Wisdom Books Psalms

Praise The King

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 100-102 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 442 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙር 102 እንደ ኃዘን መዝሙር የተገለፀ ነው ነገር ግን የመዝሙሩ መጨረሻ እንደ መሲሀዊ መዝሙር የተገለፀ ነው ፡፡ ለመዝሙር ቃላችን የክብር ንጉስ ነው ስለዚህም የዚህ ጥናት መጨረሻ ወደ ሚመጣዉ መሲህ እንድናመለክት ይረዳናል - ወደ ክብር ንጉሳችን ለማመልከት ፡፡ ዋይርስቤ መዝሙር 102 ከኢየሩሳሌም መፈራረስ/መጥፋት በኋላ እንደተፃፈ ይናገራል ፡፡ በመዝሙሩ ላይ የተቀመጠዉ መግለጫ ከዚህ በፊት ሰምተን ከማናዉቃቸዉ አንዱ ነው፡ “ ባዘነና ልመናዉን በእግዚአብሄር ፊት ባፈሰሰ ጊዜ የችግረኛ ጸሎት “ ፡፡ የፀሀፊዉን ስም አናዉቀዉም ነገር ግን በዚህ መክፈቻ መፍለጫ ላይ ራሱን ገልፆአል ፡፡ ቁጥር 8, 14 እና 16 የመከራ ጊዜ ስፍራን ያስቀመጡ ይመስላሉ ፤ ከ70 የጥፋትና የመከራ ጊዜ በኋላ ፀላዩ እግዚአብሄርን መልሶ ወደ እቅፉ እና ወደ መገኘቱ እንዲያመጣቸዉ ጠየቀው (ኤር 25፡ 11-12, 29፡ 10) ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (102፡ 1-5)፡ መዝሙረኛው እግዚአብሄርን ወደ እርሱ እንዲያደምጥ፣ ከእርሱ ፊቱን እንዳይሸሽግ፣ ወደ እርሱ በትኩረት እንዲሰማ እና በፍጥነት እንዲመልስለት ለመነው (ቁጥር 1-2) ፡፡ በቁጥር 3 ዘመኑ እንደ ጢስ አልቋል - ብልጭ ብለዉ እንደሚጠፉ ይመስላል (መዝ 31፡ 10, 144፡ 4) ፤ በቁጥር 4 መዝሙረኛው በአካሉ ላይ እና በስሜቱ ላይ እየደረሰበት የነበረዉን ገልፃል - አጥንቶቹ እንደ ተቃጠሉ፣ ልቡ መከራ በዝቶበት እንደ ነበር፣ እንደ ሳር እንደ ጠወለገ እና ምግብ እንደማይበላዉ ገልፃል (መዝ 90፡ 4-6, ሰቆ.ኤር 4፡ 8) ፡፡ ስጋዉ ላመል እየኖረ ቢሆንም እንኳን (ቁጥር 5)፣ እየገጠመዉ በነበረዉ ነገር ሁሉ መላዉ ሰዉነቱ የታመመ ሆኖ ነበር - በሁሉም ማጣቶች በአካሉ እያዘነ ነበር ፡፡

መዝሙር (102፡ 6-11)፡ መዝሙረኛው በመቀጠልም ራሱን እንደ ምድረ በዳ ርኩም ከዚያም አካባቢዉን ለመመልከት እንደሄደ እንደ ብቸኛ ድንቢጥ ገለፀ (ቁጥር 6-7) ፡፡ ጠላቶቹም በመስደብ ሁሉንም ቀን ሙሉ ቀልድን አደረጉበት (ቁጥር 8) ፡፡ የሚበላዉ ምንም ነገር አልነበረዉም አመድ ብቻ እንጂ እንዲሁም ከዉሃ ጋር እንባዉን ጠጣ ምክንያቱም ከእግዚአብሄር መገኘት ተለይቶ ተቀምጦ ስለ ነበር (ቁጥር 9-10) ፡፡ ምናልባትም ይህ በእስራኤል መጥፋት ላይ የተደረገ ለቅሶ ሌላ መልክ ነው (መዝ 51፡ 11) ፡፡ ብዙጊዜ “ ጥላ “ የሚለዉ ቃል ሕይወት በአጭር እንደምታበቃ የሚያመለክት ሀሳብ ነው ፤ መዝሙረኛው እንደ ሚሞት ሳር እንደ ደረቀ እና በምድር ላይ ያለዉ ጊዜ አጭር እንደሚሆን ተረዳ (ቁጥር 11) ፡፡

