Wisdom Books Psalms

God Is In The Highs And Lows

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 86-87 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 433 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መዝሙሩ ጸሀፊዉ የደስታን ከፍታ ወይም የብስጭት ጉድጓድ ወይም ሸለቆ እና ተስፋ መቁረጥን እየቀመሰ እንደ ነበር የተፃፈ ነበር ፡፡ ልበ ሙሉ እና ሌሎች “ እኔን “ እንድንል የሚያደርጉ መዝሙሮች አሉ ፤ በማንበብና በመማር ዉስጥ የመዝሙር መፅሀፍ የሚያስደስት ነዉ ምክንያቱም መዝሙር በጣም እዉነት ነው ፡፡

በሕይወቴ አንዳንድ ጊዜ በእዉነት ከፍ ከፍ ያሉ እና አንዳንድ ጊዜ ዝቅ ዝቅ ያሉ ነገሮች ነበሩ ፤ አስተምሮቶቼን ፅፊአቸዉ በነበር የሚያምሩ ቃላቶች ባልነበሩ ነገር ግን ስሜቱ ተመሳሳይ እንደ ሚሆን አስባለሁ ፡፡ በመዝሙር ዉስጥ ሳነብ ተመሳሳይ መንገድ እንደማስብ አስታዉላለሁ ፡፡ በመዝሙር 86 እንጀምራለን ፡፡ ሌሎች ዝቅታን ሲቀምሱ ጥቂቶች ከፍታን ለመቅመስ ወደ ዚህ ጥናት እንደመጡ አስታዉላለሁ ፤ የእግዚአብሄር ቃል ለሁለቱም ይናገራቸዋል ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (86፡ 1-7)፡ ዳዊት ወደ እግዚአብሄር በመጮኽ ስለ ስጦታና ስለ ምህረት እየጠየቀ ነበር ፡፡ ከእናንተ ዉስጥ ምን ያክላችሁ ከእነዚህ ከመጀመሪያዎቹ ሰባት ቁጥሮች ጋር ልትገናኙ ትችላላችሁ ? አሰቃቂ ወይም በህመም የሆናችሁበት ሁኔታ አላችሁ ? አለኝ ! ህመም ስሜታዊ ምላሽን ያመጣል ፡፡ መዝሙሩ ለእኔ ከስሜት የተፃፉ የነፍስ መግለጫዎች ናቸው ፡፡ እግዚአብሄር መልካም እንደሆነ ሳዉቅ ስለ እግዚአብሄር የራሴን መረዳት፣ የራሴን ምክንያት በማምጣት የታመንኩ በመሆን እቀመጣለሁ ፡፡

እግዚአብሄር አስፈላጊ ከሆነበት ጊዜ በላይ በፍፁም ቅርብ ነው ! ይህ የመደሰት ፀሎት አይደለም፣ የጭንቀት ፀሎት ነው ፡፡ ለእግዚአብሄር ሰዉነቴን በማቅረብ ተመልሶ በመምጣት “ ትታመንብኛለህ ? ታምነኛለህ ? እዚህ እንደሆንኩ ታስባለህ ? እንደምሰማህ ታስባለህ ? “ ብሎ የሚጠይቀዉን ሀሳብ እወደዋለሁ ፤ እነዚህ ሁሉም ነገሮች በእግዚአብሄር መንፈስና በነፍሴ መካከል ዝምድና ለመፍጠር ያዘነብላሉ ፡፡ ዳዊት በጣም ጎበዝ ፀሀፊ እንደ ነበር አስባለሁ ፡፡

መዝሙር (86፡ 8-11)፡ ዳዊት የእግዚአብሄርን ትኩረት ፈለገ ነገር ግን እርሱ በእግዚአብሄር እንደማይታመን እግዚአብሄር እንዲያስብ አልፈለገም ፡፡ ለእኔ የሚናገርኝ ክፍል ዳዊት “ ስሙን ለመፍራት ልቡ እንዲያስተባብር/እንዲያበረታው “ ብሎ የፃፈው ነው ፡፡ እነደነዚህ አይነት ነገሮች በምሰማ ጊዜ ዳዊት “ በዚህ ዉስጥ በእኔ ና ፤ እዚህ በአንተ ያለኝን መደገፍ/መታመን ማጣት አልፈልግም አልረዳዉምም እንጂ ፤ መንገዱን አስተምረኝ ፤ ለአንተ እንዴት እንደሚመስል እንዴት እንደማይ እርዳኝ ፡፡ እግዚአብሄር አያስብልህም ወይም ትቶኃል የሚሉ ነገሮችን አርቅልኝ ፡፡ አንተ ማን እንደሆንክ የማዉቅባቸዉን ምክንያቶች በአንድ ላይ አመጣለሁ ፤ ደስ ሲልህ እደሰታለሁ “ በማለት የሚጠይቃቸዉን እሰማለሁ ፡፡

