Wisdom Books Psalms

Godly Character Through Opposition

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 107-109 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 445 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙር 109 እንደ አንድ እርግማን መዝሙር የተመደበ ሲሆን ትርጉሙም የእግዚአብሄርን ፍርድ ወይም መቅሰፍት በጣላቶች ላይ እንዲሆን ልመና ማለት ነው ፡፡ የመዝሙር መፅኀፍ የእነዚህን መዝሙር ብዙዎች ሲይዝ ምናልባትም ይህ መዝሙር የእነዚህን ሁሉ አደገኛን ፍርድ አወጀ ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (109፡ 1-5)፡ ዳዊት በተቃርኖ ምላሽ ሰጠ ፤ የዳዊት የኑሮ ስታይል የምስጋና ስታይል ነበር (ቁጥር 1) ፡፡ በተመሳሳይ በክርስቶስ የሆንን እግዚአብሄርን ማመስገን የኑሮ ስታይላችን የሆነ መሆን አለበት “ እንግድህ ጌታን ክርስቶስን ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ ፤ ስር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ ምስጋናም ይብዛላችሁ “ (ቆላ 2፡ 6-7) ፡፡ የዳዊት ህይወት በምስጋና የታወቀ ስለ ነበር እርሱ እንደዳደረገዉ ተመሳሳይ ከማያደርጉት እግዚአብሄርን ከማይወዱት ከሌሎች ጋር በቅርርብ ይኖራል ፤ ከዚህም የተነሳ ሌሎች ዳዊትን በመጥፎ ሁኔታ ተመለከቱት (ቁጥር 2-5) ፡፡

የዳዊት ባህሪያት በመዝሙሩ በመጀመሪያዉ ክፍል ዉስጥ የተመሰረተ ነበር፡

  1. ዳዊት እግዚአብሄርን አመሰገነ (ቁጥር 1) ፤ “ ዳዊትም በጉባኤዉ ሁሉ ፊት እግዚአብሄርን ባረከ ፤ ዳዊትም አለ አቤቱ የአባታችን የእስራኤል አምላክ ሆይ ከዘላለም እስከ ተባረክ “ (1ዜና 29፡ 10) ፡፡
  2. ዳዊት ወደ እግዚአብሄር ፀለዬ ፤ “ በወደድኋቸው ፋንታ አጣሉኝ እኔ ግን እጸልያለሁ “ (ቁጥር 4) ፡፡
  3. ዳዊት ሌሎችን ይወዳል ፤ “ በወደድኋቸው ፋንታ “ (ቁጥር 4) ፤ ዳዊት ጠላቶቹን ይወዳል ፡፡

መዝሙር (109፡ 6-20)፡ ዳዊት ለተቃዉሞዉ ምላሽ ሰጠ ፡፡ ዳዊት ወዲያዉኑ በእግዚአብሄር ላይ መደገፉን እና ጠላቶቹን መዉደዱን ከመግለፅ በመመለስ እግዚአብሄር በጠላቶቹ ላይ እንዲሰራ ይጠይቃል ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን በጠላቶቹ ላይ “ ክፉ ሰዉን እንዲያስቀምጥ “ (ቁጥር 6)፣ የጠላቶቹ ፀሎት “ እንደ ኃጢዓት እንዲቆጠር “ (ቁጥር 7) እና በሌሎች ፍርዶች መካከል ለእግዚአብሄር “ ዘመኑ ጥቂት እንድትሆን “ (ቁጥር 8) ፡፡ በሐዋ (1፡ 20) ጴጥሮስ የሹመት ስፍራን ሌላ ሰዉ እንደሚወስደዉ ሐዋሪያት እንደተመለከቱ አድርጎ ቁጥር 8 ጠቅሶታል ፡፡

ዳዊት ለሌሎች በፍቅሩ ባህሪይ የታወቀ ቢሆንም እግዚአብሄርን በጠላቶቹ ቤተሰብ ላይ ከባድ ፍርድን እንዲያዉጅ ጠየቀው ፤ ዳዊት እግዚአብሄርን “ ልጆቹም ድሀ አደግ ይሁኑ “ (ቁጥር 9), ጠላቱንም “ ባለዕዳም ያለዉን ሁሉ ይበርብረው “ (ቁጥር 11) እና “ ለድሀ አደግ ልጆችም “ የሚያግዝ አይኑር (ቁጥር 12) በማለት ጠየቀ ፡፡ በተጨማሪም ዳዊት እግዚአብሄርን የጠላቶቹ ልጆች “ ልጆቹ ይጥፉ ፤ በአንድ ትዉልድ ስሙ ይደምሰስ “ (ቁጥር 13) እንዲሁም የጠላቶቹ ቤተሰቦች “ የአባቶቹ ኃጢዓት በእግዚአብሄር ፊት ትታሰብ ….. በእግዚአብሄር ፊት ሁል ጊዜ ይኑር “ (ቁጥር 13-15) በማለት ጠየቀ ፡፡

