God's Benefits To Us
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 103-104 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ መዝሙር 103 ሳስተምር የእግዚአብሄርን ምሪት ተሰምቶኛል ፡፡ በዚህ መዝሙር የምንመለከተዉ ላይ ስለ ማስታወስ/ትዉስታ ጥቂት የሚያምሩ ነገሮች አሉ፡
ትምህርት
መዝሙር (103፡ 1-19)፡ ቁጥር 1-2 “ እግዚአብሄርን ባርኪ “ በሚለዉ ፅሁፍ ይጀምራል ፤ በመሰረቱ “ ባርኪ “ የሚለዉ ቃል “ በጉልበት ተንበርከኪ “ ማለት ነው ፡፡
“ ነፍሴ ሆይ እና በእኔዉስጥ ያለዉ ሁሉ “ የሚለዉ ሀረግ መዝሙረኛው ለተስፋዉ ሁሉ እና አድርጎት ስለ ነበረዉ ሁሉ በሆነዉ ነገር ሁሉ/ከዉስጡ እግዚአብሄርን ለመባረክ እየናፈቀ እንደ ነበር ያሳያል ፡፡ ምናልባትም እነዚህ ቃሎች በምስጋና ዝማሬ ዘምራችኋል፣ በትክክልም ብለዉት እንደ ነበር የመዝሙሩ ቃላት እንደ አንድ መዝሙር እየተገለፀ ነው ፡፡ ቁጥር 2 አስፈላጊ አንድ ንግግርን ይጨምራል፡ “ ምስጋናዉን ሁሉ አትርሺ “ ፤ እንድንመለከታቸዉ የምፈልገዉ ምስጋናዉን ነው ፡፡ መዝሙረኛው በዚህ መዝሙር ከእግዚአብሄር የመጡትን ቢያንስ 30 ምስጋናዎች/ጥቅሞች ዘርዝሯል ፤ እነዚህ ሁሉ ምስጋናዎች/ጥቅሞች ከእግዚአብሄር ባህሪያ ይመጣሉ ፡፡
- እግዚአብሄር ኃጢዓታችንን ሁሉ ይቅር ብሎናል (ቁጥር 3) ፡፡
- እግዚአብሄር በሽታዎችን ይፈዉሳል ( ቁጥር 3, ኢሳ 53፡ 4-5) ፡፡
- እግዚአብሄር ከጥፋት ሁሉ ያድነናል (ቁጥር 4, መዝ 18፡ 16-17) ፡፡
- እግዚአብሄር በቸርነቱ ይከልለናል (ቁጥር 4) ዮሴፍ ከጉድጓድ ዳነ (ዘፍ 37, 41፡ 38-45) ፡፡
- እግዚአብሄር በሚያቅፍ ምህረቱ ይከልለናል (ቁጥር 4) ፡፡
- እግዚአብሄር በሚበላ መልካም ነገር ያጠግበናል (ቁጥር 5, ያዕ 1፡ 16-17) ፡፡
- እግዚአብሄር ጎልማሳነታችንን እንደ ንስር ያድሳል (ቁጥር 5, ኢሳ 40፡ 31) ፡፡
- እግዚአብሄር የፅድቅን ተግባራን በማድረግ ለተጨቆኑ ሁሉ ይፈርዳል (ቁጥር 6) ፡፡
- እግዚአብሄር መንገዱ ለእኛ እንዲታወቅ ያደርጋል (ቁጥር 7) ፡፡
- እግዚአብሄር ስራዉ ለእኛ እንዲታውቅ ያደርጋል (ቁጥር 7) ፡፡
- እግዚአብሄር የሚምረን እና ይቅር የሚለን ነው (ቁጥር 8, ኤፌ 2፡ 8) ፡፡
- እግዚአብሄር ታጋሽና ለቁጣ የዘገዬ ነው (ቁጥር 8) ፡፡
- እግዚአብሄር በምህረትና በቸርነት የተሞላ ነው (ቁጥር 8, ዘጸ 34፡ 6-9) ፡፡
- እግዚአብሄር ስለ ኃጢዓታችን የጊዜአዊ ቁጣ ይሰጣል/ማለትም ለዘላለም አይቆጣም(ቁጥር 9,ሚክ 7፡ 18)፡፡
- የእግዚአብሄር ቁጣ ለዘላለም አይቆይም (ቁጥር 9) ፡፡
- እግዚአብሄር እንደ ኃጢዓታችን አላደርግብንም (ቁጥር 10, ቲቶ 3፡ 5-7) ፡፡
