Wisdom Books Psalms

God's Promises

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 89 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 435 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ማክአርቱር መዝሙር 89 “ በአስተምሮዉና በሕዝቡ ሁኔታ እዉነታ ዉስጥ መካከል ያለዉን ተቃርኖ የሚመስለዉን ነገር ለማስታረቅ የፀሀፊዉ ሙከራ እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፤ በመጀመሪያዎቹ 37 ቁጥሮች ዉስጥ በስነ መለኮታዊ አስተምሮ የሚያዉቀዉን ትክክል የሆነዉን አንድ በአንድ ይዘረዝራል ፡ እግዚአብሄር በልዓላዊነት እስራኤል ሕዝቡ እንዲሆን መረጠው የዳዊትም ዘር እንዲያስተዳድር ፡፡ የመዝሙሩ የመጨረሻዎቹ ሰዎስቱ ሕዝቡ ጠፍተዉ እንደ ነበርና የዳዊታዊ አስተዳደርም ወደ ክብር የሌሽ መጨረሻ እንደሚመጣ መዝሙረኛው ቅሬታዉን ያሳያል “ (ዘፍ 12፡ 1-3) ፡፡ መዝሙረኛው ናታን እግዚአብሄር ለአይሁድ ሰዎች ተስፋ እንደ ነበረዉ ያዉቃል ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ጠፍተዉ ነበር ፡፡

ብዙዎች በኑሮአቸዉ የእግዚአብሄርን ተስፋ በመስማት የሚታገሉ ነገር ግን የዚያን ተስፋ ፍሬ ያላዩ እንዳሉ አምናለሁ ፤ ያ እናንተ ከሆናችሁ እንድትሆኑ አበረታታችኋለሁ ፡፡ እጃቹሁን በማረሻዉ ላይ አድርጉ ተስፋ እንዳትቆርጡ ፤ ያ በጠንካራ ጊዜ ዉስጥ እንድታልፉ ይረዳችኋል ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (89፡ 1-2)፡ የዚህ መዝሙር የመጀመሪያዉ አካል ስለ ፍቅሩና ስለ መታመኑ እግዚአብሄርን ያመሰግናል፡፡ ማክአርቱር “ መዝሙረኛው ራሱ እግዚአብሄር ለዳዊት ስሮዉ መንግስት ዘላለማዊነት ዋስትና ስለ ሚሆን እንደሚደሰት “ ፅፏል ፡፡ በሌላ ቋንቋ እግዚአብሄር ያበቃ/ያለቀ አይደለም ፤ እግዚአብሄር የታመነ ነው ፡፡

መዝሙር (89፡ 3)፡ በኃይለኛዉ እግዚአብሄር ተስፋዉን እንደሚጠብቅ እናዉቃለን ፡፡ የክብር ንጉስ አሁንም ተመልሶ ይመጣል (2ሳሙ 7፡ 10-13) ፡፡ በጠንካራ ጊዜ ዉስጥ በምናልፍ ጊዜ በተስፋዉ ላይ መፅናት እንችላለን ፤ ይህ ይበቃል ማለት አልችልም ! ዛሬ በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የማየው ማድረግ ባለባቸዉ ፊት የማይጨርሱ ናቸው ፡፡ ነገሮች አስቸጋሪ ወይም ዉጤቱ ተጠብቀዉ እንደ ነበር ሳይሆን ሲገኙ ሰዎች ተለይተዉ ይጓዛሉ ፡፡

መዝሙር (89፡ 4)፡ ከቁጥር 1-4 ዉጪ ቀሪዉ የምዕራፉ ክፍል ለማንበብ በእዉነት አስቸጋሪ ይሆናል ፡፡ ቆይቶም መዝሙረኛዉ እስራኤል እየደረሰበት ስለ ነበረዉ አስቸጋሪ ነገር አዘነ ፤ መዝ (89፡ 29-34) ተመሳሳይ ንግግር አለው ፡፡ ዋይርስቤ “ እግዚአብሄር በባህሪዉ የታመነ ነው - የተመሰገነ ይሁን “ በማለት ይናገራል ፡፡

መዝሙር (89፡ 5-18)፡ ሰማያት፣ ምድር እና የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሄርን አመሰገኑ (ዘኁ 10፡ 35, መዝ 87፡ 4) ፤ እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን አመሰገኑ ምክንያቱም ተስፋዉን ስለ ሚያዉቅ ፡፡

መዝሙር (89፡ 19)፡ መዝሙረኛዉ የእግዚአብሄር ኪዳንን ከዳዊት ጋር ያለዉን ገለፀው ፤ ከዚያም እግዚአብሄር “ ለታማኞቹ “ወይም ለነቢያቱ የተናገረበትን ጊዜ እንደ ገና ፃፈው (1ሳሙ 13፡ 13-15, 2ሳሙ 7፡ 4) ፡፡

