Wisdom Books Psalms

God's Purpose For The Israelites

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 90 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 436 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ስለዚህ መዝሙር ብዙ የሚያስገርሙ እዉነቶች አሉ ! መዝሙር 90 የቀድሞ መዝሙር ሲሆን የተፃፈዉም በሙሴ ነበር ፡፡ አንድ ስዕል መሳል እፈልጋለሁ ፡፡ ትናትና እግዚአብሄር በማናይበት ግራ መጋባት ዉስጥም በማመስገን እንዳለብን አዉርተናል ፤ ይህ መዝሙርም ተመሳሳይ ስሜት አለው ፤ ሙሴ ስለ ሕዝቡ እርዳታ እግዚአብሄርን እየጠየቀ ነበር ፡፡ ማክአርቱር የመዝሙር 90 መዝሙረኛው “ የእግዚአብሄርን ዘላለማዊነት በማንፀባረቅ ጀምሮ ከእግዚአብሄር ቁጣ ጋር ያላቸዉን ግንኙነታቸዉን ስለ ሕይወታቸዉ አጭርነትና ኃዘን የራሱን የመጨነቅ ሀሳቡን በመግለፅ ታላቅ ኑሮ እንዲኖሩ እግዚአብሄር ሕዝቡን እንደያስችላቸዉ በመለመን እንደሚያጠቃልል “ ፅፏል ፡፡

ምንም እንኳን እስራኤላዊያን ቢስቱም/ቢቆሽሹም በኑሮአቸዉ ለአላማ እግዚአብሄርን ጠየቁት ፡፡ በቃዴስ ላይ ከተፈጠረዉ ክስተት በኋላ ነገሮች ተለይተዉ የሚወድቁ መስለዋል ፤ የሙሴ እህት ማሪያምና ወዱሙ አሮን ሁለቱም ሞቱ (ዘኁ 20፡ 1, 22-29) በተጨማሪም ሙሴ ዉሃ በመፈለግ እግዚአብሄርን ሳይታዘዝ አለቱን መታው ፤ ይህ ለመዝሙር 90 መነሻ ነው ፡፡ እስራኤላዊያን ብዙ ስህተቶች ነበሯቸዉ ነገር ግን አሁንም ለአላማ ፍላጎት ነበራቸው ፡፡ በአሁን ጊዜ ብዙ ሰዎች እንደሳቱ እና እግዚአብሄር ሊያድናቸዉ ወይም ሊመልሳቸዉ እንደማይችል ይሰማቸዋል ፡፡ እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን ድነታችን በስራ የተመሰረተ ስላልሆነ ፤ በእርሱ ፀድቀናል ፡፡ እግዚአብሄር ፍፁምነትን እንደማናሳካዉ ያውቃል ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (90፡ 1-2)፡ ሙሴ ራሱን “ እንደ እግዚአብሄር ሰዉ “ ለዬ (ዘዳ 33፡ 1, ኢያ 14፡ 6) ፡፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ እኛ ተጓዦች ስንሆን እግዚአብሄር ደግሞ ቤታችን ነው “ በማለት ያሳያቸዋል ፡፡ እግዚአብሄር ቤታችን እንደሆነ፣ ማደሪያችን ስፍራ የሚለዉን ስዕል እወደዋለሁ ፡፡ ማክአርቱር “ እግዚአብሄር ስለ ጥበቃ፣ ስለ መሰረታዊ ነገር እና ስለ መፅናት የእስራኤል ማደሪያ እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡

ዋይርስቤ “ ለሁሉም ሰዉ ህይወት ከዉልደት ወደ ሞት የሚደረግ ጉዞ ነው እንዲሁም ደግሞ ለአማኞች ከምድር ወደ ሰማይ የሆነ ጉዙ ነዉ ነገር ግን መንገዱ ቀላል እንዳልሆነ “ ፅፏል ፡፡ እንደ ማስረጃ ዋይርስቤ “ ትንሽና አስቸጋሪ “ የነበረዉን የያዕቆብን መንፈሳዊ ጉዞ አመልክቷል (ዘፍ 47፡ 9) ፤ ከዚያም በ40 አመታቶቹ ጊዜ እስራኤላዊያን የሰፈሩባቸዉን 42 ስፍራዎች የሚያካትተዉን የሙሴን የ40 አመት የምድረበዳ መከራተት አመታት ነበሩ (ዘሁልቁ 33) ፡፡ በተጨማሪም ዋይርስቤ “ ሙሴ የትም ስፍራ ቢኖር ችግር የለዉም እግዚአብሄር ቤቱ ነበር ፤ በጌታም ኖረ ፤ በጌታ ብቻ እንዴት ኃይልን፣ መፅናናትን፣ ብርታትን እንደሚያገኝና ለእያንዳንዱ ቀን ፍላጎት እርዳታ እንደሚያገኝ ያውቃል “ ይላል ፡፡ በጉዞ መካከል ላይ ትኩረታችን የት ላይ ነው ? ሙሴ ከእግዚአብሄር ጋር ሰፈረ ፤ እንደ ተጓዦች ብንሆንም እንኳን እግዚአብሄር ቤታችን ነው ፡፡

በቁጥር 2 ሙሴ “ ከዘላለም እስከ ዘላለም “ በሚል ቃል ጊዜን ጠቅሷል ፡፡ ማክአርቱር “ የእግዚአብሄር ተፈጥሮ ከጅማሬና ወይም ከፍፃሜ፣ ከሁሉም ጊዜ ቅደም ተከተል ዉጪ የሆነና በራሱ የጊዜ መነሻ እንደሆነ “ ፅፏል ፡፡

መዝሙር (90፡ 3-6)፡ ዋይርስቤ ቁጥር (3-12) “ ተማሪዎች እንደሆንንና ህይወት ደግሞ ት/ቤታችን እንደ ሆነ “ አሳይቷል ፡፡ ሙሴ በቁጥር (3-12) የሰዉን ደካማነት እና በቁጥር (1-2) የእግዚአብሄርን ዘላለማዊነት መልክን ስሏል፡፡ እግዚአብሄር በጣም ትልቅ ሲሆን እድሜአችን ደግሞ በጣም ፈጣንና የሚሮጥ ነው (ዘፍ 3፡ 19፣ ኢሳ 40፡ 6-7) ፡፡

መዝሙር (90፡ 7-9)፡ ሙሴ በመሰረቱ “ መቆሸሻችንን እናዉቃለን “ እያለ ነበር ፡፡ የተደበቀ ኃጢዓት የለም ፡፡ ማክአርቱር “ በመዓትና በችግር ዉስጥ ህይወቱን ከታገለ በኋላ የአንድ ሰዉ ህይወት በኃዘን ማቃሰትና ድካም የሚያበቃ እንደሆነ “ ፅፏል ፡፡ ወደ ሰብዓዊነት እንኳን በደህና መጣችሁ ! እስካሁን ይህ በጣም አበረታች አይደለም ፡፡

መዝሙር (90፡ 10-12)፡ በዚህ ጥቅስ መሰረት አማካኝ የመኖር ጣሪያ 70 አመት ነበር ወይም ጠንካራ ከሆንክ 80 አመት ነበር ፡፡ ሙሴ 120 አመት ኖረ ፡፡ ዋይርስቤ “ በህይወት ት/ቤት ዉስጥ ሁለት አስፈላጊ ትምህርቶችን መማር ያስፈልገናል፡ ህይወት ግልፅ እና በፍጥነት የምታልፍ ስለሆነች አብዛኸኛዉን ነገር ማድረግን እና ሕይወት አስቸጋሪ ስለሆነች በጊዜም ላይ ከንቱ እንደሚመስል “ ፅፏል ፡፡

