King Of The Earth
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 96-97 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
መዝሙር 96 ንጉሳዊ መዝሙር ነው ይህ ማለት ትኩረቱ በንጉሳዊነት ላይ ነዉ ማለት ነው ፡፡ ለዚህ መዝሙር ንዑስ ርዕሱ “ የምድር ንጉስ “ ነው ፡፡ በእርሱ ላይ ስናተኩር - በክብር ንጉስ ላይ - ጨዋታ ቀያሪ ነው ፤ ከራሳችን ላይ አይኖቻችንን በማንሳት በምድር ንጉስ ላይ ስናተኩር ሁሉም ነገር ይቀየራል ፡፡ ማክአርቱር ዮሐንስ መዝሙር 96 “ ከሁሉም የምድር ሕዘቦች ለጌታ የመንግስት ምስጋናን ተስፋ ያደርጋል “ ብሏል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (96፡ 1-3)፡ መዝሙረኛዉ “ ለእግዚአብሄር አዲስ ምስጋናን አመስግኑ ፤ ምድር ሁሉ….” በሚለዉ ሀረግ ጀምሯል ፤ ይህ ወደ አይምሮ ሁሉም ሕዝቦች በአንድ ላይ ለእግዚአብሄር አዲስ መዝሙር ለመዘመር ይመጣሉ የሚለዉን ስዕል ያመጣል ፡፡ በተጨማሪም መዝሙረኛው “ ክብሩን በአሕዛብ መካከል ተናገሩ….እግዚአብሄር ታላቅ ምስጋናዉም ብዙ ነዉና “ (ቁጥር 3-4) በማለት አሳሰበ ፡፡ ሁላችንም እግዚአብሄርን ማመስገን መቀጠል አለብን ፤ ኢሳ (2፡ 2-4) የመንግስትን ምስጋና አስተሳሰብ ገልፃል ፡፡ የኢሳያስ ቃል ለእግዚአብሄር አዲስ መዛሙር ለመዘመር በአንድ ላይ እንደሚመጡ ስዕሎች/መልኮች ናቸው ፡፡
ዋይርስቤ የመጀመሪያዎቹን ሰዎስት ቁጥሮች “ ዘምሩ ! ዜናዉ መልካም ነው ! “ በቁጥር 2 “ ዕለትዕለትም ማዳኑን አዉሩ “ የሚለዉ ሀረግ የእግዚአብሄርን የተቤዢነት እቅድ ለሌሎች መመስከርን የሚያካትት የእዉነተኛ ምስጋና ስዕል ነው ፡፡ በሌላ ቋንቋ መልካሙን ዜና በመዝሙር እንሰብካለን ፤ በዮሐ (4፡ 22) ኢየሱስ እንድንናግረዉና ስለ ምንዘምረዉ ድነት ተናግሯል - በአይሁዶች በኩል ስለሚመጣዉ ድነት ፡፡ ኢየሱስ አሜሪካዊ አልነበረም፣ አሕዛብ አልነበረም፣ ወንጌላዊም አልነበረም፣ አይሁድ ነበር ፤ ስለሆነም ድነት ከአይሁዶች ይመጣል ፡፡ በዮሐ (14፡ 6) ኢየሱስ ይህን “ እኔ መንገድና እዉነት ሕይወትም ነኝ ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም “ ሲል አረጋገጠው ፤ በሐዋ (4፡ 12) ጴጥሮስ በድፍረት “ መዳንም በሌላ በማንም የለም ፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና “ በማለት ተናገረ ፡፡ ኢየሱስ አምላክ ነው ፤ እግዚአብሄር ልጁን ኢየሱስን እንደ አንድ አይሁዳዊ ሰዉ ምድር ላይ ስለላከው ድነት ከኢየሱስ ይመጣል ፡፡ ይህ ልንናገረዉ/ልናጋረዉ የሚገባን መልዕክት ነው ፤ ይህ ዜና የሆነ ስፍራ ላይ ሁሉም ህዝብ ስለሚዘምሩለት በጣም መልካም ነው ፤ ኢየሱስ ንጉስ ነው !
