God Reaches The Poor, Needy, And Barren
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 113-115 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መፅኀፍ በዝርዝር ዳዊትን እንደ ፀሀፊዉ ባይለየዉም እንኳን ብዙ ሰዎች ይህን መዝሙር ዳዊት ፅፎታል ፡፡ መዝሙር 113 እና 114 “ የሀሌ ሉያ “ መዝሙር አካል ሲሆኑ በተለይም በፋሲካ ጊዜ በመነበብ የሚዘመሩ ናቸው ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (113፡ 1-2)፡ መዝሙሩ የእግዚአብሄርን አገልጋዮች የእግዚአብሄርን ስም እንዲያመሰግኑ በመጣራት ይጀምራል ፤ የመዝሙረኛዉ ቃል ወደ ሀሳብ “ ስምህ የተባረከ ይሁን “ የሚለዉ በክሪስ ቶሚሊን የተዘመረዉን የአምልኮ መዝሙር ያመጣል ፡፡ ዳዊት ሰዎቹን እግዚአብሄርን “ከዛሬ ጀምሮ ለዘላለም “ እንዲባርኩ አሳሰባቸው (ቁጥር 2) !
መዝሙር (113፡ 3-6)፡ ዳዊት ከአሕዛቦች ሁሉ በላይ እንደሆነና ክብሩም ከሰማይ በላይ እንደሆነ እዉቅና በመስጠት እግዚአብሄርን በማመስገን ይቀጥላል (ቁጥር 4) ፡፡ በቁጥር 5 (ኒዉ ኪንግ ጀምስ እትም ላይ) ዳዊት “ በሰማይና በምድር ያሉትን ነገሮች ለመያዝ ራሱን የሚያዋርድ ማነው ? በማለት ይጠይቃል ፤ የእንግሊዘኛው መደበኛዉ እትም ይህን ጥቅስ “ አርቆ ወደ ሰማይ እና ምድር ላይ የሚመለከተዉ ማነዉ ? “ በማለት ይተረጉመዋል፡፡ በማንኛቸዉም ትርጓሜ ዳዊት የእግዚአብሄርን ታላቅነት አመሰገነ ምክንያቱም ከሰማይና ከምድር በላይ ከፍ ያለ እና በፍጥረቱ ላይ የሚመለከት ስለሆነ ፡፡
መዝሙር (113፡ 7-9)፡ ቀጥም ዳዊት እግዚአብሄር ወደ ምድር ሲመለከት ያየዉን ገለፀ ፡፡ እግዚአብሄር ሚስኪኖችንና ችግረኞችን ከሕዝቡ ኃያላን ጋር እንዲቀመጡ ያደርጋቸዋል (ቁጥር 7-8) ፤ እግዚአብሄር ለመካን ሴት ቤትንና ልጆችን ይሰጣል (ቁጥር 9) ፡፡ በቁጥር (7-8) የዳዊት ቃል በ 1ሳሙ (2፡ 8) ላይ ከሚገኘዉ ከሀና ቃል ጋር በጣም ይመሳሰላል ፡፡ ሀና ልጇን ሳሙኤልን ከወለደች በኋላ በምስጋና መዝሙሯ ዉስጥ በትክክ እነዚህን መዝሙሮች ዘምራቸዋለች ፤ በእነዚህ ቃላት ሀና እግዚአብሄር ምን እንደሚያደርግ አዉርታለች ፡፡
መፅሀፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ የሚለዉ አንድ ነገር ሰዎችን ነፃ ሊያወጣ እንደመጣ እና እግዚአብሄር ወደታች የሚመለከት ልብ ስላለዉ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ወደ ታች ምድር ላይ በመመልከት ችግረኛ ሰዎችን ከትቢያ ላይ ለማንሳት፣ ሚስኪኑን ከአመድ ላይ ለማንሳት (ቁጥር 7) እና መካኒቱ ሴት ለመናገር ልብ ካለው (ቁጥር 9)፣ ወደ እኛ እንዴት እንደደረሰ ምን ይላል ? አንዳንድ ጊዜ በእግዚአብሄር ልብ ላይ እንስታለን ፡፡ በዘፍጥረት ላይ አዳምና ሒዋን በኤደን ገነት ኃጢዓትን ካደረጉ ጊዜ ጀምሮ የሰዉን ልጅ መልሶ ከራሱ ጋር ለማስታረቅ በተልዕኮ ላይ ነው ፤ ያ ስለ ባለፀጋ ሰዎች ወይም ስለ ችግረኛ ሰዎች ብቻ አይደለም - ሁሉም ሰዉ ወደ እርሱ እንዲመጡ ይፈልጋል - ማንም እንዳይጠፋ ፡፡
