Praise The King
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 98-99 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እንደ ዋረን ዋይርስቤ ገለፃ ይስሐቅ በጣም ታዋቂዉን ዝማሬ “ ለአለም/የአለም ደስታ “ የሚለዉን ሲፅፍ በአይምሮዉ ዉስጥ 98 መዝሙሮች ነበሩት ፡፡ ዋይርስቤ መዝሙሩ ስለ ኃላፊ ሳይሆን ስለ መሲሀዊ መንግስት እንደ ነበር ተናግሯል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (98፡ 1-3)፡ በመጀመሪያዎቹ ሰዎስት ቁጥሮች የኔልሰን ማብራሪያ እንደ አዳኝ እግዚአብሄርን ለማመስገን አንድ ጥሪ እንደ ነበር ተናግሯል (ቁጥር 1-3) ፡፡ እነዚህ ቁጥሮች በብዙ የመዝሙር 96 ድግግሞሽነት ይመስላሉ ፡፡ መዝሙረኛው እግዚአብሄር አድርጓቸዉ ስለ ነበረዉ ድንቅ፣ ተዓምራትና ስላሸነፋቸዉ ድሎች አመሰገነው (ቁጥር 1)፡፡ እንደ ኔልሰን ማብራሪያ መሰረት “ የእግዚአብሄር ቀኝ እጅ እስራኤልን ከግብፅ ያደነበትን ታላቅ ማዳን የሚያመለክትበት መንገድ ነው “ ፤ ስለዚህም መሆን ከማንፈልግበት ምድር እግዚአብሄር እንዴት እንዳዳነን፣ እንዴት ከመጣንባቸዉ ነገሮች ሁሉ እንደሚያድነን የመዘመሪያ መንገድ ነበር ፡፡
በቁጥር 2 መዝሙረኛው እግዚአብሄር ራሱን ለሕዝብ ሁሉ ገለጠ አለ - ማለትም ለአሕዛብ ሁሉ ፡፡ የእግዚአብሄር አዳኝነት ለአሕዛብ ሁሉ ለመዳረስ የታደቀ ነበር ፤ እግዚአብሄር እስራኤል ለአሕዛብ ሁሉ ብርሃን እንድትሆን ማቀዱ ግልፅ ነው ፡፡ ኢሳ (42፡ 6) እግዚአብሄር የኪዳን ህዝቡ ለአሕዛብ ሁሉ ብርን እንዲሆኑ ሾማቸዉ ይላል ፤ እንዲሁም ደግሞ ኢሳ (49፡ 6) እግዚአብሄር እስራኤልን “ እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሀለሁ “ ይላል ፡፡ ኢሳ (60፡ 3) “ አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገስታትም ወደ መዉጫሽ ጸዳል ይመጣሉ “፡፡ በኑሮአቸዉ በእግዚአብሄር እንቅስቃሴ/ንቅናቄ ምክንያት አሕዛቦች ወደ መሲሁ ይሳባሉ ፡፡ እነዚህ ቁጥሮች እግዚአብሄርን እንደ አዳኝ ለማመስገን መጥሪያ ናቸው ፡፡ በቁጥር 3 እግዚአብሄር ለእስራኤል ፍቅሩንና መታመኑን ስላስታወሰ አሕዛብ ሁሉ ድል አድራጊነቱን አዩ ፤ በምድር ላይ ያለ ሰዉ ሁሉ የእግዚአብሄርን እጅ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ያያል ፡፡ እንደ ማክአርቱር ዮሐንስ አገላለፅ “ እነዚህ ቃሎች በምድር ላይ የእግዚአብሄርን የፅድቅ መንግስት መመስረት ዘይቤአዊ አነጋገሮች ናቸው “ ፡፡
መዝሙር (98፡ 4-6)፡ የኔልሰን ማብራሪያ እነዚህ ቁጥሮች እግዚአብሄርን እንደ ንጉስ የማመስገን ጥሪዎች ላይ የሚያተኩሩ ናቸዉ ይላል ፡፡