በግሌ ህመም መካከል ላይ ከኔ በበለጠ አስከፊ ህመም በነበረባቸዉ በሌሎች ላይ አተኩር ነበር ፤ ማካካስ የቻልኩበትም ያ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር እንደሚታደገኝ ካወኩኝ ስለ ሚሰማኝ ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም እሰራለሁ ስለሚል ማጣጣሬን በማቆም ስለ ፈዉስ ስለምጠይቅ ፤ ስለዚህም በዳዊት ላይ ምን እንደሚመስሉ በማሰብ በእነዚህ ነገሮች ላይ እመለከታለሁ ፡፡ በምን ዉስጥ እንደሄደ ማሰብ አልችልም ነገር ግን እንደዚህ አይነቱን መዝሙር በማይ ጊዜ የዳዊት ልብ ለእግዚአብሄር የተሰጠ እንደ ነበር አያለሁ ፡፡

መዝሙር (86፡ 12-13)፡ ዳዊት እግዚአብሄርን በማመስገን ስሙን አከበረ ፤ ዳዊት “ ለእኔ ያደረከዉን እመለከታለሁ አስታዉሳለሁም ፤ አመሰግናለሁ ! “ ማለቱን ስመለከት ዳዊት አሁንም ጉዳዩን ለእግዚአብሄር ቢያደርግም እዚህ ጋር አመስጋኝነት አለ ፡፡ እየታገለ ነበር ፤ በህመም እንደ ነበር አላስብም ነገር ግን ጠላቶቹ እየተከተሉት ስለ ነበር የኃዘን ልብ ነበረው ፡፡

መዝሙር (86፡ 14-17)፡ የትዕቢተኞች ትዕቢትና ማህበር ዳዊትን ተከትሎት ነበር ፤ ዳዊትም “ ኃይልንና ተስፋን ስጠኝ ፤ ለመልካም እንዲሆንልኝ ምልክትን አድርግ “ በማለት ፀለዬ ፡፡ ወደ እግዚአብሄር የሚጮሁትን የሚሰሙ እንዳሉ አዉቃለሁ፣ ትሰማላችሁ ? ትረዳላችሁ ? ወይስ ትጠነቀቁላቸዋላችሁ ? ስለ ምታዳምጧቸዉና አሁን ከእግዚአብሄር መስማት ስለሚያስፈልጋቸዉ እግዚአብሄር የረዳቸዉ እንዲሆንና እግዚአብሄር እንዲጠነቀቅላቸዉ እፀልያለሁ ፡፡ በጣም ተባርኬአለሁ ይሁን እንጂ በአስቸጋሪና በሚያሙ ነገሮች ላይ እፀልያለሁ ፡፡

እነዚህ መዝሙሮች በፀሎቴ በጣም ታማኝ እንድሆን ይረዱኛል ፡፡ መዝሙሮቹ ሲበዛ ግላዊ ናቸው ለዚያም ነዉ በጣም የተዛመዱ የሆኑት ፡፡ ችግርና መከራ የታሪካችን አካሎች ናቸው ፡፡ የእግዚአብሄርን ቸርነት ዳዊት ሲጠራጠር አናየውም ፤ ዛሬ አንዳንዶች ይህን መስማት እንደሚያስፈልጋቸዉ አምናለሁ፡ እግዚአብሄርን በመጣራት የምትወዱትን ነገር እርሱን መንገር ትችላላችሁ ፡፡ በሁኔታዎቻችሁ ዉስጥ አይተወንም / አያዳክመንም ፤ ሊገበኛችሁና ሊያፅናናችሁ የሚችለዉ ቅዱስ መንፈሱ/መንፈስ ቅዱስ ጥበብንና ማስተዋልን ይሰጣችኋል ፡፡ ዛሬ እግዚአብሄር እንዲናገራችሁ እንድትፈቅዱለት አበረታታችኋለሁ ፤ ጩኹ ፤ ፀሎታችሁን ይሰማችኋል ፡፡

