Wisdom Books Psalms

A Cry Of Desperation

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 88 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 434 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ከመፅሀፍ ጋር በብዙ የተለያዩ መንገዶች መስተጋብር/ተፅዕኖ መፍጠር እንችላለን፡ መፅኀፍን ማጥናት እንችላለን፣ በመፅሀፍ ላይ የታዘዙትን መዘመር እንችላለን፣ በመፅኀፍ ላይ ማሰላሰል እንችላለን፣ በቀላሉም መፅሀፍን ማንበብ እንችላለን፣ መፅሀፍን ወደ እግዚአብሄር በመመለስ መፀለይ እንችላለን እንዲሁም ሌሎች ሲያነቡ መፅሀፍን መስማት እንችላለን ፡፡ መጀመሪያ ብዙ ሰዎች ከማንበብ ይልቅ ወደ እግዚአብሄር ቃል ያደምጣሉ ፡፡ መፅሀፍን ማስታወስ እንችላለን ፤ ይህ ብዙ ጊዜ ይረሳል - በመዝ (17፡ 18) መፅሀፍን እንድንፅፍ ይመክረናል ፡፡ ሌላዉ መንገድ በመፅሀፍ ላይ መስተጋብር/ተፅዕኖ ልናደርግበት የምንችለዉ ብዙ ለማንበብ የፈጠነ ንባብ ነው ፡፡ ከመፅሀፍ ጋር መስተጋብር የምንፈጥርባቸዉን መንገዶች መቀያየር በመንፈሳዊነት እንድናድግ ሊረዳን ይችላል ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (88፡ 1-9)፡ ይህ መዝሙር በአለማቀፍ እንደ ጨለማ/መከራ መዝሙር የሚታወቅ ነው ፡፡ ቁጥር 1 በመዝሙሩ ዉስጥ በጣም ጥሩዉን ንግግር ይይዛል “ የምታድነኝ አምላኬ/መድኃኒቴ ነህ “ የሚለዉ ፡፡ መዝሙረኛዉ እግዚአብሄር ወደ ጩኸቱ እንዲያደምጥ ጠየቀው (ቁጥር 2) ፡፡ እንዲያድነዉ ወይም እንዲናገረው እግዚአብሄርን መጠየቅ ይችላል ነገር ግን እግዚአብሄር እንዲሰማዉ ብቻ ጠየቀው ፡፡ ስለ እግዚአብሄር ታላቁ ነገር ሳይናገርና ሳያደምጥ ሲቀር ነው ፡፡

መዝሙረኛው እየሞተ እንደ ነበር የተሰማዉ ስፍራ ድረስ ተረስቶ ነበር (ቁጥር 3) ፤ ለጉድጓዱ የእርሱ መግለጫ ለሲዖል ወይም ለመቃብር መግለጫ ነበር (ቁጥር 4) ፤ ያለ ኃይል ነበር (ቁጥር 4) ፡፡ በእግዚአብሄር የተረሳና የተጣለ እንደ ሆነ ተሰምቶታል (ቁጥር 5) ፤ እግዚአብሄር ከጥልቅ ጉድጓድ ዉስጥ አስቀምጦት እንደ ነበር (ቁጥር 6) እና የእግዚአብሄር ቁጣን ክብደትን ተሰምቶታል (ቁጥር 7) ፡፡ ብዙ ጊዜ ሀዘን በመናወጥ፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ደቂቃ በደቂቃ በመምጣት ያደክመናል ፡፡ ብቻዉን ነበር (ቁጥር 8) ፤ ኃዘኑን ማምለጥ አልቻለም (ቁጥር 9) ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እንዴት እንደሚሰማው ለመናገር ወደ እግዚአብሄር ይጣራል (ቁጥር 9) ፡፡

መዝሙር (88፡ 10-14)፡ መዝሙረኛው የእግዚአብሄር ታምራት ሞተዉ በነበሩት ሰዎች የታወቀ ሊሆን እንደሚችል ለማወቅ ፈለጉ (ቁጥር 10) ፡፡ የሆነ ሰዉ የእግዚአብሄርን ፍቅርና መታመንን በማወቅ ተስፋ መቁረጥንና ጨለማ ሊገጥመዉ ይችላል (ቁጥር 11-12) ፤ ኃዘን እያለበት መዝሙረኛው በእያንዳንዱ ማለዳ ፀሎቱ ዉስጥ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሄር ጮኸ (ቁጥር 13) ፡፡ እግዚአብሄር ከእርሱ ፊቱን በመደበቅ ለምን ዝም ብሎት እንደ ነበር ለማወቅ ፈለገ (ቁጥር 14) ፤ አሁን መዝሙረኛዉ “ ለምን ? “ እያለ እየጠየቀ ነው ፡፡

