Wisdom Books Psalms

Prayer For Revival

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 85 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 432 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህን መዝሙር በማስተማሬ በጣም ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ቀጥር 6 የመነቃቃት መዝሙር ስለ ሆነ ፡፡ የሪቫይቭ ት/ቤት ነን - ይህ በጣም ስሜትን የሚያነሳሳ/የሚያስደስት ነው ! ይህ መዝሙር በቆሬ ልጆች የተፃፈ ነበር ፡፡ የቆሬ ልጆች የቅድስተ ቅዱሳን በተቀደሱ እቃዎች ላይ አደራ የተሰጡ/የተሸሙ ነበሩ ፡፡ በመጨረሻም በእግዚአብሄር ላይ ፊታቸዉን አዞሩ ፤ ይህን መዝሙር የፃፉት ለእግዚአብሄር ታማኝ ሆነዉ በመቅረት የነበሩ ናቸው ፡፡ ለመነቃቃት የሚያስፈልገዉን ለመፃፍ ማን የተሸለ ነው ? ለቤተሰብ ቤዛነት/መዋጀት የሚያስፈልገዉን ለመረዳት ማን የተሸለ ነው ?

ምናልባትም ይህ መዝሙር በባቢሎን ምርኮ ከ70 አመታት በኋላ ወደ ምድራቸው የአይሁድ ሕዝቦች መመለስ በኋላ የተፃፈ ነበር (ኤርሚያስ 29) ፡፡ ምርኮኝነት ደርሶባቸዉ ነበር አሁን ደግሞ ነፃነት ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (85፡ 1-3)፡ መዝሙረኛዉ ያደረገዉ የመጀመሪያዉ ነገር ለእግዚአብሄር ምስጋና መስጠትን ነበር ፤ ይህ ለመነቃቃት ቁልፍ ስፍራ/ቦት ነው ፡፡ ነፃ ስለ ወጣችሁት ነገር እግዚአብሄርን ልታመሰግኑት ይገባችኋል ፤ አመስጋኝነት በባርነት አስተሳሰብ መቆየትን ለማሸነፍ ይረዳችኋል ፡፡ የማመስገን ልብ ሲኖራችሁ ተመልሳችሁ ምርኮኝነት አስተሳሰብ ዉስ እንዳትሄዱ ይጠብቃችኋል ፤ እግዚአብሄርን ስታመሰግኑ ያለፈዉን ነገር ሁሉ እንድትታገሉ ይረዳችኋል ፡፡

እግዚአብሄር መልሶ የተስፋይቱን ምድር ለእስራኤላዊያን እየሰጣቸዉ ነበር ፤ ሕዝቡ ምድራቸዉና ማንነታቸዉ መልሶ ተሰጣቸው ፡፡ ጥፋተኝነታቸዉ ተወስዶላቸዉ ነበር ፡፡ የሚያስደንቀዉ ነገር ይህ ሁሉም በኢሳ (40፡ 1-2) ላይ ተተንብዮ ነበር ፡፡ በግልፅ እነዚህ ቃሎች ለእስራኤላዊያን የተገቡ ነበሩ ነገር ግን ስለ ድነታችሁ ወይም ስለ ቤታችሁ ስታመሰግኑት መጨረሻ ጊዜዉ ነበር ፡፡ እዉነተኛን መነቃቃት ለመረዳት ከፈለጋችሁ የአመስጋኝ ልብ መኖር ነው ፡፡

