God's Faithfulness
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 105-106 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መዝሙር 105 እግዚአብሄር ባለፈዉ ጊዜ ታማኝ ስለ ነበር አሁን እና ወደፊት ታማኝ እንደሚሆን መታመን እንችላለን ወደ ሚለዉ እዉነት ያመለክተናል ፡፡ ነገሮች የሚያጠራጥሩ ወይም የሚያስቸግሩ በመሰሉ ጊዜ በኑሮአችን በእግዚአብሄር የታማኝነት ክስተቶች ላይ መፅናት እንችላለን ፡፡ እናቴ ሁል ጊዜ እነዚህን ክስተቶች ማክበር ያስፈልገናል ትላለች ፡፡ የመዝሙር 105 ጭብጥ ሀሳብ በቁጥር 1-2 ላይ የሚገኝ ነው ፤ እርሱን በማመስገን የእግዚአብሄርን ስራ የታወቀ እናደርጋለን ፡፡ ማክአርቱር ይህ መዝሙር “ የኪዳኑ ታቦት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም በመጣበት ክስተት ጊዜ ዳዊት አሳፍን ሲያዘዉ እንደተጀመረ “ ያመለክታል ፡፡ ማክአርቱር በመናገር የሚሄድባቸዉ አስር ትዓዛዝቶች በመዝ (105፡ 1-4) ከታች የተዘረዘሩትን ዘርዝሯል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (105፡ 1-4)፡ በቁጥር 1 መዝሙረኛው፡ 1) አመስግኑ፣ 2) ስሙንም ጥሩ እና 3) ስራዉን አዉሩ ፡፡ በቁጥር 2-3 ትዕዛዙ ይቀጥላል፡ 4) ለእርሱ ዘምሩ፣ 5) ለእርሱ ምስጋናዉን ዘምሩ፣ 6) ስለ ስራዉ ተናገሩ፣ 7) ቅዱስ ስሙን አክብሩ እና 8) እግዚአብሄርን የሚፈልጉ ልቦች ደስ ይበላቸው ፡፡ ትዕዛዞቹ በቁጥር 4 ያበቁ ናቸው፡ 9) ስለ ኃይሉ እግዚአብሄርን ፈልጉ እና 10) ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉት ፡፡
መዝሙር (105፡ 5-23)፡ በቁጥር 5-6 መዝሙረኛው ከእነዚህ ትዕዛዝቶች እግዚአብሄር ለሕዝቡ ያደረጋቸዉን ነገሮች ወደ መዘርዘር ተጓዘ - ስራዎቹን፣ ድንቆቹን፣ ፍርዶቹን እና ምርጫዎቹን (አብርሃም፣ ያዕቆብ እና ልጆቻቸዉን) ፤ ከዚያም መዝሙረኛው ከእግዚአብሄር ጋር ያላቸዉን ትናትናቸዉን እንደ ገና ፃፈ - ከእነርሱ ጋር ኪዳኑን፣ የምድረበዳ ጊዜአቸዉን እና ሰጥቷቸዉ የነበረዉን ተስፋይቱን ምድር (ቁጥር 7-23) ፡፡ በአሕዛብ መካከል ሲንከራተትና “ በቁጥር ጥቂት በነበሩ “ ጊዜ እግዚአብሄር ከአብርሃም ጋር ነበር ፡፡ እግዚአብሄር “ የመረጣቸዉን/የሾማቸዉን “ ከአሕዛብ ነገስታቶች ጠብቋቸዋል (ቁጥር 14-15) ፡፡ እግዚአብሄር ዮሴፍን ለርሃቡ እና ለዕብራዊያን ለማዘጋጀት ከሕዝቡ ፊት ወደ ግብፅ ላከው ፡፡
መዝሙር (105፡ 24-45)፡ እግዚአብሄር ሕዝቡን በመባረክ ፍሬአማ እንዲሆኑ አደረጋቸው፣ ከጠላቶቻቸዉም በላይ በጣም ብዙ ነበሩ ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቡን እንዲመሩ ሙሴን እና አሮንን በመምረጥ በመካከላቸዉ ተዓምራታዊ ምልክቶችን እንዲያደርጉ ኃይልን ሰጣቸው ፡፡ መዝሙረኛው በግብፅ የሆኑትን መቅሰፍት አንባቢዎች አሳሰባቸው ፡፡ በሁሉም ሁኔታ እግዚአብሄር ቃል ገብቶ የነበረዉን አድርጓል/አድርሷል ፡፡
መደምደሚያ
ስለ መዝሙር 105 ዋረን ዋይርስቤ የፃፈው፡
የእግዚአብሄር ሰዎች በማብራሪያ ሳይሆን በተስፋ ላይ ይኖራሉ ይህም እነዚህ ተስፋዎች ሲፈፀሙ የምናያቸዉ “ በእምነትና በትዕግስት “ ነው (ዕብ 6፡ 12) ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ተስፋዉን ይጠብቃል ማለት በጠላቶች ላይ ድል ከማድረግ እና ባለጠግነትን ከማግኘት በላይ ስለ እስራኤል ነው ፤ ይህ ለእነርሱ ታማኝ የነበረዉን የእግዚአብሄርን የመታዘዝ ኃላፊነት መቀበል ማለት ነው….. እግዚአብሄር ያደረገልንን ሁሉ ስንመለከት ተመሳሳይ ኃላፊነት እንዳለን እናገኛለን ፡፡
በጣም በብዙ እግዚአብሄርን ማመስገን እንፈልጋለን - በመነቃቃት ጊዜ ላይ (2007 አካባቢ) ለ11 አመታት ስላገኘን፡፡ በሁሉም የመንገዳችን እርምጃ ላይ እና ወደ ሄድንበት ስፍራ ሁሉ አብሮን ተጉዟል/ሄዷል ፡፡ ማመስገንን እንቀጥል፣ ስሙን መጥራትን እንቀጥል እንዲሁም ለእርሱ በመታዘዝ በመጓዝ ያደረገዉን መናገር እንቀጥል ፡፡
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 667.