በህይወት ላይ የእግዚአብሄርን መሪነት እንፈልጋለን ይህ ከሆነ ኑሮአችን ለእግዚአብሄር ፍሬአማ አገልግሎት ነው ፡፡ ሙሴ እግዚአብሄርን “ እስራኤላዊያንን ዘመናቸዉን በስርዓት እንዲቆጥሩ እንዲያስተምራቸዉ “ ጠየቀው ፤ ዘመናችሁን መቁጠር ማለት ምን ማለት ነው ? የሁሉንም እድሎች መልካሙን ነገር ማድረግ ማለት ነው ፡፡ ሁል ጊዜ እግዚአብሄር ክብር የሚቀበልበትን መንገድ ዘመናችሁን በጥንቃቄ ትቆጥራላችሁ ? “ ወደ ኋላ ተመልሼ መሄድ ብችል ሁሉንም ነገር እንደ ገና አደርጋለሁ…” ሲሉ ሰዎችን ትሰማላችሁ መዝሙር 90 ደካሞች ብንሆንም እንኳን ኑሮአችንን ማባከን መፈለግ እንደሌለብን ያሳያል፡፡ ሪቫይቭ ት/ቤት ሊያነቃቃን የሚፈልገዉን ሚስጥር በመማር ለእግዚአብሄርን ዘመናችሁን ለመቁጠር ታላቅ መንገድ ነው ፡፡

መዝሙር (90፡ 13-17)፡ ዋይርስቤ እነዚህን ቁጥሮች “ አማኞች እንደ ሆንና ወደፊትም ወዳጃችን ነዉ “ በማለት ያስቀምጣቸዋል ፡፡ የሙሴን ልመና ለምህረትና ለርህራሄ እናያለን ፤ ሙሴ ልክ ከሰማይ እንደ ወረደዉ መና በእግዚአብሄር ፍቅር ደስታን ማግኘት ፈለገ (ማቴ 5፡ 6) ፡፡ ደስታችን በግልፅ የህይወት እንጀራ ከሆነዉ ከክርስቶስ ነው ፡፡ ሁል ጊዜ በደስታ የምንጮኽ መሆን አለብን ! ሙሴ ምንም እንኳን ጠላቶቹ ቢኖሩም በህይወቱ ዘመኑ ሁሉ መደሰትን ፈለገ (ሮሜ 8፡ 18) ፡፡

መደምደሚያ

ዋጋ፣ አስፈላጊነትና ትርጉም እንዳለን እንረዳለን ፤ እንደማይሆን በሚሰማ ጊዜም እንኳን እግዚአብሄር እኛ ዉስጥ ያፈስስብናል/ይሞላናል ፡፡ እግዚአብሄር ሲያቆማችሁ፣ ሲያበረታችሁና ሲደግፋችሁ የማትደራደሩ ከሆናችሁ በሰማይ ትሆናላችሁ (1ጴጥ 5፡ 10) ፡፡ ይህ እንዴት ተስፋ ሊኖረን እንደሚችል ነው ፡፡ ዋይርስቤ የፃፈው፡

ህይወት ግልፅ ስለሆነ ሙሴ “ አስተምረን “ ብሎፀለዬ ፤ ህይወት አስቸጋሪ ስለሆነ “ እንዲያስደስታቸዉ “ ፀለዬ ፡፡ ስራዉ በጊዜዉ ላይ ከንቱ ስለመሰለ “ የእጆቻችን ስራ መስርት “ አለ ፤ እግዚአብሄር ፀሎቶቹን ለሙሴ መለሰ ለእነርሱም ይመልስላቸዋል ፡፡ ኢየሱስ አዳኛችሁና ጌታችሁ ሲሆን ከፊት ያለዉ/ወደፊት ወዳጃችሁ ነው ፡፡

ብንቆሽሽም/ብንስትም እንኳን ሙሴ እያለ ያለዉ እግዚአብሄር ትልቅ አምላክ ነው ፡፡ ህይወት አጭር እንደሆነ እናዉቃለን ነገር ግን በሂደቱ ለዘላለም ከእርሱ ጋር እስንሆን ድረስ እግዚአብሄር አላማን ተሰጥቶናል !

John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 657.

12 Wiersbe p. 256.

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 254.