መዝሙር (98፡ 4-6)፡ የኔልሰን ማብራሪያ እነዚህን ቁጥሮች እግዚአብሄርን እንደሚመጣ ዳኛ/መስፍን/ፈራጅ የማመስገን ጥሪዎች ላይ የሚያተኩሩ ናቸዉ ይላል ፡፡ እንደ ገና ይህ መዝሙር በብዙ ከመዝሙር 96 ጋር ይመሳሰላል ፤ መዝ (96፡ 1) “ ለእግዚአብሄር አዲስ ዜማ እንዲዘምሩ “ “ምድርን ሁሉ “ ይጣራል ፤ ይህ ትዕዛዝ ከመዝ (98፡ 1) አወዳድሩ ፤ ቀጥሎ መዝ (96፡ 12) ከመዝ (8፡ 8) ጋር አወዳድሩ ፡፡ ሁለቱም መዝሙሮች ተመሳሳይ መጨረሻ አላቸው ፡፡ መዝ (96፡ 13) እግዚአብሄር ምድርን በፅድቅ ለመፍረድ/ለመዳኘት ይመጣል ይላል ፡፡ መዝ (98፡ 9) እግዚአብሄር ምድርን በፅድቅ ይዳኛል ሰዎችንም በፍትህ/በቅንነት ይላል ፡፡
ኮፐር ፒ.አብራም ሰዎስተኛ በመዝሙር 98 መሰረት ስለ መሲሁ ሁለተኛ መምጣት ፅፏል ፤ ለማየት መልካም የሚሆን ሌላ አመለካከትን ያቀርባል፡፡ ለመዝሙር መፅኀፍ ሀረጋችን/ቃላችን የክብር ንጉስ እንደ ሆነ አስታዉሱ ፡፡ የመዝሙር 98 ማብራሪያ ክርስቶስ ተመልሶ ስለሚመጣ መዘጋጀት እንደሚያስፈልገን ነው ፡፡ አብራም ይህ መዝሙር ስለ ክርስቶስ መመለስና በመመለሱም ምክንያት ምድር አዲስ መዝሙር እንደምትዘምረለት ነዉ ይላል (ቁጥር 1) ፤ ቁጥር 2በዚህ ምድር ላይ ስለ ክርስቶስ እንደሚመለስ እንደሆነ ሀሳብ ሲያቀርብ ሌሎች ደግሞ “ ድል አድራጊነቱ “ አይሁዶች ወደ ምድራቸዉ በተመለሱ ጊዜ የእስራኤልን በፋሪሳዊያን (በአሁኑ ኢራን) እና በባቢሎናዉያን ላይ ድል ማድረጓን የሚጠቅስ እንደሆነ ይገምታሉ ፤ ነገር ግን አርምስትሮንግ ይህ ስለ ክርስቶስ እንደሆነና ድል አድራጊነትን እንደሰጠን ሐሳቡን ያቀርባል ፡፡ አርምስትሮንግበቁጥር 3 እግዚአብሄር በክርስቶስ ተስፋዉን ይፈፅማዋል በማለት ቀጠለ ፤ ስለሆነም በቁጥር 4 በክርስቶስ ምክንያት ምድር ሁሉ አዲስ መዝሙር ይዘምራሉ ፡፡ በቁጥር 7 በክርስቶስ መመለስ ምክንያት ምድር ሁሉ በአንድ ላይ ይመጣሉ በማለት ይቀጥላል ፡፡
ስለዚህ ክርስቶስ በምድር ላይ ሊፈርድ ተመልሶ ይመጣል በሚለዉ እዉነት ላይ ምን እናደርጋለን ? ማክአርቱር መዝ (96፡ 13) እና መዝ (98፡ 9) ክርስቶስ በምድር ላይ በሚመለስ ጊዜ ስላለዉ ጊዜ ይናገራሉ ይላል ፡፡ ሐዋ (1፡ 11) ክርስቶስ ወደ ሰማይ በተወሰደበት በተመሳሳይ መንገድ ወደ ምድር ይመለሳል ይላል ፤ ለሁለተኛ ጊዜ ሲመጣ ሊፈርድብን ነዉ የሚመጣው ፡፡ ፍርድ የሚመጣ ከሆነ ለምን የደስታ ምክንያት ይሆናል ? ምክንያቱም ኢየሱስ ለጨካኝነት፣ ለክፉ እና ለሚደርሱብን ለእነዚህ ሁሉ ነገር መጨረሻ ያስቀምጥላቸዋል ፤ ስለዚህ የሚሆነዉን ነገር እንመልከት ፡፡
በራዕ (16፡ 16-21) አርማጌዶን መካሄድ ይጀምራል ፤ በራዕ (17፡ 10) ሰባት ነገስታቶች በአንድ ላይ በመምጣት እርስ በእርሳቸዉ ይዋጋሉ ፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሲመጣ እርስ በእርስ መዋጋታቸዉን በመተዉ ከክርስቶስ ጋር ይዋጋሉ ፡፡ ክርስቶስ በምድር ላይ ለፍርድ ሲመጣ ይህ የሚደርስበት ነገር ነው ፤ ክርስቶስ ይመጣል ለዉጊያም ይመጣል ፡፡ ራዕይ 