I Have To Hear God's Voice
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ King of Glory Psalms 83 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
አንዳንዶች በቀን አምስት መዝሙሮችን ካነበባችሁ የመዝሙር መፅሀፍን በአንድ ወር ዉስጥ ታነቡታላችሁ ብለዋል፡፡ ፍሬድ መዝሙርን የመፅኀፍ ቅዱስ “ የሀሳብ ጤንነት “ በማለት ይጠራዋል ፤ በተጨማሪም በሙሉ ልባችሁ፣ በሙሉ ነፍሳችሁ፣ በሙሉ ኃይላችሁና ሀሳባችሁ እግዚአብሄርን መዉደድ መማር ከፈለጋችሁ መዝሙር ያስፈልጋችኋል ፡፡ መዝሙር 83 ስንከፋፍለዉ በዚህ መዝሙር የተጠቀሰዉን ሁሉንም ነገር ምናልባትም አዉቀነዉ/ቀምሰወነው እናየዋለን ፡፡
ትምህርት
መዝሙር (83፡ 1-4)፡ በቁጥር 1 መዝሙረኛዉ የሚያስፈልገዉን በመግለፅ ትዕዛዝን (ጥያቄን) ለእግዚአብሄር ሰጠ ፤ እንዲናገረዉ እንጂ እግዚአብሄር ዝም እንዳይለዉ ለመነው ፤ ወደ እርሱ እንዲያደምጥ እግዚአብሄር አስፈለገው ፡፡ እግዚአብሄርን ከእርሱ የተሰወረ እንዳይሆን ጠየቀው ፡፡ ከእነዚህ ጥያቄዎች በተሻለ ተግባራዊ የሆነ ነገር አለ ? በህይወታችሁ ቀድሞ ላይ በምትመለከቱ ጊዜ እግዚአብሄር ርቆአችሁ እንደ ነበር የተሰሙአቸሁ ጊዜያት ነበሩ ? ያ ወደ እናንተ አለማዳመጡ ነበር ? ያ ለእናንተ አለመናገሩ ነበር ? ምናልባትም ዘማሪው እግዚአብሄር ርቆት እንደ ነበር ተሰማዉ ምክንያቱም ሰዎች ስለ እርሱ ካለቱት ጋር በጣም የተሳሰረ ነበር - በእርሱ ላይ በሴራቸዉና በማጉረምረማቸው ፡፡ ያ የሰዉን መንፈስ አይመስልም ? ሰዎች በእኛ ላይ በሚያወሩ ጊዜ ብዙ አያስጨንቀንም ?
2 ዜና መዋዕል 20 በይሁዳ ላይ በአንድ ላይ ያሴሩትን ሕዝቦች ይዘረዝራል ፤ ሞዓባዊያን፣ አሞናዊያን እና ምዑናዉያን በኢዮሳፍጥ ላይ በጦርነት በዘመቱ ጊዜ ፆምን በማወጅ ሕዝቡን እግዚአብሄርን ወደ መፈለግ መራ ፤ ይህ ለእኛ በጣም አስፈላጊ እርምጃ ነው ፡፡ በነቃንበት ክስተት በመረጋጋት እግዚአብሄርን መፈለግ ያስፈልገናል ፡፡ መዝሙር 83 ማንን ለማዳመጥ እንድንወስን ያበረታታናል ፤ በጠላቶቻችን ላይ ወይስ ደግሞ በእግዚአብሄር ላይ እናተኩራለን ? በ2ዜና (20፡ 14) ፆሙ ባበቃ ጊዜ የእግዚአብሄር መንፈስ በመዝሙር ፀሀፊዉ በአሳፍ ዘር በየሕዚኤል ላይ መጣ ፤ ይህ የ 2ዜና መዋዕል 20 እና የመዝሙር 83 መካከል ያለ ግንኙነት ነው ፡፡ ኢዮሳፍጥ ከፀለዬ በኋላ ሕዝቡን ወደ ዊጊያ ሰራዊቱን ሲመሩ “ ለእግዚአብሄር እንዲዘምሩና እንዲያመሰግኑት ሰዎችን እንደሾመ “ መከራቸው (2ዜና 20፡ 21) ፡፡ በመዝሙር 83 ምስጋና ጦርነትን እንዳሸነፈ እያስታወሱ ነበር ፡፡
