Wisdom Books Psalms

The Priestly King

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 110-112 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 446 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙር 118 እና 110 በአዲስ ኪዳን በብዛት የተጠቀሱ መዝሙሮች ናቸው ፤ ያ ማለት ለመሲሁ ማጣቀሻ የተጠቀሱ ነበሩ ማለት ነው ፡፡ ዋይርስቤ የመዝሙር 110 ቁጥር 1 25 ጊዜ እንደተጠቀሰ፣ ቁጥር 4 አምስት ጊዜ እንደተጠቀሰ እና መዝሙሩ ደግሞ በዕብራዊ መፅሀፍ ዉስጥ አስር ጊዜ እንደተጠቀሰ አመልክቷል ፡፡ በዳዊት የተፃፈ ንጉሳዊ መዝሙር እና በጣም ዋና የሆነዉን መሲሀዊ መልክ ክርስቶስን እንደ ንጉስና እንደ ካህን የሚወክል ነው ፡፡ ለመዝሙር መፅሀፍ የክብር ንጉስ የሚለዉን ሀረግ እየተጠቀምን ነዉ ነገር ግን ለመዝሙር 110 የክብር ንጉስ እናካህን የሚለዉን መጠቀም እንችላለን ፡፡ ኢየሱስና ጴጥሮስ ሁለቱም ዳዊት ፀሀፊዉ እንደ ነበር አረጋግጠዋል (ማቴ 22፡ 43 -44, ሐዋ 2፡ 33-35) ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (110፡ 1-3)፡ንጉሱ ክርስቶስ፡ ቁጥር 1የዳዊት ስር እና ዘር ለሆነው “ ለጌታዬ “ (ለእግዚአብሄር ልጅ ) መግለጫ ያደረገዉን “ እግዚአብሄርን “ (እግዚአብሄር አብን) ይጠቅሳል (ማር 12፡ 36, ራዕ 5፡ 5, 22፡ 16) ፡፡ ክርስቶስ ወደ ምድር እስኪመጣ ድረስ በእግዚአብሄር ቀኝ እጅ ተቀምጧል (ቁጥር 1) ፡፡ ኢየሱስ እግዚአብሄር ጠላቶቹን የክርስቶስ የእግር መረገጫ እስኪያደርግለት ድረስ በክብር ስፍራ በቀኙ ተቀምጧል (ዕብ 10፡ 10-12) ፡፡ ማክአርቱር “ የእግር መረገጫ የቀድሞ ምስራቅ አቅራቢያ የአንድ ጠላት አሁን በእግር ስር መሆንን የሚስል ሙሉ የሆነ የድል አድራጊነት ስዕል እንደሆነ “ ይገልፃል (መዝ 8፡ 6-7, 47፡ 3) ፡፡ ዳዊት የኢየሱስን የመጀመሪያ መምጣት ባለማጣቀስ/በማይመስል የክርስቶስ ሁለተኛ መምጣት ስዕልን እየፃፈ ነበር (ራዕ 19፡ 11-21) ፡፡ ክርስቶስ ተመልሶ ከመምጣቱ በፊት የጠላቶቹን የተሸነፉ መሆን እየጠበቀ ነው (ዕብ 10፡ 13) ፡፡

ዳዊት እግዚአብሄር ስለሚያደርጋቸዉ በረከቶች ፃፈ ፡፡ የመጀመሪያዉ እግዚአብሄር ከፂዎን (ከኢየሩሳሌም) የሚዘረጋዉን በመንግስቱ ላይ የሚያስተዳድረዉን ኃያሉን በትሩን ክርስቶስን ይሰጣል ፤ ይህ የሰማይቱን ፂዎን ሳይሆን ወደ ምድሪቱ ፂዎን አመልክቷል ፤ ይህ ልጁ/ወልድ ስራዉን እንዲሰራ የሚፈቅድለት አባቱ/አብ ነው ፡፡ ሁለተኛው እግዚአብሄር ጠላቶቹን ያሸንፋቸዋል (ቁጥር 2) ፤ የክርስቶስ ሰዎች ለክርስቶስ “ በቅዱስ ዉበት “ ለመዋጋት ለመሄድ ፈቃደኞች ይሆናሉ (ቁጥር 3) ፡፡ ንፁህ ነጫጭ የፈረስ ሰራዊት ጭፍሮች እንደ ካህናት ነጭ ልብስን ለብሰዋል (ራዕ 19፡ 14) ፤ ማክአርቱር እነዚህን ፍቃደኛ ሰራዊት “ የዳኑት/የተዋጁት የምድር ነዋሪዎች በፍቃደኝነት የነገስታት ንጉስን እና የጌቶች ጌታን እንደሚያገለግሉት “ ይገልፃል ፡፡ “ ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ከሆድ ወለድሁህ “ (ቁጥር 3) የሚለዉ ሀረግ ክርስቶስን ይገልፃል ፡፡