መዝሙር (85፡ 4-7)፡ ዋይርስቤ በእነዚህ ቁጥሮች መዝሙረኛዉ የታደሰ ህይወትን እንደጠየቀ ተናግሯል ፡፡ ምንም እንኳን አሁን እስራኤላዊያን ነፃ ቢሆኑምአሁንም መታደስና መነቃቃት አስፈልጓቸዋል ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ የእግዚአብሄር ቁጣ ከህዝቡ ላይ ተመልሶ እንደ ነበር ፤ ይሁን እንጂ መታደሳቸዉም እስኪፈፀም ድረስ ሕዝቡ የእግዚአብሄር ቁጣ ተፅዕኖ ተሰማቸው …..የሕዝቡ ችግሮች በኃጢዓታቸዉ ምክንያት በእግዚአብሄር መቀጣታቸዉ እንደ ነበር “ ይናገራል ፡፡ መዝሙረኛው “ እንደገና አታነቃቃንምን በዚህስ ሕዝቦችህ በአንተ ይደሰታሉን ? “ በማለት ጠየቀው ፤ መነቃቃት/መነሳት ማለት እንደ ገና መኖር፣ በሕይወት የታደሰ መሆን ማለት ነው ፡፡ ቻርለስ ጂ.ፊኒይ “ መነቃቃት ለእግዚአብሄር ለመኖር በመታዘዝ በኃይለኛ ፍላጎትን ያስከተለ የኃጢዓት እና የንስሃ የታደሰ እምነት ነው ፤ በጠለቀ ትህትና ለእግዚአብሄር ፍቃድን መስጠት እንደሆነ “ ፅፏል ፡፡

እንደገና ያለማቋረጥ ሁላችንም የተነቃቃን መሆን ያስፈልገናል ፤ የሚቀጥል ዑደት ነው ፤ ለዚህም ነዉ ጳዉሎስ ወደ ተመሳሳይ ከተሞች ደግሞ ደግሞ የሚሄደው ፡፡ በዩናይትድ ስቴት ያንን ተጠቀሙ ወይም ይህን ለማንበብ ተጠቀሙ የሚሉ ክርስቲያን ለመሆን የሚጠይቁ ብዙ አማኞች አሉ ፤ ጥሪዬ ያንን እሳት ማቀጣጠል ነዉ ይህ ከሆነ ክርስቲያኖች እንደገና በወንጌል ፍቅር ይወድቃሉ ፡፡

  • ራዕ (3፡ 2-3) “ ስራህን በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን ሊሞቱም ያላቸዉን የቀሩትን ነገሮች አጽና ፡፡ እንግዲህ እንዴት እንደ ተቀበልህና እንደ ሰማህ አስብ ጠብቀዉም ንስሐም ግባ ፡፡ እንግዲያስ ባትነቃ እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ በማናቸዉም ሰዓት እንድመጣብህ ከቶ አታዉቅም “ ፡፡

እግዚአብሄር የሰጣችሁን ነገር በማስተዋል እናንተ በዚያ ላይ ምንም ነገር እንዳላደረጋችሁ ስትረዱ መነቃቃት ይሆናል ፤ ይህ የቤተ ክርስቲያን የሚያስደንቅ መልክ እንደ ሆነ አስባለሁ ፡፡

መዝሙር (85፡ 8-13)፡ መዝሙረኛው የእግዚአብሄርን ቃል እንደ ሚሰማ ማለ/ቃል ገባ ፡፡ አንዴ ከታደሳችሁ ስለ አቅጣጫ እግዚአብሄርን በመጠየቅ ወደ እርሱ መልዕክት ማዳመጥ ፡፡

መደምደሚያ

ካይል በፀሎት ደምድሞታል፡

“ ጌታ ሆይ የተሰጠንን ነገር እንድናይ እንድትፈቅድልን መፀለይ እፈልጋለሁ ፤ ለእዉነት አይኖቻችንንና ጆሮአችንን ክፈት ፤ ስላዳንከኝ፣ ስለ ቤተሰቦቼ እና ስለ ቡድኔ አመሰግንሀለሁ ፡፡ ኢየሱስ በመስቀለ ላይ ስለሞተ አመሰግንሀለሁ ! በሞት ዉስጥ፣ በመቀበር እና በትንሳኤ በኩል ስላለፈ ፤ ከአንተ ዉጪ ዛሬ እዚህ አንሆንም ፤ ምክንያቱም በክርስቶስ ላለሁት እኔ ሁሉንም ቀን የታደስኩና የተነቃቃሁ መሆን ያስፈልገኛል ፡፡ አምላክ ሆይ የማልቀሳቀስ ወይም አለማዊ አልሆንም ፤ ለሰይጣን ንገድ የተሰጠሁ አይደለሁም ፤ በእዉነት በአንተ የምነቃቃ እሆናለሁ ፡፡ የሚሰሙትን ሁሉ ወይም ይህን አሁን የሚነበበዉን እየጠየኩ ያለሁት ለዚያ ነው ፡፡ ምን እንደተሰጠን ብናስታዉልም ያ ጊዜ በጣም አጭር ነው ፤ የሰዉን መንፈስና ነፍስን እንድታነቃዉ እጠይቅኃለሁ ፡፡ እንድታድሰን እጠይቅኃለሁ ይህ ከሆነ አንተን እናንፀባርቃለን ! የሪቫይቭ ት/ቤት ተማሪዎችን አነቃቃ ! የአመስጋኝነት መንፈስም ይኖረናል ፡፡ መሰናክሎቻችንንና ግንቦቻችንን በመዉሰድ ተናገረን “ ፡፡

