Protection Through Intimacy
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 91 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የመዝሙር 91 ፀሀፊ አይታወቅም ፡፡ ማክአርቱር “ ይህ መዝሙር ሰብዓዊነታቸዉን ከሚከባቸዉ ከቀድሞ እስከ አሁን አጥፊዎችና ጭንቀት የህዝቡን የእግዚአብሄርን የቀጠለ ልዓላዊ ጥበቃን “ እንደሚገልፅ እና ወደ ዉጊያ ከመሄዳቸዉ በፊት ለአንድ ጦር የተፃፈ እንደ ነበር መቅረቡን ተመልክቷል ፡፡ ሁላችንም በኑሮአችን የእግዚአብሄርን ሉዓላዊ ጥበቃ እንፈልጋለን ፡፡ መፅሀፍ እግዚአብሄር ልክ እንደ ሙሴ፣ ዳዊት፣ ጴጥሮስና ጳዉሎስ ሰዎችን እንደጠበቀና እንደተከላከለላቸው ብዙ መንገዶችን ይመሰክራል ፡፡ ማክአርቱር ይህ መዝሙር “ እግዚአብሄር ከፈቀደዉ ነገር ዉጪ የእግዚአብሄርን ልጆች ምንም ሊጎዳቸዉ እንደማይችል “ መናገሩን ፅፏል ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (91፡ 1-2)፡ በቁጥር 1 እና 2 እግዚአብሄር “ ልዑል “ ተብሎ የተጠራ ነው ፤ እስራኤል ፀኃይ በጣም ሞቃትና ለአንድ ሰዉ ጤንነት አስቸጋሪ ሊሆንበት የሚችል ስፍራ ስለ ነበር ለጥንቃቄና ለመከላከል ጥላ ስለ ማስፈለጉ ዘይቤአዊ አነጋገር ነበር ፡፡ ዋይርስቤ የእግዚአብሄርን መግለጫዎች “ ለሁሉም ሁኔታ በቂ የሆነ የሁሉም በቂ አምላክ “ በማለት “ እንደ ሁሉን ቻይ “ በመግለፅ ፅፏል ፡፡ መዝሙረኛው በራሱ ሳይሆን በእግዚአብሄር ላይ ሙሉ ለሙሉ መታመኑን ተናገረ ፡፡ እግዚአብሄርን “ መፅናኛዬ እና መሸሸጊያዬ “ (ቁጥር 2) በማለት ሲጠቅስ ለእርሱ እነዚህ ነገሮች ሊኖሩት እንደማይችሉትና እግዚአብሄር በሁለቱም ነገር ስለ እርሱ እንደሚሆንለት መታመኑን በመግለፅ እዉቅና ሰጠ ፡፡ ይህ እግዚአብሄር አብራምን በዘፍ (17፡ 1) እንዲኖረዉ አዞት የነበረዉን የተለየ መታመን ነው “ አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሄር ለአብራም ተገለጠለትና እኔ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ ፍጹምም ሁን “ ፡፡
መዝሙር (91፡ 3-6)፡ እነዚህ ቁጥሮች የጌታ ተከታዮች የሆኑት ለመናገር የኖራቸዉ የህይወት እዉነተኛ ችግሮችን ገልፀዋል ፤ “ በቁጥር 3 ላይ “ የአዳኞች ወጥመድ/መረብ “ ወፍን የሚያጠምድ አንድ ሰዉ አደኑን ለመያዝ የተጠቀመበት የወፍ ወጥመድን ይወክላል ፡፡ እንደ ዘይቤአዊ አነጋገር የሚነገረዉ ስዕል የአንድን ሰዉ ህይወት ሊጎዱት ከሚከተሉት ከማንኛዉም እቅድ የእግዚአብሄርን ነፃ ማዉጣት እንደሚወክል አገልግሏል ፡፡
“ አጥፊዉ መቅሰፍት “ (ቁጥር 3) የሚነሱ በሽታዎችን እና ወረርሽኞችን ይጠቅሳሉ ፤ እግዚአብሄር ተከታዮቹን ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች እንደሚጠብቅ ቃል ገብቷል ፡፡ መዝሙረኛዉን እግዚአብሄርን ተከታዮቹን “ በክንፎቹ እንደሚሸፍናቸው “ ገልፆታል ትርጉሙም እግዚአብሄር ቅርብ እንደ ነበርና በእነርሱ ላይ ይመለከት ነበር አንደ ማለት ነው ፡፡ ይህ ስዕል ከእግዚአብሄር ጋር መቀራረብን “ በክንፎቹ ስር መፅናናትን አገኛለሁ “ በሚለዉ መግለጫ የተጠናከረ ነበር ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ኢየሱስ ለኢየሩሳሌም የጥበቃን አይነት ለማቅረብ ናፈቀ፡ “ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ ! አልወደዳችሁምም “ (ማቴ 23፡ 37) !
