Worship And Warning
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 94-95 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የመዝሙር መፅኀፍ እንዴት ወደ መሲሁ እንደሚያመለክት ሀረጋችን የክብር ንጉስ ነው ፡፡ ሁሉም መዝሙር በአምልኮ በመዘምራን ወይም በሕዝቡ ተዘመረ ማለት እንደ ነበር ያስታዉሳል ፡፡ ማክአርቱር መዝሙር 95 “ በምድረበዳ መንከራተት በዳስ በዓል (መዝሙር 81) በዳዊት የተቀናበረ እንደሆነ (ዕብ 4፡ 7) እንደሚያመለክት “ ያስቀምጣል ፡፡ በዳስ በዓል ጊዜ ምዕመናኖቹ በምድረበዳ ሲጓዙ በነበሩበት ጊዜ ለመቆየት እግዚአብሄር እንዴት መግቧቸዉ/አኑሮአቸዉ እንደ ነበር ለማስታወስ ጊዜያዊ ዳሶችን ይገነባሉ ፡፡ ማክአርቱር “ ለአምልኮ ከመጠራት በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ጣልቃ በመግባት የአመፅና እግዚአብሄርን የመፈተን አደገኝነትን ሕዝቡን እንደሚያሳስባቸዉ “ ይገልፃል ፡፡ ይህ የእግዚአብሄርን አምልኮና የእግዚአብሄርን ማስጠንቀቂያ ሁለቱንም አባቶቻቸዉ እንደ ነበራቸዉ እንዳልተደረገ ያቀርባል ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ በዚህ መዝሙር ላይ የምዕመናን ሰዎስት ስሜታዊ ሁኔታዎች እንዳሉ አመልክቷል፡ “ 1) በማክበር ሁኔታ እግዚአብሄርን ማምለክ (ቁጥር 1-5)፣ 2) በታሰበ ሁኔታ እግዚአብሄርን ማምለክ (ቁጥር 6-7)፣ 3) በመታዘዝ እግዚአብሄርን ማምለክ (ቁጥር 8-10) “ ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (95፡ 1-5)፡ ዋይርስቤ ቁጥር (1-5) “ በመምጣት እግዚአብሄርን ማመስገን “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ ቁጥር 1 አምላኪዎች/መዕምናን ወደ መዳኛ አለታቸው (1ቆሮ 10፡ 4) ወደ እግዚአብሄር በኃይል እንደሚጮኹ ይናገራል ፡፡ ቁጥር 2 እግዚአብሄር “ የአማላዕክት ሁሉ በላይ “ (ቁጥር 3) እና ከሁሉም ነገር በላይ ስለሆነ በአምልኮ ነዉጥ /ደስታ እንደሚሆን ይገልፃል (ቁጥር 4-5) ፡፡ ይህ እንዴት እንደሚመለክ የሚያሳየዉ መግለጫ ወደ ክብር ንጉስ ያመለክታል፡
በእነዚህ ቁጥሮች ላይ ተመልሰን በእነዚህ ሀረጎች ላይ እናተኩር፡
- የመዳኛችን አለት - በጉዞ ዉስጥ የምናገኘዉ መንፈሳዊ ፍሬ ነገርን ሰጥቶናል ፤ ኢየሱስም እንደ አለት የተገለፀ ነው (ለዘኁልቁ የሪቫይቭ ት/ቤት ቃል) ፡፡
- ታላቅ አምላክ ከአማልዕክቶች ሁሉ በላይ ታላቅ ንጉስ - በሐዋ (2፡ 33) ኢየሱስ ከሌሎች ሁሉ በመብለጥ በእግዚአብሄር ቀኝ እጅ እንደ ሆነ የተገለፀ ነው (ፊል 9፡ 2-11) ፡፡
- ምንም ከእግዚአብሄር ሊለየን አይችልም - ሮሜ (8፡ 37-39) ጳዉሎስ ከኢየሱስ ምንም ነገር ሊለየን እንደማይችል ተናግሯል ፡፡
ስለዚህ ክርስቶስን እንዴት እናመልከዋለን ? እርሱን ለማምለክ ወደ መገኘቱ በመምጣት በምስጋናና በደስታ ጩኸት ዉስጥ ፡፡
