God's Love and Faithfulness
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 92-93 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ መዝሙር 92 ላይ እንመለከታለን ፡፡ ትናትና መዝሙር 91 በችግሩ ዉስጥ ለነበሩት እግዚአብሄር መለዓክቱን እንደሚልክ ነበር ፡፡ ሁልጊዜ ከጋዜጣዎች ቢያንስ ሰባት የተለያዩ ፀሀፊዎችን በገፆች ላይ እንመለከታለን ስለሆነም ብዙ ስሜቶችን እና ምልከታዎችን እናገኛለን ፡፡ መዝሙር 92 በማይታወቅ የተፃፈ እና ለመዘምራን አለቃ ትዕዛዝ የሌለዉ ነው ፤ የተሰጠዉ ብቸኛዉ መግለጫ ስለ ሰንበት የተፃፈ እንደ ነበር ብቻ ነው ፡፡ ጥቂት መዝሙሮች በሳምንቱ ዉስጥ ተዘምረዋል ፤ ሌሎች ደግሞ በሰንበት ከአርብ ፀሀይ መጥለቅ እስከ ቅዳሜ ፀኃይ መጥለቅ ድረስ የተዘመሩ ነበሩ ፡፡ ይህ መዝሙር የተለዬ ነበር ምክንያቱም የሰንበት አምልኮ አካል እንዲሆን የተፃፈ ነበር ፡፡
በሳምንት ጊዜ አንድ በግ በማለዳ እና በምሽት በሁለቱም ጊዜ ይሰዋል ፤ በሰንበት ላይ መስዋዕቱ እጥፍ ይሆናል ፡፡ ሰንበት በእግዚአብሄርና በሰዎች መካከል ምልክት ነበር (ዘጸ 20፡ 8-11, 31፡ 12-17, ነህ 9፡ 13-15) ፤ ሰንበት እግዚአብሄር ከግብፅ ነፃ አዉጥቷቸዉ እንደ ነበር ያስታዉሳቸዋል (ዘዳ 5፡ 12-15) እንዲሁም በሰንበት አምልኮ ደስታን አምጥቷል !
ትምህርት
መዝሙር (92፡ 1-5)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮችን “ የሚያመልኩ ሰዎች “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ ሕዝቡ ምስጋናን እየሰጡና በአምልኮ እያመሰግኑ ነበር ፡፡ ኮንስታብል በአደባባይ/በሕዝብ ፊት ምስጋና መስጠት ተገቢ እንደ ሆነ ያመለክታል ፡፡ በታማኝነት እግዚአብሄርን በማለዳና በማት በበገናና በማስንቆ ያመሰግኑ ነበር (ቁጥር 1-3) ፤ በቀኑም ሁሉ እግዚአብሄርን ያመሰግኑ ነበር ፡፡ ሕዝቡ ለእነርሱ አድርጎላቸዉ በነበረው ነገር በጌታ ተደሰቱ - በደስታም ጮኹ (ቁጥር 4) ! መዝሙረኛው እግዚአብሄርን እንደ እፁብ ድንቅና ጥልቅ እዉቀት እንዳለዉ ገለፀው (ቁጥር 5) ፡፡ ትኩረቱ እግዚአብሄር እንዴት መልካም እንደ ነበር ነው ፤ አንዳንድ ጊዜ ደስታችን የት እንዳለ እደነቃለሁ !