18 የባቢሎንን መዉደቅና የክፉ ህዝቦች መጠረግን ይገልፃል ፡፡ በራዕይ 19 ከሰባት አመት በኋላ የሚከሰቱ ብዙ ነገሮች አሉ ፡፡ ይህ የሰባት አመት ጊዜ በሰዎስት አመት ተኩል የሰላም ጊዜ ይጀምራል ከዚያም ለሰዎስት አመት ተኩል ደግሞ ሀሰተኛዉ ክርስቶስ ራሱን ስለሚገልፅ ነገሮች መጥፎ ይሆናሉ ፡፡ በመጀመሪያው ሰዎስት አመት ተኩል ቤተ መቅደሱ ተመልሶ ስለሚገነባ ጥቂት የሰላም ምልክቶች/መለኪያዎች አሉ ፡፡ አዉሬዉም ራሱን ከእግዚአብሄር ጋር ለማስተካከል ራሱን በቤተ መቅደሱ በቅድስተ ቅዱሳኑ ያስቀምጣል ፤ በቀጣዮቹ ሰዎስት አመት ተኩል ሁሉም ገሀነሞች ይከፈታሉ ፡፡ አንዳንዶች እንደሚነጠቁ ስለሚያምኑ በእነዚህ ክስተቶች በዚህ አይሆኑም ፤ ነገር ግን ባጋጣሚ እዚህ ከሆናችሁ ክርስቶስ በመምጣት በሰባቱ አመት መጨረሻ ላይ ቤቱን ከሀሰተኛዉ ክርስቶስ፣ ከአዉሬዉ እና ከሀሰተኛ ነቢያቶች በማፅዳት በሚፈርድባቸዉና በእሳት ባህር በሚጥላቸዉ ጊዜ ዝግጁዎች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ ፡፡ ከዚያም ጥቂት የሁለት ቡድኖች ቅሬታ ይቀራሉ፡ የሐሰተኛዉ ክርስቶስ ቅሪቶች እና የእግዚአብሄር ቅሬቶች ፡፡ በዚህ ሁሉ የ1,000 አመት ዘመን አለ ፡፡ በራዕ (20፡ 1-6) ለጥቂት ጊዜ እስከሚለቀቅ ድረስ ለ1,000 አመታት ወደ ሚታሰርበት ጉድጓድ ሰይጣን ይጣላል ፡፡ ስለዚህም በመዝ (98፡ 9) ክርስቶስ በምድር ላይ ሊፈርድ እንደሚመጣ በምናወራ ጊዜ ይህ ስለ ምናወራዉ ሂደት ነው ፡፡ ሰይጣን በጉድጓድ ዉስጥ በሚሆንበት 1000 አመት ጊዜ ኢየሱስ በምድር ላይ ይገዛል ፡፡
በህይወት ዘመናችን ሁሉ በእዉነቱ ያሳየነዉን የክብር ንጉስ በብዙ እንደምንቀርበዉ ስለ ምናዉቅ ይህ በጣም በሚመጣዉ ፍርድ ደስተኛ የሚያደርግ ነው ፡፡ ነገር ግን በህይወት ዘመናችን ቢታይም በጣም አስቸጋሪና ጠንካራ ወቅት ሊሆን እንደሚችል እናስታዉላለን ፡፡ አዎ በክፉዎች ላይ ሁሉ ለመፍረድ ይመጣል ነገር ግን ከዚያ ጋር የሚመጣ ብዙ ነገሮች አሉ ፡፡ እግዚአብሄርን እንደ አዳኝ፣ እንደ ንጉስ እና እንደ ሚመጣ ዳኛ ስናመሰግነው ቤትን ለማፅዳት ይመጣል ፡፡ ከዚህ ሁሉ ሂደት በኋላ ራዕ (20፡ 11-15) ስላልዳኑት ፍርድ ይናገራል ፤ የሞቱት ሁሉም እንደየስራቸዉ ይፈረድባቸዋል ፡፡ በህይወት መዝገብ ላይ ተመዝግበዉ ያልተገኙት ወደ እሳት ባህር የሚጣሉበት ሁለተኛ ሞት አለ ፡፡
ስለሚመጣዉ ፍርድ በማዉራት ስለሚመጣዉ ነገር ስናመሰግን በእዉነት ስለሚመጣዉ ነገር ልንረዳ ያስፈልገናል፡፡
መደምደሚያ
ስለሚመጣዉ ፍርድ በምናስብ ጊዜ ሰዎችን ልታዘጋጁበት የምትችሉት ምርጡ መንገድ ስለ መልካሙ ዜና መንገር ነው ፡፡ ይህ ለመናገር ካልፈለጋችሁ ዘምሩት ፡፡ በመምጣቱ ለአለም ደስታ ነው ! መልካሙን ዜና በማድረስ ለክርስቶስ ተመልሶ መምጣት ሁሉም ሰዉ የተዘጋጁ እንዲሆኑ እንፈልጋለን ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 981.