መዝሙር (89፡ 20-23)፡ እነዚህ ቁጥሮች ከመዝሙር 91 ጋር ተመሳሳይ ናቸው ፡፡

መዝሙር (89፡ 24-25)፡ መዝሙረኛው እግዚአብሄር ለእስራኤላዊያን ተስፋ የገባትን ምድር ገልጧል ፡፡

መዝሙር (89፡ 26-27)፡ እግዚአብሄር ዳዊት በኩሩን በምድር ነገስታቶች ላይ ታላቅ ለማድረግ ቃል ገባ ፡፡ ስለ በኩርነት ሀሳብና እንዴት ከክርስቶስ ጋር እንደሚገናኝ ለመወያየት እፈልጋለሁ ፡፡ ዳዊት በምድር ነገስታት ላይ ታላቅ ነበር ከዚያም “ የነገስታት ንጉስ ነበር “ ፡፡ ማክአርቱር “ የበኩር ልጅ የተለዬ የክብር ስፍራንና የዉርስ እጥፍ ድርሻን የሚሰጠዉ እንደ ነበር “ (ዘፍጥረት 27, 2ነገ 2፡ 9) ፅፏል ፤ ይሁን እንጂ በንጉሳዊ ዋስትና ኪዳን የተመረጠዉ ግለሰብ የበኩር ወንድ ልጅነት ደረጃ ላይ ከፍ ሊል ይችላል ከዚያም በንጉሳዊ አገዛዝ ወራሽነት ተሳትፎ ዉስጥ ለሚቀጥለዉ ስጦታ ስልጣን ይኖረዋል (መዝ 2፡ 7) ፡፡ ስለሆነም የመጀመሪያ ብቻ አይደለም እስራኤል በሕዝቦች መካከል በኩርም ነበረች (ዘጸ 4፡ 22) ፤ ታናሹ ኤፍሬም እንደ በኩር የታዬ ነበር (ዘፍ 48፡ 13-20) እንዲሁም ዳዊት ከነገስታት መካከል በኩር ነበር ፡፡ ክርስቶስ በሁሉም ፍጥረት ላይ በኩር ተደርጎ የተጠራ ሊሆን ይችላል (ቆላ 1፡ 15)፣ በዚያም ህያዉ ሆኖ በተፈጠረዉ ፍጥረት ሁሉ ላይ መላቅ ተሰጥቶናል (ሮሜ 8፡ 29, ራዕ 1፡ 5) ፡፡

መዝሙር (89፡ 28-37)፡ እግዚአብሄር አለመታዘዝን ይቀጣል ነገር ግን ፍቅሩን አይወስድም ፡፡ ማክአርቱር “ የእግዚአብሄር ኪዳን ከዳዊት ጋር በሰማይ ላይ እንደ ፀሀይና እንደ ጨረቃ መመስረት የዘሩም እርግጠኝነት እንደዚያ እንደ ነበር “ ፅፏል ፡፡

መዝሙር (89፡ 38-52)፡ መዝሙረኛው “ በእኛ ላይ እስከመቼ ትቆጣለህን ? ሁሉንም ለከንቱ ነገር ፈጥረኃቸዋልን? የቀድሞዉ የሁል ጊዜ ፍቅር ድርጊት የታለ ? በማለት የጠየቀ ይመስላል ምክንያቱም እግዚአብሄርን እግዚአብሄር ተስፋዉን ረስቷል ብላችሁ ማየት ስለ ማትችሉ ፡፡ ይህ ለእስራኤላዊያን የቀልድ ጊዜ አልነበረም ፡፡ መዝሙረኛው ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ እግዚአብሄርን ወደ ማመስገን ተመለሰ ፡፡

መደምደሚያ

ይህ እኛ አይደለንምን ? ይህ ኑሮአችን አይደለምን ? ማመስገን፣ ማዘን እና መናገር እንችላለን ነገር ግን እርሱን ማመስገንን እንመርጣለን ምክንያቱም ተስፋዉን እንደሚጠብቅ ስለምናዉቅ ፡፡ ተስፋዬና ፀሎቴ በህይወታችሁ አስቸጋሪ ጊዜ ቢሆንም በእግዚአብሄር ተስፋ ላይ መፅናት እንችላለን ፡፡ በተለይም ሊሰማችሁና ሊያያችሁ እንደማይችል በተሰማችሁ ጊዜ እርሱን ማመስገንን እንድትቀጥሉ አበረታታችኋለሁ ፡፡

John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 655.

