Wisdom Books Psalms

Celebrating the Journey

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 84 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 431 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የመዝሙር መፅሀፍን በማጥናት ተደስቻለሁ ምናልባትም እስካሁን ካጠናናቸዉ ማንኛዉም መፅኀፍት ይበልጥ ፡፡ በግሌ በዚህ የተደሰትኩበት ምክንያት በብዛት በኢየሩሳሌም ላይ ያተኮረ ስለሆነ አስባለሁ - የጌታ ምድራዊ ከተማ እና የጌታ ሰማያዊ ከተማ በሆነችዉ ፡፡ መዝሙር 84 ወደ ላይ የመዉጣት መዝሙር በመባል የታዬ እና ሌሎች መዝሙሮች ካስቀመጡት ገፀ ባህሪያት ትንሽ የሆነ ይመስላል ፤ ሌሎች ወደ ላይ የመዉጣት/ከፍ የማለት መዝሙሮች መዝሙር (120-134) ናቸው ፡፡ ይሁን እንጂ መዝሙር 84 መዝሙር (120-134) እንደሚያደርጉት ከፍ የማለትን/ወደ ላይ የመዉጣትን ንዑስ ርዕስ አይናገርም/አይይዝም ፤ ማክአርቱር ይህን መዝሙር ልክ እንደ ሌሎች ወደ ላይ የመዉጣት መዝሙሮች “ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ የተጓዘን የአንድ መንፈሳዊ ተጓዝ ደስታን ከበዓላቱ አንዱን ለማክበር ከዚያም ወደ ቤተ መቅደሱ ድረስ ያለን ደስታ ይገልፃል… በእግዚአብሄር አምላክ መገኘት ፊት በመሆን “ በማለት ይናገራል ፡፡

ወንድ አይሁዶች ወደ ቤታቸዉ እየተመለሱ የነበሩት “ በዚህ ምድር ላይ አሁንም መንፈሳዊ ተጓዦች እንደ ነበሩ በሚያስታዉሷቸው “ ሰዎስት ቅዱስ በዓላት (ዘጸ 23፡ 17, 34፡ 23) ጊዜ ወደ ቤተ መቅደስ መሄድ ይጠበቅባቸዉ ነበር ፡፡ የመዝሙር 84 እና የሌሎች ወደ ላይ የመዉጣት/ከፍ የማለት መዝሙር ግንኙነቶች በቁጥር 7 ላይ የሚገኝ ነው “ ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ ፤ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል “ ፤ ፂዎን የኢየሩሳሌም ሌለኛዉ ስም/መግለጫ ነው ፡፡ ዋይርስቤ “ በፂዎን በእግዚአብሄር ፊት ይታያሉ የሚለዉ ሀረግ ይህ መዝሙር ከሰዎስቱ አመታዊ በዓላት አንዱን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ በማይችለዉ አንድ አይሁዳዊ የተጠቀሰ እንደ ነበር እንደ ሚያመለክት “ ይገልፃል ፡፡

ትምህርት

መዝሙር (84፡ 1-4)፡ ዋይርስቤ እነዚህን አራት ቁጥሮች እንደ “ ደስታዬ በጌታ ነዉ “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ መዝሙረኛው የእግዚአብሄርን ቤተ መቅደስ በማስታወስ እንደ ተወደደም ገለፀው (መዝ 26፡ 8) ፤ ይህ ፀሀፊ የቤተ መቅደሱ በሮች ጠባቂዎች ከነበሩት ከቆሬ ልጆች አንዱ ነበር ፡፡ አይሁዶች የእግዚአብሄር መገኘት ቤተ መቅደሱ ላይ ብቻ እንደ ነበር ተረዱ፣ እግዚአብሄር በሳጥን ዉስጥ ወይም በሕንፃ ዉስጥ አይቀመጥም መገኘቱ በሁሉም ስፍራ ነው (ሐዋ 7፡ 47-50) ፡፡ መዝሙረኛው እግዚአብሄርን ናፈቀው (ቁጥር 2) ፤ በጌታ ስናድግመገኘቱን በመቅመስ ከእርሱ ጋር ወደ ሚሻል የተለያዩ መንፈሳዊ ደረጃ እንሄዳለን ፡፡ ማክአርቱር “ መዝሙረኛው በእግዚአብሄር መሰዊያ አጠገብ በቤተ መቅደሱ አደባባይ ላይ እነዚህ ወፎች ጎጇቾዉን መስራት ይችሉ እንደ ነበር “ አመልክቷል (ቁጥር 3) ፡፡ ያለማቋረጥ እግዚአብሄር የሚያመልኩት እንዴት ደስተኞች ናቸው (ቁጥር 4) ፡፡