መዝሙር 67 ተመሳሳይ መልዕክት ይደግማል - ሕዝቦች በመደሰት ክብሩን ያውጃሉ ፡፡ አንድ ቀን የእግዚአብሄር የምህረት መልዕክት የታወቀ ይሆናል ፤ መዝ (62፡ 2) “ ማዳኑን ዕለት በዕለት እንድንናገር “ ያዘናል ፡፡ አሕዛብ ሁሉ እርሱን ለማምለክ/ለእርሱ ለመስገድ ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ ፤ ይህ ዝማሬ ትንቢታዊ ስዕል፣ መሲሀዊ መዝሙር አሕዛብ ሁሉ በመስገድ ሲያመልኩት ሁለተኛ ጊዜ ሲመጣ የሚዘመር ንጉሳዊ መዝሙር ነው ፡፡ በእዉነት የእግዚአብሄርን ማዳን ስትቀምሱት በመዘመር ትሄዳላችሁ ቢያንስ ደግሞ ስለ ነገሩ ትናገራላችሁ ፡፡
ሰዎች ወንጌልን ለመናገር ስለ ብዙ ምክንያቶች ያመነታሉ ፡፡ ወንጌልን ስለ መናገር ሊጨነቁ ወይም ተቀባይነትን በማጣት ይፈራሉ ምክንያቱም ሰዎች የሚሉትን ስለማይወዱት ፡፡ የምንፈራቸዉን ማዳመጥ ወይም የእግዚአብሄርን መንፈስ ማዳመጥ እንችላለን ፡፡ መልካሙን ዜና ከመናገራችን በፊት ሁሉም ሰዉ ኃጢዓት ማድረጉንና ከእግዚአብሄር ክብር መዉደቅን እዉቅና መስጠት አለብን (ሮሜ 3፡ 23) ፡፡ መልካሙን ዜና ለመዘመር የምንዘምረዉን ልናዉቅ ይገባናል፣ ዜማዉንም ልናዉቅ ይገባል ፡፡ አሕዛብ ሁሉ በአንድ ላይ ይመጣሉ የሚለዉ ተስፋ የሆነ ሰዉ ወንጌልን ተናግሮ መልዕክቱን ያደርሳቸዋል ማለት ነው ፡፡ ሮሜ (6፡ 23) የሚነግረን “ የኃጢዓት ደመወዝ ሞትነዉና ፤ የእግዚአብሄር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው “ ፤ ሁላችንም ኃጢዓተኞች ስለሆን ሞት ያገኘናል፣ ኃጢዓት ወደ ሞት ያመጣል ፤ ነገር ግን ገና ኃጢዓተኞች እያለን ክርስቶስ ለእኛ በመሞት እግዚአብሄር ለእኛ ፍቅሩን አሳዬም አረጋገጠም ( ሮሜ 5፡ 8) ፡፡ አሁን ስለ መልካሙ ዜና መዘመር ጀምረናል - ስለ እግዚአብሄር ፍቅር ፤ ኤፌ (2፡ 8-9) “ በእምነት በጸጋዉ ድነናል “ ፡፡ ለመዳናችን ያደረግነው መልካም ነገር ምንም የለም ፣ መዳናችን ኢየሱስ ባደረገዉ ነገር ላይ ባለን እምነት ላይ የተመሰረተ ነው ፤ ይህ ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነና እግዚአብሄር ከሞት እንዳስነሳው እምነታችንን በአፋችን እንድንናገር ይመራናል/ያደርገናል (ሮሜ 10፡ 9-10) ፡፡
መዝሙር (96፡ 4-6)፡ ዋይርስቤ ዜናዉ መልካም ስለሆነ ከመዘመር በተጨማሪ አምላካችን ታላቅ ስለሆነ እናመሰግነዋለን ብሏል ፡፡ “ የህዝቦች ሁሉም አማልዕክቶች ጣዖቶች ናቸው “ ማለትም ዋጋ ቢስ እና ደካሞች ናቸዉ ማለት ነው ፡፡ በዚህ ላይ ጥናት በምታደርጉ ጊዜ በቤተ መቅደሱ በኢየሩሳሌም ተወስኖ መኖሩን የእግዚአብሄር ክብርን መልክ በትክክል ይስላሉ ፡፡ አሁን ሕዝብ ሁሉ እግዚአብሄርን እያመሰገነ ነዉ ምክንያቱም ስሙ በቤተ መቅደሱ ላይ ታላቅ ስለሆነ ፡፡
መዝሙር (96፡ 7-9)፡ ከመዘመር እና ከማመስገን በተጨማሪ ዋይስርቤ እግዚአብሄር የተገባዉ ስለሆነ እናመልከዋለን ብሏል ፡፡ እንደ ምድር ንጉስ አሕዛብ ሁሉ፣ ምድር ሁሉ የሚያመልኩበትን ቋሚ ስዕሎችን ትወዷቸዋላችሁ ?