መዝሙረኛው የእግዚአብሄር ተከታዮችን የሚገጥሟቸዉን የተለመዱ ሁኔታዎችን ዘርዝሯል፡ ከሌሊት ግርማ፣ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፣ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር እና ጋኔን (ቁጥር 5-6) ፤ ከእግዚአብሄር ጋር ያለ ቀረቤታ ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች ተከታዮቹን ይጠብቃቸዋል ፡፡
መዝሙር (91፡ 7-9)፡ መዝሙረኛው በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች በወረርሽ እንደወደቁ ጠቅሷል ነገር ግን የእግዚአብሄር ተከታዮች የሚፈሩ እንዲሆኑ ምክንያት አይሆኑም ፤ ይህ እስራኤልን በእግዚአብሄር ነፃ ማዉጣት አካል ላይ በግብፅ ላይ የመጣዉን መቅሰፍት ሊያመለክት ይችላል ፡፡ በተጨማሪም እግዚአብሄር ተላቶቻቸዉ ባገኙአቸዉ ጊዜ ኃይላቸዉን እንደሚያበዛ ተስፋ ገብቷል፣ “ ከእናንተም አምስቱ መቶዉን ያሳድዳል መቶዉም አስሩን ሺህ ያሳድዳሉ ፤ ጠላቶቻችሁም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ “ (ዘሌ 26፡ 8) ፤ “ እርሱም አምላካቸው ካልሸጣቸው እግዚአብሄርም አሳልፎ ካልሰጣቸው አንድ ሰው እንዴት ሺህን ያሳድድ ነበር ? ሁለቱሳ እንዴት አስሩን ሺህ ያሸሹ ነበር “ (ዘዳ 32፡ 30) ?
መዝሙረኛው ጌታን የሚከተሉት እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሲሆኑ እንደሚያዩ ተስፋ ገብቷል ከእርሱ ጋር ባላቸዉ ቀረቤታ ምክንያት (ቁጥር 8-9) ፡፡ መዝሙረኛዉ በተለዬ ሕዝቡ ከእርሱ ጋር ያላቸዉን የመቀራረብ ደረጃ ለማሳዬት የእግዚአብሄርን የግል ስም “ ልዑል “ በማለት ጠቅሶታል ፡፡
መዝሙር (91፡ 10-13)፡ መዝሙረኛው የእግዚአብሄርን የጥበቃ ኃሳብ ለማጠናከር ብዙ ስዕሎችን ተጠቅሟል ፡፡ ከመቅሰፍት ሌለኛዉ የጥበቃ ተስፋ ተደርጓል (ቁጥር 10)፣ ሕዝቦቹ እግሮቻቸዉ በድንጋይ እስከማይጎዱ ድረስ (ቁጥር 12) መለዓክቶችም የእግዚአብሄርን ሰዎች ለመጠበቅ የታዘዙ እንደሆኑ ተገልጧል (ቁጥር 11) ፡፡ የእግዚአብሄር ሰዎች በአንበሶች እና በመርዛም እባቦች እንኳን ላይ መቆም ይችላሉ (ቁጥር 13) ፡፡
በሚያስደንቅ ሁኔታ ሰይጣን ኢየሱስን ሲፈትን ቁጥር 11 እና 12 ተጠቅሟል፡ “ ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደዉና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ ፤ መላዕክቱን ስለ አንተ ያዝልሀልና እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሱሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሄር ልጅስ ከሆንህ ወደ ታች ራስህን ወርዉር አለው “ (ማቴ 4፡ 5-6) ፡፡ ሰይጣን ይህንን መልዕክት ኢየሱስን ለመፈተን ለማዋቀር አሳስቶ ጠቀሰው ነገር ግን የኢየሱስ ምላሽ “ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተፅፎአል አለው “ (ማቴ 4፡ 7) ፤ ይህ ሆን ብለን እግዚአብሄር እንዲያድነን አደገኛ ሁኔታዎችን በመፍጠር የእግዚአብሄርን የጥበቃ ተስፋን ፈተና ላይ እንዳናስቀምጥ እንድናስታዉል ይረዳናል ፡፡