መዝሙር (95፡ 6-7)፡ የአምልኮ አቋቋም ተገልጧል - ወደ ታች በመደፋት በእግዚአብሄር ፊት በመንበርከክ ፡፡ ኢየሱስ ፈጣሪ/ሰሪ ነው (ዕብ 1፡ 2) ፡፡ መዝሙረኛው መዕምናኖቹን/አምላኪዎቹን እንደ ማሰማሪያዉ ሕዝቦች፣ በታላቁ እረኛ ስርም እንዳሉ በጎች ገልፃአቸዋል ፤ እዚህ ላይ ኢየሱስ እንደ መልካም እረኛ ተገልፆ ነበር (ዮሐ 10፡ 11) ፡፡
መዝሙር (95፡ 7-11)፡ ቁጥር 7 በትዕዛዝ ያበቃል፡ ድምፁን የሚሰሙ ከሆነ በእግዚአብሄር ላይ ልባቸዉን ማደንደን አልነበረባቸውም ! አባቶቻቸው እግዚአብሄር በእነርሱ ላይ “ ፊቱን እስኪያዞር “ ድረስ እግዚአብሄርን በመፈጠን ሞክረዉ ነበር (ቁጥር 8-10) ፡፡ ስለሆነም እግዚአብሄር ረፍትን አይሰጣቸዉም በምድረበዳም ያደርጋቸዋል ፡፡ ኢየሱስ እንደ እረኛ ተጣራ በጎቹም ተከተሉት ምክንያቱም ድምፁን ስለሚያዉቁ (ዮሐ 10፡ 4, 16) ፡፡ እስራኤላዊያን በግልፅ ድምፁን ይሰማሉ ነገር ግን ጥያቄው እንዴት እንደሚመለሱለት ሆኗል ፡፡
የመጀመሪያዉ ትዉልድ በቃዴስ በመሪባ የነበረዉ ክስተት በእግዚአብሄር ትዕዛዝ ላይ አመፅ ነበር (ዘኁ 20፡ 1-13) ፤ የሚያስፈልጋቸዉን ዉሃ እግዚአብሄር እንደሚሰጣቸዉ አላመኑም ምክንያቱም አድርጎላቸዉ የነበረዉን ስለረሱ ፡፡ እግዚአብሄር “ ልባቸዉ ስቶ የሚሄድ ህዝብ ፤ መንገዴን የማያዉቁ “ በማለት ገልፃቸዋል (ቁጥር 10) ፡፡
መደምደሚያ
የእግዚአብሄርን ድምፅ መስማት አስቸጋሪ አይደለም ፡፡ እንደ መልካም እረኛ በጎች የምንሰማዉ የመጀመሪያዉ ነገር የኢየሱስ ድምፅ ነው (ሮሜ 8፡ 14) ፤ ከዚያም የራሳችንን ድምፅ በመስማት በእዉነት የእግዚአብሄርን ድምፅ ሰምተን እንደሆን መጠየቅ ፤ በመጨረሻም የእግዚአብሄርን ድምፅ ሊያቃልሉ የሚሞክሩትን የጠላቶቻችንን ድምፅ እንሰማለን ፡፡ እነዚህ ሁሉ ወደ ጠንካራ ልብ ይመራሉ ፡፡ ከእኛ ዉስጥ አብዛኞቻችን በምድረበዳ እየተንከራተትን ነዉ ምክንያቱም የእረኛዉን ድምፅ መስማት ስለማንችል ፡፡ ዕብ (3፡ 7-11) መዝሙር 95 ይጠቅሳል ፡፡
ካይል፡ “ እግዚአብሄር ልቤን በመጠበቅ ልታጠራልኝ ትጀምራለህን ? ይህ በእዉነት አንተ እንትመራኝ እፈልጋለሁ ይህን በራሴ ማድረግ አልፈልግም (መዝ 139፡ 23-24) ፤ ደንዳና ልብ ዉሳኔዬን፣ ሀሳቤን እና ቃሌን ተፅዕኖ ሊያደርግበት እንደሚችል ተፅዕኖዉን አስታዉላለሁ ፤ እንዲህ አይነት ጠንካራ ልብ ስላለኝ ይቅር እንድትለኝ እጠይቅኃለሁ ፡፡ ጌታ ሆይ ጠንካራ ልብ ላላቸው እዚህ ስፍራ እንዴት መድረስ እንደሚችሉ ለማያዉቁት፣ በአንተ ድምፅ መታመን ያልቻሉትን ነገር ግን በራሳቸዉ ብቻ የሚታመኑትን ፈትነህ፣ አጥርተህ ጠንካራ ልብን በመስበር ልክ እንደ ሸክላ ተሰባሪ/ያልደነደነ ልብ ፍጠርላቸው ፡፡ ልባችንን ልል/የለሰለሰ/የሚሰበር አድርግልን ይህ ከሆነ አንተን ለመመስል የምንሰራ እንሆናለን ፡፡ እግዚአብሄር ሆይ በአንተ ብቻ መመራት፣ በእረኛ እንደሚመራ በግ ድምፅህን ብቻ መስማት እንፈልጋለን ፡፡ ወደ አንተ መምጣት በመቻል ለእርዳታ ስንጠይቅ እናመሰግንሀለን እናመልክሀለንም፡፡ ጌታ ሆይ ልባችንን የሚያጠነክሩትን እነዚህን ነገሮች ስበርልን በስምህ ስልጣን ፀለይን ፤ አሜን “ በማለት ይፀልያል ፡፡
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 661.