መዝሙር (83፡ 5-10)፡ ኤዶማዊያን፣ ፍልስጤማዊያን እና አሶራዊያን በእነርሱ ላይ ጥምረትን መሰረቱ ፡፡ መዝሙረኛው እግዚአብሄርን “ ምድያም ላይ እንዳደረክባቸዉ እነርሱም ላይ እንዲያደርግባቸው “ ጠየቀው (ቁጥር 9) ፤ ጥያቄዉ የመሳፍንትን ዘመን ወደ አይምሮ ይጠራል - የጌዴዎንን ዘመን (መሳፍንት 7) እና የድቦራን ዘመን (መሳፍንት 4) ፡፡ ይህ መዝሙር እግዚአብሄር በጥቂት ብዙ ማድረግ እንደሚችል ያብራራል ፤ ትልቅ/ሰፊ ሰራዊት ወይም ጠንካራ ተዋጊዎች አያስፈልጉንም ፡፡ እግዚአብሄር ያልተጠበቁትን ደካሞችን፣ ለማመስገን ዘማሪዉን መጠቀም ይችላል፣ እንዲሁም እግዚአብሄር ከ32,000 ዉስጥ 300 መጠቀም ይችላል (መጀመሪያ ለጥሪዉ ምላሽ ሰጥተዉ ከነበሩት ከ32,000 የጌዲዎንን 300 ሰራዊትን ) ፡፡ ዘማሪዉ እግዚአብሄር እንዲናገረዉ፣ የሆነ ነገርም እንዲያደርግ ፀለዬ ፡፡ የእግዚአብሄርን ድምፅ የመስማት የአይምሮ/የኃሳብ ተመሳሳይ ፍላጎት ካለን እደነቃለሁ ፤ ሰፊ/ብዙ ሰራዊት አያስፈልገንም ምክንያቱም የሚናገረን አንድ እግዚአብሄር ስላለን ፡፡ በዘፍጥረት 1 እግዚአብሄር በመናገሩ ሁሉም ፍጥረቶች ወደ መሆን መጡ ፡፡ ስትጓዙ ከእግዚአብሄር ድምፅ ዉጪ አብርሃም አይኖርም ፤ በሚነድደዉ ቁጥቋጦ ዉስጥ ከእግዚአብሄር ድምፅ ዉጪ ሙሴ አይኖርም ፤ በሕልም በመለዓክ እግዚአብሄር ከተናገረዉ ድምፅ ዉጪ ዮሴፍ አይኖርም ፤ ከእግዚአብሄር ድምፅ ዉጪ ማሪያም አትኖርም ፡፡ ከእግዚአብሄር ድምፅ ዉጪ በፍፁም የሕይወትን አላማ አትቀምሱትም ፤ እግዚአብሄር በድምፁ ዉስጥ ሲሰራ ሁሉም ነገር መሆን ይችላል ፡፡
ዛሬ እናንተና እኔ እንዴት የእግዚአብሄርን ድምፅ መስማት እንችላለን ? ዝርዝሩ ማብቂያ የሌለዉ ሊሆን ይችላል ነገር ግን እነዚህ ጥቂቶቹ መንገዶች ናቸው፡
- እግዚአብሄር በፀሎት ዉስጥ ይናገራል፡ የእግዚአብሄር ድምፅ በተለይም በማለዳ ግልፅ ነው ፤ ለመፀለይ፣ እንዲሰማችሁ ከእግዚአብሄር ጋር ጊዜ ለማሳለፍ የተሰጣችሁ ናችሁ ?
እግዚአብሄር በመፅሀፍ ዉስጥ/በኩል ይናገራል፡ ከመፅሀፉ የሚጣረስ ምንም አይነት ነገር እግዚአብሄር የሚል ከሆነ እግዚአብሄር አይደለም ፤ የሚለዉ ሁሉም ነገር የእግዚአብሄር ንግግር ከሆነዉና ከሚጠቅመዉ ከመፅሀፉ ቀጥሎ ይሄዳል (2ጢሞ 3፡ 16-17) ፡፡ መፅሀፍ የእግዚአብሄርን ድምፅ እንድትለዩ ይረዳችኋል ፡፡
እግዚአብሄር በመንፈስ ቅዱስ በኩል ይናገራል፡ በሐዋሪያት ስራ መፅሀፍ ሰዉ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶበት በነበረዉ ክስተት ጊዜ ለመናገር ችሎታቸዉ ሙሉ ለሙሉ ተቀይሮ ነበር ፡፡ እንዲናገራችሁ መንፈስ ቅዱስን ወደ ህይወታችሁ ጋብዙት ፡፡
እግዚአብሄር በቤተ ክርስቲያን በኩል ይናገራል፡ ዕብ (10፡ 25) አማኞች በአንድ ላይ መሰብሰብን እንዳይተዉ ያዝዛል ፤ አንዱ ከሌላዉ ጋር መገናኘትን መተዉ አንችልም “ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ “ ፤ አንድ ላይ መሆን አለብን ፡፡
እግዚአብሄር በህይወታችን ዉስጥ በአስፈላጊ ሰዎች በኩል ይናገራሉ፡ በኑሮአችን የሚወዱንና የምናምናቸዉን አምስት ሰዎች መለየት አለብን ፤ ተቆጣጣሪዎችን ማግኘት ያስፈልገናል - ወሳኝ ዉሳኔዎችን ከማድረጋችን በፊት ሊናገሩን የሚችሉ ሰዎች ፡፡