- እግዚአብሄር ስላደረግነዉ ኃጢዓት የሚገባንን አሁን ከፍሎናል (ቁጥር 10) ፡፡
- እግዚአብሄር ለሚፈሩት የማያልቅ ምህረቱን ያሳያል (ቁጥር 11) ፡፡
- እግዚአብሄር ኃጢዓታችንን አርቆ ያስወግዳል (ቁጥር 12, 2ሳሙ 12፡ 13) ፡፡
- እግዚአብሄር በልጆቹ ላይ በአባትነት ይራራል (ቁጥር 13) ፡፡
- እግዚአብሄር ስሪታችንን እና ፍጥረታችንን ያዉቃል (ቁጥር 14) ፡፡
- እግዚአብሄር ደካማነታችንን ያስባል (ቁጥር 14, መክ 12፡ 7) ፡፡
- የሰዉ ዘመኑ በአጭር የተገለፀ ነው ነገር ግን አሁንም እናፈራለን (ቁጥር 15-16, ኢሳ 40፡ 6-8) ፡፡
- የእግዚአብሄር ምህረት ከዘላለም እስከ ዘላለም ነው (ቁጥር 17) ፡፡
- የእግዚአብሄር ጽድቅ ለዘላለም የተዘረጋ/የሚደርስ ነው (ቁጥር 17) ፡፡
- የእግዚአብሄር ጽድቅ ኪዳኑን ለሚጠብቁት የተሰጠ ነው (ቁጥር 18) ፡፡
- የእግዚአብሄር ጽድቅ ለሚታዘዙት የተሰጠ ነው (ቁጥር 18, ዘዳ 7፡ 9) ፡፡
- እግዚአብሄር በሰማይ የዘላለም ዙፋኑን መስርቷል (ቁጥር 19) ፡፡
- የእግዚአብሄር ልዓላዊ እጁ ሁሉንም ታስተዳድራለች (ቁጥር 19) ፡፡
መዝሙር (103፡ 20-22)፡ በቁጥር 20 መዝሙረኛዉ ወደ እግዚአብሄር ፍጥረቶች ወደ መለዓክቶች ዞረ ፤ እግዚአብሄርን በኃይል ብርቱ የሆኑትን፣ እንደ መልዕክተኞችና አገልጋዮች የሚያገለግሉትንና የእግዚአብሄርን ፍቃድ የሚያደርጉትን መለዓክቱን እንዱባርካቸዉ ጠየቀ (ቁጥር 20-21) ፡፡ መዝሙረኛዉ ወደ መለዓክቱን እንደ ሌላ ጥቅም አመለከተ - በእኛ ላይ በኃላፊነት ስለቆሙ ፡፡ በመጨረሻም መዝሙረኛው እግዚአብሄርን እና ስለ እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር ባረከ - በፍጥረቱ ላይ ስላለዉ የበላይነት፣ ስለ መለዓክቱ እና ስለ ሕዝቡ ባረከው ፡፡
መደምደሚያ
እግዚአብሄር እንዴት ባረካችሁ ? ከእግዚአብሄር ምን ጥቅም/ምስጋና ተቀበላችሁ ? ዛሬ የእግዚአብሄርን ምስጋና ረስታችኋል ? አንዳንድ ጊዜ “ የእርሱ ምስጋና ያልሆነዉን መርሳት “ መርሳት ያስፈልገናል ፡፡ ያደረገላችሁን ሁሉ በማስታወስ ከነፍሳችሁ በመሆን አመስግኑት ፡፡
ጥያቄዎች
-
በመዝ (103፡ 3) መዝሙረኛዉ እግዚአብሄር ሁሉንም በሽታዎቻችንን እንደሚፈዉስ ፅፏል ፤ ይህን ታምናላችሁ ? አንዳንድ ጊዜ ስንፀልይላቸዉ ሰዎች ለምን እንደማይፈወሱ ምን ታስባላችሁ ? (ዘዳ 32፡ 39)
-
መዝ (103፡ 7) “ ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ “ ይላል ፤ በምድረበዳ/በበርሀ እግዚአብሄር ለ40 አመታት ከሙሴ ጋር ተጓዘ ፡፡ ሙሴ እንዳደረገበት መንገድ መንገዱን እንደምናዉቅ ይሰማችኋል ? አዎ ከሆነ እንዴት?