MacArthur, p. 661.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 712.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 259.
ጥያቄዎች
-
መዝ (94፡ 1) በቀል የእግዚአብሄር እንደሆነ ይናገራል ፤ በራሳችሁ እጅ በቀልን ለመዉሰድ/ለማድረግ የሞከራችሁበት ጊዜ አላችሁ ? ምን ተፈጠረ ?
-
በተሳሳተ ተግባር ስለ ነገሩ ማንም ሳያዉቅ ተለይታችሁ ታውቃላችሁ ? መዝ (94፡ 8-11) ስለዚህ ነገር ምን ይላል ? እግዚአብሄር የሚወዳቸዉን ለምን ይቀጣቸዋል ? (መዝ 94፡ 13-14, ምሳ 3፡ 11, 19፡ 20, ዕብ 12፡ 7, ራዕ 3፡ 19)
-
መዝ (95፡ 8) “ ልባችሁን አታደንድኑ “ ይላል ፤ በጣም ብዙ ጊዜ ለእግዚአብሄር ልባችሁን በምታደነድኑ ጊዜ ምን ሊሆን ይችላል ? (መዝ 81፡ 11-12, 95፡ 9-11, ሮሜ 1፡ 22-32, ማር 8፡ 17, ዮሐ 12፡ 40, ዕብ 3፡ 8-11)
-
በመዝሙር (94-95) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 95:7b–8
“Today, if you hear His voice: Do not harden your hearts as at Meribahas on that day at Massah in the wilderness.”
ኢየሱስ እራሱን እንደ መልካም እረኛ ነው የገለፀው ፡፡ በክርስቶስ እንደሚያምን ሰው ፣ አንተ በጉ ነህ ፡፡ የመንጋውን ጩኸት እንደሚማር እንደ አንድ መልካም እረኛ ፣ በጎቹ የእረኛውን ድምጽ መስማትና እርሱን መከተል ይማራሉ ፡፡ እናም ድምጹን ስለሚከተሉ በጎቹ ከመከራ ያመልጣሉ የተትረፈረፈ ህይወትንም ይኖራሉ ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አንተም የእግዚአብሔርን ድምጽ መስማትና መከተል አለብህ ፡፡ እንደ አማኝ መሄድ ባለብህ መንገድ እንድትሄድ የሚመራህና የሚመክርህ መንፈስ ቅዱስ አለህ ፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ምንም እንኳ እውነቱንና ቃሉን ብታውቅም ነገር ግን የእግዚአብሔርን ድምጽ አትከተልም ፡፡
ያለምንም ማንገራገር ፣ ባልደነደነ ልብ ፣ አመጸኛ ባልሆነ መንፈስ ፣ ባለፈ ጊዜ ጉዳት ላይ ባለመቆም ወይም በህይወት ውጣ ውረድ ግራ ባለመጋባት የእግዚአብሔርን ድምጽ በእምነት ብትከተል ምን ይፈጣራል ? የእግዚአብሔርን ድምጽ ንጹህ በሆነና ባልተያዘ ልብ በእውነት ብታደምጥና ብትከተል ምን ይፈጠር ነበር ? ለማድመጥ ፣ ለመከተልና ፣ በእውነት ለመራመድ የሚፈቅድ ልብን እንድፈጥርልህ እግዚአብሔርን ለምን ፡፡ ድምጹን እንደሰማህ ተራመድ ፡፡ መውሰድ የማትፈልገውን ነገር ግን ልትወስደው እንደሚገባ የሚሰማህን እርምጃ ውሰድ ፡፡ የምትጠራጠረውን ያንን ነገር አድርገው ፡፡ ከመታዘዝ ጀርባ ያለውን ነገር አታውቅም ፡፡ ለማዳመጥ ወስን፣ ታዘዝ እናም በህይወትህ የእግዚአብሔርን ታማኝነት አራምድ ፡፡ ከመታዘዝ ጀርባ ሊገለጽ የማይችል ጸጋ አለ ፡፡
“ በምድረ በዳ እንደ ተፈታተኑት እንዳስቈጡት ጊዜ፥ ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ ልባችሁን አታጽኑ ። “
- መዝሙር 95፡8
ተጨማሪ ጥቅስ
መዝሙር 95:6–7 — “ ኑ፥ እንስገድ ለእርሱም እንገዛ፤ በእርሱ ባደረገን በእግዚአብሔር ፊት እንበርከክ ፤ እርሱ አምላካችን ነውና፥ እኛ የማሰማርያው ሕዝብ የእጁም በጎች ነንና ። “
መዝሙር 139:23–24 — “ አቤቱ፥ መርምረኝ ልቤንም እወቅ፤ ፍተነኝ መንገዴንም እወቅ ፤ በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፤ የዘላለምንም መንገድ ምራኝ ። “
ዮሐንስ 10:4 — “ የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።