መዝሙር (88፡ 15-18)፡ ይህ ሰዉ ተስፋ መቁረጡን ብቻ አላወጀም ይህ በህይወቱ እጣዉ እንደ ነበርም እንጂ - ከልጅነቱ ጀምሮ ተሰቃይቶ ስለነበር ወደ ሞት ቀረበ (ቁጥር 15) ፡፡ በዚህ እንደሚጠፋ እስከሚሰማዉ ድረስ በጭንቀት ኖሮ ነበር (ቁጥር 15-16) ፡፡

ይህ መዝሙር ከሌሎች መዝሙር በጣም የተለዬ ይናገራል ፤ ሌሎች መዝሙሮች በአስቸጋሪ ነገሮች ዉስጥ ስለ መሄድ ሲያወሩ ሁሉም መዝሙር በሚባል ደረጃ መዝሙረኛዉ በአስቸጋሪ ሁኔታዎቹ መካከል ላይ በመመለስ እግዚአብሄርን ማመስገን ሲጀምር “ አንተ እግዚአብሄር “ የሚል አንድ ክስተት አላቸው ፤ ነገር ግን ይህ መዝሙር በፍፁም ያን አያደርግም ፡፡ ይህ ለብዙዎች ክርስቲያኖች የእዉነት ልምምድ ነው ፤ አብዛኛዉ ሁሉም ክርስቲያን በእርሱ/በእርሷ ህይወት ዉስጥ በእንደዚህ አይነት ክስተት ዉስጥ ይሄዳሉ ፤ ምናልባትም ለጥቂት ደቂቃ ወይም ለጥቂት ስዓታት ወይም ለጥቂት ቀናት ይቆያል ነገር ግን ለአንዳንዶች ለአሰቃቂ ረጅም ጊዜ ይቆያል ፤ አንዳንድ ጊዜ ለዘላለም ተስፋ የለሽነትን ይደርስባቸዋል ፡፡

በፀሎት ስርዓቶች ላይ ብዙ የለመደን ነን ለምሳሌ እንደ ( የማክበር፣ የንስሐ፣ ምስጋና የመስጠትና የልመና ) እና (ምስጋና፣ ይቅርታ፣ የመጠየቅ፣ የማግኘት) ሲሆኑ ነገር ግን ይህን እንደ ፀሎት ስርዓት በፍፁም አናይም ፡፡ ሁሉም ተስፋዉ ቢጠፋም፣ ተስፋ በመቁጥ ጥልቀት ዉስጥ ቢሆንም እንኳን ይህ መዝሙረኛ በእያንዳንዷ ቀን ወደ እግዚአብሄር ጮኸ ፡፡ በዚህ መዝሙር ዋናዉ ነገር ይህ መዝሙረኛ ከጥልቅ ተስፋ መቁረጡ ዉስጥ በፀሎት ላይ በመጠንከር ለእግዚአብሄር በመናገር መፈፀም ነው ፡፡

መዝሙር 88 ከመዝሙር 22 ጋር እናወዳድር ፤ መዝ (22፡ 1-15) ስታነቡ ይህ መዝሙር ስለ ስቅለት እንደሚገልፅ በጣም ግልፅ ነው ፤ ኢየሱስ ያለፈበትን ከጥማቱ በመስቀል ላይ ጅማቶቹ ከአጥንቶቹ የተለያዩ እስኪሆኑ፣ በእግዚአብሄር የተተወ መሆኑንም ሁሉንም ነገር ይገልፃል ፡፡ ከዚህ አንዱ ማበረታቻ ኢየሱስ ደርሶበት በነበረዉ ህይወት ዉስጥ ብናልፍም ችግር አለመኖሩ ነው ፡፡ ሁሉንም ድካም፣ ሁሉንም ተስፋ የመቁረጥ በተለይም በመስቀል ላይ ያለዉን ስቃይ ሁሉ ደርሶበታል ፡፡ በእነዚህ ጊዜ ዉስጥ ስንሄድ መከራዉን በመጋራት ህብረት አለ ፡፡ ከዚህ በፊት በፍፁም ገጥሞን በማያዉቀዉ ስቃይ ዉስጥ ስናልፍ ከእግዚአብሄር ቀረቤታ አለን ፡፡