Nelsons, p. 714.
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 662.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 714.
Nelson’s Commentary, p. 714.
Cooper P. Abrams, III, “2nd Coming of the Messiah,” www.bible-truth.org; audio available at https://www.bible-truth.org/1Au-Sermon7.mp3.
MacArthur, p. 662–663.
ጥያቄዎች
-
በመዝ (98፡ 2) መዝሙረኛው እግዚአብሄር በአሕዛብ ፊት ፅድቁን ገልጦ ነበር ባለ ጊዜ ምን አስቦ ነበር ? (ዘዳ 4፡ 5-6)
-
እግዚአብሄር እግዚአብሄር በመሆኑና እና ስላደረገላችሁ ነገር ለእግዚአብሄር የዘመራችሁትና በደስታ የጮኸችሁበት የመጨረሻ ጊዜ መቼ ነበር ? ይህን ያለማቋረጥ ማድረግን እንድታቆሙ ምን ምክንያት ሆናችሁ ? ለትንሽ ጊዜም ከሆነ አሁን አመስግኑት !
-
ጌታ ድል አድራጊነቱን/አዳኝነቱን እንዴት የታወቀ አደረገ ? (ዮሐ 3፡ 16, ሮሜ 5፡ 8) ?
-
በመዝሙር 99 መዝሙረኛዉ እግዚአብሄርን እንደ ቅዱስ ምን ያክል ጊዜ ገልፆታል (ኢሳ 6፡ 3) ? ቅዱስ ማለት ምን ማለት ነው ?
-
በመዝሙር (98-99) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 98:8–9
“Let the rivers clap their hands; let the mountains shout together for joy before the LORD, for He is coming to judge the earth. He will judge the world righteously and the peoples fairly.”
ምድር ሁሉ በእልልታ እና በዝማሬ ከተራራ ጫፍ እስክ ባህር ድረስ ይሰበሰባሉ ፡፡ በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ለህዝብ ሁሉ የፍርድ ቀን እንደሚሆን ይናገራል ፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን ፡- በምክንያት የሚዳኝ ብሎ ይጠራዋል ፡፡ ሞቅ ያለ ፣ ደስ የሚል መልዕክት አይደለም እናም አንዳንዴ እውነት ነው ብሎ ለመቀበል ያስቸግራል ፡፡ ነገር ግን እውነት ነው ሁሉም ህዝብ ፍርድን ያገኛል ፡፡ ሁሉንም የሚያውቀውና የሚያየው እግዚአብሔር ፤ አንድ ሰው ኢየሱስን እንደ መንገድ ፣ አውነትና እና ህይወት እንደሚያምንና እንደማያምን ያውቃል ፡፡ እነዚህ የሚያምኑት ከኢየሱስ ጋር የዘላለም ህይወት ይኖራቸዋል ፤ የማያምኑት ግን ወደ እሳት ባህር ይጣላሉ ፡፡
እስካሁን ህይወትህን ለኢየሱስ አሳልፈህ ካልሰጠህ ፣ ምን ትጠብቃለህ ታድያ ? ቀኑን ወይም ሰዓቱን አታውቅም ነገር ግን ኢየሱስ ተመልሶ ይመጣል ፡፡ ያ ማለት የፍርድ ቀን እየመጣ ነው ፡፡ ህይወትህን ለጌታ ስጥ እናም በፍርድ ቀን የዘላለማዊ ደህንነት ጥበቃ ይኖርሃል ፡፡ ፍርሃት ፣ ጭንቀት ፣ ግራ መጋባት የለም ፡፡ ሰላም ብቻ ፡፡ ህይወትህን ለጌታ አሳልፈህ ብትሰጥ ፣ ከእርሱ ጋር ለዘላለም ትሆናለህ ፡፡ ስለ ታላቅ ስራዎቹ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን ፡፡
“ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፤ ተራሮች ደስ ይበላቸው፥ በምድር ሊፈርድ ይመጣልና ። ለዓለምም በጽድቅ ለአሕዛብም በቅንነት ይፈርዳል ። “ - መዝሙር 98፡8-9
ተጨማሪ ጥቅስ
- ኢሳይያስ 44:23 — “ ሰማያት ሆይ፥ እግዚአብሔር አድርጎታልና ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና አንተ የምድር ጥልቅ ሆይ፥ ጩኽ እናንተም ተራሮች አንተም ዱር በአንተም ያለ ዛፍ ሁሉ፥ እልል በሉ ። “
- ዮሐንስ 3:16 — “ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና ። “
- ራእይ 20:11–12, 15 — “ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፥ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ ስፍራም አልተገኘላቸውም ። ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ…….. በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።