መዝሙር (96፡ 10-13)፡ ዋይርስቤ ንጉሱ ስለመጣ እንደሰታለን ብሏል ፡፡ ምን አይነት አስደናቂ መልክ ነው ! መዝሙር 96 ንጉሱ እንደሚመጣ እና የምንዘምርለትን መልካም ዜና እንዳገኘነዉ ተንብዮአል ፡፡ ማክአርቱር ዮሐንስ “ በዚህ መዝሙር ጌታ የገለፀዉ ትዕዛዝ በአሁኑ አለምአቀፍ መንግስት የሚገኝ አይደለም (መዝሙር 93) ነገር ግን ክርስቶስ ወደ ምድር በሚመለስ ጊዜ አንዴ የሚመሰረት እንደሆነ “ ተናግሯል ፡፡
መደምደሚያ
ቀላሉ ጥያቄ ለሚመጣዉ ንጉስ ተዘጋጅታችኋል ? እንዴት ተዘጋጃችሁ ? እንደሚመጣ ስለምናዉቅ እንዘምራለን፣ እናመሰግነዋለን፣ እናመልከዋለን እንዲሁም እንደሰታለን ! በራዕ (3፡ 11) ኢየሱስ በቶሎ እንደሚመጣና ያለንን አክሊል ማንም መዉሰድ እንዳይችል እንድንፀና ተናግሯል ፡፡ አምላካችን ታላቅ እንደሆነ፣ ጌታ የከበረ እንደሆነ እና ንጉሱ እንደሚመጣ በሚለዉ መረዳት ላይ ስንፀና ዛሬ በዚህ እንደሚሆን በማድረግ እንኖራለን ፡፡ በራዕ (22፡ 12) ኢየሱስ ያለው “ እነሆ በቶሎ እመጣለሁ ለእያንዳንዱም እንደ ስራው መጠን እከፍለዉ ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር ነው “፡፡ በተሰጠን በማንኛዉም ክስተት ላይ ኢየሱስ እየተመለከተ ነው፣ ተመልሶም የሚመጣ ነው ፡፡ እንዘጋጅ ፡፡
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 661
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 979.
Wiersbe, p. 980.
Wiersbe, p. 980.
MacArthur, p. 662.
ጥያቄዎች
-
በመዝሙር 96 ዉስጥ በቁጥር ሰዎስት ላይ ለአብርሃም ያያችሁት የእግዚአብሄር ተስፋ እንዴት ነበር (ዘፍ12፡ 1-3) ? ለደቀ መዛሙርቱ ለጠፋዉ አለም መልካሙን ዜና እንዲያሰራጩ የኢየሱስን ትዕዛዝ እንዴት ታዩታላችሁ ? (መዝሙር 67, ማቴ 28፡ 18-20)
-
በመዝሙር 96 መዝሙረኛዉ ሁሉንም አማልዕክቶች ከእዉነተኛዉ አንዱ እግዚአብሄር ጋር ለማወዳደር እንዴት አደረገ ?