እግዚአብሄር በፍጥረት ዉስጥ ይናገራል፡ ብዙ ሰዎች እግዚአብሄር በዉሃ ላይ ዉጪ ሲሆኑ ይናገረናል ይላሉ ስለዚህም ወደ ቤተ ክርስቲያን አይሄዱም ፤ እዉነት ነዉ እግዚአብሄር በዉሃ ላይ እየተናገራቸዉ ነው - ያለማቋረጥ ይናገራል ፡፡ የእግዚአብሄርን ንግግር ከመስማት ዉጪ በዙሪያችን ያሉ ነገሮችን በማስተዋል በከዋክብቶች ላይ ወጥተን መመልከት ወይም ፀሀይን መመልከት አንችልም ፡፡ ከዋክብትን በምትመለከቱ ጊዜ እግዚአብሄር የማይቆጠር/የማያልቅ እንደ ሆነ ማየት ትጀምራላችሁ ፡፡ የእግዚአብሄርን እጅግ ብዙ ስርዓት የምታዩበት በፍጥረቱ እንጂ ሌላ ስፍራ የለም ፡፡
እግዚአብሄር በችሎታችን እና በሌሎች ችሎታ ዉስጥ ይናገራል፡ ማገልገል፣ መዉደድ እና ስጦታችሁን መጠቀም ስትጀምሩ እግዚአብሄር እናንተን ወደ ሌላ ስፍራ መምራት ይጀምራል ፡፡ የሚጓዝን አንድ መኪና ከቆመ አንድ መኪና ከመንዳት እንደሚቀል አስታዉሱ ፤ ስንጓዝ እግዚአብሄር ወደ ሆነ አቅጣጫ መንዳት/መግፋት መጀመር ይችላል ፡፡ ድምፁን መስማት ቀላል ነው ፡፡ ከእርሱ እንደሰማችሁ ስትደነቁ እግዚአብሄር ለእናንተ መናገርን ይቀጥላል ፤ እግዚአብሄር ራሱንም ይደግማል ፡፡
እግዚአብሄር በአምልኮ ዉስጥ ይናገራል፡ አምልኮ መማረክ ነው ፤ ሁል ጊዜ ስናመልክ ለእግዚአብሄር “ እንተ እንደሆንከዉ በሙላት አይደለሁም “ እንላለን ፤ ማምለክ ስንጀምር እግዚአብሄር ወደ ኑሮአችን በትልቅ መንገድ ይናገራል ፡፡
እግዚአብሄር በሁኔታዎች ዉስጥ ይናገራል፡ ፀጥ ስትሉ እግዚአብሄር የሚናገርባቸዉን መንገዶች ቁጥር ማሰብ ትችላላችሁ ፤ ስለ ድምፁ በፊቱ የመሆን እና በእግዚአብሄር የተመራችሁ ለመሆን ጉጉት አላችሁ ፡፡
መዝሙር (83፡ 16-18)፡ መዝሙረኛዉ ለመተግበር እግዚአብሄርን ከፈለገ ከረጅም መንገድ ዝርዝር በኋላ “ ፊታቸዉን እፍረት ሙላው አቤቱ ስምህንም ይፈልጋሉ “ አለ (ቁጥር 16) ፤ ከዚያም መዝሙረኛው፡ “ ስምህም እግዚአብሄር እንደ ሆነ በምድር ሁሉ ላይም አንተ ብቻ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ “ (ቁጥር 18) በማለት አጠቃለለ ፡፡ መዝሙረኛው እግዚአብሄርን በጠላቶቹ ላይ እንዲነሳ ቢጠራዉም እንኳን እግዚአብሄር ልባቸዉን እንዲቀይር እየተጣራ ነበር - እንዲያዉቁት እና ወደ እርሱ እንዲመለሱ እንዲረዳቸው ፡፡
መደምደሚያ
አሳፍ በህይወቱ እግዚአብሄር አድርጎለት የነበረዉን ታሪኩን የሚያዉቅ አንድ ሰዉ ነበር እንዲሁም በህይወቱ ብቻ ሳይሆን በታሪክ ህይወትም ላይ እግዚአብሄር ያደረገዉን ታሪክ ለመናገር የፈራ አልነበረም ፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችሁ ያደረገዉን ታሪክ ከልጆቻችሁ እና ከልጅ ልጆቻችሁ ጋር ትነጋገራላችሁ ? ደግመዉ ደግመዉ መስማት ያስፈልጋቸዋል ፡፡
ጥያቄዎች
-
በመዝ (83፡ 2-4) መሰረት የእግዚአብሄር ጠላቶች በሕዝቦቹ ላይ እንደ ሕዝብ ሊያጠፉአቸው እቅድን አቀዱ ፤ በቅርብ ታሪክ ተመሳሳይ አስተሳሰብ መቼ አያችሁ ? ከቻላችሁ ሕዝቦች ምን ያክል ጊዜ በአይሁድ ላይ ለማስወገድ ወይም ለማጥፋት እንዳሴሩ ፈልጉ/አጥኑ (http://www.eretzyisroel.org/~jkatz/expulsions.html) ፡፡ ይህ አድሎ እና ጥላቻ ዛሬም አለ ?