መዝሙር (84፡ 5-8)፡ ዋይርስቤ ቁጥር (5-8) “ ኃይሌ በእግዚአብሄር ነዉ “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡ ከዚያም መዝሙረኛው ወደ ኢየሩሳሌም የሚኬድባቸዉን ተግባራዊ ጉዳዮችን መመለስ ጀመረ ፤ መዝሙረኛው በጉዞአቸዉ ከእግዚአብሄር ኃይልን የሆነላቸዉን አመለከተ (ቁጥር 5) ፡፡ በጉዞአቸዉ ጊዜ በሸለቆዎች ወይም በዝቅተኛ ቦታ ቢሆኑም እንኳን እግዚአብሄር የምንጭ ዉሃንና የመከረን ዝናብ ይሰጣቸዋል (ቁጥር 6)፣ ከአንዱ የእግዚአብሄር ስጦታ ወደ ሌላው ተጓዘ ፡፡ ስለ ቁጥር 7 ማክአርቱር “ በኢየሩሳሌም ደስ የሚያሰኝ አምልኮን መጠባበቅ በአስቸጋሪ ጉዞአቸው የኃይማኖት የተፈጥሮ ጉዞ ድካማቸዉን እንደተቋቋሙት “ ይፅፋል ፡፡ ይህ በጉዞ ጊዜ ከእግዚአብሄር ኃይል የማግኘት ምርጥ መልክ ነው ፡፡

ሪቫይቭ ት/ቤት ለእኛ ጠንካራ/አስቸጋሪ ጉዞ ነው ፤ ለሁለት አመታት እንዳያችሁት ከዚህ በፊት አድርገነዉ የማናዉቀዉን ልምዳችን ያልሆነዉን የሆነ ነገር በማድረግ የእግዚአብሄርን ቃል በመፈልፈል በዚህ መንገድ እያወራንና እያስተካከልን በዚህ ጥቂት ትምህርት ዉስጥ ነን ፡፡ ከዚህ ዉጪ የታየው የሚያዘጋጅ ስራ ነው ፡፡ በእርሱ ጥንካሬ/ኃይል ከሌለኝ ይህ ጉዞ የተጀመረ ቢሆንም እንኳን እንዳለ መቀጠሉ በጣም ያነሰ ነው ፤ ነገር ግን ጉዞዉ ጠንካራ ቢሆንም እንኳን እግዚአብሄር ለመጨረሻዉ እንደሚያደርሰን እናውቃለን ፡፡ ይህ አስፈሪ ስዕል ይሆናል ነገር ግን በጣም በብዙ በመኝታ ክላሴ በዋኞ ቤት ምድር ላይ አጠናለሁ ፡፡ ኋላዬን/ጀርባዬን ግድግዳዉ ላይ በማድረግ በወለሉላይ እቀመጣለሁ፣ ብዕሮቼም ከአይፓዴ እና ከወረቀቶቼና በዙሪያዬ ካሉት ሁሉ ጋር ከኔ በመቀጠል ወለሉ ላይ ይቀመጣሉ እኔም ቃሉን አጠናለሁ ፡፡ ያን ለማድረግ ከቀኑ 4 ሰዓት ወይም ከቀኑ 12፡ 30 ላይ ከባድ ነው ፡፡ ይህ በዚህ ጉዞ ዉስጥ የማለፍ የእኔ እዉነት ነው፣ እንዲሁም እግዚአብሄር ለኢየሩሳሌም እያዘጋጀኝ እንደሆነ አዉቃለሁ ለሚመጣዉ ቀን እዚህ ምድር ላይ በማዘጋጀት ወይም ለሰማያዪዉ ኢየሩሳሌም ሁኔታ ፡፡ ሁል ጊዜ አይኖቼ በብዛት በእግዚአብሄር መንፈሳዊ ጉዞዎች መለማመድ ላይ ናቸው ፡፡ እያጠናሁ በነበረበት ጊዜ መዝሙር 84 በአዲስ ኪዳን እንዲያሳየኝ እግዚአብሄርን ጠየኩት ፡፡ እግዚአብሄር ብዙ ማሳያዎችን በመስጠት ስለ ኢየሱስ እንዳወራ ነገረኝ ፡፡