-
መዝሙር 96 በሌላ ክፍል በ 1ዜና (16፡ 23-33) ላይ የሚገኝ ነው ፤ ዳዊት ለእግዚአብሄር አምልኮና ምስጋና የተናገረዉ በቁጥሮቹ ምን ተፈጥሮ ነበር ?
-
በመዝሙር 96 ላይ መዝሙረኛዉ የት ላይ ቀድሞ ስለ ሚመጣው መሲህ ዘመን ተመለከተ ?
-
መዝሙር 97 እንደ እግዚአብሄር ዙፋን መሰረት ምን አወጀ/ተናገረ ? መዝ (97፡ 2-3) እግዚአብሄርን እንደገለፀው በመፅኀፍ ሌላ የት ላይ መግለጫዉን ልታገኙት ትችላላችሁ ? (ዘጸ 19፡ 16-20)
-
በመዝሙር (96-97) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 96:10
“Say among the nations: ‘The LORD reigns. The world is firmly established; it cannot be shaken. He judges the peoples fairly.’”
እግዚአብሔር በምድር ላይ ነግሷልና ምድር ጸንታ ቆማለች ፡፡ እስኪ ለደቂቃ ያክል ይታሰብ ፡፡ ምድር ሁሉ “ እግዚአብሔር ነገሠ “ ይበል ፡፡ እግዚአብሔር የሰማይና የምድር ፈጣሪ ብቻ አይደለም ነገር ግን እርሱ ንጉሡም ነው ፡፡ እናም ኋያሉ አምላክ እግዚአብሔር እንደ ንጉሥ ስለ ነገሠ ፣ አለም አትናወጥም ፡፡ ተስፋህን በሁሉም ነገር ላይ በነገሠው በእርሱ ላይ ….. በክብር ንጉሥ ላይ አድርግ ፡፡
ዛሬ አድስ መዝሙር ዘምር ፡፡ የእግዚአብሔርን ክብር ተናገር ፤ አዳኝነቱን አውጅ እና በምድር ላይ ባሉ ህዝቦች መካከል ስለሰራቸው ድንቅ ስራዎች አመስግነው ፡፡ በቤት ውስጥ ሆነህ ብችህን የምትሆንበትን አጋጣሚ ፈልግ ወይም በመኪናህ ውስጥ አለበለዚያም ለእንቅስቃሴ ወደ ውጭ ውጣ እናም ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር ዘምር እናም ስሙን አውጅ ፡፡ ተዘጋጅ ? አፍህን ክፈት እናም ቃላቶችህ በዜማ መልክ እንደ ቅኔ ይፍሰሱ ! በእርግጥም እግዚአብሔር መመስገን ይገባዋል !
“በአሕዛብ መካከል፦ እግዚአብሔር ነገሠ በሉ። እንዳይናወጥም ዓለሙን እርሱ አጸናው፥ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል ። “ - መዝሙር 96፡10
ተጨማሪ ጥቅስ
- ነህምያ 9:6 — “አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ፤ ሰማዩንና የሰማያት ሰማይን ሠራዊታቸውንም ሁሉ፥ ምድሩንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ፥ ባሕሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ፥ ፈጥረሃል፥ ሁሉንም ሕያው አድርገኸዋል፤ የሰማዩም ሠራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ ። “
- መዝሙር 47:8 — “ እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ፤ እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል ። “
- መዝሙር 96:1–3 — “ለእግዚአብሔር አዲስ ምስጋናን አመስግኑ፤ ምድር ሁሉ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ ። እግዚአብሔርን አመስግኑ ስሙንም ባርኩ፥ ዕለት ዕለትም ማዳኑን አውሩ ። ክብሩን ለአሕዛብ ተኣምራቱንም ለወገኖች ሁሉ ንገሩ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።