  1. MacArthur, p. 656.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 251.

  3. MacArthur, p. 656.

  4. MacArthur, p. 657.

ጥያቄዎች

  1. መዝሙረኛዉ የእግዚአብሄር ታማኝነት ለሁሉም ትዉልድ የታወቀ ለማድረግ እንዴት ቻለ (መዝ 89፡ 1) ? በዙሪያችሁ ካሉት ጋር የእግዚአብሄርን ታማኝነት እንዴት ልትነጋገሩ / ልትግባቡ ትችላላችሁ ?
  2. መዝ (89፡ 11) “ ሰማያት የአንተ ናቸው ምድርም የአንተ ናት ፤ ዓለምንና ሞላዉም አንተ መሰረትህ “ በማለት ያዉጃል/ይናገራል ፤ እግዚአብሄር እንዲገዛ ለማን ሰጠ (ዘፍ 1፡ 29) ? አሁን በእጆቹ ስራ ላይ የሚያስተዳድረዉ ማነው (1ቆሮ 15፡ 27, ኤፌ 1፡ 22) ? አሁን ላይ ሁሉም ነገር ለእርሱ በመገዛት ላይ ነዉ የሚለዉን እንዴት ትገልፁታላችሁ ? (ቆላ 1፡ 15-20)
  3. መዝ (89፡ 14) የእግዚአብሄርን መንግስት ወይም ባህሪ ላልተረዳ ሰዉ እንዴት ትገልፁለታላችሁ ?
  4. በመዝ (89፡ 38) ላይ ለዉጥ አለ ፤ በመጀመሪያዎቹ 37 ቁጥሮች ላይ የሚፃረር/ አብሮ የማይሄድ ነገር ታያላችሁ ? አዎ ከሆነ ይህን እንዴት ትገልፁታላችሁ ?
  5. በመዝሙር 89 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 89:38–39

“But You have spurned and rejected him; You have become enraged with Your anointed. You have repudiated the covenant with Your servant; You have completely dishonored his crown.”

በህይወትህ እግዚአብሔር ወደ ሆነ ነገር እየጠራህ ወይም ለሆነ ለተለየ ነገር እያስነሳህ እንደሆነ ያወክበት ጊዜ አለን ? ምናልባትም ከአመታት በፊት የሆነ ሰው ትንቢት ተናግሮብህ ነገር ግን እስካሁን እግዚአብሔር ሲፈጽመው አላየህም ፡፡ እግዚአብሔር ዳዊትን ቀባው እናም ለዘላለም ትውልዱን ለማጽናት ኪዳንን አደረገ ፡፡ ግን ቢሆንም ዳዊት በህይወቱ ላይ ያለውን የእግዚአብሔርን ጥሪ ተጠራጠረ ፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ታማኝነት ያምናል ፡፡ ያህዌን ያመሰግናል እናም ሁልጊዜም የእግዚአብሔ እጅ እንደሚያበረታው ያውቃል ፡፡ ሆኖም ግን እምነቱ በሚፈተን ጊዜ ዳዊት በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ አልፏል ፡፡

ልትጠይቅ ፣ ልትጠራጠር ወይም ግራ ልትገባ ትችላለህ ፡- በእርግጥ ከእግዚአብሔር ሰምቻለሁን ? በእውነት እርሱ ታማኝ አምላክ ነውን ? መጀመሪያ መንግስቱን መፈለግ እንዳለብህ አስታውስ ፡፡ በጌታ ደስ ይበልህ ፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር በውስጥህ ባስቀመጠው ቦታ ላይ ስራ ፣ ኮትኩት እናም ያለህን አፍስስ ፡፡ በጣም እሩቅ አትመልከት ፣ እየመጣ እንደሆነ ለምታስበው ለዚያ ወርቃማ ጊዜ ብቻ ኑር ፡፡ እጆችህን ከእርፉ ላይ አታንሳ ፡፡ ጽና ፣ አይኖችህንም በእምነትህ ባለቤትና ፈጻሚ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አድርግ ፡፡ ጌታ በጊዜው ይመራሃል ፡፡ እርሱ አልተወህም ፡፡ በርታ አይኖችህንም በኢየሱስ ላይ አድርግ ፡፡

“አንተ ግን ናቅኸው ጣልኸውም፥ የቀባኸውንም ጣልኸው ። የባሪያህንም ኪዳን አፈረስህ፥ መቅደሱንም

በምድር አረከስህ ። “ - መዝሙር 89፡38-39

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 37:3–4 — “ በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ ። በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል ። “
  • መዝሙር 89:20–21 — “ ባሪያዬን ዳዊትን አገኘሁት፥ ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት ። እጄም ትረዳዋለች፥ ክንዴም ታጸናዋለች ። “
  • ምሳሌ 4:25 — “ ዓይኖችህ አቅንተው ይዩ፥ ሽፋሽፍቶችህም በቀጥታ ይመልከቱ ። “