መደምደሚያ

ተስፋ በማጣት ጊዜ ዉስጥ በመሄድ ወደ እግዚአብሄር ስትጮኹ - የመጨረሻ አይሆንም ፡፡ ወደ እግዚአብሄር መጮኻችሁን ቀጥሉ ፤ ስለ እናንተ መፀለይ የሚችል ሰዉ በዙሪያችሁ ታገኛላችሁ ፡፡ መዝሙር 88 ለእኛ በጣም ጠቃሚ ነዉ ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ለእኛ ምን እንዳለ መልካም ምሳሌ ስለሆነ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ይህ መዝሙር በቆሬ ልጆች የተፃፈ ነበር ፤ እነማን ነበሩ በአባታቸዉስ ላይ የተፈጠረዉ ታላቅ ክስተት ምን ነበር ? (ዘጸ 6፡ 24, ዘኁ 4፡ 37, ዘዳ 11፡ 6, 1ዜና 9፡ 19)
  2. በኃይል ተስፋ በመቁረጥ እና ተስፋ ከማጣት ዉስጥ እንዲጮህ የሚያደርግ በመዝሙረኛዉ ህይወት ላይ ምን እየሆነ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ? በእግዚአብሄር ላይ የወቀሳ ንግግርን ያስቀመጡ ይመስላል ? ልክ እንደዚህ ተሰምቷችሁ ያውቃል ?
  3. በመፅሀፍ ላይ ሌላ የት ስፍራ ስለ እርዳታ ተስፋ የመቁረጥ ጩኸት የት ታገኛላችሁ ? (ኢዮ 19፡ 19-30, ሰቆ.ኤር 3፡ 55)
  4. በመዝሙር 88 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 88:1–2

“LORD, God of my salvation, I cry out before You day and night. May my prayer reach Your presence; listen to my cry.”

ህይወትህ የቱንም ያህል አስቸጋሪ ፣ ጨለማ ፣ ስቃይ የሞላበት ፣ ተስፋ አስቆራጭና የሚደብር ሊሆን ይችላል ፤ አንተ ግን አሁንም ፡- “ የደህንነቴ አምላክ ነህ “ ትላለህን ? በተስፋ መቁረጥ ጊዜ ውስጥ አልፈህ ከሆነ ፣ በእግዚአብሔር ደህንነት ማግኘት መዋጀት ምናልባት ልትጣበቅበት ልትሸሸግበት የምትችልበት ብቸኛውና አንደኛው የብርሃን ፍንጣቂ እንደሆነ ታውቃለህ ፡፡ ይህ በክርስቶስ የሚገኝ ተስፋ ፤ እርሱ የእምነትህ ባለቤትና ፈጻሚ እንደሆነ እመን ፤ይህም በረጃጅሞቹ ምሽቶችና በማያልቁት ቀናት በተስፋ መቁረጥ ጊዜ ወደ እርሱ እንድትጣራ ያስችልሃል ፡፡

በጉድጓድ ውስጥ በምንም ያህል ጥልቀት ይሁን ያለኸው ፤ ምንም ያህል እንደዛልህ ይሰማህ ፣ ብቻህን አይደለህም ፡፡ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው ፡፡ እርሱ ይሰማሃል ፡፡ እርሱ መዳኛህ ነው ፡፡ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ወደ እርሱ ጩኽ ፡፡ እግሮችህን በአለት ላይ ያጸናል መንገድህንም ያቃናል ፡፡ እርሱ ህይወትህን ያስነሳል ፡፡ ወደ እርሱ ጩኽ እርሱም ያነሳሃል ፡፡

“አቤቱ፥ የመድኃኒቴ አምላክ፥ በቀንና በሌሊት በፊትህ ጮኽሁ ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትግባ፥ ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል “ - መዝሙር 88፡1-2

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 30:1 — “አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥ ጠላቶቼንም ደስ አላሰኘህብኝምና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ። “
  • መዝሙር 40:2 — “ ከጥፋት ጕድጓድ ከረግረግም ጭቃ አወጣኝ፥ እግሮቼንም በድንጋይ ላይ አቆማቸው፥ አረማመዴንም አጸና ። “
  • ዮናስ 2:7 — ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፤ በምድርና በመወርወሪያዎችዋ ለዘላለም ተዘጋሁ፤ አንተ ግን፥ አቤቱ አምላኬ፥ ሕይወቴን ከጕድጓዱ አወጣህ ። “