መፅሀፍ ስለ ችግረኛና ስለ ሚስኪን ምን ይላል ? መፅሀፍ ስለ እኛ ሚና ምን ይላል ? እግዚአብሄር እግዚአብሄር ስለሆነና እንዴት ሰዎችን እንደሚረዳ በማዉራት እግዚአብሄርን የምናመሰግን ከሆነ ቀጥለን በዚያ ሁኔታ ዉስጥ የት እንደሚገባ/ልክ እንደሚሆን ማወቅ ያስፈልገናል ፡፡ ለመመልከት ምሳሌአችን የንጉስ ሳዕል የልጅ ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ነው ፡፡ ሞግዚቱ የንጉስ ሳዖልንና የዮናታንን መሞት ከሰማች በኋላ ከእርሱ ጋር በሸሸች ጊዜ አምስት አመቱ ነበር ፤ ስትሸሽ የተጎዳዉንና ሽባ እግሮች የነበሩትን ሜምፊቦስቴን ጣለችዉ ( 2ሳሙ 4፡ 4) ፡፡
ዳዊት ንጉስ በሆነ ጊዜ ከዮናታን ጋር ኪዳን አድርጎ እንደ ነበር አስታወሰ ፤ በ 2ሳሙኤል 9 ዳዊት ከዮናትን ቤት ለሆነ ማንኛዉም ሰዉ ቸርነትን ለማድረግ ተመለከተ ፤ ስለ ሜምፊቦስቴ ሲነገረው ዳዊት ትርጉሙ “ቃል የለም “ ከሚለዉ ከሎዶባር አምጥቶት ነበር ፡፡ ዳዊት የአያቱ የሳዖል የነበረዉን መሬት ሁሉ በመመለስ ለሜምፊቦስቴ ቸርነትን አሳዬ ፤ ከዚያም ሜምፊቦስቴ በኢየሩሳሌም በመኖር ቀሪ ህይወቱን ከንጉሱ ገበታ በላ ፡፡ ዉርሱን አጥቶ የነበረ፣ በአደጋ ተጎድቶ የነበር፣ ቤተሰቦቹ ተገድለዉበት የነበረው “ ቃል የለኝም “ በሚል ስፍራ ይኖር የነበረ አንድ ሰዉ ነበር ፤ ነገር ግን ዳዊት እርሱን አግኝቶ በንጉሱ ገበታ ላይ በማምጣት ነፃ አወጣው ፡፡ በዚያን ጊዜ ከንጉሱ ገበታ ሽባ ሲበላ ተሰምቶ አይታወቅም ነበር ፤ ነገር ግን ሜምፊቦስቴ በንጉስ ገበታ ላይ በተቀመጠ ጊዜ ሽባ እንደሆነ ማዉራት አትችሉም ምክንያቱም እግሩን ማየት ስለማትችሉ ፡፡ እግዚአብሄር በኑሮአችን “ ሜምፊቦስቴዎችን “ በማግኘት እዉነትን ወደ እነርሱ በመናገር እግዚአብሄር እንዲሆኑ የሚፈልግበት ቦታ እንዲመጡ እንድናደርግ ይፈልጋል ፡፡
የእግዚአብሄር ልብ ለተጨቆኑትና ለሚስኪኖች ነው ፤ ቤተ ክርስቲያን እነርሱን ለመርዳት የምትቀድም መሆን አለባት፡፡ ከእያንዳንዱ ሰዉ ኃላ ያለዉን ታሪክ ማየት ያስፈልገናል ያ ከሆነ የተቀበልነዉን የኢየሱስን ፍቅር ለእነርሱ ለመስጠት የተዘጋጀን እንሆናለን ፡፡ በኢሳያስ 58 እግዚአብሄር ኢሳያስን ለህዝቡ መተላለፋቸዉንና ኃጢዓታቸዉን እንዲናገር ነገረው (ኢሳ 58፡ 1) ፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ በመፆም ራሳቸዉን አዋርደው እርሱን በፈለጉት ጊዜ ለምን እንደማይሰማቸዉ እየጠየቁ ነበር (ኢሳ 58፡ 2-3) ፡፡ እግዚአብሄር በፆማቸዉም እንኳን እራሳቸዉን ለማመስገን እና በስራቸዉ ለመጮቆን በመቀጠል ነዉ በማለት ገሰፃቸው (ኢሳ 58፡ 4-5) ፡፡ እግዚአብሄር የመረጠዉን አይነት ፆም፡ “ የበደልን እስራት ይፈቱ ዘንድ፣ የቀንበርን ጠፍር ይለቅቁ ዘንድ፤ የተገረፉትን አርነት ይሰድዱ ዘንድ እና ቀንበርንስ ሁሉ ይሰብሩ ዘንድ “ (ኢሳ 58፡ 6) እንደሆነ አመለከተ ፡፡ ኢየሱስ ምርኮኞችን ነፃ ለማዉጣትና የተሰበረ ልብ ያላቸዉን ለመፈወስ መጣ (ሉቃ 4፡ 18) ፡፡ ሰዎች ነፃ መሆን የሚችሉበት ብቸኛዉ መንገድ ከኃጢዓት ነፃ የሚሆኑት በኢየሱስ ብቻ ነው ፡፡ ኢሳያስ ከተራቡት ጋር ምግብ እንዲጋሩ፣ ቤት የሌላቸዉን ወደ ቤታቸዉ እንዲያመጡ እና የተራቆቱትን እንዲያለብሱ በመጣራት የእግዚአብሄርን መልዕክት ቀጠለው (ኢሳ 58፡ 7) ፡፡ እንደዚያ ከሆነ ብርሃናቸዉ እንደ ንጋት ይወጣል፣ ፈዉሳቸዉ ፈጥኖ ይበቅላል፣ ፅድቃቸዉም በፊታቸዉ ይሄዳል እንዲሁም የእግዚአብሄር ክብርም በኋላችዉ ሆኖ ይጠብቃቸዋል (ኢሳ 58፡ 8) ፡፡ እግዚአብሄር ፀሎታቸዉን በመስማት እንደሚመልስ ተስፋ ገብቷል (ኢሳ 58፡ 9) ፡፡ ለተራቡና ለተጨነቁ ነፍሳቸዉን ባፈሰሱ ጊዜ እግዚአብሄር እንደሚመራቸዉ፣ እንደሚያጠግባቸው እና ኃያላን እንደሚያደርጋቸው ተስፋ ገብቶላቸዋል (ኢሳ 58፡ 10-11) ፡፡
የምናያቸዉ ፍርስራሾች/ስባሪዎች መከፋፈሎች ምንድን ናቸው ? በአንድነታችሁ ዉስጥ ቀዳዳዎች ምንድን ናቸው ? እግዚአብሄር የተሰበሩትን እንድንጠግንና መንገድን እንድናድስ ጠርቶናል (ኢሳ 58፡ 12) ፡፡ ኢየሱስ በኑሮአችን ዉስጥ በመራመድ እነደጠገነን እና እንዳደሰን ሌሎችን ለማደስና ለመጠገን መድረስ እንችላለን ፡፡
እንደ ገና ወደ መዝ (113፡ 7) ተመልሰን በመሄድ ፤ በህይወታችሁ እንደ ችግረኛና እንደ ሚስኪን ማን ይመጣል ? በልባችሁ ላይ እግዚአብሄር ያስቀመጠዉ ማንን ነው ? ስለ ችግረኛ በአመድ ትቢያ ላይ መመልከት ስንጀምር ምን ይመስላል ? ስለ መካኖች መመልከት ምን ይመስላል ? አዎ መካን ማህፀን ሊሆን ይችላል ነገር ግን ሌላ አይነት መካንነት አለ ፡፡
መደምደሚያ
አንዳንድ ጊዜ በእግዚአብሄር ተልዕኮ የተያዝን በመሆን የእግዚአብሄርን ሰዎች እናጣቻዋለን ፤ የክርስቶስን ፍቅር የምታሳዩ ሁኑ (ሮሜ 5፡ 8) ፤ በአንድ ነገር ብቻ ጀምሩ ፤ ቀጣይ ጊዜ የሆነ ሰዉን ነገርን በመፈለግ ዉስጥ እንዳለ በማየት የእናንተ ሜሚፊቦስቴ ዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ወይም እንዳልሆኑ ታስባላችሁ ፡፡ እነዚህን እግዚአብሄር ወደ ንጉሱ ገበታ እንድትወስዷቸዉ ሊጠይቃችሁ ይችላል ?
ጥያቄዎች
-
የክብር ንጉስ ወደ ምድር ለመምጣት እና ሰዉ ለመሆን ሲል እንደፈለገዉ የመሆን መብቱን ወደጎን መተዉ መምረጡን አስቡ ፤ በመዝ (113፡ 5-6) እና ፊል (2፡ 7-8) ላይ በደንብ አሰላስሉ/አስቡ ፡፡ ለእግዚአብሄር ምስጋናችሁን የሚነግሩላችሁን ፀሎቶች እና መዝሙሮችን ፃፏቸው ፡፡
-
መዝ (113፡ 7-8) አንብቡ ፤ ይህ እንደ አንድ ፍጥረት ትረካ ይመስላልን (ትቢያን/አመድን አስቡ) ? እነዚህ ሁለት ጥቅሶች እንዴት የሁሉንም አማኞች ታሪክ ይናገራሉ ?
