክክል ያውቀዋል ፤ ምክንያቱም የንግግራችንን ድምፅ ስለሚያዉቅ ለእኛ ፍቅር ስላለዉ ፡፡ በ 1ዮሐ (5፡ 14) ሐዋሪያዉ ዮሐንስ “ እንደ ፍቃዱ አንዳች ብንለምን እንደሚሰማን “ አረጋግጦልናል ፡፡ በመዝ (116፡ 1-2) ምስጋና የፍቅር መሰረት እንደሆነ ሀሳቡን እናያለን ፡፡
መዝሙር (116፡ 3-11)፡ ከሞት ነፃ መዉጣታችንን እናያለን ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ምን ያክል እግዚአብሄርን በጥልቀት በሚወዱት እና ነፃ በወጡበት መካከል ግንኙነት ሊኖር ይችላል ? በቁጥር 3 ወጥመድ አንድን እንሰሳ ለመያዝ የሚጠቅም እናንተን የሚያደናብር ነገር ነው ፡፡ መዝሙረኛው ሞት እርሱን እንደከበበው ወይም በዙሪያዉ እንደሸፈነው ተናገረ ፡፡ “ ጣር “ መዝሙረኛዉ “ ሲዖል “ ወይም “ ሞት “ በእርሱ ላይ በወደቀበት ጊዜ የተሰማው ድንገተኛ ወይም አደገኛ ስሜታዊ ህመም እንደ ሆነ ይገለፃል (ቁጥር 3) ፡፡ በዚህ ችግር መካከል ላይ መዝሙረኛዉ እግዚአብሄርን ተጣራ (ቁጥር 4) ፡፡
መዝሙረኛው የእግዚአብሄርን ቸርነትና ምህረትን ገለፀ (ቁጥር 5) ምክንያቱም በችግራችን ዉስጥ ስለሚያገኘን ፡፡ እግዚአብሄር አያዳላም ወይም ወደ ሰራችሁት ስራ ለማየት አይመለከትም - በቀላሉ በሚያስፈልጋችሁ መካከል ላይ ያገኛችኋል ፡፡ ጭንቀታችሁን በመስማት ይመልስላችኋል (ቁጥር 6) ፡፡ መዝሙረኛው ከሞት ነፃ ያወጣዉን (ቁጥር 8) የእግዚአብሄርን ቸርነት ስላመሰገነ (ቁጥር 8) በሕያዉ አገር ከእግዚአብሄር ጋር መጓዝ ይችላል (ቁጥር 9) ፡፡ በቀደመዉ ቁጥሮች ላይ መዝሙረኛዉ ወደ ሞት በጣም ቀርቦ እንደነበርና የሞት ጣር ከብቦት እንደነበር ያስታዉሳሉ ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ከሞት ወደ ህያዉ አገር ሳበው ፡፡ በህያዉ ምድር/አገር ላይ ከኢየሱስ ጋር መጓዝን እናገኛለን ፤ በሰማይ ከእርሱ ጋር እንጓዛለን ፤ ይህ ወደ አይምሮ የሮሜ (6፡ 23) “ የኃጢዓት ደሞዝ ሞት ነዉና ፤ የእግዚአብሄር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ህይወት ነው “ የሚለዉን ቃል ያመጣል ፡፡ ከሞት ብቻ አይደለም የዳነው ከእግዚአብሄርና ከኢየሱስ ጋር እንጓዛለንም እንጂ ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር በሰማይ ስለመኖር ማሰብ ስለ እግዚአብሄር ምላሻችንን ይቀይረዋል ፡፡
ከእግዚአብሄር ጋር የጠለቀ ግንኙነት ሲኖረን ጭንቀታችንን በመስማት ከሚያጠቃን ነገር ያድነናል (ቁጥር 10) ፡፡ ለእርሱ የምንለዉን ነገር ሁሉ ይሰማል፣ ባዘነበለ ጆሮ ያደምጠዋል ፤ ለእኛ ባለዉ ፍቅር ምክንያት የምንጠይቀዉን ሁሉ ሊያደርግልን ይፈልጋል ፡፡
መዝሙር (116፡ 12-19)፡ በእነዚህ ሁሉ ዉጤቶች ለማመስገን የተሰጠን ነን ፡፡ መዝሙረኛው “ ስላደረገለት ሁሉ “ ለእግዚአብሄር እንዴት “ እንደሚመልስ “ ተጨነቀ (ቁጥር 12) ፡፡ ምስጋናዎቻችን ምንድን ናቸው ? ኃጢዓታችንን ከእኛ በመዉሰድ ከጉድጓድ አነሳን ፡፡ በዚህ ምድር ላይ ስንኖር በሰማይ ላይ ከእግዚአብሄር ጋር መኖርን እናገኛለን ፤ እንዲሁም ደግሞ በትንሳኤ ኃይል መጓዝን እናገኛለን - በዉስጣችን በሚገኘዉ መንፈስ ቅዱስ ፤ ይህ ጉዞአችንን በማጠንከር ሌሎች ሰዎችን እንድናገለግል ይፈቅድልናል ፡፡ በምንፈለገዉ በማንኛዉም ጊዜ ከእግዚአብሄር ጋር ማዉራትን እናገኛለን ምክንያቱም ድምፃችንን ስለሚያዉቅ ጆሮዎቹን ወደ እኛ ስለሚያዘነብል ፡፡ ከዚያም መዝሙረኛው “ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስዕለቴን ለእግዚአብሄር እፈጽማለሁ “ ብሏል (ቁጥር 14) ፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ያደረገልንን ለእነርሱም ፍቅሩን እንደሚቀምሱት ተስፋ በማድረግ ከሌሎች ጋር መነጋገር/ማካፈል እንችላለን ፡፡