መዝሙር (110፡ 4-7)፡ካህኑ ክርስቶስ፡ የመጨረሻዎቹ አራት ጥቅሶች ወደ ክርስቶስን ክህንነትን ያመለክታሉ ፤ እግዚአብሄር ክርስቶስ እንደ መልከፀድቅ ካህን እንደሚሆን በመኃላ ምሎ ነበር ፤ መልከጸድቅ በብሉይ ኪዳን እንደ ካህንና እንደ ንጉስ ያገለገለ ብቸኛዉ ሰዉ ስለ ነበር (ዘፍ 14፡ 17-20) የሚመጣዉ መሲህ ጥላ ነበር (ቁጥር 4) ፡፡ ካህን በእግዚአብሄርና በሕዝቦቹ መካከል እንደ አስታራቂ ሆነ ሲያገለግል ንጉሱ ዉጊያዉን ለማድረግ እንደ አንድ በፈረስ ላይ ሆኖ እንደመጣ እንስላለን ፡፡ ክርስቶስ የመጨረሻዉ ንጉሱ/ካህን ነው ፡፡

አሁን እግዚአብሄር በመሲሁ ቀኝ እጅ ስለሆነ በቁጣዉም ቀን ነገስታትን ይቀጠቅጣቸዋል (ቁጥር 5) ፤ ተግባሩ ይቀያየራል - አባቱ/አብ በልጁ/በወልድ ቀኝ እጅ በመቆም የልጁ ፍላጎቶችን ሁሉ ያቀርብለታል/ያደርግለታል ፡፡ “ የቁጣዉ ቀን “ “ የእግዚአብሄር ቀን “ ይሆናል ፡፡ ማክአርቱር “ የቁጣዉ ቀን “ የእግዚአብሄርን ቀን በመጥቀስ/በማመልከት በዳንኤል ሰባኛ ሳምንት መጨረሻ ላይ የአለምን መግለጫዉን እንደሚያገኘዉ (ዳን 9፡ 24-27) ይገልፃል ፡፡ የእግዚአብሄር ቀን የልጁን መመለስ መንገድ ለመስራት የሚመጣ ነው ፡፡

በተጨማሪም እግዚአብሄር በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፣ ሬሳዎችንም ያበዛል እንዲሁም በአለም ላይ ያሉትን መሪዎች ሁሉ ይቀጠቅጣቸዋል (ቁጥር 6) ፡፡ ለእግዚአብሄር ቀን በመፅኀፍ ዉስጥ ብዙ ማጣቀሻዎች አሉ (መዝ 2፡ 8-9, 50፡ 1-6, ኢሳ 2፡ 4, 9፡ 6-7, ዳን 2፡ 44-45, 7፡ 21-27, ማቴ 25፡ 32, ራዕ 6፡ 15-17, 14፡ 20, 16፡ 17, 18፡ 19-21) ፡፡ ከዚያም ክርስቶስ እንደ አሸናፊ ከጅረት በመጠጣት በድል/በአሸናፊነት ራሱ ከፍ ይላል (ቁጥር 7) ፡፡ ዳዊት ትንቢታዉ ቃል የተናገረ እንደ እግዚአብሄር ነቢይ በእዉነት ያገለገለ ነበር (ሐዋ 2፡ 30) ፡፡

መደምደሚያ

ዳዊት እነዚህን ቁጥሮች ለመፃፍ በመንፈስ ቅዱስ ተነሳሳ - የዚህን ትንቢት ቃል ለመመዝገብ ፡፡ ዳዊት ስለ ክብርንጉስና ካህን ፃፈ ፡፡ እግዚአብሄር የጌታን የቁጣ ቀን ለንጉሱና ለካህኑ ኢየሱስ መንገድን ለመስራት ወደፊት ያመጣዋል፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 291.