-
በመዝ (115፡ 4-7) የጣዖቶችን መግለጫዎች ባነበባችሁ ጊዜ እምነታቸዉን በጣዖቶች ላይ ስላስቀመጡት ሀሳባችሁ ምንድን ነው ? ከእግዚአብሄር ዉጪ በሆነ ነገር ላይ እምነታችሁን አስቀምጣችሁ ራሳችሁን አግኝታችሁት ታውቃላችሁ ? መዝ (115፡ 8) ምና ማለት እንደሆነ የምታስቡትን ግለፁ
-
መዝ (115፡ 3) “ የፈለገዉን ያደርጋል “ የሚለዉ እግዚአብሄር መልካም እንደሆነ ሙሉ ፅናት ከሌላችሁ ለምን የሚረብሽ እና የሚያስፈራ ይሆናል ?
-
መዝ (115፡ 16) “ የሰማያት ሰማይ ለእግዚአብሄር ነው ፤ ምድርን ግን ለሰዉ ልጆች ሰጣት “ ይላል ፤ በዘፍጥር 1 ላይ እግዚአብሄር ለሰዉ በምድር ላይ ስልጣን ሲሰጥ ታገኙታላችሁ ? መዝ (8፡ 6) እና ዕብ (2፡ 8) አንብቡ ፤ አሁን በምድር ላይ የሚገዛዉ ማነው ?
-
መዝ (115፡ 17) “ ሙታን እግዚአብሄርን እንደማያመሰግኑት “ ይናገራል ፤ ይህ የአካላዊ ሞትን የሚያመለክት ነዉ ወይስ መንፈሳዊ ሞትን ሊሆን ይችላል (ዮሐ 5፡ 25) ? አንድ ሰዉ እንዴት ከሞት ወደ ህይወት ሊሄድ ይችላል ? (ዮሐ 3፡ 16, 5፡ 21, ሮሜ 10፡ 9, 10)
-
በመዝሙር (113-115) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 113:7—9
“He raises the poor from the dust and lifts the needy from the garbage pile in order to seat them with nobles—with the nobles of His people. He gives the childless woman a household, making her the joyful mother of children. Hallelujah!”
የእግዚአብሔር መንፈስ በአንተ ላይ ነው ፡፡ ለአንተ ያለውን ፍቅር ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር አብ ልጁን ኢየሱስን መስቀል ይሸከም ዘንድ ወደ ምድር ላከው ፣ አንተም ድነትን ማግኘት ቻልክ ፡፡ እናም አሁን በውስጥህ የአብ ፍቅር አለ ፡፡ ፍቅሩ በላይህ ይፈሳል ፡፡ በውስጥህ ባላው በእግዚአብሔር ታላቅ ፍቅር አማካኝነት ሌሎችን ትወድ ዘንድ ይህ የአንተ ሀላፊነት ነው ፡፡ እንዴት ነው ለሌሎች ፍቅርን የምትገልጸው ? ከአቧራ ላይ የሚያነሳቸውን እጅ የሚሹትን እነዚህን ውደዳቸው ፡፡ በአንዱ እውነተኛ መሰረት ላይ እግሮቻቸውን ያቆሙ ዘንድ አግዛቸው ፡፡
ማን ያውቃል በህይወታቸው ያለውን ክፍተት በኢየሱስ መሙላት ያስፈልግ ይሆናል ? ባዶ ወይም በዚህ አለም ነገሮች እርካታን ያላገኙ ሊሆኑ ይችላሉ እናም ጌታ ጥማቸውን እንድያረካላቸውና ባዶነታቸውን እንዲሞላ የተዘጋጁ ፡፡ እነርሱን ልትወዳቸው ትፈቅዳለህን ? በአብ ፍቅር ልትሞላቸው ትወዳለህን ? በእርሱ መንገድ ስትሄድ ፣ ድምጹን ስትሰማ እና ከእነዚህ የሚያንሱትን ጭምር ስትወድ እግዚአብሔር ያስታጥቅሃል ፡፡ ለራስህ ክብር አይደለም ነገር ግን ለእርሱ ክብር ብቻ ፡፡ ዛሬ በኢየሱስ ስም ትወደው ዘንድ ወደ ሆነ ሰው እንድመራህ ጌታን ጠይቅ ፡፡
“ ከአለቆች ጋር ከሕዝቡም አለቆች ጋር ያኖረው ዘንድ ችግረኛን ከመሬት የሚያነሣ፥ ምስኪኑንም ከፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ ፤ መካኒቱን በቤት የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት ። ሃሌ ሉያ ። “
- መዝሙር 113፡ 7-9
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 115:1 — “ ለእኛ አይደለም፥ አቤቱ፥ ለእኛ አይደለም፥ ነገር ግን ለስምህ ስለ ምሕረትህ ስለ እውነትህም ምስጋናን ስጥ ። “
ሮሜ 5:8 — “ ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል ። “
1ኛ ዮሐንስ 4:7–8 — “ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና ።
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።