በሉቃስ 9 ኢየሱስ የእርሱ ጊዜ በምድር ላይ መጨረሱ እየመጣ እንደ ነበር ያውቃል ፤ ቁጥር 51 ጊዜዉ ኢየሱስን ወደ ሰማይ ለመዉሰድ የመጣ ነበር ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ ፡፡ በጉዞዉ ላይ ኢየሱስ በሰማሪያ ነገሮችን ለእርሱ እንዲያዘጋጁ መልዕክተኞችን አስቀድሞ ላካ ነገር ግን በደህና አልተቀበሉትም ምክንያቱም ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ስለ ነበር (ቁጥር 53) ፡፡ ሰማሪያዊያን ባልተቀበሉት ጊዜ ያዕቆብና ዮሐንስ አካባቢዉን ለማጥፋት ዝግጁ ነበሩ ነገር ግንኢየሱስ እነርሱን በመገሰፅ ወደ ሌላ አካባቢ ሄደ (ቁጥር 54-56) ፡፡ አንዳንድ በጉዞዉ ጊዜ መንፈሳዊ ጉዞዎች የተተዉ ናቸው፣ መንገዶች የተቀየሩ ሲሆኑ ጉዞዉ ቀላል አይደለም ፡፡

መዝሙር (84፡ 9-12)፡ ዋይርስቤ ቁጥር (9-12) “ መታመኔ በእግዚአብሄር ነው “ በማለት ይገልፃቸዋል ፡፡

መደምደሚያ

ወደ ኢየሩሳሌም በኢየሱስ የመጨረሻ ጉዞ ላይ ኢየሱስ ኢየሱስ የፈወሰዉን በርተሚዎስን አገኘው (ሉቃ 18፡ 35-43) ፤ ከዚያም ኢየሱስ የዳነዉን ቀረጥ ሰብሳቢዉን ዘኪዎስን አገኘው፣ በኢያሪኮ የሄሮድስን ቤተ መንግስት አለፈ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም አስቸጋሪ 18 ማይል ከፍታ ወደ ላይ በይሁዳ ምድረበዳ ላይ ወጣ ፡፡ ሁልጊዜ ጉዞ ቀላልና የተደላደለ እንዲሆን እንፈልጋለን ነገር ግን የኢየሱስ ጉዞ ከሁለቱም ዉጪ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄርን መገኘት መልመድ በጉዞ ላይ ይሆናል ፤ የኢየሱስ ጉዞ ኢየሱስ በወንበዴዎች ተደብድቦ ስለ ነበረዉ አንድ ሰዉ የተናገረበት ምሳሌ በትንሽ ሆቴል በመልካሙ ሳምራዊ ቀጠለ (ሉቃ 10፡ 30) ፡፡ የኢየሱስ ምሳሌ በመቆም አይሁዳዊዉን ሰዉ ስለረዳዊዉ በተጨማሪም በራሱም አህያ ላይ በማስቀመጥ ወደ ትንሽ ሆቴል በመዉሰድ ለእንክብካቤዉ ገንዘብ ስለ ከፈለዉ ሳምራዊዉ ሰዉ የተነገረ ነበር ፡፡ በጉዞ ላይ ምንም ይፈጠር ችግር የለዉም እግዚአብሄር ሊያነሳንና የሚያስፈልገንን ሊሰጠን በዚያ ነው ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር ጉዞአችንከምንጠብቀዉ በላይ በጣም አስቸጋሪ ነው ፤ ነገር ግን በመዝ (84፡ 7) መሰረት በዚያ ዉስጥ በማለፍ ለማፍራት ከኃይል ወደ ኃይል መጓዝ እንችላለን ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ስንደገፍ በጉዞ ዉስጥ እንቆያለን/እንድናለን ፡፡

  1. John MacArthur, John MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 652.

  2. MacArthur, p. 652.

  3. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Old Testament (Colorado Springs: David C. Cook, 2004), p. 242.