-
መዝ (103፡ 12) “ ምስራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ “ እግዚአብሄር መተላለፋችንን እንደሚያስወግድ ይናገራል ፤ ምን ያክል ይርቃል ? ኃጢዓታችንን ከእናንተ አርቃለሁ ሲል ምን ማለቱ እንደሆን ምን ታስባላችሁ ? (ኤር 31፡ 34)
-
መዝ (103፡ 13) “ እግዚአብሄር ለሚፈሩት እንደሚራራ “ ይናገራል ፤ ይህ ማለት በማያምኑት ላይ ርህራሄ የለዉም ማለት ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
እንደ መዝ (104፡ 1-2) ገለፃ እግዚአብሄር ምን ይለብሳል ? በመዝሙር 104 ላይ የተጠቀሱትን ጥቂት የእግዚአብሄር ባህሪያትን በመግለፅ አሰላስሉአቸው ፡፡
-
በመዝሙር (103-104) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 103:1–2
“My soul, praise Yahweh, and all that is within me, praise His holy name. My soul, praise the LORD, and do not forget all His benefits.”
በህይወትህ ያገኘሃቸውን ሁሉንም የእግዚአብሔር በረከቶች ማስታወስ ትችላለህ ? ለእግዚአብሔር ምስጋናን ለማቅረብና ስሙን ለማወደስ ተጠርተሃል ፡፡ ነገር ግን ግራ የምትጋባባቸው ጊዜያት ይኖራሉ፤ ምን አድርጎ ነው እግዚአብሔርን የማመሰግነው ? እኔ በጉድጓድ ውስጥ ነኝ ፡፡ ድካም እየተሰማኝ ነው ፡፡ እንደው ለመሆኑ እኔ ጋር ምን እየተፈጠረ እንደሆነ እርሱ ያውቃል ? አሁኑኑ መጽሀፍ ቅዱስህን ክፈትና ወደ መዝሙር 103 ሂድ ፡፡ መዝሙረኛው ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ የእግዚአብሔርን በረከቶች እንደገና ያስታውሳል ያወሳል ፡፡ ለአንተ የሆኑትን የእግዚአብሔርን ታላላቅ በረከቶች ከአንዱ የመጽሀፍ ክፍል ወደ ሌላው እየሄድክ ማንበብ ትላለህ ፡፡
ስለዚህ ምንም እንኳ አሁን እግዚአብሔርን እያመሰገንክ እንደሆነ ባይሰማህ እንኳ ፣ ነፍስህ ማመስገንና የእግዚአብሔርን ቅዱስ ስም መባረክ ትችላለች ፡፡ እናም ስታውጅና እነዚህን የምስጋና ቃላት ከአፍህ ስታወጣ ፣ ጠላት ይያዛል ውሸትም በእውነት ፊት አይከናወንም ! በመልካምነት ለሚያጠግብህ እናም ጉልበትህን ለሚያድሰው ለታላቅ ፍቅሩ ምስጋናን አቅርብ ፡፡ ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል ሁሉ የእርሱም ታማኝ ፍቅር እርሱን ለሚፈሩት እንድሁ ታላቅ ነው ፡፡ ዛሬ ታላቅ ፍቅሩንና እግዚአብሔር ለአንተ ያደረጋቸውን ታላላቅ በረከቶች አስታውስ ፡፡
“ ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ አጥንቶቼም ሁሉ፥ የተቀደሰ ስሙን ። ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን ባርኪ፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትርሺ “ - መዝሙር 103፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 103:8 — “ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ ። “
- 2ኛ ቆሮንቶስ 4:6–7 — “ በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና ። ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን ፡፡ “
- ገላትያ 2:20 — “ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።