መዝሙር (102፡ 12-14)፡ በቁጥር 12 መጀመሪያ ላይ መዝሙረኛው ቅሬታዉን/ጥያቄዉን ከመዘርዘር እግዚአብሄር ላይ ወደ ማተኮር ይሄዳል/ይዞራል ፡፡ ይህ በመዝሙር ዉስጥ ከምታዩአቸዉ ከጠለቀ ችግር ዉስጥ እግዚአብሄርን በመመልከት የመዉጣት አንዱ ምርጥ ሽግግር ነው ፤ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር መጓዝን ይፈልጋል ፡፡ እንደ ጌታችን እና እንደ አምላካችን “ ለዘላለም በዙፋን ላይ የተቀመጠ “ ነው ፡፡ ማክአርቱር ይህን እንቅስቃሴ “ ከምድር እስከ ሰማይ - ከአጣብቂኙ ወደ እግዚአብሄር “ እንደ ሆነ ይገልፀዋል ፡፡ መዝሙረኛው አንድ ቀን እግዚአብሄር በመነሳት ለኢየሩሳሌም ቸርነትን እንደሚያሳይ ያውቃል ምክንያቱም “ የመሾሚያ ጊዜ ስለመጣ “ (ቁጥር 13-14) ፡፡ አሁን ለዚያ ለተመረጠዉ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም እየተጓዝን እንደሆነ አምናለሁ እንዲሁም አሁን እግዚአብሄር በህይወታችሁ መንቀሳቀስ እንደሚችል አምናለሁ ! እግዚአብሄር የሚሰጠንን ያን ክስተት እንይዛለን ፡፡

መዝሙር (102፡ 15-22)፡ እነዚህ ቁጥሮች የዚህ መዝሙር መሲሀዊ ክፍል ናቸው ፡፡ ዋይርስቤ “ የዳዊት ዙፋን አልፎ ስለ ነበር የዳዊት ልጅ ምድር ላይ እስኪመጣ ድረስ የሚጠየቅ አይሆንም ነገር ግን የእግዚአብሄር ዙፋን በሰማይ ላይ የተጠበቀ እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ የክብር ንጉስ ሲመለስ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ያስተዳድራል (ቁጥር 15) ፤ ይህ ምን እንደሚመጣ የሚያምር ስዕል ነው ፡፡ ይህ መዝሙረኛ መሲሀዊን ቃል ስለሚያዉቅ እግዚአብሄር እርሱና የእርሱ ሕዝብ ደርሶባቸዉ ከነበረዉ ማንኛዉም ነገር የሚበልጥ እንደ ሆነ አስተዋለ ፡፡ ኢየሱስ በስጋ የሆነ ቃል ነው፣ በእርሱና በቃሉ ተስፋን ማግኘት እንችላለን ፤ የፂዎን መታደስ “ በሚመጣዉ ትዉልድ “ የሚመጣ ነው (ቁጥር 18)፡፡ አሌክሳንደር ማክላርን “ የፂዎን አምላክ ህያዉ ሆኖ ፂዎን ልትሞት አትችልም “ ፡፡ ኢየሩሳሌም ልትጠፋ አትችልም ምክንያቱም እግዚአብሄር ለዘላለም ስለሚኖር ፡፡

እግዚአብሄር ከሰማይ ለመሞት የተፈረደባቸዉን ነፃ ለማዉጣት እና ማቃሰታቸዉን ለመስማት ከሰማይ ወደ ታች ይመለከታል (ቁጥር 19-20) ፡፡ እግዚአብሄር የሚያድናቸዉ ሁሉም የእግዚአብሄርን ስም ያመሰግናሉ ያገለግላሉም (ቁጥር 21-22, ኢሳ 2፡ 1-4) ፡፡