መዝሙር (109፡ 16-20)፡ እነዚህ ቁጥሮች ዳዊት በጠላቶቹ ላይ እንዲሆኑ የእግዚአብሄርን ከባድ ነገሮችን የጠየቀበትን ምክንያት ያስቀምጣሉ ፡፡ ጠላቶቹ “ ለተቸገረ፣ ለሚስኪንና ልቡ ለተሰበረ “ ስለማያስብ ይልቁንም “ ለመግደል “ ስለተመለከተ (ቁጥር 16) ፡፡ የዳዊት ጠላት “ መርገምን ይወዳል “ እንዲሁም “ በበረከት ደስታን አልወሰደም “ ስለዚህም ዳዊት እግዚአብሄርን የተረገመ እንዲሆንና በረከት ከእርሱ እንድትርቅ እንዲፈቅድ ጠየቀው (ቁጥር 17) ፡፡ ዳዊት እግዚአብሄርን ይህ እርግማን የጠላቱን አካል እንዲሰብረዉ፣ እንደ ልብስ ወይም እንደ መታጠቂያ ዙሪያዉን እንዲሸፍነዉ ጠየቀ (ቁጥር 18-19) ፡፡

የዳዊት ጥያቄዎች በሰዎስት መንገድ መረዳት ይቻላል፡ መጀመሪያዉ ዳዊት ሁሉንም ቅሬታዎቹንና ምሬቶቹን ወደ እግዚአብሄር በማምጣት ፍራቱን ለእግዚአብሄር መናገር ይችላል ፤ ሁለተኛው ዳዊት በግል ድርጊት/አፀፉ ሳይወስድ እነዚህን ነገሮች በጠላቶቹ ላይ እንዲያመጣ እግዚአብሄርን በመጠየቅ መፀለይ ይችላል ፤ ሰዎስተኛው ዳዊት ነገሮቹ በጠላቶቹ ላይ እንደሚሆኑ በማመልከት መተንበይ ይችላል ምክንያቱም እንዲህ አይነት ተመሳሳይ ነገር በፈፀሙ ሰዎች ላይ እነዚህ ፍርዶች እንደሚሆኑ መፅሀፍ ስላወጀ (ዘዳ 27፡ 15-26) ፡፡

መዝሙር (109፡ 21-23)፡ ዳዊት እርዳታን ጠየቀ ፡፡ ዳዊት ለደረሰበት ተቃዉሞ ምላሹን ካደረገ በኋላ እግዚአብሄርን እርሱን በመመልከት ምህረት እንዲያደርግለት ጠየቀው (ቁጥር 21) ፤ ይህ በአመለካከቱ ላይ አስደናቂ ለዉጥ ነበር ፡፡ እግዚአብሄርን ማመስገን የዳዊትን አመለካከት በመቀየር በመዝሙር 109 ቀድመን ወዳየነው የሰዉ ባህሪይ መልሶ አመጣው ፡፡ ይህ ሰው “ እንደ ምህረቱ መጠን እንዲያድነው “ (ቁጥር 26) ሙሉ ለሙሉ በእግዚአብሄር ላይ የተደገፈ እንደ ነበር ያውቃል ፡፡ አሁን ዳዊት እርሱ እንዳደረገዉ በተመሳሳይ መንገድ ጠላቶቹ የእግዚአብሄርን ምህረት እንዲያዉቁ ፈለገ (ቁጥር 27) ፡፡ የጠላቱ ባህሪይ ላይቀየር ይችላል (ቁጥር 28-29) ነገር ግን ዳዊት እግዚአብሄርን ማመስገን ለመቀጠል ወሰነ (ቁጥር 30) ፡፡

መደምደሚያ

በክርስቶስ ስለተዋጀን ዳዊት እንዳለዉ ተመሳሳይ ባህሪይ ያለን ሰዎች ነን ፡፡ እንደ ዳዊት ተቃዉሞ የሚደርስብን ጊዜዎች ይኖሩናል ፡፡ ጠላት ወደ ብስጭት ዉስጥ እንድንገባ ሊያታልለን ይሞክራል ፤ ነገር ግን በፀሎት አቋቋም ፀንተን ከቆየን እግዚአብሄር ያን ሸክም ከእኛ ይወስዳል፣ ልባችንንም ትሁት በማድረግ መጀመሪያ ለእኛ የሚገባንን ወዳደረገልን ባህሪይ ይመልሰናል ፡፡

በተቃዉሞ መካከል ላይ ለእግዚአብሄር ክብር እንዴት እናመጣለን ?