  2. Wiersbe, p. 254.

  3. MacArthur, p. 657.

  4. Wiersbe, p. 254.

  5. Wiersbe, p. 254.

  6. MacArthur, p. 658.

  7. Wiersbe, p. 255.

  8. MacArthur, p. 658.

  9. Wiersbe, p. 255.

  10. Wiersbe, p. 256.

ጥያቄዎች

  1. መዝ (90፡ 1-2) አንብቡ ፤ ሁል ጊዜ እግዚአብሄር አለ ከሚለዉ እዉነት ጋር እስካሁን ታግላችኋል ? አዎ ከሆነ ለዚህ ትግል እንዴት ምላሽ ትሰጣላችሁ ?
  2. በመዝ (90፡ 4) ሙሴ በእግዚአብሄር አንድ ሺህ አመት እንደትናት ነዉ አለ በ 2ጴጥ (3፡ 8) ጴጥሮስ ይህን ንግግር ደግሞታል ፤ በአስቸጋሪ ጊዜያት ዉስጥ ስታልፉ ይህን እንዴት ሊረዳችሁ ይችላል ?
  3. መዝ (90፡ 12) አንብቡ ፤ “ ዘመናችንን እንቁጠር “ የሚለዉ እንዴት አስተዋይ ልብ እንዲኖረን ያደርጋል ?
  4. ስትታገሉ ልክ እንደ መዝ (90፡ 13) ወደ እግዚአብሄር ጮኋችኋል ? የእግዚአብሄር ሀዘን ምን እንደሚመስል እና ከፀጋዉ ጋር እንዴት እንደሚለያይ ምን ታስባላችሁ ?
  5. በመዝሙር 90 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 90:17

“Let the favor of the Lord our God be on us; establish for us the work of our hands—establish the work of our hands

ህይወት አስቸጋሪና አድካሚ ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን በተስፋ ስትጸና ፣ በስቃይ ውስጥ እንኳ እግዚአብሔርን በማለዳ መፈለግ ትጀምራለህ ፡፡ እርሱ ደስ ያሰኝሃል እናም በታማኝ ፍቅሩ ይሞላሃል ፡፡ ምናልባትም ጥያቄዎችህን ጭምር ፡- ምን ብታደርግ እንደሚሻል ፣ ወዴት ብትሄድ እንደሚሻል ፣ በዚህ ፈጥኖ በሚጠፋ ህይወት እንዴት ጊዜህን መጠቀም አንዳለብህ ለእግዚአብሔር ታቀርባለህ ፡፡ አስታውስ እግዚአብሔር ያስተምርሃል ደግሞም እርሱን ስትሻው ቀናቶችህን እንዴት እንድትቆጥር ጥበብን ይሰጥሃል ፡፡

ዛሬ ያለ አላማ ወይም ደግሞ ያለ ተስፋ መንከራተት አይገባህም ፡፡ ጸልይ እናም የእግዚአብሔር ሞገስ በአንተ ላይ ይሆን ዘንድ ለምን ፡፡ የእጆችህንም ስራ ያጸና ዘንድ እግዚአብሔርን ለምን ፡፡ የእግዚአብሔር ጊዜ ሁልጊዜም የአንተ ጊዜ አይደለም ነገር ግን ያ ማለት ተስፋ የሌለው የተዘጋ በር ነው ማለት አይደለም ፡፡ እንዳንድ ጊዜ በቃ እርሱ እንድትጠብቅ እንድትታገስ ይፈልጋል ፡፡ የሰማዩ አባትህም እንድህ ይልህ ይሆናል ፡ - “ ለሆነ ነገር እያዘጋጀሁህ ነው ፣ ትንስ ጠብቅ ልጄ ! “ ዛሬ እግዚአብሔር የእጆችህን ስራ ያጽና ፡፡ እርሱ ለአንተ እቅድ አለው ፡፡ ከሁሉም ይልቅ በክርስቶስ እንደተፈጠርክ አስታውስ ፡፡ በእርሱ ተተክለሃል ደግሞም በእርሱ ቆመሃል ፡፡ አንተ የእርሱ ነህ እርሱም ለአንተ ያሰበውን ስራ ያሳካል ፡፡

“ የአምላካችን የእግዚአብሔር ብርሃን በላያችን ይሁን፡፡ የእጆቻችንንም ሥራ በላያችን አቅና ። “

  • መዝሙር 90፡17

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 90:12 — “በልብ ጥበብን እንድንማር፥ ቀኝህን እንዲህ አስታውቀን ። “

ቆላስይስ 2:6–7 — “እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ ፤ ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ ። “

1ኛ የጴጥሮስ 5:10 — “ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል ። “