“ እዉነተኛ መነቃቃት ቤተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስን ስትሰማ የሚሆን ነው ፤ መንፈስ ቅዱስን ስናደምጥ እምድማደርግ የጠየቀንን እንደምናደርግ በእርግጠኝነት አምናለሁ ፡፡ አባቴ እግዚአብሄር ሆይ እንድናደርገዉ ነግረኸን ስላላደረግነዉ ነገር ይቅር በለን ፤ በወንጌል ላይ ያዥ/ዝምተኛ በሆንበት ነገር ላይ ይቅር በለን ፤ በኢየሱስ ላይ ዝም ስላልንበት ነገር ይቅር በለን ፡፡ እዉነትን ለመናገር በግልፅ እንደጠየከን እናዉቃለን ፤ ቤተ ክርስቲያንን ይቅር እንድትል እጠይቅኃለሁ ፤ ለወንጌል እዉነት ቀስቅሰን ፡፡ የተሰጠንን ምንናገር ሰዎች እንሆናለን ፤ መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ዉስጥ ለማንኛችንም/ለአንድኛችን በመናገር ምን እንድናደር እንደምትፈልግ አሳዬን ፡፡ አባት ሆይ እባክህን ምራን ፡፡ የቆሬን ልጆች እንመስላለን ከቀድሞ ስራችን በመማር ወደ አለም መንገድ የተሰጠን/የገባን አንሆንም ፤ አባት ሆይ እርዳታህና ምሪትህ ያስፈልገናል “ ፡፡

“ ኦ አምላክ ሆይ እንደ ገና አስነሳን ! ሕዝባችን መነቃቃት/መነሳት ያስፈልገዋል ፡፡ ለመዉሰድ ምን እንደሚሆን አላዉቅም ነገር ግን ስለ መንፈስህ ሀገራዊ እንቅስቃሴ እየጠየኩ ነው ፤ በእኔ፣ በቡድኔ ወይም በሚሰሙት ላይ ይጀምር ፡፡ ሰዎስተኛዉን ታላቁን መነቃቃት ለማየት እናፍቃለሁ ፡፡ ከእኛ ዉስ ማንኛችንም ማየት የምንችልበት መንገድ ወይም የምንቀምስበት ካለ እንዲሆን እጠይቃለሁ ፤ በራስ ወዳድነት መንፈስ ሳይሆን በመሰብሰብ እንጂ ፡፡ እግዚአብሄር ይህን ሀገር በማነቃቃት በቤተ ክርስቲያን ይጀምራል ፡፡ በኢየሱስ ስም ፀለይን አሜን “ ፡፡

  1. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 648.