የቅዱሳንን ሞት ለምን እግዚአብሄር እንደ ከበረ ይመለከተዋል (ቁጥር 15) ? አዲሱ ኪንግ ጀምስ የጥናት ፅሁፍ “ እግዚአብሄርን በማገልገል በሞት /እንደ ሞቱ የተቆጠሩ ለእግዚአብሄር የከበሩና የዳኑ ናቸው ፤ ከአካላዊ ሞት ባያመልጡም እንኳን የዘላለም ህይወት ይኖራቸዋል/ይቀምሳሉ “ ይላል ፡፡ አንዴ ከዳንን የእግዚአብሄር ስራን እያደረግን ነው - ጥቂት ወይም ብዙ እያደረግን ይሆናል - ስለዚህ በእርሱ ፊት የከበርን ነን ፡፡ አንዱ ሌላ ነገር በዚህ ሀሳብ ዉስጥ ልናነበዉ የምንችለዉ ስለ ራስ መሞት ነው ፤ ስለ ራሳችን ስንሞት እግዚአብሄር በእኛ ዉስጥ እንዲሰራ እንፈቅድለታለን ፡፡ ራሳችንን መካድ ስንቀጥል በማሻሻል፣ እንዲያሳድግ ወደ እግዚአብሄር በይበልጥ የቀረበ እንዲሆን እግዚአብሄርን ይፈቅድለታል ፡፡
አገልጋዩ ራሱን ከባርነቱ “ ለቅቆት “ እንደ ነበር እግዚአብሄር አገልጋይ አወጀ (ቁጥር 16) ፡፡ እግዚአብሄር መዝሙረኛውን ከሞትና በባርነት ዉስጥ ሊያቆየዉ ከሚፈልግ ማንኛዉም ነገር ነፃ አዉጥቶት ነበር ፡፡ ኢየሱስ እግራቸዉን ባጠበ ጊዜ በሰገነቱ ላይ በደቀ መዛሙርቱ ላይ ይህን አሳይቷል ፤ የአገልጋይነት አሳብ ኢየሱስ ለእነርሱ ያሳየው አንዱ የመጨረሻዎ ነገር ነበር ፡፡ እንደ አማኝ ኢየሱስንና ሌሎችን እናገለግላለን ፡፡
መዝሙረኛው “ ለእግዚአብሄር የምስጋና መስዋዕት እሰዋለሁ “ አለ (ቁጥር 17) እንዲሁም ለእግዚአብሄር ስዕለቱን ለመፈፀም ፍላጎቶን/ሀሳቡን ደገመ (ቁጥር 18) ፡፡ ለሌሎች እግዚአብሄር ለእናንተ ያደረገላችሁን ከመናገር በላይ ሌላ ታላቅ ምስክርነት ምንድን ነው ? መዝሙረኛውም እግዚአብሄርን ለማመስገን በመጨረሻ ጥሪዎ አጠቃለለ (ቁጥር 19) ፡፡ ጆሮአችንን ወደ እግዚአብሄር ማዘንበል አለብን ምክንያቱም እግዚአብሄር ለኛ የሚለን ብዙ ስላለው ፤ ወደ ኑሮአችን ዉስጥ የሚናገረዉ ብዙ እዉነቶች አሉት ፡፡ እግዚአብሄር እንድንካፈለዉ የሚፈልገዉ ብዙ ድርጊቶች እና እንድናገለግላቸዉ የሚፈልጋቸዉ ብዙ ሰዎች አሉት ፡፡ ጆሮአችንን ወደ እርሱ ለማዘንበል/ለማደማጥ ጊዜ ስንወስድ በህይወታችን ላይ ሲንቀሳቀስ እናየዋለን ፡፡
መደምደሚያ
ከእግዚአብሄር ጋር በጣም የቀረበ ግንኙነት አለን ምክንያቱም፡ 1) ከእርሱ ጋር በኪዳን ትስስር ዉስጥ ነን፣ 2) ምክንያቱም ስለሚሰማን እና 3) ምክንያቱም ስለምንሰማዉ ፡፡ ስለዚህ ከእግዚአብሄር ጋር በግንኙነታችን ብዙ ፍቅር እንዴት አድርገን እናመጣለን ? ለእርሱ ባለን ፍቅር እና እርሱ ለእኛ ባለዉ ፍቅር ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡ በህይወታችሁ ያደረገልችሁን በመዝገባችሁ ላይ ጠብቁ ፤ ከምን ነፃ እንዳወጣችሁ - ከሞት ብቻ አይደለም ነፃ ያወጣን ከሌላ ከምን ነገርስ አዉጥቶናል ? እርሱን ለማመስገን እና በሕዝቦቹ መካከል ምስክርነትን ለመስጠት የተሰጠን እንሁን ምክንያቱም በሰማይ ላይ ወደ እርሱ መመለሳችንን በጭንቀት እየጠበቀ ስለሆነ ፡፡
ጥያቄዎች
-
በመዝሙር 118 የመክፈቻ እና የመዝጊያዉ ጥቅስ በ 1ዜና (16፡ 34)፣ 2 ዜና (5፡ 13)፣ 7፡ 3 እና መዝ (106፡ 1፣ 107፡ 1 እና 136፡ 1) ላይ የሚገኙ ናቸው ፤ እነዚህ ጥቅሶች ለእስራኤላዊያን አስፈላጊ ትርጉሞችን እንደያዙ ታስባላችሁ ? እግዚአብሄር መልካም እንደሆነ መሰረታዊ እምነታችሁ ነው ? ለምን ወይስ ለምን አይደለም ?