MacArthur, p. 668.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), pp. 283–284.
ጥያቄዎች
-
በመዝ (105፡ 4) “ ፊቱን ሁል ጊዜ ፈልጉት “ ማለት ምን ማለት ነው ? ይህ ለእናንተ ምን ይመስላል ?
-
በመዝሙር 105 ዳዊት ስለ እስራኤል የእግዚአብሄርን ድንቅ ስራዎች መግለጫ ሰጥቷል ፤ እግዚአብሄር ለእናንተ ስላደረጋቸዉ ሁሉም ነገሮች ምላሽ ሰጥታችሁ ታውቃላችሁ ? ዳዊት እንዳደረገው በሁሉም ነገር እርሱን ለመታመን ይህ ያበረታታችኋል ?
-
በመዝሙር 106 መዝሙረኛው ወደ ኃላና ወደ ፊት እግዚአብሄር ሕዝቡን በማዳን ነፃ ከማዉጣት ወደ መቅጣት በሚሄድበት መካከል ሄዷል ፤ እግዚአብሄር አንዳንድ ጊዜ ምህረት የተሞላ በመመሰል ሌላ ጊዜ ደግሞ በህዝቡ ላይ ቁጣዉን ለምን እንዳፈሰሰ ምን ታስባላችሁ ?
-
በመዝሙር 106 የተጠቀሱት የእግዚአብሄር ሰዎች ጥቂት ኃጢዓቶችን ከዛሬ የእግዚአብሄር ሰዎች ኃጢዓት ጋር እንዴት ይነፃፀራል ? በማይረባ መሰረት ላይ/መሬት ላይ እየተጓዝን ያለን ሕዝቦች እንደሆንን ታስባላችሁ ? ዛሬ በኃጢዓታችን ምክንያት የእግዚአብሄርን ቁጣ እንፈራለን ወይስ ማሀሪ መሆንን እንደሚመርጥ ታስባላችሁ ?
-
በመዝሙር (105-106) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 105:1–2
“Give thanks to Yahweh, call on His name; proclaim His deeds among the peoples. Sing to Him, sing praise to Him; tell about all His wonderful works!”
እስኪ የእግዚብሔርን ሊካድ የማይቻል ታማኝነት ያየህበትን አጋጣሚ አሰላስ :- ልታስታውሰው የምትፈልገውን አጋጣሚ እናም በሚመጣው ዘመን እንኳ ልትረሳው የማትችለውን ልክ ፡- ከከባድ ህመም መፈወስ ፣ አስፈላጊ የሆነ እርዳታን በትክክለኛው ጊዜ ማግኘት ፣ ትድግናን ቤዛነትን ያስገኘ የጸና እምነት አጋጣሚ ወይም ደግሞ እግዚአብሔር በተአምራት የተገለጠበት ጊዜ ! ዛሬ እግዚአብሔርን ለማመስገን እና በዙሪያህ ላሉት ስራውን ለማወጅ ጊዜን ውሰድ ፡፡
የእግዚአብሔርን ድንቅ ስራዎች ስታስታውስ ፣ ምናልባት ለታማኝነቱ የምስጋና ፕሮግራም ማዘጋጀት ልትፈልግ ትችላለህ ፡፡ በህይወትህ የእግዚአብሔርን ታማኝነት ለመዘከር ለማስታወስ ለምን ኬክ ወይም ዳቦ አታዘጋጅም ? ምናልባት እግዚአብሔር አንተን የረዳባትን ቀን ለማስታወስ ለሆነ ሰው ለየት ያለ ስጦታ መስጠት ትፈልግ ይሆናል ፡፡ ሆኖም ግን ወደ ኋላ ስትመለከትና ስታስታውስ እግዚአብሔር ይመራሃል ፡፡ ዋናው ነገር ከኢየሱስ ጋር በመጓዝ መጽናት እናም ከዚህ ጋር የእርሱን ታማኝነት ማስታወስ ነው ፡፡ እናም የእርሱን ምስጋና መዘመር ነው ሃሌሉያ !
“ እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ጥሩ፥ ለአሕዛብም ሥራውን አውሩ ። ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፥ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ ። “ - መዝሙር 105፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
- ዘዳግም 8:2 — “ አምላክህ እግዚአብሔር ይፈትንህ ዘንድ፥ በልብህም ያለውን ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያስጨንቅህ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስብ ።
- መዝሙር 105:3–5 — “ በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው ። እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ ። የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ ተአምራቱን የአፉንም ፍርድ ።
- 1ኛ ቆሮንቶስ 11:26 — “ ይህን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ፥ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።