መዝሙር (92፡ 6-11)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ ያሸነፈ ሕዝብ “ በማለት ይገልጻቸዋል ፡፡ መዝሙረኛው “ የስንፍና ተፈጥሮ የነበራቸዉን “ እና እግዚአብሄርን የማያዉቁትን ለዘላለም ይጠፋለ በማለት ገልጧቸዋል (ቁጥር 6-7) ፤ ነገር ግን እግዚአብሄር ለዘላለም ከፍ ከፍ ይላል (ቁጥር 8) ፡፡ እግዚአብሄር በመሆኑ ምክንያት ጠላቶቹ ይጠፋሉ (ቁጥር 9) ፡፡ እግዚአብሄር የመዝሙረኛዉን ቀንደ ከፍ ከፍ አደረገው ፤ ቀንዱ ኃይልንና ግርማዊነትን ይወክላል ስለሆነም መዝሙረኛው ኃይሉ ከእግዚአብሄር እንደ መጣ እየገለፀ ነበር (ቁጥር 10) ፡፡ መዝሙረኛዉ በዘይት የተቀባም ነበር (ቁጥር 10) ፡፡ እንደ ማክአርቱር አገላለፅ በዘይት መቀባት “ የእንስሳትን ቀንድ በሰይት በመቀባት እንዲያብለጨልጩ ከሚደረግበት ተግባር ላይ የተመሰረተ ነበር “ ፡፡ አንዳንዶቹ ቁጥር 10 መሲሀዊ ማጣቀሻ ነዉ ይላሉ ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ይህ “ በግጥሙ የእግዚአብሄርን ፍላጎት አጠቃላይ ንግግር አልነበረም ነገር ግን በእግዚአብሄር የተቀባው የሚመጣዉ አመልካች እንደ ነበር “ ይገልፃል ፡፡ እግዚአብሄር ሕዝቡን ጠላቶቻቸዉን እንዲያሸንፉ ኃይልን ይሰጣቸዋል (1ሳሙ 2፡ 1, 10, መዝ 75፡ 4-5, 10, 89፡ 17, 24, ሉቃ 1፡ 69) ፡፡
በብሉይ ኪዳን የተከናወነዉን የተቀቡትን ተመልከቱ ፡፡ የእግዚአብሄር ቅባት ሕዝቡን ለተለዬ አላማ እንዲለዩት ለነገስታቶችና ለካህናት መጥቷል ፡፡ እግዚአብሄር ሰዎችን ለተለዬ ተግባር ለመጥራት ይህን ቅባት/ሹመት ተጠቅሟል፡፡ በዘጸ (29፡ 7) እንደ ካህን የአሮን መቀባት/መሾም ተካሂዷል ፤ በዘጸ (40፡ 15) እግዚአብሄርን እንዲያገለግሉ ሌዋዊያን ካህናቶች ተቀብተዋል ፤ ሌላ የመቀባት ምሳሌዎች በ 1ሳሙ (10፡ 1) ሳሙኤልን እና በ 1ሳሙ (16፡ 12-13) ዳዊትን ያካትታል ፡፡ ምንም እንኳን በእግዚአብሄር ተቀብቶ የነበር ቢሆንም የእግዚአብሄር
መንፈስ ሳዖልን ትቶት ሄደ (1ሳሙ 16፡ 14) ፡፡ በ 1ነገ (1፡ 39) እግዚአብሄር ሰለሞንን ቀባው ፡፡
አዲስ ኪዳንም የመቀባትን ጊዜያት ያካትታል፡ ሉቃ (4፡ 18-19)፣ 2ቆሮ (1፡ 21)፣ 1ዮሐ (2፡ 20, 27) ፡፡ በአዲስ ኪዳን ሁላችንም ተቀብተናል ምክንያቱም በክርስቶስ ስለሆንን ፡፡ ጃርድ ላስኬይ “ ቅባት ወደ አማኞች አያመለክትም ፤ ቅባት አማኞችን ስለሚያበረታዉ ወደ እግዚአብሄር እንደሚያመለክት “ ፅፏል ፤ ስለሆነም “ የኃይሉ ማስተላለፊያዎች “ እንሆናለን ፡፡ አይናችንን በክርስቶስ ላይ በምናደርግ ጊዜ በቅባታችን መጓዝ እንችላለን ፡፡
መዝሙር (92፡ 12-15)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮችን “ የበለፀጉ ሰዎች “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ ህይወት በእኛ ላይ የወረወረዉን ነገር ስንቋቋም በክርስቶስ እንጠነክራለን/እንዳብራለን ፡፡
መደምደሚያ
በእግዚአብሄር ኃይል እና ደስታን ስናገኝ እናድጋለን እንበለፅጋለንም ፡፡
10 Laskey.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 259.
Wiersbe, p. 259.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository Bible Notes: Psalms, p. 331; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/psalms.pdf.
Wiersbe, p. 259.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 711.
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 659.
Nelson’s Commentary, p. 710.
MacArthur, p. 659.
Jared Laskey, “5 Ways to Grow in the Anointing of the Holy Spirit,” Charisma News; available at https://www.charismanews.com/opinion/59255-5-ways-to-grow-in-the-anointing-of-the- holy-spirit.
Wiersbe, p. 260.
ጥያቄዎች
-
መዝሙረኛዉ በመዝሙር 92 እንዳደረገው ለእግዚአብሄር ምስጋና መስጠትና ስሙን ማመስገን ለእናንተ ምን ይመስላል ?