መዝሙር (102፡ 23-28)፡ መዝሙረኛው የእግዚአብሄርን ኢየሩሳሌምን መቤዘት ለማየት የሚበቃ ረጅም ህይወት ለመኖር እንደ ፈለገ ገልፆአል ፡፡ እግዚአብሄር ለዘላለም እንደሚገዛ እና በእግዚአብሄርም ፊት የራሱን ትዉልድም ይመሰርታል ፡፡ ቁጥር 27 የሚመጣዉን መሲህ “ አንተ ግን አንተ ነህ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም “(ዕብ 1፡ 10-12)፡፡ እግዚአብሄር ፊተኛና ኋለኛ ነው ፡፡ መዝሙሩ ዘላለማዊነቱንና የክርስቶስ አምላክነትን ያረጋግጣል ፡፡

መደምደሚያ

ስለዚህ ነገሮች የሚያጠቁ/የሚያደክሙ ሲመስሉ እንዴት መልካም ትግልን እናደርጋለን ? እነዚህን ፅሁፎችና የመፅኀፉን ጥቅሶች በመመልከት መያዝ እንችላለን፡

  1. ለእምነት መልካምን ትግል መታገል (1ጢሞ 6፡ 12) ፡፡
  2. በክርስቶስ ሰበሮ መዉጣታችን ቀድሞ ተፈፅሟል ፤ (ሮሜ 6፡ 10-11, 2ቆሮ 5፡ 17, ኤፌ 1፡ 3 – 2፡14) ፡፡
  3. ከእግዚአብሄር ጋር የኢየሱስ ሙሉነትና አንድነት በመፈፀሙ በእነርሱ እና በእኛ መካከል በፍፁም መራራቅ ወይም መለያዬት አይኖርም ፤ (ሮሜ 5፡ 1-2, ኤፌ 2፡ 13-18) ፡፡
  4. ለጥቅማችን በእርሱ እንድናድግ የእግዚአብሄር የፀጋ ስራ በእኛ ዉስጥ ነው ፤ (ሮሜ 8፡ 28, 32፣ ፊል 2፡ 13)፡፡
  5. በክርስቶስ የተደሰትን/ደስተኞች ነን ፤ (ፊል 1፡ 6, ዕብ 12፡ 2) ፡፡

ክርስቶስ በህይወታችሁ ዉስጥ በመሆኑ መልካሙን ትግል መታገል ትችላላችሁ ፡፡ በዚህ ከመኖር ይህን ማስተማር በጣም ቀላል ነው ነገር ግን በህይወታችሁ በክርስቶስ ላይ ስትፀኑ ሁሉም ነገር ቀላል ነው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 274.

  2. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 665.