መዝሙር (91፡ 14-16)፡ በእነዚህ ጥቅሶች ተናጋሪዉ ከመዝሙረኛዉ ወደ እግዚአብሄር ንግግር ይገባል/ይከፍታል ፤ ከራሱ የፍቅር መሰጠት የተነሳ እግዚአብሄር ራሱ ለመዝሙረኛው ከለላ እንደሚያደርግለት ቃል ገባ ፡፡ እግዚአብሄር ጥበቃ እንደሚያደርግ ተስፋ ገባ ምክንያቱም መዝሙረኛዉ “ ስሜን ስለሚያዉቀው “ (ቁጥር 14) ፡፡ እግዚአብሄር መዝሙረኛዉን እንደሚመልስለት፣ በችግሩ ጊዜ የቀረበ እንደሚሆነው እና “ እንደሚያድነዉና እንደሚያከብረው “ ቃል ገባ (ቁጥር 15) ፡፡ በመጨረሻም መዝሙረኛው “ ረጅም እድሜን “ እንደሚቀበልና እግዚአብሄር ራሱ “ ማዳኑን ያሳየዋል “ (ቁጥር 16) ፡፡
ማክአርቱር የዚህ መዝሙር ተስፋ በሁሉም ጊዜ ታሪኮ ባሉ አማኞች ላይ እዉነት መሆን ሲችል ለዚህ መዝሙር ለመሲሀዊ ንጉስ ሀሳብ በኢየሱስ ህይወት የተፈፀመ እንደሆነ በግልፅ እንደሚጠቅስ ፅፏል ፡፡
መደምደሚያ
ከእግዚአብሄር ጋር ይህን የሚያክል የትስስር ደረጃ እንዲሰጠን እንዴት ከእግዚአብሄር ጋር መቀራረባችንን እናሳድጋለን ? እዉነተኛ መቀራረብ ከእግዚአብሄር ጋር መቀራረብን ለማሳደግ/ለመንከባከብ አምስት መንገዶችን ያዛል ፡
- ከእግዚአብሄር ጋር መቀራረብን መፈለግ - ዳዊት ከፍላጎቶቹ ዉስጥ ፅፏል “ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሄር ቤት እኖር ዘንድ “ (መዝ 27፡ 4) ፡፡
- የእግዚአብሄርን የፍቅር ቋንቋ ማወቅ - እግዚአብሄር በመታዘዛችን እንድንወደዉ ይፈልጋል (መዝ 51፡ 16-17) ፡፡
- እግዚአብሄርን በፍቅር ስሜት መዉደድ ፡፡
- ተስፋ አለመቁረጥ !
- በስራዎቹ ላይ መነጋገር /መጋራት ፡፡
የቃሉ ጥበቃ በመዝሙር 91 ዉስጥ ነው ፤ ይህን ከያዛችሁ ያለፍርሃት ጥሪአችሁን መጓዝ መጀመር ትችላላችሁ ፡፡
John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 658.
MacArthur, p. 659.
MacArthur, p. 659.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 257.
MacArthur, p. 659–660.
MacArthur, p. 658.
“5 Secrets to Intimacy with God,” www.authenticintimacy.com, published June 4, 2015; available at https://www.authenticintimacy.com/resources/1409/5-secrets-to-intimacy-with-god.
ጥያቄዎች
-
በመዝሙር 90 ላይ ካሰላሰላችሁ በኋላ የምን ስሜት ተዋችሁ ? እነዚህ ቁጥሮች በሰላም፣ በመፅናናትና በፍቅር ይሞሏችኋል ? ለምን ወይስ ለምን አይሞሏችሁም ?