በተቃዉሞ ምላሽ መስጠት ፤ ጠላት እስከ ምን ያክል እንደሆነ ጊዜ በመዉሰድ በሚገባ ምላሽ መስጠት ትችላላችሁ ፡፡ ነገሩን ለእግዚአብሄር በመስጠት በመልካም መንገድ ምላሽ መስጠትን መምረጥ ትችላላችሁ ፤ በመጥፎ ነገር ምላሽ ለመስጠት ብትመርጡም እንኳን እግዚአብሄር ከዚያ ዉስጥ ሊያወጣችሁ ይችላል ፡፡

የእግዚአብሄርን እርዳታ መጠየቅ ፤ እግዚአብሄር ልባቸዉን መቀየር ይችላልም በእናንተም ዉስጥ ባለዉ በክርስቶስ ባህሪይ እንድትኖሩ ይረዳችኋል ፡፡

እግዚአብሄር ሰላምን፣ ኃይልን፣ ጥበብን እና በሆነ ጊዜ ላይ በሚቃወማችሁ ማንኛዉም ነገር ሂደት ዉስጥ እንድትሄዱ ትህትናን ይሰጣችኋል ፡፡ የእግዚአብሄርን እርዳታ ስትጠይቁ ዳዊት ወደ ጀመረበት ባህሪይ ይመልሳችኋል፡፡ ተቃዉሞ እየጨመረ የሚሄድ ነው ነገር ግን እንድታሸንፉ በእናንተ ዉስጥ ኃይል አላችሁ ፡፡

  1. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 600.

ጥያቄዎች

  1. መዝ (107፡ 2) “ እግዚአብሄር ያዳናቸው ከጠላቶች እጅ ያዳናቸው ይናገሩ “ ይላል ፤ እግዚአብሄር ከጠላቶቻችሁ አድኗችኋል ? ለሆነ ሰዉ ተናግራችኋል ? ካልሆነ ለሆነ ሰዉ እንዴት ልትናገሩ ትችላላችሁ ? የእምነት እርምጃን በመዉሰድ የእግዚአብሄርን የማዳን ኃይል ትናገራላችሁ ?
  2. በመዝሙር 107 አንድ ጥቅስ አራት የተለያዬ ጊዜ ተደግሟል ፤ ያ ጥቅስ ምን ነበር ? እግዚአብሄር ለእናንተ አስደናቂ ነገር አድርጎላችኋል ? አመስግናችሁታል ? ትንሽ ደቂቃ በመዉሰድ በዚህ ሳምንት ለሆነዉ የተለዬ ነገር እግዚአብሄርን አመስግኑ ፡፡
  3. ዳዊት “ ልቡ በእግዚአብሄር ፅኑ እንደሆነ “ ተናገረ (መዝ 108፡ 1) ፤ ልባችሁ በእግዚአብሄር ፅኑ ነው ? ለምን ወይስ ለምን ፅኑ አይደለም ?
  4. በመዝሙር (107-109) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 109:30–31

“I will fervently thank the LORD with my mouth; I will praise Him in the presence of many. For He stands at the right hand of the needy to save him from those who would condemn him.”

በመከሰስ ጊዜ እንኳ ፣ የአፍህ ቃል እግዚአብሔርን ያመስግን ፡፡ ተቃውሞ በሚገጥምህ ጊዜ ሳይቀር ፣ እግዚአብሔርን አመስግን ፡፡ ሊደክምህ ይችላል ወይም አቅም እንዳለህ ሁሉ ልትጠራጠር ትችላለህ ፤ ሆኖም ግን እግዚአብሔርን አመስግን ፡፡

መዝሙረኛው እግዚአብሔርን ማመስገንን ማምለክን “ ከፍ ባለ ስሜት “ ይህም ማለት “ ከውስጥ በሚመነጭ ጥልቅ ስሜት ወይም በጋላ ስሜት “ በማለት ይገልጸዋል ፡፡ አስበው እስኪ አንድን የስፓርት ቡድን በጥልቅ ስሜት ስትደግፍ ወይም በክብረ በዓላት ላይ በጋለ ስሜት ስትጮኽ ፡፡ እና እስኪ አሁን አስበው ይህንን ስሜትና ግለት ወደ እግዚአብሔር ስትመልሰው ፡፡ በዚህ ሁሉ ውስጥ በታቃውሞ ውስጥ እንኳ ሳይቀር ፣ ምስጋና እና አምልኮ አቅርብ ፡፡ ከነፍስህ ከውስጥህ እንደልሆነ ቢሰማህ እንኳ እግዚአብሔርን ማመስገን ማወደስ ጀምር ፡፡ ከዚያም ያንን ስሜትና ግለት ከውስጥህ ማመንጨት ትጀምራለህ ፡፡ እግዚአብሔር የሚያስፈልግህን ያያል ፣ እርሱ ረዳትህ ነው ፡፡ እርሱ ተስፋ ቢስነትህን ያያል ፣ እርሱ ተስፋህ ነው ፡፡ እርሱ ድካምህን ያያል ፣ እርሱ ብርታትህ ነው ፡፡ ስብራትህን ያያል ፤ እርሱ ጠጋኝህ ነው ፡፡ በፍቅሩ ይሸፍንሃል ፡፡ እግዚአብሔርን አመስግን ታላቅ ስሙንም አወድስ ፡፡

“ እግዚአብሔርን በአፌ እጅግ አመሰግነዋለሁ። በብዙዎችም መካከል አከብረዋለሁ ፤ ነፍሱን ከሚያሳድዱአት ያድን ዘንድ በድሀ ቀኝ ቆሞአልና ። “ - መዝሙር 109፡30-31

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ዮሐንስ 16:33 — “ በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ ።
  • 1ኛ የጴጥሮስ 2:9 — “ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ “
  • 1ኛ የጴጥሮስ 2:12 — “ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን ። “