መዝሙር (87፡ 1-3)፡ መዝሙር 87 መዝለል/መተዉ አልችልም ምክንያቱም እስራኤልና ኢየሩሳሌም የዚህ አገልግሎት መዓከላዊ አካል ስለሆኑ ፡፡ ይህ ከቆሬ ልጆች መዝሙር አንዱ ሲሆን ብቻዊን የሚቆም የሚያምር መዝሙር ነው ፡፡ ቁጥር 2 “ ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሄር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል “ ይላል ፡፡ ጽኝ ኢየሩሳሌምን ትወክላለች ፡፡ ይህ ሁሉንም እስራኤልን የሚወድበት እግዚአብሄር አንድ ማዕከላዊ ከተማ አለዉ የሚል ይመስላል ነገር ግን በሁሉም በተለዬ በከፍተኛ ምልከት/ፍላጎት የሚያዛት/የሚያፀናት አንድ ከተማ አለች ፡፡ ኢየሩሳሌም ማለት ምን ማለት ነው ? የሰላም መምህር ፤ የሰላም መምህር ማለት መለኪያ ወይም ተምሳሌ/አርማ ማለት ነው ፡፡ እግዚአብሄር ከሌላዉ ከእስራኤል ክፍል በበለጠ ኢየሩሳሌምን ይወዳታል ፡፡

መዝ (76፡ 1-2)፡ “ እግዚአብሄር በይሁዳ ታወቀ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው ፡፡ ስፍራዉም በሳሌም ማደሪያዉም በጽዮን ነው “ ይላል ፤ ሳሌም ኢየሩሳሌም ነው ፡፡

መዝሙር (87፡ 4-6)፡ እግዚአብሄር ወደ ሌሎች አማኞች በተስፋፈዉ ከእስራኤል ጋር በኪዳን ጀምሯል ፤ እግዚአብሄር የኢየሩሳሌምን ዜጋ እንደሚቆጥር ከሚያዉቁ በዙሪያቸዉ እስካሉ አሕዛቦች ፡፡ የበኩር ልጆቹ እንደሚሆኑ ይታያሉ ፤ እግዚአብሄር ራሱ ኢየሩሳሌምን ይታደጋል ይመግባቸዋል/ይሰጣቸዋልም ፡፡

መዝሙር (87፡ 7)፡ ይህ ቁጥር እግዚአብሄር እንዴት እስራኤልን እንደለዬ ያሳያል ፡፡ አሁንም እስራኤል ስለ መጨረሻዉ ዘመን በትንቢታዊ ድርሻ ላይ ትልቅ ሚና ትጫወታለች ፡፡ መሲሀቸዉን ያገኛሉ ፤ ሁሉም ነገር ከጺዎን በመመስረት ይመነጫሉ ምክንያቱም ክርስቶስ የጺዎን ማሳያ ስለ ሆነ ፡፡

የመጀመሪያዋ ስፍራ ሳሌም (ጺዎን) በዘፍ (14፡ 18) የተጠቀሰው ነው፡

“ የሳሌም ንጉስ መልከ ጼዴቅም እንጀራንና የወይን ጠጅን አወጣ ፤ እርሱም የልዑል እግዚአብሄር ካህን ነበረ ፡፡ ባረከዉም ፡፡ አብራም ሰማይና ምድርን ለሚገዛ ለልዑል እግዚአብሄር የተባረከ ነው ፤ ጠላቶችህን በእጅህ የጣለልህ ልዑል እግዚአብሄርም የተባረከ ነው አለዉም ፡፡ አብራምም ከሁሉ አስራትን ሰጠው “ (ቁጥር 14፡ 18-20) ፡፡

ዕብ (7፡ 1) ስለ መልከ ጼዴቅ የሚያወራ ሌላ ስፍራ ነው፡

“ የሳሌም ንጉስና የልዑል እግዚአብሄር ካህን የሆነ መልከ ጼዴቅ አብርሃም ነገስታትን ገድሎ ሲመለስ ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው ፤ ለእርሱም ደግሞ አብርሃም ከሁሉ አስራትን አካፈለው ፡፡ የስሙም ትርጓሜ በመጀመሪያ የጽድቅ ንጉስ ነው ኋላም ደግሞ የሳሌም ንጉስ ማለት የሰላም ንጉስ ነው ፡፡ አባትና እናት የትዉልድም ቁጥር የሉትም ለዘመኑም ጥንት ለህይወቱም ፍጻሜ የለዉም ዳሩ ግን በእግዚአብሄር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል “ (ቁጥር 1-3) ፡፡

ይህን መግለጫ ሊያሟላ የሚችል ማንንም ሰዉ አላየሁም ፡፡ ይህ መዝሙር ከእግዚአብሄር እቅድ ጋር ለመያያዝ ፍንጭ አለው ፡፡ ማንም ሊያጠፋት በማይችል በዚች ጥቂት/ትንሽ የኢየሩሳሌም ሕዝብ በኩል እግዚአብሄር ሁሉንም ነገር ይጫወታል ፡፡