  3. Wiersbe, p. 275.

  4. Alexander Maclaren; quoted in Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 276.

ጥያቄዎች

  1. በመዝሙር 100 እግዚአብሄርን ለማገልገል እንዴት እንጠነቀቃለን ? እንደ አማኝ በእግዚአብሄር መንፈስ ስለመሞላታችን ማስረጃው ምንድን ነው (ኤፌ 5፡ 18-21) ? በእግዚአብሄር ደስታ የሚሞሉን ጥቂት ሌሎች ነገሮች ምንድን ናቸው ? (ቆላ 3፡ 16-25)
  2. በመዝ (100፡ 3) ማድረግ ስላለብን ምን ይላል (1ነገ 18፡ 39) ? HCSB እግዚአብሄር እንደ ሆነ እዉቅና መስጠት ነዉ ይላል ፤ ይህን ስታደርጉ ችግር የደረሱባችሁ ጊዜያት አሉ ? ለሌሎች እግዚአብሄርን የማሳወቅ ፍራትን እንዴት ልታሸንፉት ትችላላችሁ ? (ዘዳ 31፡ 6)
  3. በቅንነት ልብ መኖር ማለት ምን ማለት ነው (መዝ 101፡ 2, 1ዮሐ 1፡ 6-7) ? በቅንነት ትጓዛላችሁ ወይስ ይህ ለእናንተ ትግል ሊሆን ይችላል ?
  4. መዝሙረኛዉ በመቅሰፍቱ/በችግሮቹ የደከመ ቢሆንም እንዴት በስራዉ/በሀሳቡ ፀና/ቀጠለ ? በእግዚአብሄር በዚህ ሀሳብ በብርሀና ችግሮች ሲኖሩ በእኛ ላይ ምን ይፈጠራል ? ስለ ክርስቶስ አምላክነት ምን ይላሉ ?
  5. የዕብራዊ ፀኃፊ በዕብ (1፡ 10-12) ለኢየሱስ መዝ (102፡ 25-27) ተግብሮታል/ተጠቅሞታል ፤ በእነዚህ ጥቅሶች መሰረት ኢየሱስ ከመለዓክቶች የሚበልጠዉ እንዴት ነው ?
  6. በመዝሙር (100-102) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 101:6–7

“My eyes favor the faithful of the land so that they may sit down with me. The one who follows the way of integrity may serve me. No one who acts deceitfully will live will remain in my presence.”

ሃቀኝነት ለእግዚአብሔር ትልቅ ጉዳይ ነው ፡፡ ይህ ታማኝ መሆንን ደግሞም ተግባርህ ንግግርህንና ልብህን እንድመስል ማድረግን ይጠይቃል ፡፡

ይህ ማለት ምንም የተደበቀ ሚስጥር ሳይኖር ይልቁንም በዚህ ፈንታ ተጨባጭ ፣ እውነተኛ እና ንጹህ መሆን ይጠይቃል ፡፡ እግዚአብሔር ቃልህ “ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም “ እንድሆን ይነግርሃል ፡፡ ህይወትህን በማታለል ስትኖር ጠላት መቆሚያ ቦታ ፣ ምክንያት ያገኛል ፡፡ ጠላት በውሸቶችህ ላይ እንድትመሰረት እንድትቆም ያባብልሃል ፤ ታማኝ አለመሆንህን መቀጠል ቀላል የተሻለ እንደሆነ እንድታምን ያደርግሃል ፡፡ እውነታው ግን ኃጢአት መስራትህን ስትቀጥል መንፈስ ቅዱስን እያጠፋኸው ነው ፡፡

መንፈስ ቅዱሥ ንጹህ ልብን ሊፈጥርልህ ፤ ድንጋይ የሆነ ልብህንም ሊያስወግድና የስጋን ልብ ሊሰጥህ መጥቷል ፡፡ ስለዚህ በውሸት ወይም በማታለል ቦታ ውስጥ ከሆንክ ፣ ልብህን ማርክ ፣ አሳልፈህ ለጌታ ስጥ ፡፡ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ “ ልብ ንጹሆች ብጹአን ናቸው ፣ እግዚአብሔርን ያዩታልና “ አላቸው ፡፡ ዛሬ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከውሸት ራቅ ፡፡ ለጌታ ፣ ለራስህና ለሌሎች ታማኝ ሁን ፡፡ እግዚአብሔርን በደንብ ማገልገል የሚያስችልህን ነጻነት በታማኝነት ተቀዳጅ ፡፡

“ ከእኔ ጋር ይኖሩ ዘንድ ዓይኖቼ በምድር ምእመናን ላይ ናቸው፤ በቀና መንገድ የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል ። ትዕቢትን የሚያደርግ በቤቴ መካከል አይኖርም፤ ዓመፅን የሚናገር በዓይኔ ፊት አይቀናም ። “

  • መዝሙር 101፡6-7

ተጨማሪ ጥቅስ

ምሳሌ 6:16–19 — “ እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች ፤ ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ ፥ ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር ፥ በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር፥ በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ ። “

ሕዝቅኤል 36:26–27 — “ አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ ። መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ፥ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ ። “

ማቴዎስ 5:37 — “ ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው ። “