  2. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 674.

  3. MacArthur, p. 674.

  4. MacArthur, p. 674.

ጥያቄዎች

  1. መዝ (110፡ 1) ስታነቡት ለእናንተ ምን ማለት ነው ? ለዚህ ድርጊት ምስክሮች ሆናችሁ ታውቃላችሁ ?
  2. በመዝ (111፡ 10) “ እግዚአብሄርን መፍራት “ ማለት ምን ማለት ነው ? በመፅሀፍ ሌላ የት ላይ እንዲህ አይነት ፍራት የታዬ ነው/ታይቷል ? (2ዜና 19፡ 7, ኢዮ 28፡ 28, ምሳ 2፡ 5, 8፡ 13, 9፡ 10, 15፡ 33, 16፡ 6)
  3. መዝሙር 112 ስለ እግዚአብሄር ሰዎች ሙሉ በመደብር ስላሉ ታላቅ ነገሮች ነው ፤ እነዚህ ነገሮች እንዴት እግዚአብሄርን ከመፍራት ይመጣሉ ? እግዚአብሄርን ትፈራላችሁ ? ያ በህይወታችሁ ምን ይመስላል ?
  4. በመዝሙር (110-112) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 110:5–6

“The LORD is at Your right hand; He will crush kings on the day of His anger. He will judge the nations, heaping up corpses; He will crush leaders over the entire world.”

እግዚአብሔር እንደ ንጉሥ ደግሞም እንደ ክብር ካህን ነገሠ ፡፡ እግዚአብሔር ጠላቶቹን ይረታል ፡፡ እግዚአብሔር መንግስቱን ያሰፋል ፡፡ ኢየሱስም ዳግም ሲመጣ ከእርሱ ጋር ታላቅ ሰራዊት ይመጣል ፡፡ ነገር ግን እስከዚያው ድረስ ኢየሱስ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ፡፡ እግዚአብሔር ጠላቶቹን የሚረታበት እና ነገሥታትን የሚያደቅበት ቁጣውንም የሚገልጽበት ጊዜው ይመጣል ፡፡

ዝግጁ ነህ ? ዝግጁ መሆን ማለት ምን ማለት ነው ? የእግዚአብሔርን ኃይል እወቅ ፡፡ እርሱ ማን እንደሆነ እወቅ ፡፡ በአለም ፍርሃት ውስጥ መኖር አይገባህም ፡፡ ስለዚህ በዚህ አለም ውስጥ ያሉ ነገሮችን መፍራት አቁም ፡፡ ይልቁንም የጥበብ መጀመሪያ ነውና እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር ፡፡ እግዚአብሔርን ስለ ኃያልነቱና ስለ ብርታቱ ፍራው ፡፡ የእግዚአብሔር ስም ታላቅ ነውና ስሙን አወድስ ፡፡ ጠላቶችህን ድል ትነሳ ዘንድ የእግዚአብሔርን ስም ጥራ እንድሁም ሌሎች ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥና የክብር ካህን መሆኑን ሌሎችም ያውቁ ዘንድ አሸናፊነቱን አውጅ ፡፡ አዎን በኢየሱስ ድልን አውጅ ስለዚህም ሌሎች ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቃሉ ፡፡ አሜን ፡፡

“ እግዚአብሔር በቀኝህ ነገሥታትን በቍጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል ። በአሕዛብ መካከል ይፈርዳል፥ ሬሳዎችንም ያበዛል፤ በሰፊ ምድር ላይ ራሶችን ይቀጠቅጣል ። “ - መዝሙር 110፡5-6

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 47:3 — “ አሕዛብን ከእኛ በታች፥ ወገኖችንም ከእግራችን በታች አስገዛልን ። “
  • ሐዋርያት ሥራ 7:55–56 — “ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና ፦ እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ ። “
  • ሐዋርያት ሥራ 15:17–18 — “ከዚህ በኋላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ ፣ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ ። “