-
መዝሙረኛው “ እግዚአብሄር የኔ ነው “/ “ እግዚአብሄር ከእኔ ወገን ነው “ / “ እግዚአብሄር ከእኔ ጋር ነው “ በማለት ተናግሯል ፤ በመዝ (118፡ 6) ቀሪዉ ላይ ተመልከቱ ፡፡ የጥቅሱ የመጀመሪያ አካል ለቀሪዉ ጥቅስ ምላሻችሁን እንዴት ተፅዕኖ ያደርጋል ? በዚህ ጥቅስ የጠለቀ ስምምነት ይሰማችኋል ?
-
በመዝሙር 118 ዉስጥ ብዙ ጥቅሶች ኢየሱስ ወደሚባለዉ የክብር ንጉስ ያመለክታሉ ፤ መዝ (118፡ 19-20) የፅድቅ በሮችን ይናገራል ፤ ዮሐ (10፡ 7-9) ላይ ተመልከቱ ፡፡ ይህ በር በመዝሙር 118 ለክርስቶስ ማሳያ/እንደ አመልካች ሊሆን ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ ? መልሳችሁን አብራሩ ፡፡
-
በመዝሙር (116-118) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 118:24
“This is the day the LORD has made, let us rejoice and be glad in it!”
ዛሬ እግዚአብሔር ሊደሰትበት ደስ ሊሰኝበት የመረጠው ቀን ነው ፡፡ ዛሬ አንተም ምርጫ አለህ ፡፡ እግዚአብሔርን ለቀኑ ምስጋና እና ክብር ስጠው ፡፡ ቀኑ የእርሱ እንደሆነ እወቅ እናም ወደ ቀኑ ከእርሱ ጋር ተራመድ ፡፡ ሀሴት አድርግ ፣ አመስግን ፣ አክብር እናም ለእግዚአብሔር ምስጋናን ስጥ ፡፡ በእርሱ እስትንፋስ ፣ ህይወት እና ደህንነት አለህ ፡፡ ደስ መሰኘትን ምረጥ ፡፡ መልካም አሳቢ ሁን ፡፡ የምታጣው ምን አለ ?
አንዳንድ ሰዎች “ ከአልጋቸው መጥፎ በሆነ መንገድ “ ሊነሱ ይችላሉ ፡፡ ሌሎች ደግሞ ወንጫቻው ሞልቶ ሳይሆን ግማሽ ባዶ ሆኖ ሊያዩ ይችላል ፡፡ ነገር ግን በየትኛውም መንገድ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ ይህን እወቅ ፣ ዛሬ ስጦታ ነች ፡፡ ተመልከት ! አይኖችህን በኢየሱስ ላይ አድርግ እናም ምስጋናን አቅርብ ፡፡ ከአፍህ የሚወጣው የመጀመሪያ ቃልህ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝና የሆነን ሰው ደግሞ የሚያነቃቃ ይሁን ፡፡ ወደ ምትወደው ወደ ሆነ ሰው ወይም በአጠገብህ የተቀመጠውን ሰው ተመልከትና “ ይቺ ቀን እግዚአብሔር የሰራት ቀን ናት ፤ ሀሴት እናድርግ በእርሷም ደስ ይበለን “ በል ፡፡ በቃ ይህን አድርገው ! ምናልባት ይህ ቀንህን ሙሉ ለሙሉ ሊቀይረው ይችላል ምክንያቱም በራስህ ላይ ሳይሆን አይኖችህን በጌታ ላይ ማድረግን ስለመረጥክ ! ቀኑ ምንም ይያዝ እርሱ ከአንተ ጋር ነው ፡፡ በል አሁን ተከተለው ! ስለ አድሷ ቀን ደስ ይበልህ !
“እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን ። “
- መዝሙር 118፡24
ተጨማሪ ጥቅስ
ዘዳግም 28:13 — “ ዛሬም ያዘዝሁህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሰምተህ ብትጠብቃት ብታደርጋትም ፥ እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁልጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም ። “
መዝሙር 19:14 — “አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን ። “
ኢሳይያስ 50:4 — “ የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል ።
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።