-
መዝ (91፡ 2) አምላኬ መታመኛዬ፣ መሸሸጊያዬ፣ አምላኬም ስለሆነ በእርሱ እታመናለሁ በማለት ይጠቅሳል ፤ እግዚአብሄርን እንደ መታመኛችሁና መሸሸጊያ ስፍራችሁ ታዩታላችሁ ? እግዚአብሄርን መታመን እንደምትችሉ ታምናላችሁ ? ከእግዚአብሄር ጋር ትንሽ ደቂቃዎችን በማሳለፍ እነዚህን ጥያቄዎች ጠይቁት
-
በዚህ መዝሙር ዉስጥ በሙሉ ምስጋና ወደ እግዚአብሄር ከፍ አድርጓል ፤ ከዚያም በመዝ (91፡ 9-10) እግዚአብሄር “ ከሆነ “ (በአንዳንድ እትሞች ) በድርሻችን ላይ ጥቂት ድርጊት ያስፈልገናል ማለት ነዉ ብሏል ፤ ሌላ የት ላይ የእግዚአብሄር ልጆች በሚሆን/ከዚያም በሚገነባ ነገር ላይ የሆነ ነገር ማድረግ የሚያስፈልግባቸው እናነባለን ? (ዘጸ 23፡ 22, ዘዳ 4፡ 29, 1ዜና 28፡ 9, 2ዜና 7፡ 14, ራዕ 3፡ 20)
-
መዝሙር 91 ከእግዚአብሄር በተስፋ የሞላ ነው ፤ መዝሙር 91 ካነበባችሁ በኋላ ዮሐ (14፡ 23-240 ላይ ተመልከቱ ፤ ምን ተመሳሳይነትን አያችሁ ? ይህ እንዴት ለእናንተ ይናገራችኋል ?
-
በመዝሙር 91 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 91:1–2
“The one who lives under the protection of the Most High dwells in the shadow of the Almighty. I will say to the LORD, ‘My refuge and my fortress, my God, in who I trust.’
በእግዚአብሔር ጥበቃ ላይ መታመን ማለት ፍጹም የሆነ ፣ ከፈተና የጸዳ ፣ ጤናማ ፣ ፈጽሞ የማትጎዳበት ህይወት ማለት አይደለም ፡፡ አዎን እግዚአብሔር ይጠብቅሃል ፡፡ አዎን እርሱ መሸሸጊያህ ነው ፡፡ አዎን እርሱ አዳኝህ ነው ፡፡ አዎን በእርሱ መታመን ትችላለህ ፡፡ ታማኝነቱ ጋሻ ይሆንሃል በክንፎቹም ጥላ ስር ይሸሽግሃል ፡፡ ነገር ግን በእምነት ስታደርገው ያ ምን ይመስል ይሆን ፡፡
በወደቀ አለም ውስጥ ከወደቁ ሰዎች ጋር እንደምትኖር ደግሞም እግዚአብሔር ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ እንደሚሰራ ይህንን አስብ ፡፡ የእርሱ መንገድ ከእኛ መንገድ ይልቃል ፡፡ እግዚአብሔር በማንኛውም መንገድ ልትገፋ እንደምትችል ይናገራል ነገር ግን እርሱ እንደማትወድቅ ይናገራል ፡፡ ግራ ልትጋባ ትችላለህ ነገር ግን ተስፋ አትቆርጥም ፡፡ ልትሰደድ ትችላለህ ነገር ግን ፈጽሞ አትተውም ፡፡ ልትወድቅ ልትያዝ ትችላለህ ነገር ግን አትጠፋም ፡፡ ደካማ ልትሆን ትችላለህ ነገር ግን በክርስቶስ ብርቱ ነህ ፡፡ ምንም ላይኖርህ ይችላል ነገር ግን እውቀትን ሁሉ የሚያልፍ ሰላም ይኖርሃል ፡፡ በመከራ እና በችግር ውስጥ ልትሆን ትችላለህ ነገር ግን ቢሆንም ይህን በደስታ ተቀበለው ምክንቱም እግዚአብሔር ፈጽሞ እንደማይተውህና እንደማይረሳህ ስለተናገረ ፡፡ እርሱ ይጠብቅሃል ደግሞም ይረዳሃል ፡፡ እርሱ መሸሸጊያህ ይሆናል ፡፡ ዋናው ነገር እሱን ማመን አለማቆም ነው ፡፡ ጮክ ብለህ እንድህ በል “ አንተ መጠለያና ጋሻዬ ነህ ፣ የምደገፍበት አምላኬ ነህ ፡፡ “ ፈተናህን ድል አድርገው እናም በህይወትህ እርሱን ስትደገፍ የእርሱን ጥበቃ ለማየት አይኖችህን ግለጥ ፡፡
“ በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል ። እግዚአብሔርን፦ አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ ። “ - መዝሙር 91፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዝሙር 91:3–4 — “ እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና ። በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል ። “
- 2ኛ ቆሮንቶስ 4:8–9 — “ በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፤ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም ፤ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም ፡፡ “
- 2ኛ ተሰሎንቄ 3:3 — “ ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።