-
በመዝሙር 83 በአይሁዶች ላይ ያመፁት የመነሳሳታቸዉ ምክንያቶች ምን ነበሩ ? (መዝ 83፡ 4, 5, 12)
-
መዝ (83፡ 12-13) የእግዚአብሄርን ግጦች መቆጣጠር የሚፈልጉ ሰዎች ምን ይመስላሉ ይላል (መዝ 1፡ 4) ? ሌላ ማነዉ ተመሳሳይ ዉጤት የሚገጥመው ? ያ ለምን እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
-
መዝ (83፡ 2) እና መዝ (83፡ 18) አወዳድሩ ፤ በእነዚህ በሁለቱ ጥቅሶች ማነዉ ከፍ ከፍ ያለው ? በኑሮአችን ጌታን እንዴት ከፍ ከፍ ማድረግ እንችላለን ?
-
በመዝሙር 83 በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Psalm 83:1–2
“God, do not keep silent. Do not be deaf, God; do not be idle. See how Your enemies make an uproar; those who hate You have acted arrogantly.”
እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር መንፈስ ቅዱስ በውስጥህ ይኖራል ደግሞም ይናገርሃል ፡፡ እንደ አማኝ የእግዚአብሔርን ድምጽ በተለያዩ መንገዶች ትሰማለህ ፡- በጸሎት ፣ በቃሉ ፣ በህልም ፣ በራዕይ ፣ በሌሎች አማኞች እና በፍጥረታት፡፡ ነገር ግን ነገሩ እንድህ ነው የእግዚአብሔን ድምጽ ለመስማት ዝግጁ መሆን አለብህ ፡፡ ነገሩ መኪና ሳይቀሰቀስ መንዳት ካለመቻልህ ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡ የመኪናውን ሞተር ለመቀስቀስ ቁልፉ እስከሚኖርህ ድረስ እና መኪናው ወደ ፊት መሄድ እስከሚጀምር ድረስ መኪናው አይነዳም ፡፡ በህይወትህ የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት ፣ ከእርሱ ጋር መመላለስ ያስፈልግሃል ፡፡ በሙሉ ልብህ በእርሱ እመን ደግሞም አውቀህ አስበህበት በህይወትህ ለእግዚአብሔር እውቅናን ስጥ ፡፡ እርሱም ይመልስልሃል እርምጃህንም ያቃናልሃል ፡፡
ነገር ግን አስታውስ ሰይጣንም ድምጽ አለው ፡፡ ሊጮኽም ይችላል ፣ ውሸትን ይነግርሃል ደግሞም ወደ አለማመን እንድትገባ ያባብልሃል ፡፡ ንቃ እናም እግዚአብሔር መልስን ይሰጥ ዘንድ ጠይቅ ፡፡ እርሱን ስትጣራ ይመልስልህ ዘንድ ቃል ገብቷል ፡፡ እግዚአብሔር በጠላት ድምጽ ላይ አሸናፊ ነው አንተም በኢየሱስ ስም የጠላትን ድምጽ ያቆም ዘንድ የመናገር ኃይል አለህ ፡፡ ዛሬ በእውነት የሚመራህን የእግዚአብሔርን ድምጽ ስማ ፡፡
“አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል ። እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና ። “ - መዝሙር 83፡1-2
ተጨማሪ ጥቅስ
- ምሳሌ 3:5–6 — “ በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል ። “
- ኢሳይያስ 30:21 — “ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ፦ መንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ ። “
- ዮሐንስ 14:16 –17 — “ እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል ፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ ። “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።