-
ይህ መዝሙር ለሰንበት ቀን የተፃፈ ነበር ፤ እግዚአብሄርን ለማመስገንና ለማምለክ በሰንበት አስባችሁ ጊዜን ለይታችሁ ታስቀምጣላችሁ ? ዛሬን እንደ ሰንበት መመልከት እንዴት ይጠቅማል/ያስፈልጋል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
መዝ (92፡ 4) “ አቤቱ በስራህ ደስ አሰኝተኸኛልና ፤ በእጅህም ስራ ደስ ያለኛልና “ ይላል ፤ በዚህ ንግግር ላይ አሰላስሉ ፡፡ ይህንን ስታደርጉ ወይም ለዋስትና የእግዚአብሄርን ፍጥረት ስትወስዱ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ? የእግዚአብሄር እጅ ስራዎች በአካል የሚታየዉን ነገር ብቻ ነዉ የያዙት ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
የእግዚአብሄርን ግርማዊነት (መዝ 93፡ 1) በዚህ በምድር ላይ ባለግርማ ወይም ንጉሳዊ እንዲሆኑ ከተጠሩ ሰዎች ጋር አወዳድሩ ፤ አንዳንድ መመሳሰሎቹ ምንድን ናቸው ? ልዩነቶቹስ ? እግዚአብሄር እኛን የሚያይበት አንዱ መንገድ ምንድን ነው ? (1ጴጥ 2፡ 9)
-
በመዝሙር (92-93) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 92:1–2
“It is good to praise Yahweh, to sing praise to Your name, Most High, to declare Your faithful love in the morning and Your faithfulness at night.”
ዛሬ ልክ ከእንቅልፍህ ስትነሳ ፣ የእግዚአብሔን ፍቅር በህይወትህ ላይ አውጅ ፡፡ የእግዚአብሔርን ምስጋና አውጅ ፡፡ ዛሬ ማታ ወደ መኝታ ከመሄድህ በፊት ፣ የእግዚአብሔርን ታማኝነት በህይወትህ ላይ አውጅ ፡፡ የገጠመህ ፣ የተሸከምከው ሃላፊነት ወይም ያለህበት ውጊያ ምንም ይሁን ፣ የእግዚአብሔርን ታማኝነት አውጅ ፡፡ እርሱ ትላንትና ፣ ዛሬ ፣ ነገም ታማኝ ነው ፡፡ በህይወትህ እግዚአብሔር ታማኝ ነው ፤ ይህንን እውነት ጮክ ብለህ ስታውጅ ፣ የሆነ ኃይለኛ ነገር ይሆናል !
በጭንቅላትህ ውስጥ ለሚመላለሰው እውነት ድምፅ ስጠው ፡፡ “ ደስታ “ የሚለውን ቃል ጮክ ብለህ በለው ፡፡ አጠገብህ ያለ የሆነ ሰው አይና “ ደስታ “ በል ! ምናልባት ደስታ ላይሰማህ ይችላል ነገር ግን በቃ “ ደስታ “ እያልክ በማንሾካሾክ ጀምር ፡፡ ከዚያም ድምፅህን ከፍ በማድረግ አንሾካሹክ “ ደስታ “ ፡፡ ከዚያም በቃ በተለመደ መካከለኛ በሆነ ድምፅ በለው “ ደስታ “ ፡፡ አሁን ደግሞ ትንስ ጮክ በል “ ደስታ “ ፡፡ አሁን ጩኽ “ ደስታ ! “ እስካሁን አልሳክም ? በርግጥ መሳቅ ብቻውን ደስተኛ ነህ ማለት አይደለም ፡፡ ሆኖም ግን የእግዚአብሔርን ታላቅ ፍቅር እና ታማኝነት በምታስብበት በዚያ ሰዓት በእርግጠኝነት መሳቅ ያለህበትን ሁኔታ ቀለል ያደርግልሃል ! ይህንን የደስታ ድምፅ በምስጋና ለእግዚአብሔር ተናገር ! እግዚአብሔር ይወድሃል እርሱም ስለ አንተ ይሰራል ይተጋል ! ደስታ !
“ እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህም ዝማሬ ማቅረብ ፤ በማለዳ ምሕረትን፥ በሌሊትም እውነትህን ማውራት “ - መዝሙር 92፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 92:4 — “ አቤቱ፥ በሥራህ ደስ አሰኝተኸኛልና፤ በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና ። “
- መዝሙር 100:4 — “ወደ ደጆቹ በመገዛት፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፤ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ “
- ያዕቆብ 1:12 — “ በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።