  2. Earl D. Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 704.

  3. Charles G. Finney, 10 Charles Finney Quotes; available at https://www.viralbeliever.com/charles-finney-quotes/..

ጥያቄዎች

  1. በዉድቀት ጊዜ ዉስጥ ካለፋችሁ ወይም በእግዚአብሄር የተቀጣችሁ ሆናችሁ ከሆንም እንኳን በዚህ መዝሙር ልትከተሉት የምትችሉት የተሰጧችሁ ጥቂት ጥዕዛዞች ምንድን ናቸው ?
  2. በመዝ (85፡ 2) መዝሙረኛዉ ለእግዚአብሄር አመስጋኝነቱን ለማሳየት እንዴት አደረገ (መዝ 32፡ 1-11) ? ይህ ታላቅ እዉነት ከእግዚአብሄር ጋር ያላችሁን ጉዞ እንዴት ተፅዕኖ ያደርግባችኋል ? አሁንም እግዚአብሄር ንስሀ እንድትገቡ እነየጠየቃችሁ እንደ ሆነ የምታዉቁት የፀናችሁበት ኃጢዓት አለ ?
  3. በመዝ (85፡ 6) መዝሙረኛዉ ወደ እግዚአብሄር ለምኖት ከነበረዉ ኋላ ትርጉሙ ምን ነበር ? አዲስ ሕይወት ከየት ይመጣል (ሕዝ 36፡ 25-27, ዘካ 4፡ 6, ዮሐ 6፡ 63) ? ለመነቃቃት መቼ ነዉ የምንፀልየው (መዝ 85፡ 1-5) ? ለማን ነዉ መፀለይ ያለብን ?
  4. እግዚአብሄር ለሕዝቡ የሚያመጣዉን መዳን/ድነት መዝሙረኛዉ እንዴት ገልፆታል ? (ዮሐ 1፡ 14, 17)
  5. በመዝሙር 85 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 85:6

“Will You not revive us again so that Your people may rejoice in You?”

“ ጌታ ሆይ እንደገና አታነቃቃንም አታነሳሳንምን ? “ ትገረማላችሁ ? እግዚአብሔር ለራሱ እንድህ ቢያስብ ፡- የምር እኔ እናንተን መቀስቀስ ያለብኝ ለምን ያህል ጊዜ ነው ? ከኔ ፊታችሁን ወደ ሌሎች አማልክቶችና ወደዚህ አለም ነገሮች እየመለሳችሁ ፣ ሰልችታችሁኛል ፡፡ እናም ከዚያ በኋላ ወደ እኔ ትመለሳላችሁ እናም ደግሜ አነቃቃችኋለሁ ፡፡ በቃ ምልልሱ እንድህ እያለ ይቀጥላል ፡፡

የሚያስገርመው ነገር እግዚአብሔር እንደዛ አያስብም ፡፡ ያ የኛ የሰዎች ምልከታ ነው ፡- የሱን የቤዛነት ፍቅር ለመቀበል ብቁ እንዳልሆንን ማሰብ ፡፡ የሰማዩ አባታችሁ ቆሞ እጆቹን ዘርግቶ ፍቅር በተሞላ ልብ እናም በርህራሄ “ እንኳን ተመለስክ ልጄ ፣ እወድሃለሁ ፣ እንኳ ተመለስክ ልጄ “ ይላል ፡፡

እግዚአብሔር እንደገና ያነቃቃችኋል ፡፡ እርሱ ይቅር ይላችኋል ፡፡ ዛሬ የትም ቦታ ይሁን ያላችሁት ፣ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ ፡፡ ስለ ድንቅ ጸጋውና ስላ ታማኝ ፍቅሩ አመስግኑት ፡፡ ይቅር እንድላችሁ ጠይቁት እናም ከዚያ እርሱ ለእናንተ ያለውን መልዕክት አድምጡ ደግሞም መንገዱን ተከተሉ ፡፡ ለራሳችሁ መኖር አቁሙ ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ እናም አምሯችሁን እንድያድስና ነፍሳችሁን እንድያነቃቃ ፍቀዱለት ፡፡ ዛሬ ለቤተክርስትያን እንድትነቃ ጸልዩ ፡፡

“አቤቱ፥ ትመለሳለህ ታድነንማለህ፤ ሕዝብም በአንተ ደስ ይላቸዋል ። “ - መዝሙር 85፡6

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 2ኛ ዜና 7:14 — “ በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ ። “
  • ያዕቆብ 4:8 — “ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ ። “
  • 1ኛ ዮሐንስ 3:1 — “ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም ። “