  4. Wiersbe, p. 242.

  5. Wiersbe, p. 242.

  6. MacArthur, p. 652.

  7. Wiersbe, p. 243.

  8. MacArthur, p. 652.

  9. Wiersbe, p. 243.

ጥያቄዎች

  1. መዝሙረኛዉ የእግዚአብሄርን ቤት በጣም ለምን ይወደዉ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ (መዝ 26፡ 8) ? በመዝ (84፡ 1-2) የእግዚአብሄርን ቤት ለመግለፅ የተጠቀመዉ ቋንቋ ምን ነበር ?
  2. በዚህ መዝሙር ላይ ሰዎስት ጊዜ መዝሙረኛዉ ደስተኛ እና የተባረከ መሆን የሚለዉን ጠቅሷል ፤ እነዚህን የተለዩ ቃላቶች በመጠቀም ምን እየገለፀ ነበር ? እነዚህ ሰዎስት ነገሮች ይገልፁአችኋል ?
  3. ወደ ቤተ መቅደስ “ ልባቸዉ በመንፈሳዊ ተጓዥነት የተቀመጠው “ (መዝ 84፡ 5) ሰዎች መነሳሳታቸዉ ምን ነበር ? ወደ ቤተ ክርስቲያን በምትሄዱ ጊዜ ወይም ከሌሎች አማኞች ጋር ህብረት ስታደርጉ ደስተኞች ናችሁ?
  4. በቁጥር 8 ላይ ፀሎቱን እንዲሰማዉ ከፀለዬ በኋላ መዝሙረኛዉ ምን ልመና አደረገ ? ለንጉሱ/ለተቀባዉ ለመፀለይ ለምን እየጠየቀ እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ (2ሳሙኤል 7) ? በስልጣን ለእነዚያ ነገሮች ስለ ሚስማሟችሁ ብቻ ሳይሆን ስለ ማትስማሙባቸዉም ምን ያክል ትፀልያላችሁ ? (1ጢሞ 2፡ 1-4)
  5. መዝ (84፡ 10) ከማቴ (6፡ 33) እና ፊል (1፡ 21) ጋር አወዳድሩ ፤ በእነዚህ በሁሉም ጥቅሶች ላይ ማብራሪያዉ የት ላይ ነው ?
  6. በመዝሙር 84 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ ያስረዳችኋል (ያሳያችኋል) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Psalm 84:4–5

“How happy are those who reside in Your house, who praise You continually. Selah Happy are the people whose strength is in You, whose hearts are set on pilgrimage.”

ደስታን እንዴት ነው የምታገኘው ? አለም ደስታን ለማግኘት መንገዶቹ ሁሉ ያሏት ይመስላል ፡፡ ነገር ግን በእውነቱ ሲታይ በአለም ሚዛን ያለው ደስታ ይደበዝዛል ይጠፋል ፡፡ እነዚህ በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ ጊዜን የሚያሳልፉት እናም ሳያቋርጡ እርሱን የሚያመሰግኑት ፣ እነርሱ በእርግጥ ደስተኞች ናቸው ፡፡ በጉዞህ እርዳታን ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትፈልግ ፣ ያኔ ደስታን ታገኛለህ ፡፡ በእግዚአብሔር ብቻ ስትታመን ፣ ያኔ ደስተኛ ነህ ፡፡ በምድር ላይ ያለ ግንኙነት ፡- ይጠወልጋል ፣ ቅር ያሰኛል ፣ ይጠፋል ይደበዝዛልም ፡፡ በዚህ ምድር ላይ ያሉ ነገሮች ይዝጋሉ ይጠፋሉም ፡፡ እግዚአብሔር እንድትጠቀምባቸው ብዙ መልካም ስጦታዎችን ይሰጥሃል ነገር ግን ደስታህን ሙሉ ለማድረግ አይደለም ፡፡ ስለዚህ አሳብህን በጌታ ላይ አድርግ ፣ አሳብህን በመንግስቱ ላይ አድርግ እናም በእርሱ መገኘት ውስጥ ጊዜን አሳልፍ ፡፡

ውሳኔን የምትወስነው ደስተኛ በሚያደርግህ ነገር ላይ ተመርኩዘህ ከሆነ ፣ አቁም ፡፡ ደስታኛነት በዚያ በአንድ ነገር ውስጥ ለረጅም ጊዜ አይገኝም ፡፡ ውሳኔህን በእግዚአብሔር ምሪት ፣ በቃሉ እና በእርሱ አውነት ወስን ፡፡ ወደ እርሱ ተጣራ እርሱም ይመልስልሃል ፡፡ እርሱ ረዳትህ ነው ፡፡ ዛሬ ደስታን ለማግኘት አትመራመር ፣ ይልቁንም ለህይወትህ የእግዚአብሔርን ፍቃድ እሻ ፡፡

“በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፤ ለዓለምና ለዘላለምም ያመሰግኑሃል ። አቤቱ፥ እርዳታው ከአንተ ዘንድ የሆነለት፥ በልቡም የላይኛውን መንገድ የሚያስብ ሰው ምስጉን ነው ። “

  • መዝሙር 84፡4-5

ተጨማሪ ጥቅስ

መዝሙር 32:8 — “አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ ። “

መዝሙር 84:11–12 — “ እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም ። የሠራዊት አምላክ ሆይ፥ በአንተ የታመነ ሰው ምስጉን ነው ። “

1ኛ የጴጥሮስ 1:24–25a — “ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል ፤ የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል ። “