መደምደሚያ

እነዚህ ሁለት ምዕራፎች በአንድ ላይ እንደማይሄዱ እናስተዉላለን ፡፡ በጣም የተለያዩ ሁለት ምዕራፎች ላይ ተናግሬአለሁ ይሁን እንጂ መንፈስ ቅዱስ በሁለቱ መካከል ያለዉን ትስስር ገልጦልኛል ፡፡ መዝሙር 87 የፃፈዉ እግዚአብሄር በመዝሙር 86 እኔን ከሚያየኝ እግዚአብሄር ጋር ተመሳሳይ ነው ፤ ተመሳሳይ አምላክ አንድ እቅድን ለሺህ አመታት ያስቀመጠው ስሜን ከሚያዉቀዉ እግዚአብሄር ጋር ተመሳሳይ ነው ፤ የእነዚህ ምዕራፎች ዉበት ያ ነው ፡፡ በችግርና በመከራም እንኳን እግዚአብሄር ታላቅ ነው ! ከፍ የሚያደርግብን ጥንካሬዉ ነው !

ጥያቄዎች

  1. በመዝ (86፡ 11) ዳዊት “ አቤቱ መንገድህን ምራኝ በእዉነትህም እሄዳለሁ ፤ ስምህን ከመፍራት ልቤ ደስ ይለዋል “ በማለት ፅፏል ፤ እንዲህ አይነት ፀሎት ፀልያችሁ ታዉቃላችሁ ? ሁልጊዜ የእግዚአብሄር መንገድ የእናንተ ነው ?
  2. የእግዚአብሄር ከእዉነታችን እንዴት የተለዬ ነው ? እግዚአብሄርን የፈራን እንድንሆን ተመርጠናል / ተለይተናል አዎ ከሆን በምን አይነት ሁኔታ ?
  3. በመዝ (86፡ 17) ዳዊት ለምልክት ጠየቀ ፤ እግዚአብሄርን ለምልክት ጠይቃችሁት ታዉቃላችሁ ? በአዲስ ኪዳን ስር የተለዬ ምልክት እግዚአብሄርን መጠየቅ ችግር የለዉም ብላችሁ ታስባላችሁ ? (መሳ 6፡ 36-40, ማቴ 12፡ 39, ሮሜ 8፡ 14, 1ቆሮ 1፡ 22, 2ቆሮ 5፡ 7)
  4. መዝሙር 87 ፂዎንን ባመለከተ ጊዜ ሰለ ምን ወይም የት እያወራ ነው ? (ዕብ 11፡ 9-10, ራዕ 21፡ 10-27)
  5. በመዝሙር (86-87) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 87:7

“Singers and dancers alike will say, ‘My whole source of joy is in you.’”

ራስህን ጠይቅ ፡- የደስታዬ አጠቃላይ ምንጭ በጌታ ነውን ? ደርቆና ዝሎ ከመኖር ይልቅ የጌታ ህያው ምንጭ የህይወትህ የደስታ ምንጭ እንድሆን ፍቀድ ፡፡ እርሱ ብቻ ልብህን ደስ ማሰኘት ይችላል ፡፡

በህይወት ሁሉም ነገሮች መንገዳቸውን የሚያገኙትና የሚከናወኑት በእግዚአብሔር ነው ፡፡ ከጉድጓድ ያስመልጥህ ፤በርህራሄውና በጸጋውም ያውጣህ ፡፡ እግዚአብሔር ለቁጣ ይዘገያል ፣ በእውነት ባለጸጋ በፍቅሩም ታማኝ ነው ፡፡ ያ ነው እግዚአብሔር ማለት ፡፡ የታላቅ ፍቅሩ ወንዝ ፤ የጸጋውም ፈሳሽ እንድሁም ምህረቱ እንደ አንድ እውነተኛ የጸጋ ምንጭ እንድፈስ ፍቀድ ፡፡ ወደ ሌላ ማየቱን አቁም ፡፡ ትንስ ደስታ ከዚህ አለም ነገሮች ፣ ትንስ ደስታ ከጊዜያዊ እርካታ ፣ ትንስ ደስታ ከምድር ወዳጅነት እናም ከዚያ ትንስ ደስታ ከኢየሱስ መፈለጉን አቁም ፡፡ ይልቁንም በሁሉም ነገር ጌታ የደስታህ ምንጭ እንድሆን ፍቀድ ፡፡ እናም አንዴ ጌታ የደስታህ ሁሉ ምንጭ እንደሆነ ካወቅህ ፣ ይህ መዝለል እንድትፈልግ ያደርግሃል ፡፡

“በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል ። “ - መዝሙር 87፡7

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 86:13 — “ ምሕረትህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥ ነፍሴንም ከታችኛይቱ ሲኦል አድነሃታልና ። “
  • ኢሳይያስ 58:11 — “ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ ። “
  • 2ኛ ቆሮንቶስ 3:5 – “ ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም “